#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ፔሩ/አማዞን ወንዝ ላይ
ደግላስ እና ኑሀሚ እታች ወርደው ካፌ ቁጭ ብለው ያዘዙት ቁርስ እስኪመጠ ያነሳቸውን ፎቶና ቪዲዬ ትናንት ከተማውን እየዞሩ ሲጎበኙ የተነሱትንም ጭምር በኢሜሉ ላከችለት፡፡ሁለት ሰዓት ሲሆን ቁርሳቸውን በልተው ጨርሰው ወደ ኤርፖርት ለመሄድ ዝግጁ ሆነው ነበር፡፡እርግጥ ኤርፖርቱ ካረፉበት ሆቴል 15 ደቂቃ ያህል ብቻ ነው የሚርቀው፡፡ቢሆንም ቀድመው ሄደው እዛው ለመጠበቅ ተስማሙና ለሆቴሉ አስተናጋጅ ታክሲ እንዲጠራላቸው ነገሩት፡፡በአምስት ደቂቃ ውስጥ የፈለጉት ታክሲ መጣና ጫናቸው፡፡ሁለቱም ከኋላ ወንበር ተጠጋግተው ተቀምጠው በፀጥታ ጉዞቸውን ጀመሩ፡፡ሹፌሩ ታክሲ ከሚነዳ ይልቅ ቱርቦ ወይም ግዙፍ ተሳቢ መኪና ቢነዳ ከአቋሙ ጋር ይሄድ ነበር…እጆቹና አንገቱ ጠቅላላ በንቅሳት የተዝጎረጎረ.. ግዙፍ ግን ባለ አስፈሪ ጡንቻ ባለቤት የሆነ ሰው ነው፡፡የከተማውን ግራና ቀኝ ፎቆች እና የንግድ ተቋሞችን እየተመለከቱ ለ15 ደቂቃ ከተጓዙ በኃላ ሹፌሩ ወደኃላ በመዞር…‹‹ካላስቸገርኳችሁ እዚህ ፊት ለፊታችን ካለው ቅያስ ጋር የምቀበለው እቃ ነበረኝ..ሁለት ደቂቃ ባዘገያችሁ ነው››ሲል በተሰባበረ እንግሊዘኛ ፍቃድ ጠየቃቸው፡፡
ቢያንስ ከ30 ደቂቃ በላይ ትርፍ ሰዓት ስላላቸው እና ከዛ ላይ አንድ 5 ደቂቃ ቢለግሱት የሚጎዳቸው መስሎ ስላልተሰማቸው አልተቃወሙትም፡፡
‹‹..ችግር የለም.. እንችላለን፡፡››ስትል ሁለቱንም ወክላ ፍቃዱን የሰጠችው ኑሀሚ ነች፡፡ እንዳለውም በመጀመሪያው ቅያስ ወደግራ ታጠፈና ጠባብ የድንጋይ ንጣፍ የሆነ መንገድ ውስጥ ገባ፡፡ጭር ያለ መንገድ ነው፡፡ሁለት መቶ ሜትር ያህል ከተጓዘ በኃላ ጥግ አሲይዞ መኪናውን አቋመና ፡፡‹‹መጣሁ ሁለት ደቂቃ›› በማለት ሞተሩን ሳያጠፋ ታክሲዋን ለቀቀና ወጥቶ አንድ የብረት በር ግቢ ገፋ አድርጎ ገባ ፡፡ሁለቱም አይናቸውን እሱ የገባበት ግቢ ላይ ተክለው ከአሁን አሁን ወጣ እያሉ ሲጠብቁ በቅፅበት ከግራና ከቀኝ ያለው በራፍ ተከፈተና ጭንብል ያጠለቁና ሽጉጥ የደቀኑ ሰዎች የመኪናውን በራፍ ከፍተው ገቡና ሁለቱን አንድ ላይ አጣብቀው ከመሀላቸው በመክተት በሽንጣቸው አቅጣጫ ሽጉጣቸውን ደቀኑባቸው፡፡ ኑሀሚም ሆነች ዳግላስ በድንጋጤ ትንፋሽ አጠራቸው፡፡ ልክ ቀድመው እንደገቡት ጭንብል ያጠለቀ ሌላ ሰው ከፊት ለፊት የሹፌሩን ቦታ ያዘና መኪናውን አንቀሳቀሳት፡፡ቀጥታ ወደፊት ለፊቱ ነው እየነዳ ያለው፡፡ከ10 ደቂቃ በኃላ ሙሉ በሙሉ ከከተማ ወጡና ረግረግ የሆነና ግራና ቀኙ በደን በተሸፈነ ከዛም አልፎ በጭቃ የላቆጠ ወጣ ገባ መንገድ ውስጥ ገቡ፡፡
‹‹ምንድነው የምትፈልጉት….?ገንዘብ ነው…?››ኑሀሚ ነች ጠያቂው፡፡
