‹‹እኔ እንጃ …ትኑር አትኑር አይታወቅም..ሰው ልኬ ነበር… ሲያንኳኩ ከውስጥ የሚመልስ ሰው የለም አሉኝ…ግን ምንድነው? የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ?››
‹‹ገመዶ ይህቺ የሰሎሜ ልጅ በጣም አደገኛ ነች..ቀድማ ጥቃት ጀምራለች….ሳታጠፋን የምታቆም አይመስለኝም››
‹‹ምን ተፈጠረ››
‹‹ቴሌግራምህን ክፈት የተፈጠረውን ልኬልሀለው….ዛሬውኑ አፍነን ወደተዘጋጀላት ቦታ መውሰድ አለብን…ቤት ካለች እንዳትለቃት ..እስክመጣ አብረሀት ሁን››ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡
ገመዶ መኪናውን ዳር አሲይዞ አቆመና ቴሌግራሙን ከፈተ …ከጁኒዬር አንድ ቪዲዬ ተልኳለታል፡፡
‹‹የሻሸመኔ ከተማ ወክሎ ለምክር ቤት የሚወዳደረው እጩ ተወዳዳሪው ስለእናቴ ግድያ ያውቃል!!››ይላል ርዕሱ…በንዴት እየተንቀጠቀጠ ከፈተው፡፡ሙሉ የአለም ምስል በእስክሪኑ ሞላ….፡፡በእናቷ እና በጁኒዬር..በእናቷ እና በገመዶ መሀከል ያለውን የልጅነት ግንኑኙነት ትዘረዝርና…እሷ እስከተወለደችበት ጊዜ ያለውን ታሪክ ተናግራ…ቀጣዩን ከሶስት ቀን በኃላ በተመሳሳይ ሰዓት ይጠብቁ በሚል ይቋረጣል፡፡ቪዲዬ ከተለቀቀ ገና አንድ ሰዓት ቢሆነውም..8 ሺ እይታ አግኝቷል…ከአንድ ከሁለት ቀን በኃላ በመላው ሀገር እንደሚዳረስ እርግጠኛ ነው…..ስልኩን ወደኪሱ አስገባና መኪናዋን አንቀሳቀሰ…አለም ቤት ጋር ሲደርስ ሳጂኑ በታዘዘው መሰረት በረንዳው ላይ ቆሞ እየጠበቀው ነበር፡፡
‹‹እ ምንም ነገር የለም››
‹‹አይ ምንም ነገር የለም››መለሰለት፡፡ኩማንደሩ ወደ ጓሮ ዞረ…ሳጅኑ ተከተለው….የጓሮውን በር ገፋ ሲያደርገው ተከፈተለት..ተንደርድሮ ወደውስጥ ገባ፡፡ በየክፍሉ እየተዘዋወረ ፈለገ…የለችም…መኝታ ቤቷ ገባና ቁም ሳጥኗን ከፈተ ባዶ ነው…ልብሷ ..ሻንጣዋ…ላፕቶፖ የለም፡፡አንድ ብጣሽ ወረቀት ጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል፡፡አነሳና ተመለከተው፡፡በንዴት ወደሳጅኑ ዞረና፡፡‹‹ምንድነው ኦና ቤት ነበር እንዴ ስትጠብቁ የነበረው?››
‹‹ ሄዳለች ማለት ነው››ሳጅኑ በድንጋጤ እና ግራ በመጋባት መልሶ ጠየቀ፡፡
‹‹ብሽቅ ናችሁ….››አለና በንዴት የፊት ለፊቱን በር ከፍቶ ወደበረንዳ ሲወጣ ጁኒዬር እየተንደረደረ ሲመጣ ተገጣጠሙ፡፡
‹‹አገኘሀት…?የት አለች?››
‹‹የለችም?››
‹‹የለችም ማለት?››
ኩማንደሩ ለጁኒዬር ሌላ መልስ ከመመለሱ በፊት ወደ ሳጅኑ ዞረና ‹‹ሳጅን በቃ አሁን አታስፈልግም..እዚህ ያላችሁ ስራ ተጠናቋል መሄድ ትችላለህ›› በማለት አሰናበተው፡፡
‹‹ግን እኮ መኪናዋ እንደቆመች ነው፡፡››
ገመዶ ‹‹መኪናዋን ከተጠቀመችማ በቀላሉ እንደምንከታተላት ታውቃለች..ለዛ ነው ማንም ሳያያት በጓሮ በር ወጥታ የተሰወረችው፡፡እቅዳችንን በሆነ መንገድ ያወቀችብን ይመስለኛል››ሲል ጥርጣሬውን ተናገረ፡፡
‹‹እንዴት ልታውቅ ትችላለች…?.ማን ሊነግራት ይችላል?››
‹‹አላውቅም…ግን እቃዎቾን ጠቅልላ ማንም ሳያይ በጓሮ በራፍ ወጥታ ነው የተሰወረችው….እና መኝታ ቤቷ ይሄንን ወረቀት ጥላ ነው ሄደችው..››አለና አንድ ብጣሽ ወረቀት አቀበለው፡፡
ለገመዶ..ጁኒዬርና ለአቶፍሰሀ….
እኔን ከዚህ ጫወታ ገለል ማድረግ እንደዚህ ቀላል አይሆንላችሁም፡፡ከዛሬ ጀምሮ ከፍትህ ይልቅ በቀልን መርጫለው፡፡ አድናችሁ ካገኛችሁኝ ግደሉኝ….ግን ያንን ማድረግ ከመቻላችሁ በፊት በየቀኑ አንድ አንድ ክንፋችሁን....ቀጥሎ እጆቻችሁን …ከዛም እግራችሁን… ከዛም አይኖቻችሁን..እያልኩ አጠፋችኋላው…..፡፡በማንኛውም ሰዓት ከመሀከላችሁ(ማለት..ገመዶ፤ጁኒዬር፤ስርጉት፤አቶ ፍሰሀ፤ሳራ)ከአምስታችሁ እናቴን የገደለው ሰው ወንጀሉን አምኖ አጅን ለመንግስት ከሰጠ በቀሌን አቆማለው
….ካለበለዚያ ሁላችሁንም አጠፋችኋላው….የማስጀመሪያው ርችት ተተኩሷል …ሰዓቱ እየቆጠረ ነው…ለእኔም ለእናንተም መልካም እድል፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍43😱22❤18🔥1