አትሮኖስ
282K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
493 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ _ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ባልና ሚስቶቹን ቤታቸው ወስዶ እንደጣላቸው ቀጥታ የመኪናውን መሪ ወደአስቴር ቢሮ ነው የጠመዘዘው…ገብቶ ምሳ እንዲበላ ቢለምኑት እንኳን እሺ አላለቸውም፡፡እንደሚመጣ አልነገራትም ቀጥታ ከቢሮዋ ፊት ለፊት አቆመና ደወለ
‹‹ሄሎ ወንድሜ….እንዴት ነው ቢሾፍቱ በጣም ተመችታሀለች መሰለኝ?፡፡››
‹‹መጥቻለው….ምሳ አትጋብዢኝም?፡፡››
‹‹የእውነት መጣህ?››
‹‹አዎ ቢሮሽ ፊት ፊት መኪናዬን አቁሜያለው፡፡››
‹‹በቃ መጣሁ››ብላ ስልኩን ዘጋች….5 ደቂቃ ነው ያስጠበቀችው፡፡ገና የቢሮዋን የህንፃ ደረጃ ስትወርድ ጀምሮ ነው አይኑ ውስጥ የገባችው…ሙሉ ሮዝ ቀለም ያለው ጉረድ ቀሚስና ኮት ለብሳለች…ፀጉሯ ወደኃላዋ ትከሻዋ ላይ እንዲተኛ ተደርጎል…ውብ ሆናለች….መኪናዋን ስለምታውቃት ብዙም ሳትደነጋገር ቀጥታ ወደእሱ ነው ያመራችው…ይህቺ ሴት እህቱ እንድትሆን አይደለም የሚፈልገው…ጓደኛም እንድትሆነው አይደለም…የፍቅር አጋሩ ሚስቱ ሊያደርጋት ነው ምኞቱ..ይሄ ምኞቱ ደግሞ አሁን በቅርብ በውስጡ የበቀለ ስላልሆነ ህመሙ ቀላል አይደለም…ገና አፍ ፈቶ በኮልታፋ አንደበት መንተባተብ በጀመረበት በጮርቃነት እድሜው ጀመሮ እሷ ሚስቱ እንደሆነች ያስብ ነበር፣እርግጥ በዛን እድሜ ሚስት ማለት እራሱ ትርጉሙ ምን ማለት አንደሆነ አያውቅም ነበር፣ቢሆንም ጭላንጭል የሆነ ግንዛቤ ነበረው…ሚስት ማለት አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ ሁሌ አብራ

የምትተኛ ሴት እንደሆነች ከአባትና ከእናቱ ግንኙነት መረዳት በቻለበት ጊዜ ነው፣ከእሱ ጋር ለዘላለም መተኛት ያለባት ሴት አስቴር እንደሆነች ወስኖ የነበረው፣በዛን የልጅነት ጊዜ እናቷ የቤታቸውን እንጀራ ልትጋግር ስትመጣ አስከትላት ስትመጣ ጀምሮ እዛው እሷን ማስቀረት ምኞቱ ነበር…እና ያ ምኞት ግለቱን ጠብቆ እየፋመ ነበር የቀጠለው…
ጊዜው ሲደርስ ግን ነገሮች ቀደም ብሎ እንዳሰባቸው ቀላል አልነበሩም…ገቢናውን ከፈተላት ገባች.. ጉንጩን አገላብጣ ሳመችው…ሁል ጊዜ የእሷ መሳም ከሌላው መሳም በጣም ይለይበታል…ወፈር ብሎ ወደፊት ግልብጥ ያለው ፍም ከንፈሯ ሰውነቱ ላይ ሲርፍ የተለየ ሙቀት ነው ሰውነቱ የሚያመነጨው…ልክ የጋለ ቢላዋ አካል ላይ ሲያርፍ የሚሰማው አይነት ትሽሽሽ..የሚል የማቃጠል የመለብለብና የመላጠ ስሜት……