አንደኛው መናገር ጀመረ፡፡ኑሀሚ ግን ምንም እየገባት አይደለም፡፡ቋንቋው እስፓኒሽ ነው፡፡እሷ ደግሞ ከእንግሊዘኛ ውጭ ሌላ የውጭ ቋንቋ አታውቅም፡፡ እርግጥ ራሺኛ ትችላለች..ያ ግን እዚህ አካባቢ እርባን ያለው መስሎ አልተሰማትም፡፡አጠገቧ ወዳለው ዳግላስ ዞረችና አፍጥጣ አየችው‹‹አፍሽን ዝጊ ነው የሚሉት፡፡››ሲል ተረጓመላት፡፡
‹‹ቋንቋውን ትችላለህ እንዴ?››
‹‹የሚሉትን መስማት የቻልኩት ብችል ነዋ››ሲል መለሰላት፡፡
አስር ደቂቃ በኋላ ጫካና ቁጥቆጦ እያቆራረጡ ከተጓዙ በኃላ መኪናዋ ቆመች፡፡ግራና ቀኛቸው ተቀምጠው ሽጉጥ የደቀኑባቸው ሰዎች አንዳንዳቸውን ይዘው ከታክሲዋ ወረዱ፡፡ሹፌሩም የታክሲዋን ሞተር አጥፍቶ ወረደ ፡፡
መኪናዋን ሲሾፍር የነበረው..ከጃኬቱ ኪስ ውስጥ እነሱ የለበሱትን አይነት ጥቁር የፊት ጭንብል አወጣና ተራ በተራ አጠለቀባቸው፡፡፡ከዛ ሌላ ጥቁር ጨርቅ አወጣና በአይናቸው ዙሪያ በማሽከርከር አሰረና ሙሉ በሙሉ እንዳያዩ አደረጋቸው፡፡ከዛ እየጎተቱና እያመናጨቁ በእግር ይዘዋቸው መጓዝ ጀመሩ፡፡ኑሀሚ በጣም ተረበሸች፡፡በቀልቃላነቷም እራሷን በጣም ወቀሰች፡፡‹‹እንዴት ሰው በማያውቀው ሀገር የማያውቀውን ሰው ለመርዳት ይሄን ሁሉ ርቀት ይጓዛል ?ለዛውም ምን እንደሆነ እና ማን መሆኑን ለማያውቅ ሰው?ከእኔ እንደዚህ አይነት ስህተት ፈፅሞ አይጠበቅም፡፡››ስትል አሰበች፡፡
.እርግጥ ኑሀሚ በህይወቷ ከህፃንነቷ ጀምሮ ብዙ ይሄንን መሰል አደጋዎችና አሳልፋለች፡፡ሞትኩ በቃ አበቃልኝ ካለች በኋላ ባልተጠበቀ ቅፅበታዊ ገጠመኝ ከመከራውም ወጥታ ህይወቷንም ያተረፈችበት አጋጣሚ በርካታ ናቸው፡፡ግን ያን ሁሉ ፈተና ያን ሁሉ ተስፋ መቁረጥ አጋጥሟት የነበረው በገዛ ሀገሯ በገዛ ህዝቦቾ ውስጥ ነው፡፡በሀገር ውስጥ በገዛ ምድር ላይ እየተራመዱ ተስፋ መቁረጥ በሰው ሀገር ውስጥ የሰው ምድር ላይ እየተራመዱ ተስፋ ከመቁረጥ ፍፁም የተለየ ነው፡፡በገዛ ሀገር ሆኖ ተስፋ መቁረጥ ማለት ሁል ጊዜ የተደበቀች ተስፋ ትኖራለች፡፡ያቺ ተስፋ ከእናት የምትገኝ ወይ ከአባት የምትቸር ወይም ወንድም የሚለኩሳት..ወይ ደግሞ እህት የምታበራት የአይዞህ ባይነት ተስፋና አለውልህ የሚል ማፅናኛ ነች፡፡ያ ቃል ደግሞ የተገነዘ ተስፋን ከሞት የሚያስነሳ ይሆናል፡፡በሰው ሀገር ተስፋ ሲቆረጥ ግን እነዚህ ሁሉ የሉም፡፡
እየተደናበሩና እየተገፋፉ 15 ደቂቃ ከተጓዙ በኃላ ተረጋጉ፡፡ከአይናቸው ላይ የታሰረው ጥቁር ጨርቅም ሆነ ጭንብል ተነሳላቸው፡፡ከጀርባቸው ጥቅጥቅ ጫካ …ከፊት ለፊታቸው የተንጣለለ የአማዞን ወንዝ ነው የሚታየው፡፡እነሱ ከቆሙበት በሁለት ሜትር ርቀት መለስተኛ የሞተር ጀልባ መልህቋን ጥላ ቆማለች፡፡አንዱ እጇን ያዛትና እየጎተተ ወሰዳት እና አንደኛው ጀልባ ላይ ጫናት…ልክ እንደእሷ ሁሉ ዳግላስንም አምጥተው ከጎኔ ያስቀምጡታል ብላ ስትጠብቅ..በተቃራኒው ወሰዱና ሌለኛው ጀልባ ላይ ጫኑት፡፡
