አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍9
‹‹እያንገላቱን..እነማን ናቸው?››
‹‹እኛ በስም አናውቃቸውም..ሮንድ መሆናቸውን ብቻ ነው የምናውቀው፡፡›› ኑሀሚ ነች ተናጋሪዋ፡፡
‹‹በቃ ሳጆን ሮንድ ለሚያሰማሩ የቀበሌ ሰዎች ንገራቸው፡፡በተለይ እነዚህን ሁለት ልጆች እንዳይነኳቸው፡፡እናንተም ከአሁን ወዲህ ምንም አይነት ችግር ካጋጠማችሁ…ማለቴ ሮንድም ሆነ ሌላ ማንም ሰው ሊተናኮላችሁ ከሞከረ መጥታችው ቀጥታ ለሳጅን ንገሩት..እሱ ሁሉን ነገር ያስተካክልላችኋል ..አይደል ሳጅን?››
‹‹በትክክል ኮማንደር››ብሎ ትዕዛዙን ተቀብሎ ወታደራዊ ሰላምታውን ሰጥቶ ወጥቶ ሄደ፡፡
…‹‹በሉ አሁን መሄድ ትችላላቸሁ፡፡››
‹‹ኮማንደር እናመሰግናለን..እግዜር ይስጥልን፡፡››ብለው ተያይዘው ወጡ፡፡ኮማንደር ሌላ ባለጉዳይ እንዳይገባ ቶሎ ብሎ ቢሮውን ከውስጥ ቀረቀረና ወለል ላይ ተንበርክኮ ጠረጴዛ ስር ገባ፡፡ፈለገ አገኘው፡፡ በስነስርአት ትክክለኛው ቦታ ላይ ተቀምጧል፡፡ አነሳው..እና ወጣ፡፡ስልኩን አንሰቶ ደወለ
‹‹ሀለቃ፡፡››
‹‹እሺ እየተመለከትኳችሁ ነበረ እኮ፡፡››
‹‹ልጆቹ  መአተኞች  ናቸው፡፡እያወቅኩ  እራሱ  እኮ  አሳመኑኝ፡፡ በምን  አይንሽ  አየሻቸው?…ይገርማል፡፡››

‹‹አንድ ወር ሙሉ የቀንና ሌት ውሎቸውን ተከታትዬለሁ፡፡ሁሉንም መስፈርቶቼን የሚያማሉ እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ይሄው የመጨረሻ ፈተናውን አልፈዋል፡፡ እግዲህ እነዚህን ለአንድ ስድስት ወር ሲሰለጥኑ ምን አይነት እሳት የላሱ ሰላዬች እንደሚወጣቸው መገመት ቀላል ነው፡፡››የሚል አስተያየት ነበር የሰጠችው፡፡
‹‹በዛ ጥርጥር የለኝም…››
‹‹ኩማንደር በፈተናው ስለተባበርከኝ አመሰገናለሁ፡፡››
‹‹ሀለቃ….ለእንደዚህ አይነት ለሀገር ወሳኝ ለሆነ ሰራ የራሴን የሆነ ጥቂትም ቢሆን አስተዋፅኦ እንዳበረክት እድሉን ስላገኘው እኔ ነኝ ክብር የሚሰማኝ፡፡››
‹‹እሺቸው፡› ስልኩተዘጋ፡
ይሄ ለስለላ ተግባር ብቁ እንዲሆኑ ያስቻላቸው የመጀመሪያ የተግባር ፈተናቸው ነበር፡፡
ከዚህ ሁሉ ረጅም የልጅነት የመከራ ወቅት ትዝታዋን ስታመነዥግ ለሳዕታት ስላሳለፍች አእምሮዋንም ደከማትና አይኖቾን ከደነች…ወዲያው እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍62🥰8👏7🔥65👎2
‹‹አይ አመሰግናለው ..እኔው አደርጋዋለው፡፡››ብሎ በድንጋጤ ሀውልት ሆኖ ከቆመበት ተንቀሳቀሰና ኑሀሚ ወዳለችበት ጎጆ መጠጋት ጀመረ፡፡እነሱ እንዲገድሏት ማድረግ እችላለሁ ማለቱ ሰውነቱን በድንጋጤ ነው ያደነዘዘው…እነዛ ለአውሬ የቀረበ ባህሪ ያላቸው የእድሜ ዘመናቸውን በጫካ ሲሹለከለኩ የሚኖሩ ስለሆነ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሲያገኙ በተለይ ተገዳዮ ሴት ስትሆን ምን እንደሚያደርጉ ከልምድ ያውቀዋል፡፡‹‹መሞቷ ካልቀረማ ቢያንስ በክብር እንድትሞት ማድረግ አለብኝ›› ሲል አሰበ፡፡ሽጉጡን ከወገቡ አወጣና ውስጡ ስንት ጥይት እንዳለው አረጋገጠ…በትከሻው አንጠልጥሎት የነበረውን ጠመንጃ በቅርብ ርቀት ለሚገኝ ለአንድ አቀበለውና ልክ የገዛ ራስህን ግደል እንደተባለ ሰው እግሮቹን መሬት ላይ እየጎተተ ኑሀሚ ወዳለችበት ክፍል መራመድ ጀመረ..፡፡
‹‹ስማ…››ትዕዛዝ ሰጪው ድጋሚ አስቆመው፡፡

‹‹ተቀያሪ ትዕዛዝ ይኖር ይሆን በሚል ተስፋ በፍጥነት ዞረ…፡፡እዚህ እሷን መግደል የመንደሩን ኑዋሪዎች ትኩረት ይስባል…አንድ ሰው ጨምርና ወደጫካው ወስደችሁ በማስወገድ በስርአት ቅበሯት…ደግሞ እንዳትዝረከረኩ››
ምንም ሳይመልስለት ወደውስጥ ገባ፡፡ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ይዞታል፡፡ተጠጋትና ስሯ ብርክክ ብሎ ተቀመጠ፡፡በትኩረት አያት ፡፡ይህቺን ሴት ካያት ቀን አንስቶ በልቡ ፈልጓታል.. በነፍሱ ተርቧታል..ደግሞ በሚገርም ሁኔታ ተግባብተዋል፡፡በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደአጋችና ታጋች ሳይሆን የአማዞን ተፍጥሮዊ ውበትን ለማድነቅና በእግዜር ተአምራዊ የመፍጠር ብቃት ለመደነቅ ከሆነ የአለም ጥግ ተስማምተው በመምጣት አብረው እየተጓዙ እንዳሉ የልብ ጓደኛሞች ብዙ ብዙ ነገሮች ተጨዋውተዋል፡፡አብረውት ለአመታት ከቆዩት ከአንዳንድ ጓደኞቹ ይልቅ ስለእሷ የህይወት ታሪክ በተሻለ ጥልቀት ማወቅ ችሏል፡፡ኢትዬጵያዊ እንደሆነች፤በልጅነቷ እናትና አባቷ እራሳቸውን አጥፍተው እንደተገኙ..እሷ ግን በሰው እጅ ተገድለዋል ብላ እንደምታምን፤አንድ ከራሷ በላይ የምትወደው መንትያ ወንድም እንዳላት..ከወንድ ጋር የህፃናት ማሳደጊያ ገብተው እንደነበር..ከዛ ጎዳናም ወጥተው ለአመታት ኖረው እንደሚያውቁ ..ብዙ ብዙ ነገር ነግራዋለች፡፡፡አንድ የደበቀችው አንኳር ነገር ቢኖር ለኢትዬጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት ሰላይ በመሆን ለአመታ መስሯቷንና የስለላም ሆነ የወታደራዊ እውቀት እንዳላት ነው፡፡
እና የሰው ልጅ ተፈጥሮ ደግሞ ስለአንድ ሰው ታሪክ የበለጠ እያወቀን በሄደን ቁጥር በሰውዬው በተለየ መልኩ እየተሳብንና እየተመሰጥን እንሄዳለን፡፡በተለይ የሰውዬው ታሪክ አሳዛኝና በመከራና በአድቬንቸር የተሞላ ከሆነ በቃ በቀላሉ በሰውዬው ተፅዕኖ ስር መውደቃችን አይቀሬ ነው፡፡ከእንደዚህ አይነት ሰው ጋር ብዙ እየተቀራረብን በሄድን ቁጥር በፍቅሩ የመውደቃችን እድል ለመቶ ፐርሰንት የቀረበ ነው፡፡አሁን ካርሎስን ያጋጠመው ያ ነው፡፡
በሀዘን ልቡ እንደተኮማተረች ሚንቀጠቀጥ እጁን ትከሻዋ ላይ አሳረፈና ነቀነቃት፡፡ማራኪ ህልም ላይ ስለነበረች በርግጋ ተነሳች፡፡
‹‹አይዞሽ አትደንግጪ..ተነሽ ፈልጌሽ ነው››አላት፡፡

