አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?


አሁንም ግፍ አይበቃሽም
ዘንድሮም ለምለም ትያለሽ
ካቀፍሽው ቅጠል ባለፈ
የለመለመ ምን አለሽ?

ካቻምናም አምናም መተሻል
አቅፈንሽ አጥነን ደግሰን
አመትሽ ውበቱ ላይቆይ
እያደር ሊያተራምሰን

አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?

አምና ተስፋ አስደረግሺኝ
ደክሜ ቤቴን ሰራሁኝ
አልቅሼ ልገባበት ስል
ይፈርሳል ሁሉ ሰማሁኝ
አሁንም ተስፋ አልቆረጥኩም
ቃልሽን ስመላልሰው
አመትህ ተባርኳል ብለሽ
የላክሺኝ እንደ ሞኝ ሰው
ስታገል ከማይሽር ህይወት
መቀመቅ ነፍሴን ሲውጣት
ወደፊት ፈቀቅ እያልኩኝ
ሞት ልቤን እንዳይለውጣት

"አበባ አየሆሽ" አትበዪኝ
አበባ አልቸገረኝም
ዘፈንሽ አንገሽግሾኛል
ጨዋታሽ አይሰማኝም
በያመት ደምቀሽ ስትመጪ
ህፃን ልጅ ለምትመስዪው
ግጥሙን በምነግርሽ ቃል
ስትዘፍኚ አስተካክዪው

"የሀገሬ ልጆች ውጡ በተራ
ቅስም ሰብሬ  ሰው እስክሰራ
እንኳን ሰውና  የለኝም እድል
ሁሌ መጣለው አመት ላጎድል
አመት አጉድዬ ስገባ ቤቴ
ደስታ ይሰማታል የእንጀራ እናቴ"
አደዪ
የሞት ጉዳዪ
"ኡኡ" በዪ

እንደዚህ ብለሽ ዝፈኚ
ግጥሙን አስተካክለሽው
በቃ አንቺም እንዳገሬ ሰው
ጊዜን ነው የተማመንሽው?

"ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ
ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ"

ሆሆሆሆ!

አታፍሪም ደግሞ
ልክ እንደ ንፁህ እንዳልበደለ
ተስፋሽ ምስኪኑን እየገደለ
ከዘመን ዘመን ማትለወጪ
ጉድ ያዘለ አመት አቅፈሽ ምትሰጪ
ሆ ብለሽ መጣሽ?
ሆ ብለሽ ውጪ!

ለተድላ ሳይሆን
ለሞት ዋዜማ ፡ እያስጨፈርሺኝ
በመጣሽ ቁጥር
ሆ የምልልሽ ፡ ሞኝ አደረግሺኝ?

አሁን ንገሪኝ
ስለ አመትሽ
ይብስብኛል ወይስ ድናለው?
ዘፈኑን ተዪ ፡ ያንቺን ስሞታ ለምጄዋለው

ባለእንጀሮችሽ በተራ ገቡ
አዝማች አባትሽ ሌላ አገቡ
እንጨቱን ሰብረሽ ቤት እስክትሰሪ
ለእንጀራ እናትሽ ሳትናገሪ
እድጅ አድረሻል ኮከብ ስትቆጥሪ

እኔ ምስኪኑ

ምን ያገባኛል ስላንቺ ኮከብ
ምን ያገባኛል የእንቅልፍሽ ማጠር
የኔ ችግር ነው ወሰን የሌለው
የኔ ስቃይ ነው  የማይቆጠር

እህት አበባ  ፡ እህት አበባ
እህት አበባ  ስትልሽ ከርማ፤
ጥላሽ ብትሄድም በሀምሌ ጭለማ
እኔ ላይ "አዬዬ".. አትበዪብኝ፡
ለኔ አመቱ ነው  የጨለመብኝ።

ተይ ባለጊዜ..
ተይ እንቁጣጣሽ..
ሀገር ጉድ አቅፈሽ ፥
ሁሌ እየመጣሽ፦

እንኩ አትበዪን፡

ሀዘን ቁስላችን ፡ ድኖ ሳይገግም፤
ካምናው የሚብስ
ሌላ አዲስ አመት ..አንፈልግም!

🔘ሚኪያስ ፈይሳ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢128👏3