#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
ጁኒዬር አለምን ይዞ ወደ ወላጆቹ ቤት ሲደርስ ሳሎን ያለው አባቱ ብቻ ነው፡፡አቶ ፍሰሀ ከመቀመጫቸው ተነስተው እጇን እየጨበጡ"ጁኒየር ስላገኘሽ እና እንድትመጪም ስላሳመነሽ ደስ ብሎኛል" አላት፡፡
"እኔም እዚህ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ።"
"ደህና….ተቀመጪ››
ተቀመጠች፡፡
"ምን ትጠጫለሽ?"ሲል ጁኒዬር ጠየቃት፡፡ "ነጭ ወይን ካለ ደስ ይለኛል…. እባክህ" አለች.
አቶ ፍሰሀ በጥቋቁር አይኖቹ ትኩር ብሎ እያያት "ነጭ ወይን,? እንዳጋጣሚ ባለቤቴም የነጭ ወይን አፍቃሪ ስለሆነች ከእኛ ቤት ጠፍቶ አያውቅም… አሁን ትመጣና ትቀላለናለች
፡፡››አላት
ጁኒየር መጥሪያውን ሲጫን የቤቱ አገልጋይ ከውስጠኛው ክፍል እየሮጠች መጣች…ነጭ ወይን አምጥታ ለአለም እንድትቀዳላት አዘዛት፡፡ወይኑ መጣና ተቀዳላት..አቶ ፍሰሀና ልጃቸው ጁኒዬር ቢራ ያዙ፡፡
‹‹ጁኒዬር ወደቤት ይዞሽ እንዲመጣ ጠይቄው ነበር..እንዲህ በፍጥነት ይሳካለታል አላልኩም ነበር፡፡››
አለም ግራ ተገባች..እናም ወደ ጁኒዬር ዞር ብላ‹‹ወደእዚህ እንድመጣ ያንተ ፍላጎት መስሎኝ ነበር እኮ››
‹‹እሱማ የእኔም ፍላጎት ነው››አላት በእፍረት አንገቱን አቀርቅሮ፡፡ አለምም ወደ ፍሰሀ ዞራ "እሺ ለምን ነበር የፈለከኝ?"አለችው፡፡
በእሷ ቀጥተኛነት ለጊዜው ያልተደሰተ ይመስላል፣ ቢሆን እሱም በተመሳሳይ መንገድ መለሰላት
"ጠላቶች እንድንሆን… አንቺን በደንብ ማወቅ እፈልጋለሁ።"አላት፡፡
"እኔም የመጣሁት ለዚህ ነው አቶ ፍሰሀ።"አለችው ፍርጥም ብላ፡፡
እሷን ትንሽ ጊዜ ወስዷ ሊያጠናት ሞከረ። "እንዴት ጠበቃ ለመሆን ፈለግሽ?"የተለመደ ግን ደግሞ ድንገተኛ ጥያቄ ጠየቃት፡፡
"የእናቴን ግድያ ለመመርመር ወንጀለኛውን ለፍርድ ለማቅረብ እንድችል.››
መልሱ በድንገት ወደ ከንፈሮቿ የመጣ ነው፣ ይህም መልሷ እንሱን ብቻ ሳይሆን አለምን እራሷን አስገርሟታል። እሷ ከዚህ በፊት የእናቷን ገዳይ መፈለግ ዋና ግቧ እንደሆነ ተናግራ አታውቅም።በዚህ የእናቷ ግድያ ወንጀል ላይ እሷ ራሷም በአያቷ ዘንድ ይፋዊ ተጠርጣሪ ሆና መቅረቧ ነገሩን በቁርጠኝነት እንድትይዘው ገፊ ምክንያት ሆኗታል፡፡ በመጨረሻ ሞት አፋፍ ላይ የምትገኝ አያቷ ለእናቷ ሞት ዋና ተጠያቂ እሷ እንደሆንች በግልፅ ቃል ደጋግማ ነግራታለች።አያቷ የተናገረችው ስህተት እንደሆነ የሚያረጋግጥ ሌላ ማስረጃ እስካላገኘች ድረስ ጥፋቱን እስከ ህይወቷ ድረስ ይዛ ለመኖር ትገደዳለች ። እና አሁን ከሻሸመኔ ከተማ ሃያሎቹ ጋር ተፋጣ የምትገኝት ዋና ምክንያት ራሷን ነፃ ለማውጣት ነው፡፡
አቶ ፍሰሀ "ባል የለሽም? ልጆችስ?"ሲል ሌላ ጥያቄ ጠየቃት፡፡
"አይ የለኝም።
" "ለምን?"