‹‹አይዞሽ አትደንግጪ›› ማለቱ ለራሱ አስገረመው፡፡ልክ ቀይ የፅጌረዳ አበባ አስታቅፎ ፍቅር ወደምትሰራበት ልዩ ሰገነት ላይ ይዞት እንደሚሄድ ነገር ነው ያስመሰለው..ለጊዜው ሊጠነቀቅላት ፈልጎ ቢዋሻትም ከደቂቀዎች በኃላ እንደምትገደል ስታውቅ በህይወቷ ከደነገጠችው ድንጋጤ የመጨረሻውን ድንጋጤ መደንገጦ የት ይቀራል፡፡
ቀልጠፍ ብላ ተነሳችና ቆመች‹‹ምነው ጉዞ ልንጀምር ነው አይደል?፡፡››

‹‹አይ እኛ ቀድመን መጓዝ ልንጀምር ነው..እነሱ ቀስ ብለው ይከተሉናል፡›› አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ እንደሆነ ባያውቅም ዋሻት፡፡ተያይዘው ሲወጡ ከእሱ ጋር የተመደበው ሰው መሳሪያውን በትከሻው አንጠልጥሎ የእሷን ቦርሳ በእጁ ይዞ እየጠበቃቸው ነው፡፡ዝም ብሎ እጇን ያዘና ከአማዞን ወንዙ በተቃራኒ ወደጥቅጥቁ ጫካ የምትወስደውን ቀጭን የእግር መንገድ ተያያዘው ፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
🥰42👍37😢87
‹‹ጥሩ እዚህ ሁሉ ውስጥ ታዲያ እኔ ምንድነው ያደረኩተት?፡፡››ስትል በአግሯሞት ጠየቀችው፡
‹‹ከእሱ ጋር አንድ ቀን አሳልፈሻል…. አንድ ቀን አብረሽው አድረሻል…ስለእሱ ምን መረጃ እንዳወቅሽ አይታወቅም…መጀመሪያውኑ ከእሱ ጋር ያንን ጊዜ ያሳለፍሽው ዝም ብለሽ በየዋህነት ነው..?በውበቱ ተማርከሽ ሴትነትሽን ልትሰጪው ነው..?ወይንስ የሆነ የደህንነት ተቋም ያሰማራሽ ሰላይ ነሽ…?ይሄ ነው ጥርጣሬችን››
‹‹ታዲያ ይሄንን የምታጣሩበት ዘዴ የላችሁም?፡፡››

‹‹አለን…እኔም እንደዛ እንደሚደረግ ነበር ተስፋ ያደረኩት…በተጨማሪም ከሰውዬው ጋር ባሳለፍሽው አንድ ቀን ጥሩ ጊዜ ካሳለፋችሁ ያንን ከግንዛቤ አስገብቶ የተሻለ ውሳኔ ይወስናል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር..ግን ሁሉ ነገር ካሰብኩት በተቃራኒ ነው የሆነው…ለነገሩ ሰውዬው ሁሌ እንደዚህ ነው..የመግደል ሱስ አለበት፡፡››
ጓደኛው በስፓኒሽኛ ያወራው ጀመር ..ትንሽ ተጨቃጨቁና ተስማሙ፡፡

‹‹ምንድነው የሚለው?››

‹‹አይ ይበቃናል..በቃ የምትቀበርበትን ጉድጓድ ትቆፍር ነው የሚለው፡፡›› ዝም አለች፡፡
‹‹እዛ ድንጋይ ላይ ተቀመጪ››አላት..ዝም ብላው ሄደችና እንዳላት ተቀመጠች፡፡

ካርሎስ አካፋውን ከጓደኛው ተቀበለውና የመቆፈሪያውን ክፍል አስተካክሎ እራሱ መቆፈር ጀመረ..መሬቱን በሚቆፍርበት መጠን የገዛ ልቡም እየተቆፈረበት ነው፡፡‹‹አሁን የእውነት ይህቺን የመሰለች ልጅ ተኩሼ ገድላታለው?፡፡››እራሱን ይጠይቃል፡፡አይ እንደዛማ ማድረግ አልችልም፡፡ለራሱ ይመልሳል፡፡ግን ደግሞ ትዕዛዙን ተግባራዊ አለማድረግ ከለምንም ምህረት ምን እንደሚያስከትልበት በደንብ ያውቃል፡፡በቃ ሞት ነው..ለዛውም ለሌሎቹ መቀጣጫ በሚሆንበት መንገድ አሰቃቂ የሆነ ሞት ነው የሚጠብቀው፡፡
‹‹ለዚህች ለአራት ቀን ብቻ ለማውቃት ሴት ህልሜንም ህይወቴንም ልሰዋላት ዝግጁ ነኝ?››ሲል እራሱን ጠየቀ….መልሱ ቀላል እልሆነለትም፡፡
ጓደኛው ሊያግዘው ወደእሱ ተጠጋ፡፡ ከጉድጓዱ እንዲወጣ ጠየቀው ..መሳሪያውን ከትከሻው አነሳና አቀበለውና ወደጉድጓዱ ገባ…እየተፈራረቁ ጉድጓዱን ቆፍሮ ለማጠናቀቅ 30 ደቂቃ ያህል ፈጀባቸው፡፡ከዛ የመጨረሻውን ርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ሆኑ፡፡ አነሱም ለመግደል እሷም ለመሞት …ድንገት ወደ እሷ ሄደና ‹‹በጣም አዝናለሁ….ላድንሽ ባለመቻሌ በራሴ አፍሬለሁ››አለና ጉንጮን ስሞ ብድግ አለና ፊቱን አዞረ ፡፡
ካርሎስ ‹‹በቃ አንተ አድርገው…….እኔ ወደእዛ ዞር ብዬ ላጭስ››ብሎ ለጓደኛው ነገረውና ወደግራው ዞር ብሎ ሶስት ያህል  ርምጃ እንደተራመደ…ኑሀሚ ልክ እንደተናዳፊ ንብ ከተቀመጠችበት ተስፈነጠረችና የካርሎስን አንገት በእጆቾ ፈጥርቃ ይዛ በሌላ እጇ ወገቡ ላይ ያለውን ሽጉጥ መዘዘችና ግንባሩ ላይ ደቀነችበት‹‹አንተ ብቻ አይደለህም እኔም አንተን የመሰለ ቅን ፤መልካምና ፤ጀንትል ሰው ጋር የገዛ ህይወትን ለማትረፍ መፋለም በመገደዴ በጣም አዝናለው፡፡››አለችው
በዚህ ጊዜ ሁለተኛው ታጣቂ የያዘውን ዘመናዊ መሳሪያ በእሷ ትክክል ደቅኖ በማይገባት ቋንቋ ይለፈልፋ ጀመር፡፡
‹‹አይ አትዘኚ….ምን አለ በራሷ ተነሳሽነት የሆነ ነገር ማድረግ በቻለች እያልኩ ስፀልይ ነበር….የቻልሺውን አድርጊ ..በፀጋ እቀበላለው፡››አላት
‹‹እሺ ጓደኛህ መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ ንገረው፡፡››

