#ተስፋ_እንደ_ምትሐት
የግዜር ስውር መዳፍ
ልክ እንደፓፒረስ፥ እንደግብጦች መጣፍ
ወይም እንደጥንቱ፥ ያባጅፋር ምንጣፍ
ጨለማውን ስቦ፥ በወግ ሸበለለ
ስማይ የጠፈር ዓይን፥ ብርሃን ተኳላ
ከዶሮ ጩኸት ውስጥ፥ አዲስ ጎሕ ተወልዶ
ፍጥረቱ በሙሉ፥ ማርያም ማርያም አለ፤
#ነጋ
አልጋየን ሰብሬ
አንሶላ ተርትሬ
ባዲሱ ጉልበቴ
በታደላ አሞቴ
ልኖር ተዘጋጀሁ
እንደጣዝማ ቅንጣት
ከሚጣፍጥ ሞቴ
ትንሳኤየን ዋጀሁ፤
#ነጋ
እንደምትሐተኛ፥ ተስፋ ሲያታልለኝ
አዲሱ ማለዳ፥ “ዛሬን ሞከር” ሲለኝ
የዛሬው እጣየ
ከትናንት ጣጣየ
የሚለይ መሰለኝ።
የግዜር ስውር መዳፍ
ልክ እንደፓፒረስ፥ እንደግብጦች መጣፍ
ወይም እንደጥንቱ፥ ያባጅፋር ምንጣፍ
ጨለማውን ስቦ፥ በወግ ሸበለለ
ስማይ የጠፈር ዓይን፥ ብርሃን ተኳላ
ከዶሮ ጩኸት ውስጥ፥ አዲስ ጎሕ ተወልዶ
ፍጥረቱ በሙሉ፥ ማርያም ማርያም አለ፤
#ነጋ
አልጋየን ሰብሬ
አንሶላ ተርትሬ
ባዲሱ ጉልበቴ
በታደላ አሞቴ
ልኖር ተዘጋጀሁ
እንደጣዝማ ቅንጣት
ከሚጣፍጥ ሞቴ
ትንሳኤየን ዋጀሁ፤
#ነጋ
እንደምትሐተኛ፥ ተስፋ ሲያታልለኝ
አዲሱ ማለዳ፥ “ዛሬን ሞከር” ሲለኝ
የዛሬው እጣየ
ከትናንት ጣጣየ
የሚለይ መሰለኝ።