"አባ" አለ ጁኒየር በአባቱ እፍረት ማጣት አፍሮ ‹‹አለም ልተዝናና እንጂ በጥያቅህ እንድታጨናንቃት ይዣት አልመጣሁም››
" ጁኒየር ምንም ችግር የለውም። ይህ የተለመደ ጥያቄ ነው።"አለች አለም፡፡
" እሺ እንደዛ ካልሽ መልስሽ ምንድነው?"አቶ ፍሰሀ ጠየቃት፡፡
"ጊዜ ወይም ዝንባሌ የለኝም."
"በዚህ በእኛ አካባቢም ተመሳሳይ ብዙ ጊዜ እና በቂ ዝንባሌ የለንም."
ጁኒየር በጠወለገ እይታ አባቱን ተመለከተው።የተነገረው አሽሙር እሱን የሚመለከት እንደሆነ ያውቃል"አባዬ የከሸፉብኝን ትዳሮቼን እየጠቀሰ ነው።››በማለት አብራራላት፡፡
"ጋብቻዎች? ስንት ነበሩ?"አለም በጉጉት ጠየቀች
"ሶስት" በማለት ተናዘዘ።
"እና አንዳቸውም እኔን አያት የማድረግ ፍላጎቱም ሆነ ብቃት አልነበራቸውም››አቶ ፍሰሀ ዋና ቅሬታውን ተናገረ፡፡
በዚህ መካከል ከፎቁ ወደታች የሚወርድ የጫማ ኳኳታ ሰሙና በተመሳሳይ ሦስቱም ዞሩ። አንዲት ሴት በተከፈተው በር ላይ ቆማ ነበር። አለም የአቶ ፍሰሀ ሚስት እና የጁኒዬር እናት መሆኗን አወቀች። ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ፀጉሯ ድረስ ምን እንደምትመስል አእምሮአዊ ምስል ቀርጾ ነበር። ወይዘሮዋ ግን የአለምን አእምሮአዊ ምስል ተቃራኒ ነበረች።
ጁኒዬር እናቴ ጀማይካዊት ነች ስላላት..የሆነች ፈርጣም ..ጠቆር ያለች.. ከንፈረ ትልልቅ…የፀጉሯ ድሬድ መቀመጫዋን የሚነካ አይነት አድርጋ ነበር የሳለቻት…እሷ ግን ቅንጥስጥስ ያለች ቀጭን…ቀይ ቆንጆ ግን ደግሞ ስልችት ያለው ፊት ያየዘች…ሀበሻ መሳይ
ሴት ነች፡፡ጁኒዬር ያንን አፍዛዣ መሳይ ውበቱን እና ለስላሳ ባህሪውን ከማን እንደወረሰው አሁን በግልፅ ገባት ፡፡
"ሃኒ ይህቺ አለም ጎበና ነች" አለ አቶ ፍሰሀ ።
የጁኒዬር እናት ባለቤቷን ችላ ብላ ፈካ ያለ ፊቷ አብርቶ ቀጥ ያለ ቀጭን ከንፈሯ ወደቀኝ በመጠምዘዝ ‹‹አለም ወደቤታችን እንኳን በሰላም መጣሽ…ሳራ እባላለው..የጁኒዬር እናት ነኝ
››አለችና ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡
አለም ከሴትዬዋ ንግግር የፍሰሀ ባለቤት ከመሆኗ በላይ የጁኒዬር እናት በመሆኗ ኩራት እንደሚሰማት ነው የተረዳችው፡፡
"አመሰግናለሁ።"ስትል መለሰች፡፡
ጁኒየር ከተቀመጠበት ተነሳና አንድ ብርጭቆ ነጭ ወይን ቀዳና ለእናቱ አቀበላት.. ። በሚያብረቀርቅ ፈገግታ‹‹አመሰግናለው የእኔ ልጅ››በማለት ተቀበለችው፡፡
እሱም ጎንበስ ብሎ እናቱን የለሰለሰ ስርጉድ ጉንጯን ሳመ። "ራስ ምታትሽ እንዴት ነው?"