‹‹አንተ ወፍረህ ነው የመጣሀው….ስራ ላይ ነበርክ ወይስ ጫጉላ ሽርሽር ላይ?››
‹‹በይው…አንቺም ተመችቶሻል…ምሳ የት አንብላ?››
‹‹ወደ እኔ ቤት ንዳው››
‹‹ምነው ከሰዓት ስራ የለሽም እንዴ?››
‹‹ዛሬ ቅዳሜ እኮ ነው…ግማሽ ቀን ነው የምንሰራው››
‹‹እና አራበሽም ..በልተን ብንሄድ አይሻልም?››
‹‹አይ ሰራተኛዬ አዘጋጅታ እየጠበቀችን ነው…ዘና ብለን ቤታችን ብንበላ ይሻላል….ወንድሜ ስለመጣህ ደስ ብሎኛል››
‹‹እኔም ከሰዓት ስራ ስለሌለሽ ደስ ብሎኛል››ብሎ መኪናዋን ወደ አስፓልት መሀል አስገባና ነዳት….የእውነትም ከሰዓት ስራ የለኝም ብላ ወደቤቷ ይዛው እየሄደች በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ ተስምቶታል…ከአመታት በኃላ መልሶ ዛሬ እድሉን ይሞክራል፡፡አዎ በስደት ከሄደበት ባእድ ሀገር ተመልሶ የመጣውም ለዚሁ ነው፡፡ከባሎ እንደተለያየችና እሱም በዛ ንዴት ከሀገር ውጭ መሰደዱን ሲሰማ ነው ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ የመጣው…አንሆ ተመልሶ በመጣበት ባለፉት ስድስት ወሮች እሷን ከገባችበት ድባቴ እንድትወጣና ያልተሳካ ትዳሯ ከፈጠረባትን የስነልቦና መሰበር እንድታገግም እንደወንድም እንደ ጓደኛም ከዛም አልፎ እንደባለሞያም  ከጎኗ  ሆኖ  ሲያግዛትና  ሲደግፋት  ነበር…አሁን  ግን  ልቧ  ሌላ  ፍቅር

ለማስተናገድ ዝግጁ ነው ብሎ ያስባል..በዛ ላይ የእሱ እና የእሷ ፍቅር አዲስ ዛሬ የበቀላ ሳይሆን ድሮ በየሁለቱም ልብ ተዳፍኖ ያለ ነው…አሁን ያንን መቆስቆስና መልሶ እንዲቀጣጠል ትንሽ የፍቅር ቤንዚል ማርከፍከፍ ነው…ለዚህ ድርጊት ያበረታታው ሰሞኑን ያየው በአቶ ሃይለልኡል እና በወ.ሮ ስንዱ መካከል የተከሰተው የፍቅር ግርሻ ነው፡፡
‹‹አዎ…አስቴርን አገባታለሁ…ከበፊት ባሏ የወለደችውን አንድ ልጅም እንደልጄ አድርጌ አሳድገዋለው››በውስጡ አልጎመጎመ…‹‹እና በቅርብ ቀን እሷም ወንድሜ የምትለውን ጥሪ ትተውና ባሌ ብላ ትጠራኛለች…ልጇም አጎቴ ብሎ የሚጠራውን አቁሞ አባቴ እንዲለኝ
አደርጋለው››ይሄንን ስላሰበ ብቻ ውስጡ በደስታ ተፍነከነከ..ቤት ሲደርሱ እውነትም እንዳለችው ቆንጆ ምሳ ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቃቸው፡፡እየተጎራረሱ በሉ፡፡ከምግብ በኃላ ብና ተፈላላቸው..እሷ ሁለት ሲኒ እሱ አንድ ሲና ጠጡና ተጠናቀቀ፡፡
