አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
"አይደለም…..ክርምት ቤተሰቦቼን ልጠይቅ ብላ ኮፈሌ ሄዳ ነበር….ግን ስትንዘላዘል አንቺን ፀንሳ ተመለሰች….አላወቀችም ነበረና ሀገር ሳላም ነው ብላ ከገመዶም ሆነ ከልጄ ጋር ያላትን ግንኙነት ቀጥላበት ነበር….በኃላ ግን ማርገዟን አወቀች….ማስወረድም አልቻለችም መሰለኝ መልሳ ወደኮፈሌ ተመልሳ ጠፋች….ዘመዶቾ ልጁን አስገድደው እንዲያገባት አደረጉ
…ግን ሰማንያውን ፈረመ እንጂ አንድ ቤት እንኳን አልገቡም ነበር…ከዛሬ ነገ እቤት ተከራይቶ እና እቃ አሞልቷ ይጠቀልለኛል ብላ ስትጠብቅ እሱ ሹልክ ብሎ ውትድርና ተቀጠረና ሄደ… እሷም የተቀበተተ ሆዷን እና የሰማንያ ወረቀቷን ይዛ አይኗን በጨው አጥባ ወደእዚህ ተመለሰች….ደጋግሜ እንደነገርኩሽ ሁሉንም ወንዶች የሚያደነዝዝ አዚም ስላለባት ሁለቱም ቢበሳጩባትም ከህይወታቸው ሊያስወግዷት አልፈቀዱም…..እስከነ ዲቃላዋ ይንከባከቦት ጀመረ…. ከዛ አንቺም ተወለድሽ.. ዲቃላ ያስታቀፋትም እዛው ወታደር ቤት እንደገባ መሞቱን መርዶ መጣላት፡

"ውሸትሽን ነው!" አለም እንዳትወድቅ ስለፈራች  የወንበሩን እጄታ ያዘች።

"ለምን እዋሻኛለሁ?ቤተሰቦቼን ከአንቺ የበቀል ጥፋት ለመጠበቅ እየሞከርኩ ነው። ፍሰሀ በአመታት ልፋት የገነባውን ሁሉ እንድታጠፊ አልፈቅድም። በቤተሰቤ ውስጥ አለመግባባት እንድትፈጥሪ አልፈቅድም። ከዚህ በፊት እናትሽ እንደዛ አድርጋ ነበር… አሁን.. ግን አልፈቅድም።

"ሴቶች… ሴቶች." ጁኒየር እየሳቀ ወደ ክፍሉ ገባ።‹‹ ይህ ጩኸት ምንድነው? ሸረሪት ተመለከታችሁ እንዴ?"

በመካከላቸው ያለውን ጥላቻ ሲታዘብ ቀልዱን አቆመና ግራ በመጋባት እያፈራረቀ ያያቸው ጀመር ። በአቅራቢያው መብረቅ የወረደ ይመስል አለም ደርቃና ገርጥታ ተመለከታ፡፡

"እናቴ? አሌክስ? ምን ተፈጠረ?"

አለም ምንም ሳትናገር ወንበሩ ላይ የተንጠለጠለውን ቦርሳዋን አነሳችና ከክፍሉ በፍጥነት ወጣች እና ሄደች ፡፡ጁኒየር አለምን ከኋላ ተከትሎ ከመግቢያው በር ጋር ደረሰባት ፡፡

"ምንድን ነው የተፈጠረው?"

አለም እንባዋን እንዳያይ ፊቷን በእጆቾ ሸፈነች።

"ምንም።"

" ሻይ ለመጠጣት እንደተቀጣጠራችሁ ስሰማ እኮ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር››

"ሻይ? ሃ!ሻይ እንድንጠጣ አይደለም የጋበዘችኝ››

‹‹እና ለምንድነው?››

እንባዋ እንዳይወርድ ለማድረግ ብላ ዓይኖቿን ብታሽም አልተሳካላትም "ለነገሩ ስለነገረችኝ ማመስገን አለብኝ ።"

"ምንድነው የነገረችሽ?" "እኔ ዲቃላ መሆኔን ."

የጁኒየር ፊት በድንጋጤ ባዶ ሆነ።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍4418😢1
በሃሳቡ ሳቀች። "እንዴት እንደ አንቺ ያለች ደካማ ሴት ከመካከላችን ትልቅ እና የታጠቁ ወንዶችን ልትጠብቅ ትችላለች ለማለት ነው?አታስተውልም እንዴ ጁኒየር እኮ ከእሷ ጋር ፍቅር እየያዘው ነው."