እንዳለችው በሚገባው የስፓኒሽ ቋንቋ ነገረው፡፡መለሰለት፡፡

‹‹ምን አለ?››ጠየቀችው፡፡

‹‹በተአምር የሀለቃዬን ትዕዛዝ እንዲከሽፍ ማድረግ አልችልም….››ነው ሚለው፡፡

‹‹እንዴ ….ካለስቀመጠ እኮ ተኩስብሀለው..ይሄንን አልነገርከውም?››

‹‹ነግሬዋለው..እሱም ገብቶታል፡፡ ግን እንደእሱ ውሳኔ እኔን ለማትረፍ በመጣር ነገሩን ከማበላሸት እኔን መስዋእት ማድረግን መርጧል፡፡››
‹‹እንደዛ የሚያደርግ ይመስልሀል?››

‹‹እንደአለመታደል ሆኖ ይመስለኛል….አንድም ቀን በመሀለከላችን መግባት ኖሮ አያውቅም….እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን ለአመታት ሲጠብቅ እንደነበረ ነው የሚገባኝ፡፡››
እንግዲያው….አለችን በብርሀን ፍጥነት ሽጉጦን ከእሱ ግንባር አንስታ አቅጣጫውን ቀየረችና ተኮሰች …ደገመችው…ሰውዬው በቆመበት አይኑ እንዳፈጠጠ ተመለከታት..ከመሀል ግንባሩ ደም ቡልቅ ቡልቅ እያለ መውረድ ጀመረ ..ወዲያው ሽብርክ ብሎ ወደፊት ተደፋ፡፡ከዛ ለቀቀችውና ፈንጠር ብላ ቆመች፡፡
አንዴ መሬት ላይ ተዘርሮ በደም የታጠበው ጓደኛውን አንዴ እሷን እያፈራረቀ እያየ ግራ በመጋባት ደቂቃዎች አሳለፈ….ከዛ በርከክ ብሎ ጓደኛውን ገለበጠው…እጁን ወደ አንገቱ ልኮ በህይወት መኖር አለመኖሩን ተመለከተ፡፡
ሞቷል፡፡ኪሱን ፈተሸና የያዛቸውን እቃዎች አወጣ፡፡ እየጎተተ ለኑሀሚ ወደተቆፈረው ጉድጓድ ወሰደውና ውስጥ ከተተው፡፡ከዛ በአካፋው አፈሩን መለሰና ደለደለው..ካዛ አዲስ የተቆፈረ መሆኑን እንዳያስታውቅ የደራረቁ ቅጠሎችና እንጨቶችን ከአካባቢው እየሰበሰበ አለበሰባትና በተቻላ መጠን ከአካባቢው መሬት ጋር በእይታ እንዲመሳሰል አደረገ፡፡መሳሪያውን ታጠቀ…ከኪሱ ያወጣቸውን እቃዎች የገዛ ኪሱ ውስጥ ጨመረ.. .ሟቹ ጓደኛ ይዞት የነበረውን የእሷን ቦርሳ አቀበላትና ….ከዛ ጎደኛው ጀርባ ላይ ከነበረው የመንገድ ሻንጣ ጠቃሚ ነው ያላቸውን እቃዎች…ባትሪ ከነተለዋጭ ድንጋዩ፤የተወሰኑ የታሸጉ ምግቦችን፤ሲቆፍሩበት ያነበረውን አካፋ መርጦ ወደረሱ ቦርሳ በመጨመር ‹‹በይ ፈጠን በይ እንሂድ›› አለትና ወደፊት መጓዝ ጀመረ፡፡
‹‹ወደየት ነው የምንሄደው?፡፡››

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ…?በቃ እኮ አልቆልናል..ከተያዝን ሁለታችንም እንገደላለን..ስለዚህ ቢያንስ በተቻለን መጠን ለማምለጥ መሞከር አለብን፡፡››
‹‹እርግጠኛ ነህ ራስህን የምታድንበት ሌላ መንገድ የለም?፡፡››

‹‹ነገርኩሽ..ይልቅ እያንዳንዷ ደቂቃ የህይወት ዋጋ አላት…ምንም ነገር መፈጠሩን ከማውቃቸው በፊት ከዚህ በጣም ርቀን መሄድ አለብን ››
..መጓዝ ጀመረች፡፡ተከተለችውና ደረሰችበት፡፡
‹‹እንካ…..››ሽጉጡን ወደእሱ ዘረጋች..ቀና ብሎ በትዝብት አያትና‹‹አሁንም ያንቺው ሆነ እኮ…ያዥው››አላት፡፡

‹‹ምንም ሳትከራከር…ሽጉጡን ቦርሳዋ ውስጥ ከተተችና በትከሻዋ አንጠልጥላ ወደጥልቁ የአማዞን ሚስጥራዊና ትንግርተኛ ደን በደነዘዘ ስሜት ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
53👍47👏8🤔1
‹‹አንደኛ እዚህ የአማዞን ደን ውስጥ ግማሽ እድሜዬን አሳልፌለሁ …ስለዕጽዋቱና እንስሳቱ ባህሪ ጥሩ የሚባል እውቀት አለኝ፡፡የትኛው እንስሳ አደገኛ እንደሆነ የትኛው ዕፅዋት ለየትኛው አይነት በሽታ መድሀኒት እንደሚሆን አውቃለሁ….››
‹‹እሺ ሁለተኛውስ?››

‹‹ሁለተኛው…..ሰው ያለበት አካባቢ ስንደርስ ብራዚላዊ ስለሆንኩ በቃለሉ ከሀገሬ ሰዎች መግባባትና እርዳታ ማግኘት እንችላለን…በዛ ላይ ከሁለት የአገረቱ ቋንቋዎች በተጨማሪ ፖርቹጊዝም እችላለሁ፡፡ታውቂያለሽ ብራዚል ብሄራዊ ቋንቋ እንደፔሩ ስፓንሽ አይደለም ፖርቹጊዝ ነው፡፡
‹‹ለመሆኑ ስንት ቋንቋ ነው የምትናገረው››

‹‹ሰባት››

‹‹ጥሩ… እሺ ሶስትኛውስ?››

‹‹ሶስተኛው ከዚህ አደገኛ ጉዞ በሕይወት ተርፎ ለመውጣት ዋናው አስፈላጊው አድቫንቴጃችን የአንቺ ጀግንነት፤ የመፋለም ብቃትና ቅልጥፍና ነው፡፡››
‹‹እየቀለድክ ነው?››

‹‹በፍፅም ….ስትፋለሚ እኮ ልክ እንደነብር ነው….ኢንተርፖል ነው ወይስ ሲአይ ኤ ነው የምትሰሪው?›› እንደቀልድ አስመስሎ በውስጡ ሲያብሰለስለው የቆየውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
ዝም አለች….ለደቂቃ ትንፋሽ ወሰደችና..‹‹አንተም ሀለቃችሁን ለመሰለል በሆነ አካል ተቀጥሬ የተላኩ ሰላይ ነገር አድርገህ አምነኸል አይደል?››ስትል ጤቀችው፡፡
‹‹በፊት ፈጽሞ አላመንኩም ነበር…በህይወቴ ሁሉ ላሲዝ እችል ነበር፡፡ጥዋት እዛ የቆፈርነው ጉድጓድ ጋር እንዴት እኔን እንዳገትሺኝ.. እንዴት ሽጉጠን እንደነጠቅሽና ጓደኛዬንም የገደልሽበት ብቃትና ቅልጥፍናን ከየሁ በኃላ ግን እነሱ የጠረጠሩት ትክክል እንደሆነ እርግጠኛ ሆኜለው፡፡በጣም ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠና የወሰደና የረጅም ጊዜ የመስክ የፍልሚያ ልምድ የሌለው ሰው ካልሆነ በዛ ብቃት በመጨረሻው ሰዓት የሚፋለም ሰው የለም፡፡››
‹‹ስለወታደራዊ ስልጠናው ምናምን ትክክል ነህ…እኔ ግን ከኢንተርፖል ጋረም ሆነ ከምትላቸው ሲአይኤ ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም ..ሀለቃህን ያገኘሁት እንደማንኛውም ተራ ሰው በአጋጣሚ ነው፡፡››አለችው፡፡
ዝም አላት…የተናገረችውን እንዳላመናት ተሰምቷታል፡፡ ግን ደግሞ እሱን ለማሳመን ከዚህ በላይ ዝርዝር ጉዳዮችን ልትነግረው አልቻለችም….እሱን ከዚህ በላይ ትመነው ወይስ ይቅርባት መወሰን ተቸግራለች፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍679🥰2
#ነገሩ_ገብቶኛል !