‹‹እዚሁ ልንገራት ወይስ ይዣት ወጣ ልበልና ዘና ያለ ቦታ ወስጄ ዘና ባለ ስሜት ላይ ከሆነች በኃላ ልንገራት ››እያለ ሲወዛገብ ቆየና‹‹እ…ፕሮግራማችን እንዴት ነው….?ወጣ እንበል ወይስ እዚሁ ነው የምንቆየው?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አይ…ወጣ እንላለን..ሱፐርማርኬት ወጥቼ መሸማመት አለብኝ..መጠነኛ ድግስ ደግሳለው፣ማታ እንግዳ አለብኝ››
ንግግሯ ግራ አጋባውም.. ደነገጠም፡፡
‹‹የማታ እንግዳ ምን አይነት ነው?›› our
‹‹አንተም አለህበት…ዛሬ እዚህ ነው አይደል የምታድረው?››
እሷ ጋር እንዲያድር ስለጠየቀችው ደስ ብሏታል ..ግን እንግዳውስ…?ለመሆኑ ማን ነው
…?ሴት ነው ወንድ?፡፡‹‹እሺ ..እዚህ ነው የማድረው…ግን እንግዳውስ?››
‹‹እንግዲህ እሱን ከመጣ በኃላ ነው የምናውቀው…ልደር ካለ ግን እምቢ ማደር አትችልም የምለው አይነት ሰው አይደለም››በማለት ግራ አጋቢ መልስ ሰጠችው፡፡መልሷ ይብልጥ ቁርጠት ለቀቀበት…ይሄኔ ከመስሪያ ቤቷ ባለደረቦች አንዱ ነው….ሀለቃዋ ይሆን እንዴ…?ቢሆንስ ልደር ስላለ እንዴት እሺ ልትለው ትችላለች..?››ወይ ሴቶች ምን አይነት ቅኔ የሆኑ ፍጡሮች እንደሆኑ ሁሌ እንደደነቀው ነው፡፡ወንድም ሴትም በአንድ ላይ ሰው ተብሎ

መፈረጁ  አግባብ  አይደለም….አስተሳሰባችን  እምነትና  ፍላጎታችን  ምኑም  እኮ አይገናኝም››ሲል በውስጡ አብሰለሰለና..ነገሮች እስኪደርሱ ጠብቆ ለማየት ወሰነ…
‹‹ከዛ በፊ የተመቻቸ ጊዜ ካገኘው ነግራታለሁ…እንደውም ከማታው ፕሮግራሞ በፊት የእኔን ሀሳብ መስማት አለባት››የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰ‹‹በቃ እንሂዳ››አላት፡፡
‹‹እሺ፣ተነስ ብላ ቦርሳዋን አንጠለጠለችና ተነሳች..ተያይዘው ወጡ ..ያለችው ሱፐር ማርኬት ይዛው ከገባች በኃላ ምትፈልገውን ነገሮች ሁሉ ተገዝተው በመኪናው ከተጫኑ በኃላ.. ማኪያቶ እንጠጣ ብሎ አንድ ፀጥተኛ ካፌ ይዞት ገባና..ፊት ለፊት እንደተቀመጡ እንደምንም እራሱን አጠንክሮ ወደነጥብ መንደርደር ጀመረ
‹‹ለምን ወደውጭ እንደሄድኩ ታውቂያለሽ አይደል?››
‹‹ሁለተኛ ዲግሪህን ለመማር ነዋ››
‹‹አይ ያማ ሽፋን ነው….እውነተኛ ምክንያቴን አንቺም በደንብ ታውቂዋለሽ..ወደውጭ የሄድኩት ባንቺ ተበሳጭቼ ነው፡፡››
‹‹አንተን ለማበሳጨት ብዬ ግን ምንም ያደረኩት ነገር የለም››
‹‹እሱን ማግባት አልነበረብሽም››
‹‹ለምን …ታዲያ አንተን ወንድሜን ማግባት ነበረብኝ?››
‹‹ምን ችግር አለው?እርግጥ እንደወንድምና እህት አንድቤት አድገናል..ግን የስጋ ትስስር አልነበረንም››