‹‹ለምንድነው የምትለያዩን..?ወዴት ነው የምትወስዱን ..?እኔ እኮ ምንም አላውቅም፡፡ከእሱ ጋር የተገናኘሁት ትናንትና ነው፡፡ምንም ማውቀው ነገር የለኝም…?››ኑሀሚ ለፈለፈች፡፡ቁብ ሰጥቶ እያዳመጣት ያለ ሰው የለም፡፡እሷ ራሱ ያንን ሁሉ ስትለፈለፍ የነበረው በአማርኛ ነበርና ያ ትዝ ሲላት የምሬት ፈገግታ ፈገግ አለች፡፡ሁለት ሽጉጥ የደቀኑ አጋቾች በአንድ ሜትር ከእሷ ፈንጠር ብለው ሁለት ሌላ መሳሪያ የታጠቁ ደግሞ ከጀርባዋ ተቀመጡ፡፡ጀልባዋ አስደንጋጭ የሞተር ጩሀት ድምፅ አሰማችና ወደባህሩ መሀከል ተፈተለከች፡፡…ወንድሟ ትዝ አላት…፡፡እህቴ ከዛሬ ነገ ትመጣለች እያለ ሲጠብቅ…..መኖር መሞቷን እንኳን ማረጋገጥ ሳይችል በስቃይ ሲኖር አሰበችና ስቅጥጥ አላት ..አይኖቾን አሻግራ ላከችና ዳግላስ የተጫነበትን ጀልባ ለማየት ሞከረች፡፡እነሱ እየተጓዙ ካሉበት አቅጣጫ በተቃራኒው ነው ይዘውት እየሄዱ ያሉት፡፡በቃ መቼም እንደማይገናኙ አሰበች…..እሷ እራሷ አሳዛኝ ሁኔታ ላይ ብትሆንም ለእሱ ከማዘን እራሷን ማቀብ አልቻለችም፡፡
ፔሩና/ኮሎምቢ ድንበር
በአለም ላይ በውሀ ከተከበብት ከተሞች መካከል ግዙፍ የሆነችውንና እስከ 200 ሺ ህዝብ በላይ ከሚኖርባትን የኢኩኢቶስ ከተማ ነጥቀው በአማዞን ወንዝ ላይ እያንሳፈፉ አርቀው ወሰዷትና አማዞን ደን ውስጥ ከተቷት።ከጀልባው ወርዳ መሬት ላይ ስታርፍ ይዛዋት የመጡት አራት ሰዎች በመጡበት ጀልባ ወደኃላ ሲመለሱ …መሬት ላይ ቆመው ሲጠብቋት የነበሩ ከነዛኞቹ በላይ አስፈሪ የሆኑ በቁጥር 9 አካባቢ ሰዎች ነበሩ የተቀበሏት፡፡‹‹በዚህ ሁሉ ትጥቅና አጀብ የሚቀበሉኝ ማነች ብለው ነገሯቸው ይሆን?›› ስትል በውስጧ አልጎመጎች፡፡አራቱ ከኃላዋ አራቱ ደግሞ ከፊት አንዱ ከመሀከላቸው በአቋሙ ቀጠን የሚል በአለባበሱ ስርአት ያለውና ..ለስላሳ ቢጤ የሆነ ሰው ወደእሷ ቀረበና

👍83❤3🤔3👎2🤩1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
ፔሩ/አማዞን ወንዝ
ዳግላስን ከኑሀሚ ነጥለው በአማዞን ወንዝ ላይ የተወሰነ ይዘውት ከተጓዙ በኋላ ሌላ እጅግ በጣም የተቀናጣ ግን ደግሞ መለስተኛ ዘመናዊ ጀልባ አጠገብ አቆሙና አሸጋገሩት፡፡ምንም እየገባው ነገር ባይኖርም ግን ደግሞ መከራከርና መጨቃጨቅ ባለመፈለጉ እንዳደረጉት እየሆነላቸው ነው፡፡ልክ ከትንሿ ጀልባ ወደቅንጡ ውሀና ዘመናዊው ጀልባ አሸጋግረውት ገና ወለሉ ላይ እንዳረፈ..