"ታዲያ ቢይዘው ምን ችግር አለው ?" አለ በሚያብረቀርቅ ፈገግታ። ሳራ "እናቷ ልቡን ሰብራው ነበር ፣ ያ አያስጨንቅህም?"።
ፍሰሀ ፊቱን አኮሰታትሮ፣

"ያ ከረጅም ጊዜ በፊት የሆነ ነው። እና አለም እንደ እናቷ አይደለችም።"

"በዛ እርግጠኛ መሆን አልችልም." አለችና ሳራ ወደ ኮርኒሱ ተመለከተች።

"አለም እንደ ሰሎሜ ተለዋዋጭ እና ?ገራሚ ሴት አይደለችም….እንደውም እሷ በጣም ጎበዝ ሴት ነች ፣ ምናልባት ለጁኒየር የምታስፈልገው እንደእሷ አይነት ሴት ልትሆን ትችላለች
… እስከአሁን ብዙ ሴቶች ለማግባት ሞክሮ አንዱም ትዳር ሊሰምርለት አልቻለም፤እንደ እሷ  ምን እንደሆነ የምትነግረው ሴት ይፈልጋል ።"

"በነገራችን ላይ አሁን የት ነው ያለው? አሁንም እንደተናደደብኝ ነው?" ብላ በጭንቀት ጠየቀች።

" ተበሳጨቷል … ነገር ግን እንደ ሁልጊዜውም በመስከር ብስጭቱን ሊረሳ ሄዷል ." ሁለቱም ተሳሳቁ።

" ተጠንቅቆ እንደሚነዳ ተስፋ አደርጋለሁ።"
‹‹ምን አልባት …ሌሊቱን እዛው የሚያሳልፍ ይመስለኛል ." "ወይ ተው እንጂ ?"
"እንደዛ ቢያደርግ …አይገርመኝም" አለ ፍሰሀ

"አለም እራሷን ለማስተካከል የተወሰነ ጊዜ ያስፈልጋታል። ዛሬ ማታ የሚፈልገውን መጽናኛ የምትሰጠውን ሌላ ሴት ያገኛል።››
የአቶ ፍሰሀ አይን  ወደ ሚስቱ ዳሌ  ዝቅ አለ፣ …እጁ ሰውነቷን ሲዳብሳት  በድካም ቃተተች።

"እናንተ ወንዶች ! ስለእዛ ጉዳይ ብቻ ነው የምታስቡት? -"ተነጫነጨች "እንዲህ አይነት ቋንቋ አትጠቀሚ። ጭካኔ ነው።››
‹‹ ዛሬ ማታ ይህን ማድረግ አልፈልግም። ራስ ምታቴ እየተመለሰ ነው።››
የእሱ መሳም ተጨማሪ ተቃውሞዎችን አስነሳ. ። እሷ ሁል ጊዜ መቃወሟ የማይቀር ነው፡፡ ግን በጭራሽ አይቀበላትም። ከስሜታዊነት ይልቅ በግዴታ ስሜት ለእሱ ምላሽ መስጠቱ እሷን ከመፈለግ አግዶት አያውቅም። እንደውም በተቃራኒው ፍላጎቱን ከፍ ያደርግለት ይሆናል ። ፈጥኖ ልብሱን አውልቆ አንሶላውን ገልጦ ገባ ፡፡

ሳራ የሌሊት ልብሷን ጫፍ ወደላይ ሲሰበስባ እጁን ያዘችና ከለከለችው፡፡ አቶ ፍሰሀ ወደእሷ ተጠጋና ጉንጯን ሳመ እና አቀፋት። ለስላሳ እና፣ ጥሩ መዓዛ ያለው ቆዳዋን መዳበስ ክፉኛ ፈልጎ ነበር … ከእሷ ግር ፍቅር መስራት አምሮታል፡፡

"ፍሰሀ አሁን ተኛ … ይህን የጀመርኩትን ምዕራፍ መጨረስ እፈልጋለሁ" አለችው።

እንደ ፍቅሯ ደረቅ እና ህይወት የሌለውን ልቦለድዋን እንደገና ከፍታለች። ፍሰሀ ከማንበቢያዋ መብራት ርቆ ወደ ሌላኛው የአልጋው ጠርዝ ተጠጋና ፊቱን አዞሮ ተኛ ፡፡ እንደፍላጎቱ ስላልሆነችለት ተበሳጭቶ ነበር፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3217