አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
578 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እማማ_ዣ


#ክፍል_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

“አ…ቡ.…ቹ…ኡ…” ይላሉ፣ ከቤታችን ፊት ለፊት ያለ ባለ ግንብ አጥር ቤታቸውን የብረት በር ገርበብ አድርገው፡፡

“አቤት! እማማ !” እላለሁ፡፡ ሁልጊዜም ሲጠሩኝ ስለምጮህ እናቴ ትበሳጫለች፡፡
የእርሳቸውን ጥሪ ሳትሰማ፣ ድንገት እኔ ስጮኽ ደንግጣ በቁሟ የለቀቀችው የሸክላ ሰሃን ተንኮታኩቶ ያውቃል፡፡ ብዙ ጊዜ “ሲጠሩህ ወጣ ብለህ አቤት በል እሰው ጆሮ ግንድ ስር አታንባርቅ?” እያለች በቁጣ ብትመክረኝም፣ እማማ ዣ ሲጠሩኝ ግን ምክሯን እረስቼ መጮኼን ልቆጣጠረው አልቻልኩም፡፡ መጮህ ብቻ አይደለም …የቤት ሥራ እየሰራሁ ከሆነ እስክርቢቶና ደብተሬን፣ እየበላሁም ከነበር ያዘጋጀሁትን ጉርሻ ከእጄ ላይ ርግፍ
አድርጌ፣ወደቤታቸው ሮጣለሁ። እናቴ ታዲያ “ወታደርም እንዲህ በተጠንቀቅ አይቆምም” ትላለች፡፡

በርሬ ሄጄ “አቤት! እማማ ዣ” እላለሁ በሕፃንነቴ ያንዣቡ የሚል ስማቸው አልያዝልኝ ብሎ “ዣ” አልኳቸው፡፡ካደኩም በኋላ “ዣ" ብያቸው ቀረሁ።

“ናማ! ቶሎ በል… ወሞ ገዝተህልኝ ና …ቱ! ይች ምራቅ ሳትደርቅ!”

“ያባባ ጃንሆይን ታሪክ ከነገሩኝ ነዋ?!”

“ና! ዝም ብለህ ሂድ .…ወተፈናም !… የጃንሆይ ታሪክ ለማንም ተላላኪ የሚሰጥ ድርጎ አረከው እንዴ? ሻይና ዳቦ ካገኘህ ምን አነሰህ?! ለባሪያ ነብስ አባት፣ ዲያቆን ምን አነሰው አሉ.ሆሆሆ ግዛ ያሉኝን ኦሞ የተባለ የዱቄት ሳሙና ለመግዛት፣ ወደ ዘመናይ ሱቅ ቁልቁል እበራለሁ…

ዘመናይ ማርየ
ዘመናይ፣ ገበያ ለመሳብ አጉል ወሬና ሽንገላ ስለምታበዛ ብትሰለቸኝም፣ ሱቋ ግን ትልቅና በብዙ መብራት የተንቆጠቆጠ ስለሆነ ደስ ይለኛል፡፡ በነጭ “ፍሎረሰንት” አምፑሎች
የተንቆጠቆጡትና በተንሸራታች መስተዋት የሚዘጉት መደርደሪያዎች፣ የተለያዩ ቀለማት ካላቸው የሱቅ ዕቃዎች ጋር ተዳምረው፣ ተልኬ በሄድኩ ቁጥር ከሱቁ ውጣ ውጣ አይለኝም:: በዚያ ላይ ዘመናይ ራሷ ዘናጭ የሃያ አምስት ዓመት ሴት ነበረች፡፡(እንደቀልድ ሃያ አምስት ሞላኝ ስትል ሰምቻታለሁ) የምትቀባው ሽቶ ብቻ በመንገድ የሚያልፍ ሰው
የሚጠራ ፤ ሲበዛ ንጹሕ ሴት፡፡ በተለይ ጣቶቿ! ሸቀጣሸቀጥ መኻል እየዋለች እንዴት ጣቶቿ እንደዚያ ንጹሕና የሚያንጸባርቁ እንደሚሆኑ ይገርመኛል፡፡ ደግሞ ሱቁ ውስጥ ሁልጊዜ ደስ የሚሉ ሙዚቃዎች ይከፈታሉ፡፡ ራሷ ዘመናይ ድምጿ ደስ ይላል፤ ሳቋንና የምትናገረውን ነገር ግን አልወደውም፡፡ በተለይ ሳቋን! አንዳንዴ ታዲያ ድምጿ የሚሽከከው አማርኛ አስተማሪያችን የምታወራልን አጓጊ ተረቶች፣ በዚች ዘመናይ በተባለች ባለ ሱቅ ድምፅ ሲተረክ እያልኩ አስባለሁ፡፡

