አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሁቱትሲ


#ምእራፍ_አስራ_አንድ


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#እምነቴን_ስጠብቅ


ገዳዮቹ ስሜን ሲጠሩ ሰምቻቸዋለሁ፡፡
የፍርሃት መአት በውስጤ ተሠራጨ፡፡ ዲያብሎስም ድጋሚ በጆሮዬ አንሾካሾከ - አሁን የት እንዳለሽ አውቀውታል… አሁን የት እንዳለሽ አውቀውታል… አእምሮዬ ወደ ድሮው ተመለሰና ራሴን ሳትኩ፡፡ ለምን ስሜን ተጣሩ - እዚህ እንዳለሁ እንዴት ሊያውቁ ቻሉ? ወደ መታጠቢያ ቤቱ እየመጡ ይሆን እንዴ?
አምላክን ለመጥራት ብሞክርም የምሰማው ብቸኛ ነገር ግን በቤቱ ከሚያስተጋቡት ከገዳዮቹ ክፉና አረመኔያዊ መዝሙሮች ጋር አእምሮዬን የተቆጣጠሩትን አሉታዊ ድምጾች ነው፡፡ ልብሶቼ በላብ ተጠምቀው እምነቴን ፍለጋ እፍጨረጨር ገባሁ፡፡
የመጡት በመቶዎች ሆነው ነው፡፡ ቄሱን የዛቻና የውንጀላ መዓት ያወርዱባቸዋል፡፡ ‹‹የት ነች?›› ሲሉ አንባረቁባቸው፡፡ ‹‹እዚህ እንዳለች እናውቃለን፡፡ ፈልጓት… ኢማኪዩሌን ፈልጓት፡፡››
ከግንቡ በስተጀርባ በቄሱ መኝታ ቤት ናቸው፡፡ ከግማሽ ጋት ያነሰ ውፍረት ያለው ጭቃና ዕንጨት ይለያየናል፡፡ እርምጃዎቻቸው ቤቱን አንቀጠቀጡት፣ ገጀራዎቻቸውና ጦሮቻቸውም ከግንቡ ጋር ሲጋጩ ይሰማኛል፡፡
በረብሻው መካከል አንድ የቤተሰቤ ወዳጅ የሆነን ሰው ድምፅ መለየት ቻልኩ፡፡ ‹‹399 በረሮዎችን ገድያለሁ›› በማለት ጉራውን ይነፋል፡፡ ‹‹ኢማኪዩሌ 400 ታደርግልኛለች፡፡ ይህም ቀላል የሚባል ቁጥር አይደለም፡፡››
በጥጋቷ እንደተሸሸግሁ ዲያብሎስ በጆሮዬ ይስቅብኛል፡፡ ስምሽን ያውቃሉ… እዚህ እንዳለሽ ያውቃሉ፡፡ አሁንስ አምላክሽ የት አለ?
ገዳዮቹ ቄሱን ተጫኗቸው፡- ‹‹ቱትሲዎቹ የት ናቸው? ካገኘናቸው ምን እንደምናደርጋቸው ታውቃለህ፡፡ የት አለች፤ ቄሱ፣ ኢማኪዩሌ የት ነች? መጨረሻ የታየችበት ስፍራ እዚህ ነው፡፡ የት ነው የደበቅሃት?››
መንፈሴ በፍርሃትና ጥርጣሬ ክንዶች ላይ ተመልሶ ወደቀ፡፡ እናም ገዳዮቹ መጀመሪያ በመጡበት ጊዜ ከፈራሁትም በላይ በጣም ፈራሁ፡፡ ድምጾቻቸው ሥጋዬን ሸነታተሩት፤ በመቀጣጠል ላይ ባለ ከሰል ላይ የተኛሁ ያህል ተሰማኝ፤ ሁለመናዬን የህመም አበላ ዋጠው፤ ሺ የማይታዩ መርፌዎች በሰውነቴ ላይ ተሰገሰጉብኝ፡፡ ቢሆንም ግን ለመጸለይ ሞከርኩ፡- ውድ እግዚአብሔር፣ ስለ እምነቴ መድከም ማረኝ… አምንሃለሁ… እንደምትምረንም አውቃለሁ፡፡ በዚህ ቤት ውስጥ ካለው ርኩስ መንፈስ ታይላለህ፡፡