"ሙሉ በሙሉ አልተወኝም፣ ነገር ግን እንቅልፍ ረድቶኛል። ስለጠየቅከኝ አመሰግናለሁ።"
አለም የሴትዬዋን እጇች ስታይ ተገረመች …እጇ ነጭ ሲሆኑ … በአውሎ ንፋስ እንደተመታ አበባ በቀላሉ ተሰባሪ ይመስላል።
ባሏን " መቼስ ስለከብቶችና ፈረሶች እያወራህ እያሰለቸሀት ነው አይደል?"አለችው፡፡
"በራሴ ቤት ውስጥ፣ ስለምንስ ባወራ አንቺን ምን ጨነቀሽ?" አቶ ፍሰሀ ቱግ አለ፡፡ ጁኒየር ንግግራቸውን ከዛ በላይ እንዳይጠነክርና አለም ፊት እንዳያሳፍሩን ፈጠን ብሎ ጣልቃ ገባ፡፡
"እማዬ ስለ እርባታ አይደለም እያወራን ያለነው ። አባዬ ከሚስቶቼ ወራሽ የሚሆን ልጅ ለመውለድ ባለመቻሌ እየወቀሰኝ ነበር።"ሲል አብራራላት፡፡
"ጊዜው ሲደርስ ከትክክለኛ ሴት ጋር ልጆች ትወልዳለህ››.አለችና ወደ አለም ዘወር ብላ ጠየቀች፡- “ወ.ሪት አለም በፍፁም አላገባሁም ስትይ ሰምቻለሁ ልበል ?” ብላ ጠየቀችው።
"ልክ ነው"
"እንግዳ ነገር ነው…ቢያንስ የወንድ ጓደኛ ሊኖርሽ ይገባ ነበር፡፡››
"አለም የወንድ ጓደኛ የለኝም አላለችም እኮ
››ጁኒየር አስተካከላት. "በቃ መራጭ ነች"ሲል አከለበት፡፡
"አዎ ከጋብቻ እና ቤተሰብ ከመመሥረት ይልቅ ሙያዬን መርጫለሁ።ለጊዜው፣ ለማንኛውም ነገር ጊዜ የለኝም። ግን እናቴ የሆነ ሙያ ባለቤት ለመሆን ፍላጎት እንዳላት ገልጻ ታውቃለች?"
