አትሮኖስ
282K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
490 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንም_አልል...

እኽ..ሺ እንግዲህ በዝምታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የደቂቅ እድሜን ትዝታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
እያዳመጥኩ እያስታመምኩ ፥ ጊዜዬን እያሠላሠልኩ
ሳልናገር ሳልጋገር ፥ እየደገምኩ እያሠለሥኩ
ሳልሰለች እየመላለስኩ......
እኽ ሺ እንግዲህ በፀጥታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የእስትንፋሴን ቃል ጉምጉምታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
ሳልሰለች እየደጋገምኩ
በእግረ ህሲና እያደቀቅኩ
እየቋጠርኩ እየቆጠርኩ......
እሺ እንግዲህ አልናገርም
በአንደበቴ አልተነፍስም
በልሳኔ አመሰክርም
አልልም። ምንም አልልም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም ዝም
የልቤ ደም ሥር ሲያቃጭል
ልሳኔን ሲያስነሳ ሲያሰጥል
ቃላቴን ሲቃኝ ሲያጋግል
ትንፋሼን ሲያንር ሲያዳውል
ክል ሲል ትር ድም ሲል
ማዳመጥ ማስታመም እንጂ ፥ ሌላ ምንም ምንም አልል።

ጥቅምት ፦ ፲፱፻፷፫ ፒያሳ
ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድሕን
" እሣት ወይ አበባ "
#ምንም

ወታደር የራሴ የሚለው
የግሉ ኑሮ ምን አለው?
በህሊናው የታተመው የሃገሩ ፍቅር በልጦበት፣
በደሙ ውስጥ የሰረጸው የወገን ክብር አይሎበት፣
ምቾቱን ለወገን ምቾት
እስትንፋሱን ለሀገር ነጻነት
እድሜውን ለባንዲራው ክብር ሁሉን አሳልፎ የሰጠ
የራሴ የሚለው የሌለው፣
ወታደር የሃገር ወጋግራ
ለሃገሩ ኖሮ የሚሞት . . . ለድንበሩ የሚሰዋ ነው፡፡
ወታደር የራሴ የሚለው
የግሉ ንብረት ምን አለው?
እንጂማ ቢኖረው ኖሮ፣
የራሴ የሚለው የግሉ ኑሮ፣
በረሀውን እንደ ለምለም መስክ
እንደ ምቹ ስፍራ ቆጥሮ፣
ለሀገር ክብር መሰዋት. . . ምትክ የለሽ ነፍሱን ገብሮ
የበረሀው ቋያ ንዳድ . . . ለአንዲት ጀንበር ሳይበግረው፣
ለወገኑ ፍቅር እንደ ሻማ . . . ነዶ ሲቀልጥ ባላየነው፡፡
ወታደር የራሴ የሚለው
የግሉ ንብረት ምን አለው?
እንኳንስ ሃብትና ንብረት
ለችግር ጊዜ የሚመካበት፣
ይቅርና ወርቅና ገንዘብ
አለኝ ብሎ ሚኮራበት፣
የህይወት ቁልፍ የሆነውን
የተፈጥሮ ነፋሻ አየር፣
እንደ ልቡ ማ...ግ አድርጎ
ተንፍሶ አያውቅም ወታደር።
እርግጥ ነው ወታደር ከልብ
የሚመካበት ንብረቱ፣
ህዝብና ሰንደቅ አላማው
እነሱ ናቸው ቅርስ ሀብቱ፡፡
እንጂማ ከነሱ ሌላ
ወታደር የራሴ የሚለው፣
የግሉ ንብረት ምን አለው?
ምንም! 💚💛❤️

🔘ሻለቃ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
👍1
#ምንም\_አልል

እሺ እንግዲህ በዝምታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
በደቂቃ ዕድሜን ትዝታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
እያዳመጥኩ እያስታመምኩ ጊዜዬን እያሰላሰልኩ
ሳልናገር ሳልጋገር፤ እየደገምኩ እያሰላሰልኩ
ሳልሰለች እያመላለስኩ ..........
እሺ እንግዲህ በጸጥታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የእስትንፋሴን ቃል ጉምጉምታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
ሳልሰለቸ እየደጋገምኩ
በእግረ ሕልና እያደቀቅኩ
እየቋጠርኩ እየቆጠርኩ
እሺ እንግዲህ አልናገርም
በአንደበቴ አልተነፍስም
በልሳኔ አልመሰክርም
አልልም፡፡ ምንም አልልም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም ዝም ............
የልቤ ደም ሥር ሲያቃጭል
ልሳኔን ሲያስነሳ ሲያስጥል
ቃላቴን ሲቃኝ ሲያጋግል
ትንፋሼን ሲያንር ሲያደውል
ክል ሲል ትር ድም ሲል
ማዳመጥ ማስታመም እንጅ ፤ ሌላ ምንም ምንም አልል

🔘ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
9👍5