ገዳዮቹ ተንቀሳቃሽ ምስሉን ባየንበት ክፍል የቤት እቃዎቹን ያገላብጣሉ፤ የእኔንም ስም ደጋግመው ይጠራሉ፡፡ ‹‹ኢማኪዩሌን እንፈልጋታለን… ኢማኪዩሌን መግደያችን አሁን ነው፡፡››
ጆሮዎቼን በእጆቼ ይዤ ከገዳዮቹ ገጀራዎች አንዱ የኔ እንዲሆን፣ ጆሮዎቼንም ቆራርጬ መስማት እንዳቆም ተመኘሁ፡፡ ‹‹ወይ አምላኬ …›› ጮክ ብዬ መጸለይ ጀመርኩ፤ ምንም ቃላት ግን ማውጣት አልቻልኩም፡፡ ለመዋጥ ሞከርኩ፤ ጉሮሮዬ ግን ተዘጋ፡፡ ምንም ምራቅ አልነበረኝም፤ አፌም እንደኩበት ደርቋል፡፡ ዓይኖቼን ጨፈንኩ፡፡ ብጠፋም ተመኘሁ፤ ድምጹ ግን እየጨመረ መጣ፡፡ ምንም ዓይነት ምኅረት እንደማያደርጉልኝ አውቃለሁ፡፡ አእምሮዬም አንድ ሐሳብ ብቻ ያስተጋባ ጀመር - ከያዙኝ ይገድሉኛል፡፡ ከያዙኝ ይገድሉኛል፡፡ ከያዙኝ ይገድሉኛል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሴን በአፌ ያዝኩና በጥርሶቼ መካከል ጥብቅ አድርጌ ነከስኩት፡፡ የእግዚአብሔርን ቃላት ልውጣቸው ፈለግሁ፣ ወደ ነፍሴ ጥግ ጭልጥ አድርጌ ማስገባትንም ተመኘሁ፡፡ ጥንካሬውን በድጋሚ መፈለግ አሻኝ፣ ለረጅም ጊዜ ሲያስቸግረኝ የነበረው አሉታዊ ኃይል ግን በአእምሮዬ አስፈሪ ምስሎችን ያሳየኝ ይዟል፡፡ ገዳዮቹ ሲያገኙኝ ምን እንደሚያደርጉኝ ታየኝ - ግርፋቱን፣ ማሸማቀቁን ብሎም ግድያውን አየሁት….
ተው እግዚአብሔር፣ እባክህ! በጸጥታ ጮህኩ፡፡ በዚህ ውስጥ እንዳልፍ ምነው ፈለግህ? ለምን? ፍቅሬን ላንተ ለማሳየት ምን ላድርግ? አንተው እንደምታድነን ለማመን እፈልጋለሁ፡፡ ከዚህ የበለጠ እምነት እንዴት ሊኖረኝ ይችላል? በጣም
እየጸለይኩ ነው፣ እግዚአብሔር፣ በጣም… ግን በጣም ቀርበዋል፣ በቃ በጣም ደክሜያለሁ! እግዚአብሔር ሆይ… ደካክሜልሃለሁ፡፡
ራሴን የሳትኩ መሰለኝ - በቤቱ ዙሪያ የሚሰማው የገዳዮቹ ጆሮን እንደ መብረቅ የሚያደነቁር ድምጽ እስኪቀዛቀዝና በሩቅ የሚሰማ ሁካታ እስኪሆን ድረስ ራስን መግዛት የሚባል ነገር ከኔ ሸርተት አለ፡፡ ከዚያም ተኛሁ፤ የኢየሱስንም ጣፋጭ ሕልም አልም ገባሁ፡፡
ከሌሎቹ ሴቶች በላይም እንደ ላባ ተንሳፈፍኩ፡፡ ከበታቼ በወለሉም ላይ መጽሐፍ ቅዱሶቻቸውን በራሶቻቸው ላይ አድርገው እግዚአብሔርን ለምኅረት በመለማመን ሲንቀጠቀጡ አየኋቸው፡፡ ቀና ስል ኢየሱስን በወርቃማ ብርሃን ታጅቦ ከበላዬ ሲያንዣብብ አየሁት፤ እጆቹም ወደ እኔ ተዘርግተዋል፡፡ ፈገግ ስል ለሳምንታት ኩርምት ከማለቴ የተነሣ በሰውነቴ ላይ የነበሩት ቋሚ ሕመሞች ጠፉልኝ፡፡ ምንም ዓይነት ረሃብ፣ ጥምም ሆነ ፍርሃት የለ - በጣም ሰላም ተሰማኝ… ደስም አለኝ፡፡
