አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮዛ


#ክፍል_ስምንት (🔞)


...የገረመኝ ነገር ጀኔራሉ በዚህ የደስታ ቀኑ እንኳ አንሶላ ሊጋፈፈኝ አለመሞከሩ ነው.
መጋፈፉን እንኳ ተጋፈናል ግን ሴከስ የሚባል ነገር አላረገም ሌሊቱን ያሳለፈው ወደ አገሩ ሊቢያ ስልክ በመደወልና በምላሹ ደግሞ የደስታ መልእክቶችን በመቀበል ነበር ይሄ በእውነት ከአንድ አረብ የጠበቅኩት ነገር አልነበረም ማለዳ ላይ ሻወር ከወሰደ በኃላ ልብሱን ለባብሶ ተሰናብቶኝ ሊወጣ ሲል አይኔን እያሻሸሁ በቂ ገንዘብ እንዳልያዝኩ ነገርኩት ትንሹ ሻንጣው ዉስጥ ያለውን ብር ዝም ብሎ አፍሶ
ሁሉንም አልጋዬ ላይ በተነው፡፡ ደነገጥኩ፡፡ ስላልቆጠርኩት ብዙ ብር የሰጠኝ መስሎኝ ፈነጠዝኩ።
ተሳስቻለሁ እሱ ከወጣ በኃላ ብሮቹን በሙሉ ሰብስቤ ስቆጥራቸው ያገኘሁት አንድ ሺ አምስት መቶ ዶላር፣ ሁለት መቶ ዩሮ፣ ሌላ 450የ ሳኡዲ ሪያል፣ ሌላ ዘጠኝ መቶ የሊቢያ ዲናርና ምንም የረባ ወጋ
የሌላቸው ጥቂት የጂቡቲ ፍራንኮች ነበሩ፡፡ ብሽቅ እንዳልኩኝ ተመልሼ ተኛሁ፡፡

#እሮብና_ሃሙስ_በሸራተን

ኡስማን አስቀድሞ እንደጠቆመኝ እሮብ እና ሀሙስ ምሸት በዚያው ባረፉበት የሸራተን ቪላ ውስጥ በቅርቡ ለገዙት አየር መንገድ ሆስተሶች ስለሚመለምሉ ለዚያው የስነልቦና ዝግጅት ማድረግ ጀመርኩ፡፡ ከጋዳፊ ጋር በቅርብ የመገናኘት እድል የሚኖረው በዚህ ወቅት ብቻ እንደሚሆን ተረድቻለሁ፡፡ እድሌን ለመሞከር ራሴን አሳምኛለሁ

ኡስማን ዘ ፒምፕ ለምን እንደሆነ አላውቅም በኔ በጣም ይተማመናል፡፡ ከሶስት ቀናት በፊት አግኝቼው
ይህንን ተናግሮኛል፡፡
“የትኛውንም ወንድ የሚያስደነግጥ ቁመናና ውበት አለሽ፡፡አረብኛ የመረዳት ችሎታሽ ለክፉ የሚሰጥ
አይደለም፡፡ እድሉ ከተመቻቸልሽ ካንቺ የተሻለ ቃዛፊን ወይም ረዳቶቻቸውን ለመማረክ የምትችል ሴት አላውቅም፡፡ እኔም “የምትመጥን ሴት አቅርብ” ብባል ካንቺ ሌላ ማንን እንደምጠቁም አላውቅም ፡፡

ምልመላው የሚካሄድበትን ቦታና ሰዓት ኡስማን ከተረዳ በኃላ ዘወትር የምንገናኝበት ሂልተን መናፈሻ
ውስጥ መጥቶ አገኘኝና ወደ ምልመላው አዳራሽ የሚወስደኝን የመግበያ ካርድ ሰትቶኝ ሄደ ከመልማዬቹ አንዱ ማንኛውም አይነት ጥያቄ ከጠየቀኝ ወይም ራሴን እንዳስተዋውቅ ከተጠየኩ አንድ ነገር እንዳልዘነጋ አበከሮ አሳሰበኝ፡፡ ይኸውም ጋዳፊ በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነት በመመረጣቸው የተሰማኝን ደስታ እንድገልጽላቸው ነበር፡፡ ጋዳፊ ለአፍሪካ አንድነትና ሰላም እያደረጉ ያለውን ያላሰለሰ ጥረትም በየአጋጣሚው
እያነሳሁ እንዳደንቅም እሳሰበኝ ይህን ጊዜ ሳቄ መጣ፡፡ «እኔ ፖለቲከኛ መሰልኩህ እንዴ እንደዚህ አይነት ንግግር የማድረገው? አብደሃል እንዴ? >>ብዬ ሳቅኩበት እሱ ግን ኮስተር ብሎ ቀጠለ።