ገና ወደ ሱቁ ስገባ፣ “አቡቹ ማሬ! …ምን ልስጥሽ?” አለችኝ፡፡ የአፍ መብለጥለጥ
ይደክመኛል! በተለይ “አንች!” እያሉ የሚያናግሩኝ ሰዎች ጤነኛ አይመስሉኝም እንዲህ ዓይነት ሰዎች ጠበል ቢወሰዱ ይኼ ነገራቸው ሰባት ጊዜ ጩኾ የሚወጣ አጋንት ነው የሚመስለኝ፡፡ ሁልጊዜ ስትፈጥንብኝና በማያባራ ፈጣን ልፍለፋዋ ስታጣድፈኝ፣ የተላኩት ነገር ይጠፋብኛል፡፡ ስንት ቀን ያልታዘዝኩትን ነገር አንጠልጥዬ ሄጄ መልስ ተብያለሁ! (ገና ካሁኑ ልቡ የት ሂዷል!? ከሚል ወቀሳ ጋር) የተገዛ ዕቃ እንደመመለስ
ደግሞ የሚያሳፍረኝ ነገር የለም! ዘመናይ ግን ዕቃ ልመልሰም፣ ልመልስ መሄዴን
እስከምረሳው፣ በዚያ ምላሷ ትንቀለቀልብኛለች፡፡ “እቡቹ ነፍስ ነገር፣ ችግር የለውም ይመለሳል…ግን ፍቅር ያዘሽ እንዴ? መርሳት አብዝተሻል ...ከእኔ እንዳይሆን ብቻ
…ባረገው ካካካካካካካካካ !!”

“እ… ኦሞ ስጭኝ አልኳት የጨበጥኳትን ብር ባንኮኒው መስተዋት ላይ እያስቀመጥኩ፡፡

ይሰጥሃላ! እንደሱማ በግንባርህ አታየኝም! ካካካካካ…” እያለች ፈጽሞ ያላዘዝኳትንና ከዚያ በፊት አይቼው የማላውቀውን፣ በቢጫ ላስቲክ የታሸገ የዱቄት ሳሙና አንስታ
“ይኼን ውሰድና እቤት ይሞክሩት ..እዲስ ነው፣ ቆሻሻን ድራሽ አባቱን የሚያጠፋው” ብላ ብር ያስቀመጥኩበት መስተዋት ላይ ወረወረችው፡፡ ተሽከርክር . እፊቴ ሲደርስ ቆመ፡፡ ዕቃዎችን ከሩቅ ወርውሮ ደንበኞቿ ፊት ባለው መስተዋት ላይ ማሽከርከርን እንደሆነ አራዳነት ነው የምታየው! አንዳንዴ ዕቃ ልታወርድ
ከተንጠላጠለችበት መሰላል ላይ እንደ ቆመች፣ ገዥው የፈለገውን ዕቃ ወርውራ
መስተዋቱ መኻል ላይ ቁጭ ታደርገዋለች

በእርግጥ እኔም ቤታችን መኻል ላስቲክ ለብሳ በምትቀመጥ የምግብ ጠረጴዛ ላይ ዕቃ እየወረወርኩ፣ ዘመናይ እንደምታደርገው ተሸከርክሮ እንዲቆም ለማድረግ ብዙ ጊዜ ሞክሪያለሁ፤ ግን አሪፍ ለመሆን ብዬ አይደለም፡፡ በቃ እንዲሁ ለመሞከር፤ አንድም ጊዜ
ግን የምወረውረው ዕቃ ተረጋግቶ ጠረጴዛዋ ላይ ቁሞልኝ አያውቅም፤ ተምዘግዝጎ መሬት ላይ ይወድቃል፡፡ ምናልባት የጠረጴዛችን እግሮች ጤነኛ ስላልሆኑና፣ አንዴ ወደ ሰሜን አንዴ ወደ ደቡብ ትንሽ ዘመም ስለምትል ይሆናል።

