አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
በሃሳቡ ሳቀች። "እንዴት እንደ አንቺ ያለች ደካማ ሴት ከመካከላችን ትልቅ እና የታጠቁ ወንዶችን ልትጠብቅ ትችላለች ለማለት ነው?አታስተውልም እንዴ ጁኒየር እኮ ከእሷ ጋር ፍቅር እየያዘው ነው."

"ታዲያ ቢይዘው ምን ችግር አለው ?" አለ በሚያብረቀርቅ ፈገግታ። ሳራ "እናቷ ልቡን ሰብራው ነበር ፣ ያ አያስጨንቅህም?"።
ፍሰሀ ፊቱን አኮሰታትሮ፣

"ያ ከረጅም ጊዜ በፊት የሆነ ነው። እና አለም እንደ እናቷ አይደለችም።"

"በዛ እርግጠኛ መሆን አልችልም." አለችና ሳራ ወደ ኮርኒሱ ተመለከተች።

"አለም እንደ ሰሎሜ ተለዋዋጭ እና ?ገራሚ ሴት አይደለችም….እንደውም እሷ በጣም ጎበዝ ሴት ነች ፣ ምናልባት ለጁኒየር የምታስፈልገው እንደእሷ አይነት ሴት ልትሆን ትችላለች
… እስከአሁን ብዙ ሴቶች ለማግባት ሞክሮ አንዱም ትዳር ሊሰምርለት አልቻለም፤እንደ እሷ  ምን እንደሆነ የምትነግረው ሴት ይፈልጋል ።"

"በነገራችን ላይ አሁን የት ነው ያለው? አሁንም እንደተናደደብኝ ነው?" ብላ በጭንቀት ጠየቀች።

" ተበሳጨቷል … ነገር ግን እንደ ሁልጊዜውም በመስከር ብስጭቱን ሊረሳ ሄዷል ." ሁለቱም ተሳሳቁ።

" ተጠንቅቆ እንደሚነዳ ተስፋ አደርጋለሁ።"
‹‹ምን አልባት …ሌሊቱን እዛው የሚያሳልፍ ይመስለኛል ." "ወይ ተው እንጂ ?"
"እንደዛ ቢያደርግ …አይገርመኝም" አለ ፍሰሀ

"አለም እራሷን ለማስተካከል የተወሰነ ጊዜ ያስፈልጋታል። ዛሬ ማታ የሚፈልገውን መጽናኛ የምትሰጠውን ሌላ ሴት ያገኛል።››
የአቶ ፍሰሀ አይን  ወደ ሚስቱ ዳሌ  ዝቅ አለ፣ …እጁ ሰውነቷን ሲዳብሳት  በድካም ቃተተች።

"እናንተ ወንዶች ! ስለእዛ ጉዳይ ብቻ ነው የምታስቡት? -"ተነጫነጨች "እንዲህ አይነት ቋንቋ አትጠቀሚ። ጭካኔ ነው።››
‹‹ ዛሬ ማታ ይህን ማድረግ አልፈልግም። ራስ ምታቴ እየተመለሰ ነው።››
የእሱ መሳም ተጨማሪ ተቃውሞዎችን አስነሳ. ። እሷ ሁል ጊዜ መቃወሟ የማይቀር ነው፡፡ ግን በጭራሽ አይቀበላትም። ከስሜታዊነት ይልቅ በግዴታ ስሜት ለእሱ ምላሽ መስጠቱ እሷን ከመፈለግ አግዶት አያውቅም። እንደውም በተቃራኒው ፍላጎቱን ከፍ ያደርግለት ይሆናል ። ፈጥኖ ልብሱን አውልቆ አንሶላውን ገልጦ ገባ ፡፡

ሳራ የሌሊት ልብሷን ጫፍ ወደላይ ሲሰበስባ እጁን ያዘችና ከለከለችው፡፡ አቶ ፍሰሀ ወደእሷ ተጠጋና ጉንጯን ሳመ እና አቀፋት። ለስላሳ እና፣ ጥሩ መዓዛ ያለው ቆዳዋን መዳበስ ክፉኛ ፈልጎ ነበር … ከእሷ ግር ፍቅር መስራት አምሮታል፡፡

"ፍሰሀ አሁን ተኛ … ይህን የጀመርኩትን ምዕራፍ መጨረስ እፈልጋለሁ" አለችው።

እንደ ፍቅሯ ደረቅ እና ህይወት የሌለውን ልቦለድዋን እንደገና ከፍታለች። ፍሰሀ ከማንበቢያዋ መብራት ርቆ ወደ ሌላኛው የአልጋው ጠርዝ ተጠጋና ፊቱን አዞሮ ተኛ ፡፡ እንደፍላጎቱ ስላልሆነችለት ተበሳጭቶ ነበር፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3217