👍859😁2🔥1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በማግስቱ የናፈቀው ቢሮ የገባው አራት ሰዓት አካባቢ ነበር….የማታው ስካር አንጎበሩ ሙሉ በሙሉ አለቀቀውም…አሁንም ጭንቅላቱን እየወቀረው ነው፡፡ለፀሀፊው መምጣቱን
ስላልነገራት አልገባችም…ከፍቶ ገባና ቁጭ አለ ..የሚሰራው ስራ ስላልነበረ የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው..ስልክ አውጥቶ ደወለ፡፡
‹‹እንዴት ነሽ…ለሊሴ?››
‹‹ደህና ነኝ ሰለሞን…እንዴት ነው ስራ?››
‹‹አሪፍ ነው..አሁን ተመልሼለሁ…ቢሮ ነው ያለሁት››
‹‹ውይ ለምን ሳትነግረኝ..ቀድሜ ገብቼ አፀዳድቼ ጠብቅህ ነበረ እኮ››
‹‹አይ ችግር የለውም..ቢሮው አሁንም ንፅና የተስተካከለ ነው››
‹‹አዎ እሱማ በሶስት ቀን አንዴ ከፍቼ አናፍሰዋለው….እና ስራህን ጨረስክ ማለት ነው?››
‹‹አይ አልጨረስኩም…በመሀል የሶስት ቀን እረፍት ስላለኝ ነው የመጣሁት…ለመሆኑ ያንቺ ነገር እንዴት ሆነ?››
‹‹የቱ?››
‹‹የሁለቱ ፍቅረኞችሽ ነገር?››
ለሊሴ ሰለሞን ባቀረበላት ሀሳብ መሰረት ከሁለት ፍቅረኞቾ መካከል አንዱን ለባልነት ለመምረጥ ምታደርገውን ጥረት ወዲያው ነበር የጀመረችው ….መጀመሪያ ነጋዴውን ለአንድ ወር ላታገኘው እንደማትችል ነግራ ከመንግስት ሰራተኛው ጋር ነበር የቀጠለችው..ሲደውልላት ትሄዳለች..ዝም ሲላት ትደውልለታልች….ከስራ መልስ ሳታገኘው ወደቤት አትገባም…እሁድ ቢያንስ ግማሹን ሰዓት ከእሱ ጋር ነች፡፡ይበልጥ ትኩረቷን ሰብስባ ከእሱ ጋር ባሳለፈች መጠን በፊት ከምታውቀው በላይ እያወቀችው …በፊት ከምታዳምጠው በላይ እያዳመጠችው መጣች፡፡አሁን ያለበትን የኑሮ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ..

የወደፊት እቅዶቹንና እነዛን እቅዶች ለማሳካት እያደረገ ያለውን ተጋድሎም እየተረዳችና እየተገነዘበች መጣች…..እሱ ላይ ያላት ቅሬታ ባገባው እኔን አኑሮ ቤተሰቦቼንም እንድረዳ የሚያበቃኝ ህይወት ሊሰጠኝ አይችልም የሚል ነበር…አሁን ስታስበው ግን ያንን ከእሱ ብቻ መጠበቅ እንደሌለባት ነው የገባት…እሱ ባለው ቁርጠኝነት ላይ እሷ ተጨምራበት ካገዘችውና ከጎኑ ሆና አብራው ከታገለች ጎዶሎው ሊሞላ የሚችል አይነት እንደሆነ ተረድታለች…ግን ውሳኔ ላይ ከመድረሷ በፊት ለእሱ የመደበችለት ወር ተገባደደ እና ለዛኛው የሰጠችውን ተመሳሳይ ምክንያት ሰጥታ ..ለአንድ ወር ያህል ልትደውልለትም ሆነ ልታገኘው እንደማትችል ነገራ ወደነጋዴው ሄደች፡፡
