አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
"ሰሎሜ አንተን ሁለቴ ከድታሀለች ..ከማንም አስበልጣ ብታፈቅርህም ልብህን ግን ደጋግማ ሰብራዋለች። ከእኔ መወለድ በፊትም ሆነ ከእኔ መወለድ በኋላ ያደረገችብህን ነገር ቂም በሆድህ ቆጥርህ ነበር፡፡ያንን ይቅር ማለት እና መርሳት አልቻልክም፣ ጁኒየር ግን እንደአንተ ስላልሆነ እሷን በደስታ ነው የተቀበላት ፡፡ ቀስ በቀስም ትኩረቷን ማግኘት ጀመረ እና ጥረቶቹ ውጤት አስገኙለት… አንተን ረስታ ከእሱ ጋር ፍቅር እንደያዛት ስታስተዋል ከነከነህ፣ይባስ ብለው ሊጋቡ እንደሆነ ደረስክበት ….ከዛ ምን አደረክ ቀጥታ ገድለሀት ከእነሱ አንዳቸው እንደገደሏት እንዲያስቡ አደረክ ወይስ ምን አይነት የበቀል ዘዴ ነው የተጠቀምከው…..?ምን አልባት እናቴን ብቻ ሳይሆን ጁኒዬርንም ተበቅለኸው ይሆናል…?››

"በጣም ጥሩ አቃቢ ህግ ነሽ።በእውነት አድናቂሽ ነኝ…. ግን በዚያ መላ ምትሽ ትልቅ አመክንዬ ጥሰት አለበት፡፡››አለና የተቀመጠበትን ኩርሲ ወደእሷ አስጠጋ ….ምን ሊያደርግ ነው በሚል ስጋት በትኩረት ተመለከተችው፡፡

"አንቺ ..በብዙ ግምቶች እየተወዛገብሽ ነው…አንዱንም ማረጋገጥ አትችይም…በእኔ ላይ ምንም መረጃ የለሽም…ስለዚህ, ለምን የሁላችንንም ህይወትን ቀላል አታደርጊልንም ››አለና እጆቹን ትከሻዋ ላይ ጭነ… ወደራሱ ጎተተና ጉንጮን ሳማት፡፡
"ምክንያቱም አልችልም።›› ከንግግሯ በስተጀርባ ያለውን የተስፋ መቁረጥ ስሜት ሰማ እና እሷን ለመስበር ከግማሽ በላይ መንገድ ላይ እንደደረሰ አወቀ።

"ለምን አትችይም?" ጠየቃት፡፡

‹‹ምክንያቱም እናቴን የገደላትን፤መገደሏን አውቆ ገዳዩን ለመታደግ የተባበረውን በጠቅላላ መቅጣት እፈልጋለሁ።››
እጁን ከትከሻዋ ላይ አነሳና …አይን አይኗል በትኩረት እያየ….."ይህን ለሰሎሜ ብለሽ አይደለም እያደረግሽ ያለሽው… ለራስሽ ነው የምታደርጊው"አላት፡፡

"ያ እውነት አይደለም!"

" አያትሽ በጭንቅላትሽ ውስጥ የፈጠረችብሽ የማይሆን ሀሳብ አለ ፡፡እናም በእናትሽ ህይወት ውስጥ በተሳሳተ ጊዜ በመምጣትሽ እና ኑሮዋን በማበላሸትሽ ራስህሽ ይቅር ማለት አልቻልሽም።"

"በፈጣሪ አንተው ነህ ስለ ስነ ልቦና ግጭት ለእኔ የምታወራው?" ብላ በቁጣ ጠየቀችው። ቀጠለችናም "ገመዶ ራስ ወዳድ መሆንህን ለማወቅ ስለአንተ በቂ እውቀት አለኝ። ሌላ ሰው እንደግል ንብረትህ ስለምትቆጥር  ሲነኩብህ ትበሳጫለህ ።››

"አገላለጿ  ፈታኝ ነበር። ››
"ገመዶ ፣እናቴን ይቅር ለማለት በጣም የከበደህ ነገር ለምንድን ነው? እሷ ከሌላ ወንድ ጋር ስለተኛች ነው? ወይስ እድሉ እያለህ እሷን ባለማግባትህ ራስህን ይቅር ማለት አልቻልክም?"
ገላዋን በእጁ ነቀነቀ፣ ከዚያም እስኪነካኩ ድረስ ወደ ፊት አዘነበለ። "አንድ ጊዜ አስጠንቅቄሻለሁ ….እናትሽ ከጁኒየር ጋር የነበራትን ግንኙነት ለማስቀጠል እና ለምን እንደዛ እሷን ሊያፈቅራት እንደቻለ ለማወቅ ያለሽን የማወቅ ጉጉት ማርካት እየጣርሽ ነው"