.እንደ ሊቢያ ህገመንግስት የሚያገለግሉ
ቃዛፊ የፃፉት the Green Book የሚባል መጽሀፍ አላቸው አንድ ሁለት ጥቅስ እንደምንም ከኢንተርኔት ፈላልጊና እሱን መጸሐፍ እንደወደድሽው ተናገሪ ሮዛ እመኚኝ ያንቺንም የኛንም ህይወት የሚለውጥ ነገር ይከሰታል፡፡”

"ኡስማን...what are you talking about? I am is just an ordinary hooker... እንደዚህ አይነት ፖለቲካ
ማውራት አልችልም ደሞ በዛ ላይ ሰውየው እስከዚህ ድረስ ጃጅተዋል እንዴ እንዲህ ፊት ለፊት ሲሸነገሉ የማይባንኑት?come on Usman, that doesn't make a lot of sense!»

ኡስማን ምላሽ ነበረው፡፡

እኔ የምነግርሽን ሳታወላውይ አድርጊው፡፡ያንቺ ጥርጣሬ ይገባኛል ሆኖም አምባገነኖችን የሚያመሳስላቸው ነገር ለራሳቸው የሚሰጡት ቦታ ነው፡፡…›› ትንፋሹን አሰባሰበና ቀጠለ፡፡

like it or not, Most Arabs are assholes.sorry to say this. ቃዛፊ ለምሳሌ ጤናማ ሰው አይደለም፤ወፈፌ ነው፤ይህን አለም ያውቀዋል፤አጠቃላይ የህይወቱን ታሪክ ስትመረምሪም የምታገኘው ይሄንኑ ሀቅ ነው ጋዳፊ ለስሙ የአምስት ወቅት ሰላት ሳያቋርጥ ይሰግዳል፡፡ ሆኖም የራስ አምልኮ
የተጠናወተው ሰው ነው፤ሁሌም ውዳሴን ይፈልጋል ታምኚያለሽ? በየቀኑ ስለሱ ታላቅነት ግጥም እየጻፉ ቤተመንግስቱ ድረስ እየሄዱ የሚያነቡለት የአረብ ደራሲዎች በሊቢያ የባህልና የኃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር መስሪያ ቤት በኩል እንደተቀጠሩ? ይህንን የነገረኝ እሱ ቤተሰብ ሰርክል ውስጥ ያለ ሊቢያዊ ነው
you can't believe it can you? ለምሳሌ ቃዛፊ ከጉርምስናው እድሜ ጀምሮ የእስልምናን ሱና ጠብቆ
ሳያቋርጥ ሰኞና ሀሙስን ይጾማል ሰኞና ሀሙስ ደናግል ነርሶቹ እንኳ እንዲነኩት አይፈቅድላቸውም በተቃራኒው ከአምላክ ይልቅ በራሱ ፍቅር እና አምልኮ የሰከረ ወፈፌ ነው.ሮዛ! Trust me!እድሉ
ከተሰጠሽ ያለምንም ርህራሄ በረቂቅ መንገድ ሳይሆን ፊትለፊት ደረቅ ዉዳሴ ከማቅረብ ወደኋላ አትበይ!
እመኚኝ ሮዛ… ስለ ሰውየው እኔ የማውቀውን ሚስጢር ሩቡን ያህል እንኳ እንቺ አታውቂም፡፡”