በእውነት ነገዴው ጋር ልክ እንደወትሮ ሁሉ ነገር ተሰርቶ ያለቀ ሆኖ ነው የጠበቃት…ቤቱ የተዘጋጀ..እቃዎቹ የተደራጁ ናቸው…አዎ እያንዳንዱን ሀብቱንና አኗኗሩን ተራ በተራ አሳያት፣ቀጥታ እንዳገባችው ሕይወቷን ወደመስራት ሳይሆን የተሰራ ህይወት ውስጥ ገብቶ ለመኖር መሞከር ብቻ እንደሚጠበቅባት ተረዳች ፣ግን ለምን ልቧ ወደኃላ እንደሚጎትታት ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም‹‹…ታግዬ ያላሸነፉኩት በሌላ እጅ የተሰራ ህይወት ምን ትርጉም ይኖረዋል?››እራሷን ጠየቀች… መልሱ ቀላል አልነበረም….፡፡
ሁሉንም ሂደት አንድ በአንድ ዘርዝራ አስረዳችው፡፡ ሰለሞንም‹‹እና ምን ተሰማሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አሁንም እንደተወዛገብኩ ነው…ግን በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱ ጥያቄዎች በፊት ከሚመላለሱት የተለዩ ናቸው…እንግዲህ እኔ በህይወቴ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ ከፍተኛ ድክመት እንደለብኝ ነው የተረዳሁት፡፡››
‹‹አይ እንደዛ አይመስለኝም …አንቺ ቀሪ ህይወትሽን አብሮሽ በደስታ የሚዘልቅና ከቤተሰቦችሽም ጋ ተሰስማምቶ የሚያኮራሽ ለፍፅምነት የተጠጋ ባል እየፈለግሽ ነው….በዚህ ምድር ላይ ደግሞ ለፍጽምና የተጠጋ ነገር መምረጥ ቀላል ነገር አይደለም፡፡አንድ ታሪክ ልንገርሽ..
‹‹ደስ ይለኛል››
ደቀ መዝሙሩ  መምህሩን ‹‹ፍፁምና በህይወታችን እንዴት አድርገን ነው ፍፅማዊ የሆነ ነገር መጎናፀፍ የምንችለው? ሲል ጠየቀው ፡፡ መምህሩም አሰብ አደረገና ‹‹የዚህን መልስ

እንድነግርህ ከፈለክ በፊት ለፊት በር ወደ ግቢው የአትክልት ስፍራ ቀጥ ብለህ ግባ ።በመንገድህ ከምታገኛቸው አበቦች መካከል በጣም የሚያምረውንና ደስ ያሰኘህን ቀንጥስና በጎሮ በር ውጣ …አንዴ ያለፍከውን አበባ ከእንደገና ወደኃላ ተመልሰህ መቅጠፍ አትችልም አሉት።›› አለው ።እሱም ትዕዛዙን አክብሮ እንዳተባለው ወደ አትክልቱ ስፍራ ገባና እስከመጨረሻው ጥግ ከተጓዘ በኃላ ባዶ እጅን በጓሮ በር ወጣ።
መምህሩ ‹‹ለምንድነው አንድ ቀንበጥ አበባ እንኳን ይዘህ መውጣት ያልቻልከው?››ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹ምርጥ የተባለውን አበባ ወዲያው እንደገባሁ ነበረ ያገኘሁት... ግን የተሻለ አገኛለሁ ብዬ በማሰብ ሳልቀነጥስ ወደፊት ቀጠልኩ .. መጨረሻው ላይም ደረስኩ.. ወደኃላ የመመለስ እድል ስለሌለኝ ባዶዬን ለመውጣት ተገደድኩ›› ሲል መለሰ።