ጠዋት ቤትሽ መጣሁ
አንቺ ግን የለሽም፤ ቤተስኪያን ሄደሻል::
ያዉ፤ የገላገልሽዉ
የጉደሩ ጠርሙስ ባዶዉን ተኝቷል::
ስትንፈራገጪ ድንገት የረገጥሽዉ
ብርጭቆ ተሰብሮ፣ ወለሉን ሞልቶታል::
ብርድ ልብስሽ የለም
እንደአድፋጭ ዉሽማ፣ አልጋሽ ሥር መሽጓል::
አንሶላሽ ከፍቶታል
በሌሊቱ አበሳ ሽንሽን ቀሚስ መስሏል::
ግድየለሽም ፍቅሬ ነገሩ ገብቶኛል
በህልምሽ ከኔ ጋር፣ ተቃቅፈሽ አድረሻል::
እኔ አኩርፌሽ ብዬ፣ ጅሉ ልቤ ወልቋል::
አይ የልብሽ ጉዱ !
ዕምነትን መሻሩ፣ ልማድን መካዱ
ለብቻ እንዳደረ፣ ደሞ እንደጨዋ ልብ፣ ቤተስኪያን መሄዱ::
አይ የልብሽ ጉዱ !

ከስውር-ስፌት

🔘ነብይ መኮንን🔘


#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍2710😁4👏1
#አርምሞ.

.
.
ፍቅርና
ህብረት፥
አጥሩን ካልጣሰ
.
ንስሃና
ይቅርታ፥
ተበዳይ ካልካሰ
.
ፍርጠማና
ጡንቻ፥
ማዕበል ካልገታ
.
ጥበብና
ብስለት፥
ቋጠሮ ካልፈታ
.
ብትነቃም
ብታውቅም
አቅምህን
ሰብቀህ፥
እንደ ናዝሬት ጌታ
.
ሀቅህን
ባደራ
የምታኖርበት፥
የምትሰጥበት፥ ለጊዜ ይሁንታ
.
ሽንፈት
እንዳይመስልህ
ቀን
ቆጥሮ
እሚያደባይ
አቅም ነው
ሃይል ነው
ጉልበት ነው #ዝምታ

🔘ረድኤት አሰፋ🔘

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍281
‹‹ቅድም እዛ ካፌ ለአስተናጋጁ 5 ብር ቲፕ ሰጠሸ…አሁን ደግሞ ለእኛ አንድ ሺ ብር ጭማሪ ተሰጠን፡፡››
‹‹እሱስ ይገርማል…እውነትህን ነው፡፡››
‹‹አሁን ምን እናድርግ?››
‹‹እስከዛሬ አድርገነው የማናውቀውን ሌላ አንድ ነገር እናድርግ፡፡››አለችው ..ሀሳቡ ድንገት ነው በአእምሮዋ ብልጭ ያለው፡፡እሱ ያሰበችውን ለመስማት በጉጉት ይጠብቅ ጀመር፡፡
‹‹ምን እህቴ..?››
‹‹አልጋ ተከራይተን እንደር፡፡››
‹‹ምን?››ግራ ገባው ፡፡..እንዴት አሰበችው ሲል ተገረመ….?በቅፅበት በምታመጣቸው አስደንጋጭ ሀሳቦች ሁሌም እዳስደመሙት ነው፡፡ማብራራቷን ቀጠለች‹‹አዎ ይሄን ሁሉ ብር ይዘን ለምን እዚህ አፈር ላይ እንተኛለን፡፡ሻወር ወስደህ…ንፅህ አልጋ ላይ አንሶላ ገልጠህ ከላይ ንፅህ ብርድ ልብስና አልጋ ልብስ ደርበህ..ግድግዳና ጣሪያ ያለው ቤት ውስጥ መተኛት አልናፈቀህም..?››

‹‹በጣም እንጂ እህቴ በጣም ናፍቆኛል…ግን እውር ገና አይኑ እንደበራለት ምርኩዙን እንደሚጥል እኛም እንዳዛ መሰልን፡፡››አላት

‹‹ግድየለህም ይምሰል….በል ተነስ…..››ተያይዘው ሆቴሎች በርከት ብለው ወደሚገኙበት ሰፈር ሄዱ፡፡ መታወቂያ ስላልነበራቸው እና እድሜያቸውም ገና ጮርቃ በመሆኑ ምንም እንኳን ብሩ ቢኖራቸውም ቤርጎውን መከራየት ቀላል አልሆነላቸው፡፡ግን እነሱም በተለይ ኑሀሚ በቀላሉ ተስፋ የምትቆርጥ ልጅ ስላልሆነች ሌላ ዘዴ ዘየደች ፡፡ለአልጋ ክፍሏ ተጨማሪ 50 ብር ሰጥተው ያሰቡትን አልጋ አግኝተው በአሰቡት መንገድ ለማደር ቻሉ፡፡ያም ካሰቡት በላይ ጥልቅ ደስታና ለፍፁምነት የተጠጋ እርካታ አጎናፀፋቸው፡፡ናኦል በጥዋት ነበር ኑሀሚን አግለብልቦ ከቤርጎ ይዞት የወጣው፡፡ ሲቀሰቅሳት‹‹ወንድሜ ደግሞ ምን አለ ትንሽ ብንተኛ..?›ብላ ለምናው ነበር፡፡
‹‹ምነው ለሊቱን ሙሉ ተኝተሸ አይደል ያደርሽው ?አልጠገብሽም?››
‹‹እንዴ ትቀልዳል እንዴ ?እንዲህ እይነት ምቹ ክፍልና አልጋ ውስጥ ስልሳ ሶስት ቀን በተከታታይ ብተኛ እራሱ አልጠግብም፡፡››ስትል የእውነት የምታስበውን ነገረችው፡፡
‹‹እንደዛ ከሆነ ምን ችግር አለ? ብር አለን ዛሬ ማታም ደግመን እናድራለን..፡፡››ቃል ገባላት፡፡
‹‹አንተ ልጅ ይሄን ምቾት ለምደህ ወደጎዳናችን አልመለስም ብለህ እንዳታስቸግረኝ፡፡››ስጋቷን ተነፈሰች፡፡እንዲህ ልትናገር የቻለችው..በራሷ ሀሳብ ውስጥ እየበቀለ ያለው ተመሳሳይ ስሜት ስላለ ነው…ምን አለ ወደእዛ ጎዳና ባንመለስ የሚል…እሱም‹‹ባልመለስ ደስ ይለኛል.፡፡ለማንኛውም አሁን ቶሎ እንሂድ ምስራቅ መጥታ እንዳታጣን፡፡››አላት፡፡
‹‹ብታጣንስ ምን ችግር አለው?››በብስጭት ጠየቀችው፡፡
‹‹እንዴ ቁርስ ገዛልሻለሁ ብያትለሁ እኮ..አሁን ብታጣን ብሩን ሰስተን ነው የሚመስላት…ትቀየመናለች፡፡››
ሳቀችና‹‹ይሁንልህ፡፡››ብላ ክፍሉን ለቃ መንገድ ጀመረችለት፡፡ ..እሱም በደስታ ከኃላ ተከተላት፡፡ማደሪያቸው የነበረ ቦታ ሲደርሱ ገና አንድ ሰዓት ከሩብ ነበር…ምስራቅን ለማግኘት ግን እስከሁለት ሰዓት መጠበቅ ነበረባቸው፡፡
‹‹ጩጬዎቹ ሰላም ናችሁ?››በተለመደ ሰላታዋ ተቀላቀለቻቸው፡፡
‹‹አለን..ሰላም ነን…ቆየሽ፡፡››አላት ናኦል፡፡
‹‹ባሌ አለቅ ብሎኝ ነው የቆየሁት››ስትል መለሰችለት፡፡፡
‹‹እንዴ..ባል አለሽ እንዴ?››በድንጋጤ እና በቅሬታ ጠየቃት፡፡፡
‹‹አለኝ ..ግን ፀባይ የለውም ..ሌላ ባል ካገኘው እፈታዋለሁ፡፡››አለችው፡፡
‹‹አዎ ብትፈቺው ይሻላል፡፡››አላት ናኦል
‹‹ፈታውስ ….አንተ ልታገባት ነው?››ኑሀሚ በንዴት ጠየቀችው፡፡
‹‹እስካድግ ከጠበቀቺኝ አገባታለሁ፡፡››
ምስራቅም‹‹አረ ጠብቅሀለው፡፡››አለችው በፈገግታ ተሞልታ፡፡
‹‹ብትጠብቅህስ ምን ዋጋ አለው…አንተ እስክታድግ እኮ እሷ ታረጃለች፡፡››ኑሀሚ ነች አብሻቂ ንግግር የተናገረችው፡፡
ናኦል እንደመበሳጨት ብሎ‹‹አንቺ ደግሞ ታርጃ ምን ችግር አለው…አሁን እንሂዳ ..ቁርስ እንብላ፡፡››አለ
‹‹..እኔም የመጣሁት ለቁሩሱ ነው፡፡››ብላ ተያይዘው ሄዱ፡፡እስከ 3 ሰዓት ድረስ እዛው ቁርስ ቤት ሲበሉና የባጥ የቆጡን እያወሩ ሲጫወቱ ነው የቆዩት፡፡
ከዛ ድንገት ‹‹የሆነ ቦታ አብራችሁኝ ትሄዳላችሁ?››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡

