አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አንቺና_ጨረቃ

መብረቅ ብልጭ ብሎ
ምስልሽን ሲፈጥር፤
ፀሀይ ስትስቅ ነው
አንቺን የምትመስል፣
ኩልል ያለ ውሃ
ሲያይሽ ይጠራል፣
ከዋክብትን አይተሽ
ስንቴ አሽኮርምመሻል።
ጨረቃ ደግሞ አይታ፣
ካንቺ ካልተዋስኩኝ ብርሃንሽን ብላ፣
እንደዘብ ጠባቂ
አንቺን ተከትላ፣
ከአጼ ቤት ጎጆ
ገባች ሰተት ብላ።
አውቀሽ ነው ቢባልም
አሁን አምኛለሁ፣
አንቺን ለመፈለግ፤
አይደለም ጨረቃ እኔም ደክሜያለሁ።
ሰአሊ እንዳይስልሽ
ቀለምሽ አይገባም፣
ገጣሚ እንዳይገጥምሽ
ያለው ቃል አይበቃም።
ሆኖብኝ ነው እንጂ
እንደ አጼ ቤት ልጆች፣
መች እዋስ ነበረ
ዋንጫና ቁልፊቶች።
አውቃለሁኝ አዎ
በዚ ውስጥ አትቆዪም፣
በፍቅርሽ ተይዤ፤
በልቤ ብልቃጥ ውስጥ
አንቺን ባስቀምጥም፣

ሰበርሽው እሱንም፣

አንቺና ጨረቃ
ጭራሽ አትያዙም፣
ድንገት ብትያዙ፤
የያዛችሁን ነገር ከመስበር አትቀሩም፣
አንቺና ጨረቃ
መስበርን አተዉም፣
አንቺም ጨረቃም
ወደኋላ አትሉም።


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
9👍2