ከዚያም ኢየሱስ ተናገረ፡ ‹‹ተራሮች በእምነት ይገፋሉ፣ ኢማኪዩሌ፣ እምነት ግን ቀላል ቢሆን ሁሉም ተራሮች ይሄዳሉ፡፡ በኔ ካመንሽብኝ መቼም ቢሆን እንደማልተውሽ እወቂ፡፡ በኔ እመኚ፣ ምንም ዓይነት ፍራቻም ዓይኑርሽ፡፡ በኔ እመኚ፤ አድንሽማለሁ፡፡ መስቀሌን በዚህ በር ላይ ስለማኖረው አይደርሱብሽም፡፡ እመኚብኝ፤ ትኖሪማለሽ፡፡››
ወደ ወለሉ በድንገት ተመልሼ ሌሎቹን ተቀላቀልኩ፡፡ ዓይኖቻቸውን አሁንም እንደጨፈኑ ነው፤ የኔ ዓይኖች ግን በመታጠቢያ ቤቱ በር ፊት ለፊት ከግንብ ግንብ በተንጣለለው አንጸባራቂ ነጭ የብርሃን መስቀል ላይ አፍጥጠው በሰፊው ተከፍተዋል፡፡ ሳየውም አንጸባራቂው ኃይል ፊቴን ነካው፤ እንደ ጸሐይ ሁሉ ቆዳዬንም አሞቀው፡፡ በደመ-ነፍስም ገዳዮቹን የሚመልስ አንዳች መለኮታዊ ኃይል ከመስቀሉ እየወጣ እንደሆነ አወቅሁ፡፡ እንደምንጠበቅና ደኅና እንደምንሆን ተገለጠልኝ፤ ስለሆነም የአንበሳ ጥንካሬ እንዳለኝ ሁሉ ተሰማኝ፤ ዘልዬም ቆምኩ፡፡ አምላኬን በፍቅሩ ድጋሚ ስለነካኝ አመሰገንኩት፤ ከዚያም ሌሎቹን ቁልቁል አየሁኋቸው፡፡ በመታጠቢያ ቤቱ ቆይታዬ ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ አብረውኝ ባሉት ሰዎች ላይ ጮህኩባቸው፤ ‹‹ምንም አንሆንም! እመኑኝ… ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል!›› የድምጼ ጉልህነት በፊታቸው ላይ እንደተሰነዘረ ጥፊ ሁሉ መታቸው፡፡ እንደ እብድ አይተውኝ ተንጠራርተው ወደ ወለሉ ሳቡኝ፡፡ ፈገግ አልኩ - ምንም እንኳን ከዚያ ወዲያ መስቀሉን በበሩ ላይ ማየት ባልችልም እዚያ እንዳለ ግን አውቃለሁ፡፡ ገዳዮቹ ከቤቱ ሄደዋል…. እየዘመሩ ሲሄዱም ሰምቻቸዋለሁ፡፡
ሌሊት ቄሱ ሊያዩን መጡ፡፡ ‹‹በቀጥታ የሄዱት ተንቀሳቃሽ ምስሉን ወዳሳየኋችሁ ስፍራ ነው›› ሲሉ አብራሩልን፡፡ ‹‹ክፍሉን ገነጣጠሉት፡፡ ምንም ማግኘት ሳይችሉ ሲቀሩ ሠራተኛዬን በድብደባ ሊቦጫጭቁት ምንም አልቀራቸው፡፡ ይቅርታ ጠይቀው ሄዱ፡፡ ቢሆንም ይህ ስፍራ ለእናንተ ደህንነት ከአሁን በኋላ ጥሩ አይደለም፡፡ ሠራተኛዬን አባርሬዋለሁ አሁን ተናዷል፤ ጥርጣሬም ገብቶታል፡፡ ከሌሎቹ ሠራተኞች ጋር ጓደኛ ስለሆነ ከአሁን በኋላ በእርግጠኝነት ሁሉም እያንዳንዷን እንቅስቃሴዬን ይከታተላሉ፡፡ ብቻ የፈረንሳይ ወታደሮች ወደ አካባቢያችን በቶሎ እንዲደርሱ ተስፋ እናድርግ
ቀጣዩን ሳምንት በሙሉ ተደናግጠን
👍2