መምህሩ መልሱን ሲሰሙ ፈገግ አሉና ‹‹አዎ! ትክክል ነህ ፤ህይወት እንደዛ ነው ።ፍፁምናን ለማግኘት ይበልጥ በዳከርን ቁጥር ብኩን እየሆንክ ትሄዳለህ።እውነተኛ ፍፁምናን መቼም የትም አታገኝም።››ሲሉ መለሱለት። ‹‹ገባሽ አይደል?››
‹‹አዎ ገብቶኛል››
‹‹እንግዲያው ፍፅም በምናብ አለም ካስቀመጥሽው ወንድ ጋር የሚስማማ ባል እንደማታገኚ አውቀሽ ለሚማጡት 10 ቀናት ሁለቱንም ሳታገኚ አስቢበት..ከዛ ማንኛቸው ናቸው የበለጠ የሚናፍቁሽ..የትኛው ቢያቅፍሽ ትፈልጊያለሽ ….?ማንኛቸው የልጆችሽ አባት ቢሆኑ ይሻላል..?በህልምሽ እየደጋገመ የሚመጣው የትኛው ነው?፡፡ለ10 ቀን አስቢበት፡፡››
‹‹እሺ እንደዛ አደርገላው..ግን አሁን አሁን እየገባኝ ያለው እኔ ከባሌ ምን እጠብቃለው ብቻ ሳይሆን ለባሌስ ምን ይዤለት ሄዳለው…?የሚለውን በጥልቀት ማሰብና መዘጋጀት እንዳለብኝ ነው፡፡ ››
‹‹ጎበዝ ነሽ…ይሄ ትልቅ መረዳት ነው..በይ ደህና እደሪ››
‹‹ውይ …ከመዝጋትህ በፊት…ድፍረት አይሁንብኝና ዛሬ ቤት ለምን አትመጣም››
‹‹ለምን?››
‹‹እማዬ የማሪያም ድግስ አለባት….ማህበርተኞቹ እስከ10 ሰዓት ነው የሚቆዩት 11 ሰዓት ብትመጣ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…››
‹‹አረ ተይ››
‹‹ምን አለበት…ቤተሰቦቼ በጣም ነው ደስ የሚላቸው››
‹‹11 ሰዓት ነው ያልሽኝ?፡፡››
‹‹አዎ 11 ሰዓት››
ብቻውን ሆኖ ስለአስቴር እያሰበ ከሚሰቃይ ከሰው ጋር ተቀላቅሎ የባጥ የቆጡን እያወራ ሊረሳት ቢሞክር እንደሚሻለው አሰበእና ‹‹በቃ እሺ መጣለሁ››አላት፡፡
‹‹በቃ አቃቂ ፖሊስ ጣቢያው ጋር ስትደርስ ደውልልኝ..ወጥቼ እቀበልሀለው››
‹‹እሺ ደውላለው››
ስልኩን ዘጋው፡፡ እሺ ማለቱን ፍጽም አላመነም….ጠበል ለመቅመስ ከሜክሲኮ
አቃቂ….ለመሆኑ በህይወቱ ጠበል የተጠራውና ጥሪውን አክብሮ የሄደው መቼ ነው..?ፍጽም አያስታውስም….
እንዳለችው …..እንደደወለላት ደቂቃ ሳታባክን ነው ወጥታ የተቀበለችው….መኪናውን
እዛው አስፓልት ዳር ፓርክ አደረገና ተከትሏት ይዛው ሄደችው.. ግን ወደሚያስደነግጥ ቦታ ነው ይዛው የሄደችው…ይሄንን ግቢ ትናንትና በዚህን ሰዓት መኪና ውስጥ ሆኖ ከአሰሪዎቹ ጋር በመሆን ሲሰልለው ነበር …‹‹ምን አይነት መገጣጠም ነው?››ለለሊሴ ምንም አይነት የመደነቅና የመገረም ስሜት ሳያሳያት ተከተላት፡፡አሁን ነገሮችን ገጣጥሞ ሲያስብ በፀሎት እሱን እንዴት እንዳገኘችውና ስልኩን ከማን እንደወሰደች ተገለፀለት፡፡
👍723👎2