#ሁቱትሲ
፡
፡
#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች
፡
#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ
፡
፡
#ምዕራፍ_ሁለት
#ከመቀመጫችን_ሲያስነሡን
‹‹ቱትሲዎች ከመቀመጫችሁ ተነሡ!››
አንድ ቀን አራተኛ ክፍል ሆኜ እማርበት በነበረው መማሪያ ክፍል ውስጥ ስድስት ልጆች ከመቀመጫቸው ተስፈንጥረው ሲቆሙ ግማሽ ደርዘን ወንበሮች ወደ ኋላ ተንጓጉ፡፡ ከዚያ በፊት ሁልጊዜ እናቴ በምታስተምርበት አነስተኛ ትምህርት ቤት ውስጥ እማር ስለነበር ምን እየተከሰተ እንደነበር ልገምት አልቻልኩም፡፡ በዚያን ወቅት አሥር አመቴ ስለነበርና ትንሽ አደግ ላሉ ልጆች የሚሆን ትምህርት ቤት ውስጥ ስማር የመጀመሪያ ቀኔ በመሆኑ የልጆቹ መራበሽ ግራ አጋብቶኛል፡፡ ከዚያ በፊት አስተማሪ የዘውግ ጥሪ ሲያካሂድ በፍጹም አይቼ አላውቅም፡፡
‹‹ቱትሲዎች በሙሉ ከመቀመጫችሁ ተነሡ!›› መምህራችን፣ ቡሆሮ፣ አምባረቀ፡፡ በትልቅ እርሳስ ከዝርዝሩ ላይ ከተማሪዎች ስም አጠገብ ምልክት እያደረገ ነበር፡፡ ከዚያም አቆመና በቀጥታ እኔ ላይ አፈጠጠ፡፡
‹‹ኢማኪዩሌ፣ ሁቱ ስል አልተነሣሽም፤ ትዋ ስል አልተነሣሽም፤ አሁንም ቱትሲ ብል ልትነሺ አልቻልሽም፡፡ ለምንድነው?›› ቦሆሮ ፈገግ እያለ ቢሆንም ድምጹ ግን ክፋቱን ያሳብቅበታል፡፡
‹‹አላውቅም መምህር፡፡››
‹‹ምን ዘውግ ነሽ?››
‹‹የት አውቃለሁ፣ መምህር?››
‹‹ሁቱ ነሽ ቱትሲ?››
‹‹እኔ - እኔ አላውቅም፡፡››
‹‹ካላወቅሽ ውጪያ! ከዚህ ክፍል ውጪ፤ እና ምን እንደሆንሽ ሳታውቂ ተመልሰሽ አትምጪ!››
መጻሕፍቴን ሰበሰብኩና በሃፍረት አንገቴን ደፍቼ ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ፡፡ ገና ያልታወቀኝ ቢሆንም በሩዋንዳ የዘውግ ክፍፍል ላይ የመጀመሪያዋን ትምህርቴን
ተማርኩ፤ ይህም ክው ነበር ያደረገኝ፡፡
ወደ ትምህርት ቤቱ ጓሮ ሮጬ ወንድሜ ዳማሲን የዕለቱን ትምህርት እስኪጨርስ ድረስ ከቁጥቋጦ ጀርባ ተደብቄ መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ እንባዬን ማቆም ተስኖኝ ሰማያዊ የትምህርት ቤት የደንብ ልብሴ እስኪረጥብ ድረስ ነፈረቅሁ፡፡ ምን እንደተከሰተ ስላልገባኝ ወደ ክፍል ሄጄ የቅርብ ጓደኛዬን ዣኔትን ጉዳዩን ታብራራልኝ ዘንድ ለመጠየቅ በጣም ፈለግሁ፡፡ መምህሩ ሁቱ የሚለውን ስም ሲጠራ ተነሥታለች - ምን አልባትም መምህሩ ለምን እንዳመናጨቀኝ ታውቅ ይሆናል፡፡ በቁጥቋጦው ውስጥ ተኮራምቼ ዳማሲን እዚያ እስኪያገኘኝ ድረስ እንባዬን ሳዘራ ቆየሁ፡፡
