አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የህይወት_ጫፍ....


#ከያሬድ


#ክፍል_ሶስት (የመጨረሻው ክፍል)

ልቤ በሞት ጫፍ ላይ እንደተጠለጠለች ነፍስ ትር ትር እያለች እንደቆምኩ ቁልቁል እያየሁት ጠየኩት እሱም ቀና ብሎ እያየኝ በሀዘን ምክንያት እየፈሰሱ ያሉትን እንባውንና በአፍጫው የመጣውንን ፈሳሽ በእጁ ጠረገና....

" እስቲ ቁጭ በል.... ያኔ እራሴን ባጠፋ ያኔም ዛሬም ባልተገናኘን ነበር ... በል ተቀመጥ...." አለኝ። ተመልሼ ወንበሬ ላይ ቁጭ እያልኩ።
" ያኔ ሞክረህም ቢሆን አግባብ አይደለም " አልኩት እሱም ፈገግ ብሎ አየኝና አለመሞከሩን ጭንቅላቱን ከግራ ወደ ቀኝ በመወዝወዝ ጭምር ነገረኝ በዛው ንግግሩን ቀጠለ።
".... ታውቃለህ በጭንቅላቴ ውስጥ እንደዚህ አይነት ነገር መፈጠሩ ብቻዬን ስለሆኩኝ እንደሆነ አሰብኩ ከመኝታዬ ተነስቼ ከሰው ጋር ለመደባለቅ ወደ ውጭ ወጣሁ ግን ማን አለኝና ማን ጋር ልሂድ በበአል ተርቤያለው ህፃናት እንኳን ብር ኪሳቸው በማያጡበት እኔ ባዶ ኪስ አስር ሳንቲም የሌለኝ የፀዳ ልብስ ሳለብስ መሄጃ ሳይኖረኝ ክርር ባለ የምሳ ሰአት ፀሀይ አስባልት ዳር ቆሜ ደስተኛ ቤተሰቦችን ህፃናትን እያየሁ በሀዘን ልቤ እየተወጋ አይኖቼ እንባ ቋጥረው ሳለ አንተንና ጭንቅላቱን ቢፈልጡት እንኳን ገንዘብ አይደለም ደም እንኳን የማይወጣው ከልጅነት ጭቃ አብኩተን ያደግነውን አማረን ተያይዛቹሁ ስትሄዱ አየኋቹሁ አንተን አላውቅህም እሱን ጠራሁትና ጠጋ ብያቹሁ ሰላም ካልካቹሁ በኋላ እራሴን ዝቅ ማድረጌ እያሸማቀቀኝ እርሀብ ክብርህን ያወርደሀል እናም "እርቦኛል ሳንቲም" ...አላስጨረሰኝም እንደሌለው ነግሮኝ ተያይዛቹሁ መንገድ ጀመራቹሁ እኔ ሽምቅቅ አልኩኝ በመጠየቄ አንተን እንደ እኔ ህይወት በጠቆረው አስፓልት ላይ አይኔን ተከልኩኝና ቀና ስል አንተ ከፊቴ ቆመህ ድፍን ሀምሳ ብር ይዘህ እጅህን ዘርግተሀል የገረመኝ የተናገርከው ቃል ነው ይቅርታ ለታክሲ ከያዝኩት ውጪ ሌላ ምንም ገንዘብ እንደሌለህ ነግረህኝ ሄድክ በጣም ገረመኝ የሰው ልጅ ለሰው የሆነ ነገር ሲያረግ መልስ ይፈልጋል ልጠይቅህ አንተ ግን ምን ፈልገህ አደረክልኝ?" ....አለኝ።
እውነት ግን ምን ፈልጌ አረኩት አላውቅም እናም መለስ ብዬ ጊዜውን ለማስታወስ አሰብኩ አንድ ጊዜ ብልጭ ሌላ ጊዜ ጥፍት በሚል ሁኔታ አስታውሳለው ግን ማንነቱ ትዝ አይለኝም አማረ ማለት ባለ ትዳር ነው ልጅ ግን ያኔ አልወለደም አብረን ነው የምንሰራው ደመወዙ ከእኔ የተሻለ ነው እንደተባለው ገንዘብ ማውጣት አይወድም ያኔ ስራ ቦታችን እዛው እነሱ ሰፈር ስነበር ለበአል ጠርቶኝ ሄጄ ነው ይህ የሆነው ግን ማንነቱን አላስታውስም ........