“አይ ኦሞ ነው የተባልኩት ኦሞ ስጭኝ!” አልኳት የምፈልገው የዱቄት ሳሙና ወደ
ተደረደረበት እየጠቆምኩ…

“ወ...ይም ይኼንኛውን ውሰድላቸው ዋጋው እኩል ነው!.…ኦሞኮ ፋሽኑ አልፎበታል አቡችዬ ..እያለች ሌላ ድርፉጭ ያለ ካርቶን ከመደርደሪያው ላይ አወረደች፤የመወርወር ትርኢቷን ሳታሳይ በፊት፣ በብስጭት መስተዋቱ ላይ ያስቀመጥኩትን ብር አፈፍ አድርጌ፣
ሱቋን ትቸላት በሩጫ ወጣሁ፡፡ ከኋላየ ዴጋግማ ስትጠራኝ እሰማታለሁ፡፡ በሷ እልህ (ኦሞ ያለው እሷ ሱቅ ብቻ መሰላት እንዴ? እያልኩ) ወለኔ ወደሚባለው በበሩ እንኳን ሳልፍ ወደሚቀፈኝ ሱቅ ተጣደፍኩ!

#ነገረ_ወለኔ
እውነቱን ለመናገር ይኼን ወለኔ የሚባል ሱቅ፣ እንኳን ውስጡ ገብቼ፣ እንዲሁ በዛ
በኩል እያለፍኩ ሳየው ራሱ የምቆሸሽ ነው የሚመስለኝ፡፡ እዚህ ሱቅ በረንዳ ላይ ናፍጣ ስለሚሸጥ፣ ከሁሉም ነገር ቀድሞ የሚቀረና የናፍጣ ሽታ ነው ከስር ላይ የሚቀበለው፡፡የዚያ ቤት ዕቃ ሁሉ ጋዝ ጋዝ ይሸታል፡፡ በውጩ የጭቃ ግድግዳ ላይ “ምንትስ አለ”
የሚሉና በተለያዩ ቀለማት በወልገድጋዳ የእጅ ጽሑፎች የተጻፉ ብዙ ማስታወቂያዎች ተለጥፈዋል፡፡ ማስታወቂያዎቹ ያስቃሉ ...

የአይጥ መርዝ አለ!

የአይጥ ወጥመድ አለ ...

አይጥ የማይበላው የእህል ጆንያ አለ (ደግሞ ይኼ ምንድነው?) “አይጥ አለ” ብለው መለጠፍ ነው የቀራቸው ...(መኖርም አለበት! ይኼን ሁሉ አይጥ ነክ ነገር በምን ሞክረው ለገበያ አቀረቡት ታዲያ?!) የተነጠረ ቅቤ አለ ..ትንባሆ አለ ..የኑግ ዘይት አለ...

ከትልቅ የቆሸሽ ሰማያዊ በርሜል እየቀነሱ የሚሸጡት የኑግ ዘይት፣ እዚያና እዚህ ተነካክቶ፣ ከመደርደሪያው እስከ ሱቁ ወለል ድረስ ወዛም እድፍ ተለድፎ
አጠቋቁሮታል፡፡ ሁልጊዜ ደግሞ እዚያ ሱቅ የሚነጠር ቅቤ ይሸተኛል፤ ሱቁ የናፍጣ፣ የእጣን፣ የቅቤና የሲጋራ ሽታ ተቀላቅሎበት የሚያቅለሸልሽ ስሜት ይፈጥራል…ደግሞ የት እንደተቀመጠች የማትታይ ሬዲዮ እዚህ ሱቅ በገባሁ ቁጥር ሽሽሽሽሽ የሚል ድምፅ ጋር
የተቀላቀለ ዜና ስታሰማ ነው የምደርሰው ብዙውን ጊዜ የዚህ ሱቅ ደንበኞች፣ በወረቀት የሚጠቀለል ነገር የሚያጨሱ የገጠር ሰዎች ናቸው፤ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም፣ በተለይ ጠዋት ጠዋት…ፊት ለፊት የበረንዳው ቋሚ እንጨት ላይ ታስሮ የሚቆም፣ የዝንብ ሰርገኛ የሚጨፍርበት፣ ገጣባ አህያ በሩ ላይ አይጠፋም፡፡ ቢሆንም እንደ ዘመናይ በአጉል አራዳነትና አብረቅራቂ ውበት ታጅቦ ያልፈለጉትን አስገድዶ ከሚያስገዛ ብልጣብልጥ
ይልቅ፣ ቃል ሳይተነፍስ የጠየቁትን የሚሰጠው የዚህ ሱቅ ባለቤት ይሻላል! ስሙ አይያዝልኝም፣ ምናልባትም ከመጀመሪያውም አላውቀውም ይሆናል! ..ሱቁ በልምድ “ዘይት ቤቱ” ነው የሚባለው!
👍2