"እሷን እስከማውቃት ድረስ እንደዛ አይነት ምኞት አልነበራትም" ሲል ጁኒየር መለሰ፣ አለም በፀፀት ስሜት "በጣም ቀድማ በልጅነቷ ነበር የወለደችኝ" አለች።
"ምናልባት ያለዕድሜ ጋብቻ ውስጥ መግባቷ እና ልጅ መውለዷ ወደ ሥራ እንዳትገባ አግዷት ይሆናል….ሰሎሜ የራሷን ምርጫ ነው ተግባራዊ ያደረገችው."ሲል መለሰላት፡፡
"የምታውቀውን ስለነገርከኝ አመሰግናለሁ.››
‹‹ አንድ ጊዜ እኔ እሷና ጀማል ለመዝናናት ወደወንዶ ገነት ሄደን ነበር፡፡በፍል ውሀ ስንታጠብና ስንዋኝ ከዋልን በኃላ በጣም ደክሞን ዛፍ ጥላ ስር ሳሩ ላይ ተዘርረን ሰማዩን አንጋጠን ስለ ምኞታችን ስናወራ እንደነበር ትዝ ይለኛል…ሁላችንም የዋና ልብስ ብቻ ነበር የለበስነው…እና እሷም በመሀላችን ተኝታ ነበር፡፡

❤43👍2
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
ከዛ ጉሮሮውን አሟሸና መናገር ጀመረ"ከእድሜሽ በላይ ለማሸነፍ ስጥር ነው የኖርኩት…እናም ቡዙ ነገር አግኝቼ .. ብዙ ነገር አጥቻለሁ፣ ወጣቷ ሴት…ኪሳራ አያስደነግጠኝም። ሀብታም መሆን የበለጠ አስደሳች ነገር ነው፣ ግን ኪሳራም የበለጠ አስደሳች ነው። እራስን የሚያንፁና የሚገነቡ ጥቅሞች አሉት። ››
‹‹ከከተማዋም አልፎ በሀገሪቱም የተሳካልህ የቢዝነስ ሰው መሆንህን አውቃለው፡፡ገንዘብ ስላለህም የፈለከውን ነገር በፈለከው ሰዓት ማድረግ እንደምትችል እንደምታምንም አውቃለው፡፡››አለችው በልበሙሉነት፡፡
"ታዲያ ካወቅሽ ይህን አስቂኝ ምርመራ ለምን አትተይውም?"ሲል ቀጥታ ወደሚፈልገው ርዕስ ገባ፡፡
"ይህ መቼም የሚሆን አይመስለኝም ..አላደርገውም››
"እናትሽን የገደልኩት እኔ እንደሆንኩ እንዴት ታስቢያለሽ? እሷ ከጁኒየር ምርጥ ጓደኞች መካከል አንዷ ነበረች:: በየእለቱ ከዚህ ቤት ትወጣና ትገባ ነበር::እርግጥ ካገባች በኋላ ብዙም አትመጣም ነበር… እናትሽን ለመጉዳት ጣቴን አንስቼ አላውቅም።››
አለም እሱን ማመን ፈለገች። በወንጀል ጉዳይ ተጠርጣሪ ቢሆንም እሷ ግን በጣም ታደንቀው ነበር። በውይይታቸው ከተገነዘበችው እና ለምርመራዋ ስትል ከሰበሰበችው መራጃ እንደተረዳችው ከምንም ነገር ተነስቶ ኢምፓየር መገንባት ችሏል።በማህበረሰቡ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ነበር. አሳማኝ ባህሪ ነበረው። ነገር ግን በቀለማት ያሸበረቀ ስብዕናው ከጀርባ ሚሰራቸውን ቆሻሻ ድርጊቷች በቀላሉ እንዳይገለፁ ምክንያት እንደሆኑ በደንብ ታውቃለች።ቢሆንም ግን ለፍሰሀ ያላት አድናቆት እንደፍላጎቷ ሙሉና ጠንካራ አልነበረም..፡፡
ደገመችና ‹‹ምንም ቢሆን ምንም ምርመራውን ማቋረጥ አልችልም" አለች ።
‹‹ለምን ?››
" ብፈልግ እንኳን ዋና አቃቢ ህጉን በስንት መከራ ካሳመንኩት በኃላ ወደኃላ እንድመለስ መጠየቅ ያሳፍራል ፡፡"
"ስሚ" አለና አይኖቾን በትኩረት እያየ " ስህተት እንደሰራሽ ንገሪው፣ እናም ነገ በዚህ ሰአት እዚህ የመጣሽበትን ጉዳይ እንኳን እንደማያስታውስ ዋስትና እሰጥሻለሁ..ስራውንም ለቀሽ ወደአዲስአበባ መመለስና ቆንጆ የጥብቅና ቢሮ ማቋቋም ትችያለሽ….እናትሽ የልጄ የልብ ጓደኛ ነች…አንቺን ለማቋቋም የሆነ ነገር ማድረግ ለእኔ ያን ያህል የሚከብድ ጉዳይ አይደለም ።"
" አላደርገውም "
"እሺ፣ እንግዲያውስ ዋና አቃቢ ህጉን ለእኔ ተይልኝ..እኔ አናግረዋለው።"
"አቶ ፍሰሀ… ››ጮክ ብላ ተናገረች "የኔ ሀሳብ አልተረዳህልኝም"ትኩረቱን እንዳገኘች እርግጠኛ ስትሆን "ልጅህ በምርጫ ያለውን ተሳትፎ የሚጎዳ ምንም ነገር ለማድረግ እቅድ የለኝም…ያ እንዳይሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንደማደርግና እያንዳንዱን እንቅስቃሴዬንና ምርመራዬን በከፍተኛ ሚስጥር እንደማከናውን ቃል እገባለው…ማድረግ የምችለው ያንን ብቻ ነው፡፡››
"የአንድ ሙሉ ከተማ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አደጋ ላይ ቢሆንም ሀሳብሽን አትቀይሪም ማለት ነው?"