ለ ጋዳፊ final exam ስለ መዘጋጀት

ረቡእ ጥር 27/2008

በውበትም፣በስራ ልምድም፣በቋንቋ ክህሎትም ሆነ በእውቀት ከኔ የሚልቁ በርካታ ከባድ ተወዳዳሪዎች ሊገጥሙኝ እንደሚችሉ ገምቼያለሁ፤አንድ የቢሮ ጸሀፊ ተፈልጎ በሺዎች የሚቆጠሩ ስራ ፈላጊ ጸሀፊዎች የሞት ሽረት ትግል የሚያደርጉበት አገር ውስጥ እንዳለሁ አሳምሬ አውቀዋለሁ፤በተቻለኝ መጠን
አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ ጥሬያለሁ፤አርባ አመት በስልጣን ላይ የቆዩት የ67 አመቱ ሙአመር ጋዳፊ
ወጣት ሳሉ የጻፉትን አረንጓዴውን መጽሀፍ የእንግሊዝኛውን ቅጂ ከኢንተርኔት በማውጣት የተወሰነ
ከፍል ትኩረት ሰጥቼ አንብቤዋለሁ መሐል ላይ በጣም አንገሽግሾኝ አቋረጥኩት፡፡ የጋዳፊን የግል
እና የፖለቲካ ህይወት የተቻለኝን ያህል ለማጥናት ሞክሬያለሁ፤ዛሬ ማታ የመናገር እድል ከተሰጠኝ ጋዳፊ
ለመንግስቱ ሀይለማሪያም ያደረጉትን አንዳንድ ድጋፍ መግለጹ አስፈላጊ መስሎ ተሰምቶኛል፡፡

ከዩኒቨርሲቲ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ይመስለኛል እንደዚህ አምርሬ ሳነብ ግን በሰበቡ ብዙ ነገር አወቅኩ
። ለመንግስቱ የመጀመሪያውን ብሄራዊ ውትድርና ተመልማች የመለዮ ልብስን ጨምሮ ለስንቀና ትጥቅ በገንዘብ መደገፋቸውን፤የጦላይ፣የዲዴሳና የመስኖ የወታደር ማሰልጠኛ ካምፖች ሲቋቋሙ
ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን፤በ77ቱ ድርቅም የገንዘብ ድጋፍ በራሳቸውና በሊቢያ ህዝብ ስም ማበርከታቸውን አነበብኩ፡፡ኮሎኔል መንግስቱን እና ኮሎኔል ጋዳፊን በተመለከተ ከልጅነቴ ጀምሮ በተደጋጋሚ የሰማሁት አንድ ታሪክም ትዝ አለኝ፤ሙአመር ጋዳፊ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመሳተፍ አዲስ አበባ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ወታደር አጃቢዎቻቸው ጋር የጦር ታንክ ጭምር ይዘው ከትርፖሊ ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ፤ኮሎኔል መንግስቱ አመታዊ ጉባኤው ላይ ለመካፈል የመጡትን ኮሎኔል ጋዳፊን ከበራፍ ላይ እንዲህ ሲሉ ይመልሷቸዋል

"ወንድም ጋዳፊ!ይሄ እኮ ሰላማዊ የውይይት መድረከ ነው፣ታንክ እዚህ ምን ይሰራል! የጦር ካምፕ አስመስልከው እኮ”
ጋዳፊ አኩርፈው እጃቢዎቻቸውን አስከትለው አህጉራዊው ጉባኤ ላይ ሳይካፈሉ በመጡበት ወደ አገራቸው
ተመለሱ አሉ፡፡ ይህ ታሪክ እውነት ይሁን ዉሸት አላውቅም ግን ከድሮ ጀምሮ ሲወራ እሰማዋለሁ፡፡

ኮሎኔል መንግስቱ በትሪፖሊ ጉብኝታቸው ወቅት ስለ ጋዳፊ የታዘቡትን መጥፎ ጠባይ ሳነብ በጣም ተገረምኩ መንግስቱ በሊቢያ ቆይታቸው ሙአመር ጋዳፊን በእንብርክክ እየሄዱ ጋዳፊ የጠየቁትን ትእዛዝ የሚያስፈጽሙ በርካታ የምስራቅ አውሮፓ ሴቶችን ቤተመንግስት ውስጥ መመልከታቸውን ጽፈዋል
ለነዚህ ታዛዥ ነጭ አሽከሮቻቸው ጋዳፊ
👍6🔥32