" እኔንጃ ለምን እንደሰጠሁሁ በቃ ወይ አሳዝነህኝ ....." አልኩት እሱም ተገርሞ ፈገግ አለና።
" ... ሰው ስለሆኩ ችግሬ ተሰምቶህ ነው ... ከዛ ቀን በኋላ መስራቤትህ በር ላይ ሲርበኝ መጥቼ እለምንህ ነበር ባይኖርህ እንኳን አመጣለው ብለህ ትገዛልኛለህ አንዴ የምጠላውን ጥያቄ ጠየከኝ ተናደድኩኝ ... ስራ ለምን አትሰራም እንዴ? አልከኝ ሰው እየራበው አልሰራም ይላል እንዴ? አይለም ለሆዱ ሲል ወይ ይሰርቃል ወይ ይሰራል አሊያም ይደበድባል ብሎም ሊገል ይችላል ቁጭ ብሎ እርሀቡን አይራብም ለምን አትሰራም ከማለት ስራ ሰጥቶ ያን ሰው ምን እንደሚወስን ማየት .... በወቅቱ ስራ ሰጠህኝ እንቢ ሳልልህ መስራት ጀመርኩ አንተንም አብላኝ ከማለት አቆምኩ ሰርቼ ስበላም ውስጤ የነበረው እርካታ ልነግርህ አልችልም ከ15 ቀን በኋላ ሌላ ቦታ ተመድበህ ስትሄድ እንድበረታ ነገርከኝ ነበር .... ያኔ ከጀርባህ እያየሁሁ ፈጣሪን አንድ ነገር ለመንኩት ሰው አርገኝና ብድርህን እንድከፍል...." አለኝና ጥቂት ደቂቃ ፍዝዝ ብሎ ዝም አለኝና ቀጠለ......
" ..... የሚገርምህ በችግሮቼ ወቅት አንድ ቀን ከእንቅልፌ ደስተኛ ሆኜ ተነስቼ አላውቅም እናም..... ያኔ አንተ ከሄድክ በኋላ ሁለት ወር ሳልሰራ አሰናበቱኝ እጅግ አለቀስኩ እንደገና እርሀቤን ሳስብ የረሳሁትን ሞት መመኘት ጀመርኩ....
ሁሌም ከፍቶኝ እነሳ እንዳልነበር ከቀናት በኋላ እየራበኝ ነገር ግን ደስተኛ ሆኜ ተነሳው ገረመኝ እርሀቤን ሳይሆን ደስታዬን ማሰብ ጀመርኩ ፈጣሪን ሳማርር እና እንደረሳኝ አምኜ ተመስገን ማለት ትቼ እንዳልነበር ተመስገን አልኩኝ በባዶ ሆዴ ግን ደስተኛ ሆኜ ከደሳሳዋ ቤቴ ወጣሁ ለካ ፈጣሪ ይዘገያል እንጂ ለጥያቄዎች መልስ አለው የራስን ይመስለናል እንጂ አይረሳንም እናም ያኔ ትልቅ ነገር አዘጋጅቶልኝ ነበር እኛ ሰዎች ችኩል ስለሆንን ነው ስለ አንተም ብዙ ነገር ሰምቻለው ተስፋ አትቁረጥ ያቺ ቀን ትመጣለች ...." አለኝና የእጅ ሰአቱን ተመለከተና".... አሁን ወደ ውጭ በረራ አለብኝ ቸኩያለው ስመጣ እደውልሀለው እሺ ማናችንም በየዕምነታችን ተስፈችንን በፈጣሪ ላይ እናርግ እንገናኛለን....." አለኝና ትከሻዬን ነካ ነካ አርጎኝ ተሰናበተኝ እኔም ፈጣሪን ያማረርኩበትን ወቅቶች እያሰብኩ በሀሳብ ተመስጬ ሳለው ከአጠገቤ ተነስቶ ሄዷል ።
ከሀሳቤ ነቅቼ ዙሪያዬን ተመለከትኩኝና ሳለስበው ከተቀመጥኩበት በደስታ ውስጥ ሆኜ ከሆቴሉ ወጣሁ ፈገግና በርታ እንደወጣችው ቀን የእኔም ህሊናና መንፈስ ፍክት ብሎ ውስጤ በደስታ ተሞልቶ መንገድ ጀመርኩ።

አለቀ

ነገ በሌላ ታሪክ እንገናኝ እስቲ እናንተም #Share እያደረጋችሁ።

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ።
👍2