‹‹ማን መታሽ ኢማኪዩሌ?›› ሲል ታላቅ ወንድሜ ባለችው የ13 ዓመት ሥልጣን ጠየቀኝ፡፡ አለኝታዬ ዳማሲን አንድ ሰው ጫፌን ከነካኝ ለመፋለም የተዘጋጀ ልጅ ነው፡፡ ቡሆሮ ያለኝን ነገርኩት፡፡
‹‹ቡሆሮ ጥሩ ሰው አይደለም›› አለ ወንድሜ፡፡ ‹‹ቢሆንም አትጨነቂለት፡፡ ሌላ ቀን ስም ሲጠራ እኔ የማደርገውን አድርጊ፤ ከጓደኞችሽ ጋር ተነሺ፡፡ ጓደኛሽ ዣኔት ስትነሳ ተነሺ፡፡››
‹‹ዣኔት ሁቱ ብሎ ሲጠራ ነበር የተነሣችው፡፡››
‹‹በቃ እንደዚያ ከሆነ ሁቱ ሲሉ ተነሺ፡፡ ጓደኞቻችን የሆኑት ያንን ከሆነ መቼም እኛም የምንሆነው እንደዚያው መሆን አለበት፡፡ ሁላችንም አንድ ሕዝብ ነን፣ አይደል?››
በዚያን ወቅት የማውቅበት መንገድ አልነበረኝም፤ ዳማሲንም እንደኔው በሩዋንዳ ስለነበረው ዘውገኝነት ግንዛቤ አልነበረውም… ይህም በአካባቢው በጥሩ ሁኔታ ይማሩ ከነበሩት ልጆች ውስጥ ከመመደባችን አንጻር እንግዳ ነገር ነው፡፡ በየዕለቱ ከትምህርት መልስ ወንድሞቼና እኔ ወደ ቤታችን በእናታችን ተቆጣጣሪነት የቤት ሥራችንን እንድንሠራ ከመጠራታችን በፊት የ90 ደቂቃ የእረፍት ጊዜ ነበረን፡፡ አባታችን ከራት በፊት የትምህርት ቤታችንን ሰሌዳዎች የምታክል ጥቁር ሰሌዳ በቤታችን መካከል አድርጎ ከአንድ ሰዓት ለሚበልጥ ጊዜ ያስጠናናል፡፡ የሒሳብ፣ ሰዋስውና መልክዓምድር ጥናት ጠመኔ እየሰጠ ያለማምደናል፡፡
ይሁን እንጂ ወላጆቻችን ስለራሳችን ታሪክ አላስተማሩንም፡፡ ሩዋንዳ የሦስት ዘውጎች፣ ማለትም የሚበዛው ሁቱ፣ አናሳ ቱትሲዎችና በጣም ትንሽ ቁጥር ያላቸው በጫካ ውስጥ የሚኖሩት ትዋዎች ስብስብ እንደሆነች አላስገነዘቡንም፡፡ የጀርመን ቅኝ ገዥዎችና ከእነርሱ በኋላ የመጡት ቤልጅየሞች የሩዋንዳን ነባር ማኅበራዊ አወቃቀር ማለትም ሩዋንዳን ለምዕተ-ዓመታት ሰላምና ስምምነት የሰጣት ቱትሲ ንጉሥ የሚመሩትን ዘውዳዊውን ሥርዓት በአግላይ ዘውግ-ተኮር የመደብ ሥርዓት ቀይረውት እንደነበር አልተማርንም፡፡ ቤልጅየማውያኑ የቱትሲውን ገዥ መደብ ደግፈውና በመሪነት ደረጃ ያለውን አስተዋፅኦም ተቀብለው፣ አገሪቱን በተሻለ መንገድ ለማስተዳደርና ለቤልጅየማውያኑ ከፍተኛ ትርፍ ለማስገኘት ያግዝ ዘንድ ቱትሲዎች የተሻለ ትምህርት እንዲያገኙ አድርገዋል፡፡ ቤልጅየሞች በሁቱና ቱትሲ መካከል ፈጥረውት የነበረውን ክፍተት በማባባስ ሁለቱን ዘውጎች በቀላሉ ለመለየት የዘውግ መታወቂያ ደብተር አስተዋውቀዋል፡፡ እነዚያ የማይረቡ ስህተቶችም በሁቱዎች ዘንድ ዘላቂ ቁጭት በመፍጠር ለዘር