‹‹የት?››ኑሀሚ በተለመደ ጥርጣሬዋ ጠየቀች፡፡
‹‹እሱ ሚስጥር ነው..ስንደርስ ታዩታላችሁ፡፡››
‹‹እሺ እንሂድ››ነኦል በግብዣው ተስማምቶ ከመቀመጫው ቀድሞ ተነሳ፡፡ምስራቅ እየፈገግች ኑሀሚ እየተነጫነጨች ከኃላው ተከትለው ተያይዘው ሄድ፡፡ቀጥታ ታክሲ ተራ ነበር ይዛቸው የሄደችው፡፡ከዛ ስታዲዬም ተሳፈሩ፡፡ከዛ ጎተራ ታክሲ ውስጥ ገቡ፡፡መጨረሻ ሲደርሱ ወረዱና ፡፡በእግር መጓዝ ጀመሩ፡፡በዝምታ ወደምትወስዳቸው እየተከተሏት ነው፡፡ቀጥታ ወደኮንደሚኒዬም ነው ይዛቸው የሄደችው፡፡አንዱ ኮንዲንዬም ውስጥ ይዛቸው ገባችና በደረጃው እየወጡ የመጨረሻ ፎቅ ላይ ወደሚገኝ ክፍል ይዛቸው ገባች ፡፡ቁልፍ ከኪሷ አወጣችና ከፈተቸ፡፡ቀድማ ገባችና ‹‹ግቡ›› አለቻቸው…ግራ በመጋባትና በመደነቅ ተከትለዋት ገቡ፡፡
የሚያምር ቤትና የሚያማማሩ እቃዎች ያሉበት ባለሁለት  መኝታ ክፍል ቤት ነው፡፡ሳሎኑ መሀከል ወለል ላይ ቆመው በመገረምና በመደነቅ ዙሪያ ገባውን እየተቁለጨለጩ ማየት ቀጠሉ፡፡እለፉና ሶፋው ላይ ተቀመጡ፡፡
‹‹በስመአብ ዘናጭ ቤት ነው…የድሮ ቤታችንን ይመስላል…ያንቺ ነው እንዴ?››ናኦል በአድናቆት እንደተሞላ ጠየቃት፡፡
‹‹አይ የወንድሜ ነው…ታስሮብኛል ያልኳችሁ ወንድሜ፡፡››
‹‹እ ነው… ታድሎ…››
‹‹ምን ታድሎ ትላለህ ..አምስት አመት እኮ ነው የተፈረደበት…ገና እስር ቤት ከገባ ስድስት ወሩ ነው..ቢያንስ ከሶስት አመት በላይ አዛ ይኖራል፡፡››
‹‹ያሳዝናል…››
‹‹አዎ ያሳዝናል..በሉ ዘና በሉ ፡፡ሱቅ ደርሼ መጣሁ፡፡›› ብላ ቴሌቪዢኑን ከፈተችላቸውና የፈለጉት ጣቢያ ላይ መቀያየር እንዲችሉ ሪሞቱን አቀብላቸው ወጥታ ሄደች፡፡