"ከተራቡ ህፃናት ዳቦ እየወሰድኩ ነው የሚመስልህ…?ነው ወይስ ያንተ ልጅ ይህቺን ከተማ ወክሎ የተወካዬች ምክር ቤት ከገባ በኩልፎ ወንዝ ወተት እንደሚንዠቀዘቅ እና ህዝቡ በቁንጣን እንደሚሰቃይ ነው የምታስበው?"
" ተይ እንጂ ..እኔ እንደዛ አላልኩም "
" እንግዲያው አቋሜን በግልፅ አሳውቂያለው..እኔ ሁላችሁንም በግል ለማጥቃትና ለማውደም ምንም እቅድ የለኝም…ግን ደግሞ የእናቴን ገዳይ ለፍርድ ለማቅረብ ህይወቴንም የሚያስከፍለኝ ቢሆን ግድ የለኝም..እስትንፋሴ እስካለች ድረስ ወደፊት እቀጥላለው››
‹‹በቃ የመጨረሻ ውሳኔሽ ይሄ ነው?"
‹‹አዎ..እኔን ማስቆሚያ ብቸኛው መንገድ እኔንም እንደእናቴ ማስወገድ ነው….በዛ ጉዳይ ላይ ልታስብበት ትችላላችሁ፡፡››
‹‹ንግግርሽ በጣም….››አቶ ፍሰሀ ንግግሩን አቋረጠ..እንደዛ ያደረገው ልጁ ጂኒዬር በራፉን ከፍቶ ስለገባ ነው፡፡
ጁኒየር በሩን በድንገት ከፍቶ አንገቱን ወደ ውስጥ አሰገገና"ሄይ, በሰላም ነው ..በጣም መሸ እኮ…እራት ሊቀርብ ነው" ፡፡
"በጣም ጥሩ ….ውይይታችን ጨርሰናል…..ግን እራቱ ይቅርብኝ ….ቀጥታ ወደቤቴ ነው መሄድ የምፈልገው››አለች አለም።
አቶ ፍሰሀ ንዴቱን መቆጣጠር አቃተው "እዚህ በቁም ነገር እየተነጋገርን ነበር። ዳግመኛ በግል ቢሮዬ ውስጥ ከሰው ጋር እያለው አንዳታቋርጠኝ፣ ።››
ጁኒየር "ንግግራችሁ በጣም ግላዊ ወይም በጣም ከባድ እንደሆነ አላውቅም ነበር።"ሲል ለአባቱ ቅሬታ ምላሽ ሰጠ፡፡
"አቶ ፍሰሀ.. እባክህ, ምንም አይደለም…በበቂ መጠን ተጋግረናል እኮ..የቀረም ነገር ካለ ሁለተችንም እዚሁ ከተማ ውስጥ ነን..ደጋግመን መገናኘታችን አይቀርም በእውነቱን ለመናገር፣ ጁኒየር ስላቋረጠን ደስተኛ ነኝ። ምን ያህል እንደመሸ አሁን ነው ያስተዋልኩት… አሁን መሄድ አለብኝ።"
ሁሉም ተያይዘው ወደሳሎን ተመለሱ፡፡ሳሎኑ ባዶ ነበር፡፡ገመዶም ሆነ ሳራ አልነበሩም፡፡
‹‹ለራት ብትቆይ ግን ደስ ይለኛል››አቶ ፍሰሀ ናቸው ተናጋሪው
‹‹አይ ይቅርብኝ..ደህና እደሩ››
ጁኒየር ኮቷን ከያዘላት በኋላ መኪናዋ ድረስ ሸኛት ..ወደ እሱ ዘወር አለችና ።"ጁኒየር አመሰግናለው …ደህና እደር።"አለችው
" እጇን ያዘና ጎንበስ ብሎ ሳመው… ከዛ መዳፏን ወደ ላይ አዙሮ ሳመው። "የምታገኛቸው ሴቶች ሁሉ እንደዚህ ታሽኮረምማለህ?"