ጭፍጨፋ መሠረት ለመጣል አገዙ፡፡ ቱትሲዎች የተሻለ ነጻነት በጠየቁ ጊዜ ቤልጅየማውያኑ በጠላትነት አዩአቸው፡፡ በ1959 ደም-አፋሳሽ የሁቱ አመፅን ደግፈው ዘውዳዊው ሥርዓት እንዲገረሰስ አደረጉ፡፡ ከ100 000 በላይ ቱትሲዎች በበቀል በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ተገደሉ፡፡ በ1962 ቤልጅዬም ከሩዋንዳ ለቃ ስትወጣ የሁቱ መንግሥት አንቀጥቅጦ በመግዛት ላይ ሲሆን ቱትሲዎችም በሁቱ አክራሪዎች ማሳደድ፣ ሽብርና ግድያ የሚፈጸምባቸው ሁለተኛ ዜጎች ለመሆን በቁ፡፡ በብዙ አሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ቱትሲዎች ግድያዎች የዕለት ከዕለት ክስተት በነበሩባቸው አሥርት ዓመታት ውስጥ ሞቱ፡፡ የሽብር ዑደቱ ተጧጡፎ መድሎ መፈጸሙ ቀጠለ፡፡ የሁቱው መንግሥት ከቤልጅየሞች የአገዛዝ ዘመናት የወሰደው የዘውግ መታወቂያ ደብተር አሠራር መድሎውን የበለጠ ይፋና ቀላል አደረገው፡፡
ወላጆቻችን እኔና ወንድሞቼ ቢያንስ በልጅነታችን እንዳንማራቸው ያልፈለጓቸው የታሪክ ትምህርቶች እነዚህ ነበሩ፡፡ ስለ መድሎም ሆነ ስለ ግድያ ዘመቻዎቹ፣ ስለ ዘር ማጽዳቱም ሆነ የዘር መታወቂያ ካርዶቹ አላወሩንም - እነዚህ ነገሮች ፈጽሞ የልጅነቴ አካል አልነበሩም፡፡
ዘርን፣ ሃይማኖትን ወይንም ዘውግን ከግምት ውስጥ ሳናስገባ በቤታችን ማንንም ሰው በደስታ እንቀበላለን፡፡ ወላጆቼ የእርስዎን ሁቱ ወይንም ቱትሲ መሆን ከስብዕናዎ ጋር አያገናኙትም፡፡ ጥሩ ጸባይ ካለዎትና ገራገር ከሆኑ እጆቻቸውን ዘርግተው ሰላምታ ያቀርቡልዎታል፡፡ ወላጆቼ ራሳቸው ግን በሁቱ ጽንፈኞች የደረሱባቸው የተወሰኑ አሰቃቂ ችግሮች ነበሩ … እንዲያውም አንደኛውን ትንሽ ትንሽ አስታውሳለሁ፡፡ ያኔ የሦስት ዓመት ልጅ ነኝ፡፡ ነፍስ ባለማወቄ ምን እየተከሰተ እንደነበር አልገባኝም፡፡ የምሽቱን ሰማይ እሳት ሲንቦገቦግበት፣ እናቴም በእጆቿ ጥብቅ አድርጋ ታቅፋኝ ከቤታችን ስትሮጥ ይታወሰኛል፡፡ ይህ የሆነው ብዙ ቱትሲዎች በተሳደዱበት፣ ከቤቶቻቸው በተነዱበትና በየመንገዱ በተገደሉበት የ1973ቱ መፈንቅለ-መንግሥት ወቅት መሆኑ ነው፡፡ በኛ ክፍለሀገር ሁቱ ጽንፈኞች የቱትሲዎችን ቤቶች በየተራ አቃጥለዋል፡፡ እሳቱ ወደኛ ሽቅብ ሲገሰግስ መላው ቤተሰቤ አብሮ ቆሞ ወደ ኪቩ ሐይቅ ቁልቁል በማስተዋል ላይ ነበረ፡፡ ሩታካሚዜ ወደተባለው ጥሩ ሁቱ ወዳጅ ጎረቤታችን ቤት ሸሸን፡፡ እርሱም ግድያዎቹና ቃጠሎው እስኪያቆሙ ድረስ ሸሸገን፡፡ ወደ ቤታችን ስንመለስ የሚጫጫስ

👍2