"አይ ..ያ እውነት አይደለም" ብላ በቁጣ ካደች

" አይመስለኝም።"

‹‹ አንተ ታመሃል…?"አለችው፡፡

አንገቱን ጎንበስ አድርጎ ሳማት። በዝምታ ተቀበለችው….ከንፈሮቹን ወደከንፈሯ አስጠጋት…
…ባለችበት ሳትነቃነቅ ጠበቀችው፡፡ ከንፈሮቾን በስሱ ይመጣቸው ጀመር … ከንፈሯቾ እርጥብ እና ሙቀት የሚረጩ ከመሆናቸውም በላይ ጣፋጭ ነበሩ፣ ቀኝ እጁን አንቀሳቀሰና
በለበሰችው ሹራብ ውስጥ ሰቅስቆ ጡቷን በእጁ ጨመቀ። የጡቷን ጫፎች በሁለት ጣቶቹ ማፍተልተል ጀመረ… ጩኸት የተቀላቀለበት የጣር ድምፅ ከጉሮሮዋ ወጣ።አንገቱን ቀና አደረገና ቁልቁል ፊቷን ተመለከተ። በእጁ መዳፍ ውስጥ ተፈጥርቃ እንደተያዘች ትንሽ የዱር ፍጡር ልቧን ሲንፈራገጥ ይሰማዋል። አይኖቿ ተጨፍነው ነበር። መልሶ ከንፈሯን ጎረሰ…ምላሱን ወደውስጥ ከተተ…ከተቀመጠችበት ኩርሲ ተንሸራተተችና ደረቱ ላይ ተለጠፈችበት….ከተቀመጠበት ተነስቶ ልክ እንደህጻን ልጅ አቅፎ ወደቤቱ ውስጥ ይዞት ሄዶ አልጋው ላይ ሊዘርራትና ያለምንም ገደብ ሙሉ በሙሉ ከእሷ ጋር ለመቅለጥ እና ከእሷ ጋር ለመጥፋት ከፍተኛ ፍላጎት ጉሮሮዋ ስር ተሰነቀረበት…..እንደዚህ ካደረገ ወደኃላ መመለስ እንደማይችል እና ምንም ነገር እስከአሁን እንደነበረው እንዳማይሆን ያውቃል፡፡ምን ያድርግ…ልቡና አእምሮው ከፍተኛ ፊልሚያ ላይ ገቡበት፡፡ በመጨረሻ አእምሮው በልቡ ተሸንፎ እሷን ወደውስጥ ተሸክሞ ሊገባ ሲንቀሳቀስ የውጭ በራፍ በሀይል ሲንኳኳ ሰማ….ሁለቱም ከገቡበት መደንዘዝ እኩል ነቁ…..የበራፉ መንኳኳት ቀጠለ….ገመዶና አለም ተላቀቁ….ከተቀመጡበት የተዘበራረቀ ልብሷንና የተጎሳቆለ ፀጉሯን ማስተካከል ጀመረች….እሷ ሙሉ በመሉ እራሷን እንዳስተካከለች እርግጠኛ ከሆነ በኃላ በንዴት ሄዶ በራፉን ከፈተው..አቶ ፍሰሀ ነበር፡


ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
58👍13🔥4👎1
‹‹እኔ እንጃ …ትኑር አትኑር አይታወቅም..ሰው ልኬ  ነበር… ሲያንኳኩ ከውስጥ የሚመልስ ሰው የለም አሉኝ…ግን ምንድነው? የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ?››

‹‹ገመዶ ይህቺ የሰሎሜ ልጅ በጣም አደገኛ ነች..ቀድማ ጥቃት ጀምራለች….ሳታጠፋን የምታቆም አይመስለኝም››

‹‹ምን ተፈጠረ››

‹‹ቴሌግራምህን ክፈት የተፈጠረውን ልኬልሀለው….ዛሬውኑ አፍነን ወደተዘጋጀላት ቦታ መውሰድ አለብን…ቤት ካለች እንዳትለቃት ..እስክመጣ አብረሀት ሁን››ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡

ገመዶ መኪናውን ዳር አሲይዞ አቆመና ቴሌግራሙን ከፈተ …ከጁኒዬር አንድ ቪዲዬ ተልኳለታል፡፡

‹‹የሻሸመኔ ከተማ ወክሎ ለምክር ቤት የሚወዳደረው እጩ ተወዳዳሪው ስለእናቴ ግድያ ያውቃል!!››ይላል ርዕሱ…በንዴት እየተንቀጠቀጠ ከፈተው፡፡ሙሉ የአለም ምስል በእስክሪኑ ሞላ….፡፡በእናቷ እና በጁኒዬር..በእናቷ እና በገመዶ መሀከል ያለውን የልጅነት ግንኑኙነት ትዘረዝርና…እሷ እስከተወለደችበት ጊዜ ያለውን ታሪክ ተናግራ…ቀጣዩን ከሶስት ቀን በኃላ በተመሳሳይ ሰዓት ይጠብቁ በሚል ይቋረጣል፡፡ቪዲዬ ከተለቀቀ ገና አንድ ሰዓት ቢሆነውም..8 ሺ እይታ አግኝቷል…ከአንድ ከሁለት ቀን በኃላ በመላው ሀገር እንደሚዳረስ እርግጠኛ ነው…..ስልኩን ወደኪሱ አስገባና መኪናዋን አንቀሳቀሰ…አለም ቤት ጋር ሲደርስ ሳጂኑ በታዘዘው መሰረት በረንዳው ላይ ቆሞ እየጠበቀው ነበር፡፡

‹‹እ ምንም ነገር የለም››

‹‹አይ ምንም ነገር የለም››መለሰለት፡፡ኩማንደሩ ወደ ጓሮ ዞረ…ሳጅኑ ተከተለው….የጓሮውን በር ገፋ ሲያደርገው ተከፈተለት..ተንደርድሮ ወደውስጥ ገባ፡፡ በየክፍሉ እየተዘዋወረ ፈለገ…የለችም…መኝታ ቤቷ ገባና ቁም ሳጥኗን ከፈተ ባዶ ነው…ልብሷ ..ሻንጣዋ…ላፕቶፖ የለም፡፡አንድ ብጣሽ ወረቀት ጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል፡፡አነሳና ተመለከተው፡፡በንዴት ወደሳጅኑ ዞረና፡፡‹‹ምንድነው ኦና ቤት ነበር እንዴ ስትጠብቁ የነበረው?››

‹‹ ሄዳለች ማለት ነው››ሳጅኑ በድንጋጤ እና ግራ በመጋባት መልሶ ጠየቀ፡፡

‹‹ብሽቅ ናችሁ….››አለና በንዴት የፊት ለፊቱን በር ከፍቶ ወደበረንዳ ሲወጣ ጁኒዬር እየተንደረደረ ሲመጣ ተገጣጠሙ፡፡

‹‹አገኘሀት…?የት አለች?››

‹‹የለችም?››

‹‹የለችም ማለት?››

ኩማንደሩ ለጁኒዬር ሌላ መልስ ከመመለሱ በፊት ወደ ሳጅኑ ዞረና ‹‹ሳጅን በቃ አሁን አታስፈልግም..እዚህ ያላችሁ ስራ ተጠናቋል መሄድ ትችላለህ›› በማለት አሰናበተው፡፡

‹‹ግን እኮ መኪናዋ እንደቆመች ነው፡፡››
ገመዶ ‹‹መኪናዋን ከተጠቀመችማ በቀላሉ እንደምንከታተላት ታውቃለች..ለዛ ነው ማንም ሳያያት በጓሮ በር ወጥታ የተሰወረችው፡፡እቅዳችንን በሆነ መንገድ ያወቀችብን ይመስለኛል››ሲል ጥርጣሬውን ተናገረ፡፡

‹‹እንዴት ልታውቅ ትችላለች…?.ማን ሊነግራት ይችላል?››

‹‹አላውቅም…ግን እቃዎቾን ጠቅልላ ማንም ሳያይ በጓሮ በራፍ ወጥታ ነው የተሰወረችው….እና መኝታ ቤቷ ይሄንን ወረቀት ጥላ ነው ሄደችው..››አለና አንድ ብጣሽ ወረቀት አቀበለው፡፡

ለገመዶ..ጁኒዬርና ለአቶፍሰሀ….
እኔን ከዚህ ጫወታ ገለል ማድረግ እንደዚህ ቀላል አይሆንላችሁም፡፡ከዛሬ ጀምሮ ከፍትህ ይልቅ በቀልን መርጫለው፡፡ አድናችሁ ካገኛችሁኝ ግደሉኝ….ግን ያንን ማድረግ ከመቻላችሁ በፊት በየቀኑ አንድ አንድ ክንፋችሁን....ቀጥሎ እጆቻችሁን …ከዛም እግራችሁን… ከዛም አይኖቻችሁን..እያልኩ አጠፋችኋላው…..፡፡በማንኛውም ሰዓት ከመሀከላችሁ(ማለት..ገመዶ፤ጁኒዬር፤ስርጉት፤አቶ ፍሰሀ፤ሳራ)ከአምስታችሁ እናቴን የገደለው  ሰው  ወንጀሉን  አምኖ  አጅን  ለመንግስት  ከሰጠ በቀሌን  አቆማለው
….ካለበለዚያ ሁላችሁንም አጠፋችኋላው….የማስጀመሪያው ርችት ተተኩሷል …ሰዓቱ እየቆጠረ ነው…ለእኔም ለእናንተም መልካም እድል፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍42😱2218🔥1