ኑሀሚም ኮቴዋ መራቁን እርግጠኛ ከሆነች በኃላ‹‹አልሰማ አልከኝ እንጂ ንግሬሀለው››አለችው፡፡
‹‹ምኑን ነው የነገርሺን?››
‹‹ይህቺ ሴት ማፍያ ነገር ነች…እያት እስኪ በየቀኑ እንድ አዲስ ነገር ታሳየናለች፡፡››
‹‹ቢሆን ግን ለእኛ እኮ ደግ ሆናልላለች፡፡››
‹‹የሸከከኝ እኮ እሱ ነው፡፡ለምን ደግ ሆነችልን….?ለምን አላማ ፈለገችን…?ብቻ ዝም ብለህ እትንሰፍሰፍላት፤በጥንቃቄ ተከታተላት፡፡››
በምትናገረው ነገር ሙሉ በሙሉ ባያምንበትም ከእሷ ጋር ጨከን ብሎ መከራከሩን ሳላልፈለገ ‹‹እሺ እንዳልሽ፡፡››አላት፡፡
ወዲያው ምስራቅ በኩርቱ ፔስታል ሙሉ የቤት አስቤዛ ገዝታ መጣችና ፍሪጅ ውስጥ ትጠቀጥቀው ጀመር፡፡
../////
ካርሎስ ከጥልቅ እንቅልፉ ባኖ ሲንሳቀስና ነበር እሷም ከጥልቅ ትዝታዋ ባና ከሀገር ቤት የቆየ ታሪኳ አሁን ወዳለችበት ነባራዊ ሁኔታ የተመለሰችው ፡፡በዛ ድቅድቅ ለሊት በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ማህፀን ውስጥ የተንጠለጠሉበት ግዙፍ ዛፍ ቀርንጫፍ ላይ ከአንድ ጎረምሳ ደረት ላይ ተለጥፋ መገኘቷን ስተስበው ተአምር የሚያስብል ሆኖ ነው ያገነችው፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍9823🥰5👏1
ስለእሱ ምንም እንዳትናገርና ከዛም አልፎ መልሳ በፍቀዷ እጁ እንድትገባ ማድረግ የሚያስችል ዘዴ ነው የመጣለት፡፡በጣም ደስ አለው፡፡በጥንቃቄ አስቦ ቆንጆ ኢሜል አዘጋጀ፡፡ኢትዬጵያ ለሚኖረው ለኑሀሚ ወንድም ኑሀሚ እሱ ጋር እንዳለች አስመስሎ ከፎቶ ጋር በማያያዝ ..እህቱን ማግኘተ ከፈገ ጉዳዩን ለማም ሳይናገር በሚስጥር ሹልክ ብሎ በአስቸኳይ ወደደቡብ አሜሪከ መምጣት እንዳለበት ገልፆ ላከለት፡፡ መልስ እስኪመለስለት የኬኬይን ቅመማውን እና የምርት ስራውን ለማየት ወደቤዝመንት ተጓዘ፡፡
አዲስ አበባ-ኢትዬጵያ
ናኦል የእህቱን መጥፋት በተመለከተ እስከአሁን ምንም አይነት ተጨባጭ የሆነ መረጃ ከመስሪያ ቤቷም ሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እያገኘ አይደለም፡፡ምስራቅም ሳምንቱን ሙሉ የሆነ ነገር ለማግኘት የተቻላትን ሁሉ እየጣረች ቢሆንም እስከአሁን ስለመሞቷም ሆነ በህይወት ስለመኖሯ ምንም አይነት ፍንጭ ልታገኝ አልቻለችም፡፡ዛሬ ግን እቤቱ ቁጭ ብሎ በእንባ እየታጠበ ማህራዊ ሚዲያዎቹን እያየ ባለበት ሰዓት በኢሜል አዲስ አይነት መረጃ ደረሰው፡፡መልክቱ ሲነበብ
እህትህን በህይወት ማግኘት ከፈለክ ለየትኛውም መንግስታዊ ተቋም መረጃ ሳትሰጥ ወደ ፔሩ ና …ወደ እህትህ የምትመጣበት 50 ሺ ዶላር በሳምንት ውስጥ ይላክልሀል፡፡ ማን ናቸው? ለምንድነው ይሄንን መልዕክት የላኩልኝ ?ብለህ ሌላ ምርምር ውስጥ እንዳትገባ…እንደዛ ከሆነ ግን እህትህን ታጣታለህ፡፡
ብሎ ከእህቱ ፎቶ ጋር አያይዞ ተልኮላታል፡፡
ወዲያው ስልኩን አነሳና ደወለ፡፡ያው ወደመከረኛዋ ምስራቅ ጋር ነው የደወለው፡፡
‹‹ምስራቅ እህቴን››
‹‹ምን ሆነች? ምን ሰማህ?፡፡››በድንጋጤ ተውጣ ጠየቀችው፡
‹‹አሁኑኑ መገናኘት አለብን ..››
‹‹የት ነህ ?››
‹‹እቤት ነኝ…የት ልምጣ?››
‹‹አይ እኔ መጣሁ… እዛው ጠብቀኝ፡፡››ብላ ስልኩን ዘጋችበት፡፡
በተቀመጠበት ሆኖ እስክትመጣ መጠበቅ አልቻለም፡፡እቤቱን ለቆ ወጣና ግቢ ውስጥ መንጎራደድ ጀመረ….‹‹ማነው የሚቀልድብኝ?››ጥያቄውን ጠየቀ እንጂ መልስ ማግኘት አልቻለም፡፡
‹‹ደግሞ ቀልድ ነው እንደይባል ፎቶውን ከየት ሀገር ውስጥ የተነሳችው እንዳሆነ ያስታውቃል፤የለበሰችውን ልብስ እንኳን ከሚያውቃቸው የእሷ ልብሶች መካከል አይደሉም‹‹እዛ ከሄደች በኃላ የገዛችው መሆን አለበት›› ሲል አሰበ፡፡ከ20 ደቂቃ ጥበቃ በኃላ የውጭ በራፍ መጥሪያ ተንጣራራ፡፡ ሰራተኛዋ ለመክፈት ከሳሎን ስትወጣ ተንደርድሮ ቀደማትና ሄዶ ከፈተው፡፡ምስራቅ ነች፡፡፡በራፍን በደንብ ከፈተው፡፡ መኪናዋን ወደጊቢው አስገባች፡፡እንዳቆመችና ከመኪናው እንደወረደች ክንዷን ይዞ እየጎተተ ወደ መኝታ ቤቱ ይዞት ገባ፡፡ ሰራተኛዋ ሁኔታውን በገረሜታ እያየች በድንጋጤ እጇን በአፏ ከድና ወደስራዋ ተመለሰች፡፡
መኝታ ቤት እንደገቡ ቀጥታ ላፕቶፑ ወዳለበት ቦታ ነበር ይዞት ነው የሄደው፡፡ላፕቶፑን ከፈተና ኢሜሉን እንድታነበው ዞር አለላት፡፡አንብባ እና ፎቶውንና አይታ እስክትጨርስ መኝታ ቤቱ ውስጥ እየተንጎራደደ በጭንቀት ተወጣጥሮ ይጠብቅ ጀመር፡፡
‹‹የሚገርም ነው፡፡››
‹‹አዎ ከመግረምም በላይ በጭንቀት ልፈነዳልሽ ነው፤አሁን ምንድነው የምናደርገው?፡፡››

‹‹ቆይ እስኪ መጀመሪያ የመልዕክቱን ትክክለኝነት እናረጋግጥ፡፡››

‹‹እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?፡፡››

እንደማሰብ አለችና ከለበሰችው ጅንስ ሱሬ ኪስ ውስጥ እጇን ሰዳ አንድ ፍላሽ አወጣችና ላፕቶፖ ላይ ሰካች ፡፡››
‹‹ምን እያደረግሽ ነው?››
‹‹አንድ ዋናው መስሪያ ቤት የምንጠቀምበት ሶፍት ዌር አለ ፡፡ በትክክል ኢሜሉ ከየት እንደተላከ የሚያሳውቀን ሶፍትዌር ነው…››
‹‹ያማ ከተቻለ ጥሩ ነዋ..ኢሜሉ ከየት እንደተላከ ካረጋገጥን እህቴም የት እንዳለች የምናረጋግጥ ይሆናል››በደስታ ዘለለ፡፡
‹‹በጣም እድለኞች ከሆን አዎ…ግን አማተሮች ከሆኑ ነው እንደዛ የሚያደርጉት፡፡››

ሶፍት ዌሩን ጫነችና ኤሜሉን ከፈተች …አስሶ ውጤቱን እስኪያሳውቃት ለደቂቀዎች በዝምታ ስታሰላስል ቆየች፡፡
‹‹እ ምን አገኘሽ?››
‹‹ሁለት ነገር ነው ያገኘሁት..››
‹‹ምንና ምን?››
‹‹ኢሜሉ የተላከው ከዛው ኑሀሚ ካለችበት ደቡብ አሜሪካ ነው››
‹‹አሪፍ ነዋ…መልዕክቱ የእውነት ነው፡፡››
‹‹አዎ መሰለኝ፡፡››
‹‹እሺ ሁለተኛውስ?››
ይሄ ሶፍትዌር አሁን እያሳየን ያለው ኢሜሉ የተላከበትን ቦታ ማለቴ ነጥቦችን ነው የሚያሳየው ፡፡ለምሳሌ ከአዲስ አበባ ከሆነ ቀበሌውን ሳይቀር ያሳያል…ናይሮቢ ከሆነ እንዳዛው..››
‹‹እና አሁን ደቡብ አሜሪካ የትኛው ሀገር የትኛው ከተማ ነው ምልክቱ የሚያሳየው፡፡››

