አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
494 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የታል_ልጅነቴ?

እነ ጋሽ አበበ ሚጡዬና ቹቹ

እነ ትዬ ፀሐይ እንዲሁም ሌሎቹ

ወዴት ተሰደዱ የታሉ ሰዎቹ የሰፈሩ ሜዳ የለም ከኖረበት መንገዱም ተለምቷል ሱቅ የተላኩበት የታሉ ዛፎቹ ምሽግ መስሪያዎቹ ልጥ የላጥንባቸው ኳስ ማሰሪያዎቹ ካሬ ስድስት ቆርኪ የተጫወትኩበት የት ሄደ ደስታዬ የት ሄደ ልጅነት ሸርተቴ ያልኩበት የጭቃው ተራራ

ልጅነቴን ትቶ ፎቅ በላዩ ሠራ

መርቅ አልመርቅም የተጣላሁበት

የከድር ሱቅ የለም ፈልጌ አጣሁት

ቡልኮ ጠጅ ቤት ጉልት የሰፈሩ

ተሰደዱ መሰል እነሱም ሳይቀሩ

ከቤቴ በር ላይ ወጥቼ ቆሜአለሁ

ሰላም የሚለኝ ሰው በዓይኔ እፈልጋለሁ

በተወለድኩበት ባደኩበት ሰፈር

ሆኛለሁ ባይተዋር

የለም ልጅነቴ

ማርና ወተቴ

🔘እመቤት መንግሥቴ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍26😢116👎2