የማይገባ ፈገግታ ፈገግ አለላት ፡፡
"ለፍቅር በቀላሉ ተጋላጭ ነህ እንዴ?"ሌላ ጥያቄ አስከተለች፡፡ "እንደዛ ነኝ እንዴ..?አይ አይደለሁም."ፈገግታው እየሰፋ ሄዶ ፡፡
‹‹ለማንኛም መልካም ምሽት››አለችና መኪና ውስጥ ገብታ አካባቢውን ለቃ ተፈተለከች ጁኒዬር ወደቤት ተመለሰና ቀጥታ ወደእናቱ መኝታ ክፈል አመራ እና በስሱ አንኳኳ
‹‹እማዬ ፣ ልግባ?››
" ውዴ እባክህ ግባ" ሳራ ፈቀደችለት… በልጇ ጉብኝት በጣም እንደተደሰተች ግልጽ ነው። ርካሽ የንባብ መነፅሯን አውልቃ እያነበበች የነበረውን መፅሃፉ ከጎኗ አስቀመጠች፡፡
‹‹አትቀመጥም››
‹‹አይ ይሁን›› አለና አልጋው ጎን በመቆም፡፡
"መጽሐፉ እንዴት ነው?" ሲል ጠየቃት፡፡መፅሀፉን ገዝቶ ያመጣላት እሱ ነበር፡፡
"በጣም አስደሳች ነው።››ስትል በአጭሩ መለሰችለት፡፡ "ጥሩ፣ ስለተደሰትሽበት ደስ ብሎኛል"
ሳራ እናቱ እንደመኆኗ መጠን በውስጡ የሚገላበጠውን ጭንቀት ተረዳችና። "ምንድነው ችግሩ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
"ምንም።"
"አንድ የተሳሳተ ነገር ሲኖር ማወቅ እችላለሁ."
"ከተለመደው የተለየ ነገር የለም ከአሌክስ..ማለቴ ከአለም ጋር የነበራቸውን ውይይት በማቋረጤ አባቴን አበሳጭቼዋለው››
"አባትህ የጋራችን በሆነው መኖሪያ ቤታችን ውስጥ ሲኖር ራሱን እንዴት መምራት እንዳለበት እስካሁን አልተማረም። በቤታችን የጋራ እንግዳችን ሆና የመጣችን ሴት ለግል ውይይት ብሎ ክፍል ውስጥ በማስገባት ማዋራት ጨዋነት የጎደለው ተግባር ስለሆነ አንተም ፣ ውይይቱን በማቋረጥ ባለጌ የመሆን መብት አለህ።››አለችው
‹‹እማዬ…››
"ለማንኛውም በግል ምን እየተወያዩ ነበር?"
"ስለ እናቷ ሞት ይመስለኛል….ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም."
"እርግጠኛ ነህ? ዛሬ ማታ ሁሉም ሰው በጣም የተጨናነቀ ስሜት ላይ እንዳለ መረዳት ችያለው።"
" ችግርም ካለ አባዬ ሁል ጊዜ እንደሚያደርገው ይቆጣጠረዋል። በእርግጠኝነት ምንም የሚያስጨንቅ ነገር አይኖርም።››

❤38👍4