‹‹ችግሩ ያ ነው..ሰዎቹ ፕሮፌሽናል ሳይሆኑ አይቀርም፡፡ነጥብ በአህጉሪቱ ባሉ ሶስት ሀገሮች ውስጥ ባለ የተለያዩ ሀያ ቦታዎች ላይ ነው የሚያመለክተው፡፡ብራዚል ፤ቤሩ፤ ኮሎምቢያ፡፡
‹‹የሚገርም ነው፡፡ቆይ ከእህቴ ምንድነው የሚፈልጉት…የኢትዬጵያ መንግስትን አምርረው የሚቃወም አሸባሪ ቡድን እዛ አካባቢ ይንቀሳቀሳል እንዴ?ምን አልባት በእናንተ ስራ እህቴን የመስዋእት ጭዳ አድርጋችኋት ይሆን ?››ሲል ሰሞኑን በአእምሮ ሲጉላላበት የነበረውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
‹‹እስከአሁን ከእኛ መስሪያ ቤትም ሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዛም አልፎ በአካባቢው ሀገሮች ካሉን የእኛ ኢንባሲዎች ባጣራሁት መሰረት ከእኛ ስራ ጋር ሆነ ከሀገራችን ጋር ምንም የሚያገኛኘው ነገር የለም፡፡ .እንደውም አንድ ያለው ጥርጣሬ የአማዛን ደን ጥሬ ዕቃ የጎማ ተክል እየመነጠሩ ለፋብሪካቸው ጥሬ እቃ በማጋበስ ዶላር የሚዝቁ ኩባንያዎች ስብሰባውን ያዘጋጀው የአለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ እንቅስቃሴን ሴሚናሩ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ሲቀነቀን የነበረው እንዴት አድርገን በደኑ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱትን አውዳሚ ካማፓኒዎችን አደብ እሲዘን ከአካባቢው እስከወዲያኛው እንዴት እናስወግዳቸዋለን የሚል እንደሆነ ሰምቼለው፡፡እንደዛ አይነት ቅስቀሳና እንቅስቃሴ ደግሞ በዶላር ጡንቻቸው የፈረጠመውን እነዛን ከደኑ ተጠቃሚ የሆኑ ካማፓኒዎቹን ሳያስቆጣ አልቀረም፡፡እንደኔ ጥርጣሬ ምንአልባት ከካማፓኒዎች አንዱ እንቅስቃሴውን ለማኮላሸት በቅጥር ነፍሰ ገዳዬች ወይም አጋቾች ቀጥሮ ያስደረጉት ሊሆን እንደሚችል ነው፡፡››
‹‹ያልሽው ሊሆን ይችላል…ለጊዜው ግን እሷን ለመፈለግ እስካልረዳን ድረስ የተጠለፈችበት ምክንያት ምንም አይረባንም፡፡ለማንኛውም አሁን ሳስበው በኮምፒተሩ ላይ ኤሚሉ የተላኩባቸው ያልሻቸው ሀያ ቦታዎች እኮ ብዙ አይደሉም፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተባበረን በአካባቢው ያሉ ኤምባሲዎቻችን የየሀገሩን መንግስት ትብብር ካገኙ ሀያ ቦታዎችን ፈልጎ ማረጋገጥ በሁለት በሶስት ቀን የሚሰራ ቀላል ተግባር ነው፡፡››
‹‹አዎ ባልከው እስማማለሁ፡፡እነዚህ ሀያ ቦታዎች ልክ እንደ አዲስአበባ፤ሀዋሳ ፤መቀሌ፤ድሬደዋ…ምናም አይነት ከተሞች ቢሆኑ ቀላል ነበር፡፡ግን እነዚህ ሀያ ቦታዎች በሶስት የተለያዩ መንግስታት በሚተዳደሩ ሶስት የተለያዩ ሀገራት ውስጥ በሚገኙ በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ሰው ይኑርበት አይኑርበት በማይታወቁ ቦታዎች የተበተኑ ምልክቶች ናቸው፡፡እንዴት አድርገህ ነው ምስራቅ አፍሪካን ከሚያህል የደን ውስጥ አንድ ሰው ፍልጎ ማግኘት የሚቻለው››
ተስፋ ቆርጦ በቆመበት ግድግዳውን ተደገፈና ቀስ እያለ የተንሸራተተ …ወደወለሉ ወረደና በቂጡ ዝርፍጥ ብሎ ተቀመጠ፡፡


ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍9611👏4😢3🤔2🥰1
ናኦል በእህቱ መልስ ግራ ተጋባ፡፡እሷ ከመቀመጫዋ ተነሳችና ወደመስኮት ሄደች፡፡ቀስ ብላ የመጋረጃውን አካፋይ ላይ ከፈት አደረገችና አይኖቾን አጨንቁራ ወደ ታች ተመለከተች…‹‹ና እስቲ››
ምን ልታሳየው እንደሆነ ባይገባውም ከተቀመጠበት ተነሳና ሄደ.. እሷ እንደምታደርገው አይኖቹን አጨንቁሮ ተመለከተ፡፡‹‹ ያቺን ጥቁር መኪና አየሀት…እኛን መከተል ከጀመረች ሳምንት ሆናት፤እንዳትፈራ ብዬ አልነገርኩህም እንጂ ወደከታማ ስንሄድ በሔድንበት ሁሉ እየሄዱ ሲከተሉን ነበር፡፡ወንድሜ የገባንበት ወጥመድ እንዲህ ቀላል አይደለም፡፡ይህቺ ያንተ ተመራጭ ምስራቅም እንደምታያት ቀላል ሴት አይደለችም፡፡እኛ ደግሞ ስለእሷ የሆኑ የሆኑ ነገሮችን ነቄ ብለናል..አሁን ባቀረበችልን ሀሳብ አንስማማን ብለን እንንካው ብንላት…ዝም ብለው በቃ ቸው ብለው ሚሸኙን ይመስልሀል..አታስበው››
ናኦል እርግጠኝነት በማይነበብበት ስሜት ‹‹አረ እህቴ ምስራቅ በእኛ ላይ እንዲህ ታደርጋለች››በማለት ሊሞግታት ፈለገ፡፡
‹‹አይ ይሄ እኮ የስራው ፀባይ ነው፡፡የስጋ ወንድም እህቶቾም ብንሆን ተመሳሳዩን ነው የምታደርገው፡፡በል ተነስና አሁን የነገርኩህን ነገሮች በሆድህ አስቀምጠህ ባቀረበችልን ሀሳብ መስማማታችንን እንንገራትና ለሊት ወደሚወስዱን ቦታ ለመሄድ ዝግጁ እንሁን፡፡››
ተስማሙና ወደሳሎን ሄደው መሳማማታቸው ነገሯት፡፡በደስታ ከተቀመጠችበት ተነሳታ አቀፈቻቸውና ሁለቱንማ ሳመቻቸው፡፡አንስማማም ቢሉ ስለሚሆነው ነገር እንደተጨነቀች ከሁኔታዋ ያሳታውቃል፡፡ እንደተባለውም ጥዋት ወስዳቸው ፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍61🥰176👏4🤔1
‹‹ቢያንስ ፊትህን ወደእዛ አዙር እንጂ››
==
በንጊት ጉዞዋ ያስደመሟት ሁለት ነገሮች ናቸው፡፡ አንደኛው የወፎቹ ዝማሬ ነው፡፡በየዛፎቹ ቅርንጫፎች መኖሪያቸውን የቀየሱት የተለያየ ዝርያ ያላቸው ወፎች… የተለያየ የዝማሬ ቅኝት ያለው ድምፅ ከዚህም ከዛም ሲለቁ ዋው ሙዚቃ ማለትስ ይሄ ነው እንድትል ነው ያሰኛት…በጣም የገረማት ደግሞ ብዛት ያላቸው ወፎች ብዛት ያለው የተለያየ አይነት ድምፅ
የሚያሰሙ ቢሆንም እሷ ጆሮ ሲደርስ ግን ፍፅም ስምም ፍፅም ህብር ፈጥሮ ነበር የሚሰማት፡፡ልክ የአንዷ ወፍ ድምፅ ጊታር..የሌላዋ የዋሽንት..የሌላዋ የክራር…የዛችኛዋ ደግሞ የፒያኖ .. እንደሆነ አይነት፡፡አዎ ሁሉም በተለያየ የሙዚቃ መሳሪያ አንድ አይነት መንፈሳዊ ህብረዝማሬ እንደሚዘምሩ አይነት ነው፡፡
ካርሎስ እንደነገራት ከሆነ አማዞን በእንስሳት ክምችቱ የአለም ግዙፉ መጋዘን ነው፡፡ከነዛ እንስሳት መካከል ደግሞ ወፎችም ይገኙበታል፡፡በአለማችን አስር ሺ ያህል የወፍ ዝርያዎች ሲኖሩ ከነዛ መካከል 3000 የሚሆኑት በዚሁ አሁን እሷ በምትገኝበት በአማዞን ደን ውስጥ የሚገኙ መሆናቸው አስደማሚ ነው፡፡እሷም እንደምታውቀው የገዛ ሀገሮ በእነዚህ የወፍ ዝርያዎች ክምችት ከአለም ቀላል ድርሻ የላትም…850 የሚሆኑ የወፍ ዝርያዎች በሀገረ ኢትዬጵያ እንደሚገኙ ማወቅ ልብን ያሞቃል
በዚ የለሊት ጉዞዋ በሁለተኛ ደረጃ የስደመማት ደግሞ ንጊቱ ቀርቦ ጭለማው ገፎ ፀሀዬ ስትወጣ ያለው እይታ ነው፡፡…. እሷ ከዛ በፊት በእኩለሊት ሰማይ ላይ አይኖቾን ሰቅላ ጨረቃን በማየት በውበቷ መፍዘዝና ከእሷ ጋር ማውራት ነበር ልምዷ፡፡በተለይ ከ15 ዓመታ በፊት እዛ በረንዳ ላይ ከወንድሟ ጋር በምትኖርበት ጊዜ ለሌት ላይ አንዳንዴ እንቅልፏ እንቢ ሲላት የለበሰችውን አሮጌ ብርድልብስና ከላይ የተደረበውን ጆንያ ስትገልጥ ቀጥታ የምታዬው ኮርኒስ ወይም ቆርቆሮ ሳይሆን ሰማዩን ነበር፡፡ሳማዩ ላይ ደግሞ ጨረቃዋ አንዳንዴ ሞልታ አንዳንዴ በግማሽ ትታይ ነበር፡፡እሷ ዙሪያ ደግሞ የተለያ ቅርፅና አቀማመጥ ያላቸው ለቁጥር የሚያታክቱ ኮከቦች፡፡ከኮከቦቹ መካከል ጎላ ጎላ ብለው አንድ ላይ ተጣብቀው የሚንቀሳቀሱ ስታይ እናትና አባቷ ይመስሎትና ከእይታዋ እስኪሰወሩ በስስትና በናፍቆት ታያቸው ነበር፡፡አዎ የእሷ ልምድ ያ ነው…የጨረቃንና የከዋክብቱን ብሩህናትና ውበት በጨለማ ማድነቅ፡፡
ፀሀይ ግን በአዲስ አበባ ስትወጣ ወጣች ነው…ስትገባ ደግሞ ገባች ነው፡፡ልብ ብላ አስተውላትም አታውቅም፡፡ፀሀይን ከሙቀቷና ከቃጠሎዋ ጋር እንጂ ከውበት ጋር በፍፅም የማየት እድሉ ገጥሟት አያውቅም፡፡ምን አልባት በወቅቱ የራበው ሆድ ውበትን ለማድነቅ ከባድ ሆኖባት ሊሆን ይችላል፡፡አሁን ግን ፊት ለፊት ካለው ተራራ እንደብርሀን አምድ ክብ ሰርታና ሚንቀለቀል እሳት መስላ እየተሸኮረመመች ብቅ ስትል ስታያት በረሽ ሄደሽ እቀፊያት የሚል ስሜት ነው የተፈታተናት፡፡ደግሞ ነፀብራቋ እዛ ደን ውስጥ እየተጠማዘዘ፤ እየተዘረጋና እየተሰበሰበ ልክ እንደአናኮናዳ በጉዞው አክሮባት የሚሰራው የአማዞን ወንዝ እና ሀይቅ መሰል የተለያዩ የውሀ አካላት ላይ አርፎ መልሶ ነፀብራቁን ሲረጭ ያለችበትን ቦታና ሁኔታ ነው ያስረሳት፡፡
ከካርሎስ እንደተረዳችው ከሆነ በአማዞን ደን ከ390 ቢሊዮን በላይ ዛፎች ይገኛሉ፡፡በአማዞን ደን ውስጥ እንደ ክረምት ፣ በጋ ፣ መኸር እና ፀደይ ያሉ  ወቅቶች የሉም ፡፡ አነዚህ ጥቅጥቅ ደኖች አመቱን ሙሉ በዝናባማ ወቅቶች የተሸፈኑ ናቸው፡፡ይሄንን እራሷም አረጋግጣለች፡፡ይሄው በዚህ ደን ውስጥ መጓዝ ከጀመረችበት ቀን ጀምሮ የቀኑን አብዛኛውን ሰዓት በጀርበው አህያ የማይችለው የሚባል አይነት ዝናብ ስለሚንዠቀዘቅ ብረት እንደሚያነሳ ስፖርተኛ ደረቷ እየሰፋ ሁሉ እየመሰላት ነው….አማዞን ከ90 እስከ 140 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን ካርቦን በውስጡ በመያዝ የአለምን የካርቦን ልቀት ይቆጣጠራል፡፡የአለማችን 20 በመቶ ኦክስጅን የሚመረተውም በዚሁ እሷ በምትገኝበት በአማዞን ደን መሆኑን እና በዚህም ምክንያት “የፕላኔታችን ሳንባ ”ብለው እንደሚጠሩት አስረድቷታል፡፡
አዲስ አበባ /ኢትዬጵያ
ምስራቅ ለናኦል ከአምስት ቀን በኃላ ደወለችለት፡፡
‹‹ሄሎ ምስራቅ፡፡››
‹‹ሄሎ ጎረምሳው..ዝግጅትህን አጠናቀቅክ?››
‹‹አዎ ለጉብኝት አልሄድ ምን ዝግጅት ያስፈልጋል ብለሽ ነው..?ይልቅ አንቺ እንዴት ነው አለቀለሽ?››
‹‹አዎ …አሁን ሁሉን ነገር መቶ ፐርሰንት ጨርሼ በእጄ እንዳስገባው ነው የደወልኩልህ፡፡››
‹‹እንደው ምን ላድርግሽ?››
‹‹አጠገብህ ብሆን ጉንጮቼን ትሰመኝ ነበር?››ጠየቀችው፡፡
‹‹‹በትክክል..ግን ለምን  ያለሽበት ድረስ መጥቼ  እራት ምናምን ጋብዤሽ አላመሰግንሽም…በዛውም ሰነዶችን ወስዳለው፡፡››

‹‹አይ አያስፈልግም..ይልቅ ነገ ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ቦሌ አየር ማረፊያ እንገናኝ… እሸኝሀለው…ሰነዶቹንም በዛን ጊዜ አስረክብሀለው፡፡››ብላ ያልጠበቀውን የምስራች አበሰረችው፡፡
‹‹ነገ …?እርግጠኛ ነሽ?››
‹‹አዎ… ምነው አይመችህም እንዴ?››
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..ነገሮች ሁሉ ካሰብኩበት ጊዜ ቀድመው ሲከሰቱ ስለተመለከትኩ ተደምሜ ነው፡፡››
‹‹በል ..ነገ ሁለት ሰዓት..ቸው››ብላ ስልኩን ዘጋች፡፡ናኦል ይህቺን ሴት ይወዳታል…መውደድ ብቻ ሳይሆን ከምሩ ያፈቅራታል፡፡በህይወቱ ከምስረቅ ውጭ ሌላ  ሴት አፍቅሮ አያውቅም፡፡.(እርግጥ ወሲባዊ ስሜቱን ለማርካት ሲል ከብዙ ሴቶች ጋር ወጥቷል)ግን ከእሷ ውጭ ያፈቀራት ሌላ ሴት የለችም…በእድሜ የእጥፍ ያህል ብትበልጠውም ድሮም ልጅ ሆኖም ሆነ አሁን ያፈቅራታል፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍6718👏6🔥3🥰3