አንድ ሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ፤ደማቅ ጥቁር ፀጉሯ መቀመጫዋ ላይ የደረሰ ፤መልኳ ጉርድርድ ያለ ግን ደግሞ ሳቢ የሚባል የደም ግባት ያላት ሴት ከውስጥ ወጣችና ተንደርድራ መጥታ ተጠመጠመችበት፡፡ግራ ገባው፡፡ብዥም አለበት፡፡ይህችን ሰውነቱ ላይ ተጠምጥማ በእንባ በመታጀብ እየሳመችው ያለችውን ልጅ የሆነ ቦታ የሆነ ጊዜ ያውቃታል..አዎ በአእምሮ ብልጭ ድርግም እያለችበት ነው ..ግን የት እና እንዴት እንደሚያውቃት ምንም ትዝ ያለው ነገር የለም፡፡
‹‹ቤብ..ሰላም ነህ…?ወይኔ በኢየሱስ……ምንም አልሆንክም…?›› መላ እሱነቱን እየተሸከረከረች አያች ግንባሩን ጉንጮቹን እጆቹን እያፈራረቀችና እያገለባበጠች ትሰመው ጀመር፡፡ በዙሪያቸው ያሉ ወጠምሻና አብረቅራቂ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች አንገታቸውን አቀርቅረው ዙሪያቸውን ከበው እየሆነ ያለውን በቆረጣ እየተመለከቱ ናቸው፡፡ልጅቷ እየጎተተች ወደውስጥ ይዛው ገባች ፡፡ደረጃውን እየወረዱ ወደውስጠኛው መኝታ ክፍል ይዛው ገባች፡፡ ሰፊውን ክፍል አልፋ አልጋ ወደ ተነጠፈበት መለሰተኛ ክፍል ይዛው ገባቸው፡፡ባለመሳሪያዎቹ ባሉበት በረንዳ እንደቀሩ ናቸው፡፡
ዳግላስ በገባበት የቅንጡ ጀልባዋ መኝታ ቤት ውስጥ የምታምር ድንብሽብሽ ያለች በግምት ሶስት ወይም አራት አመት የሚሆናት ጥቁር ሉጫ ፀጉሯ ግንባሯ ላይ ድፍት ብሎ ግማሽ ፊቷን የሸፈናት ልጅ ጭልጥ ያለ የሰላም እንቅልፍ ውስጥ ገብታለች፡፡ህፃኗን በትኩረት ሲያያት የሆነ ብዙ ቀለማቶች በአእምሮው ብልጭ ድርግም ብልጭ ድርግም እያሉ ይረብሹት ጀመረ፡፡በፀጥታ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠና ቀኝ እጁን ወደ ልጅቷ ልኮ በቀስታ ግንባሯ ላይ የተደፋውን ፀጉሯን ከግንባሯ ላይ እያነሳ ትራሱ ላይ አስተኛው..እናትዬዋ ስሩ በፀጥታ ቆማ የሚያደርገውን እየተመለከተች ነው፡፡አሁን ሙሉ በሙሉ የልጅቷ ገፅታ ይታያል፡፡ይህቺ ልጅ ልብ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ነፍሱ ውስጥም እንዳለች እርግጠኛ ነው፡፡ይሄንን የተረዳው ደመነፍሳዊ በሆነ ስሜቱ ነው፡፡በትክክለኛው ግን ምንም ትዝ እያለው ያለ ነገር የለም፡፡
አንገቱን ቀና አደረገና ጎኑ የቆመችውን አማላይ ሴት ተመለከታት‹‹የምታግዢኝ ነገር የለም?››ሲል ጠየቃት፡፡
የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ሙሉ ፍቃደኛ እንደሆነች በሚያረጋግጥ ንግግር ‹‹ምን ላድርግልህ የእኔ ፍቅር? የፈለከውን ጠይቀኝ››አለችው፡፡
‹‹አሞኛል ..በፊት የምወስዳው መድሀኒት ወይም ኪኒን ነገር ይኖራል?፡፡››
ደነገጠች….የእሷን መደንገጥ ተከትሎ እሱም ደነገጠምም ግራ ተጋባምም‹‹ዛሬ መድሀኒትህን አልወሰድክም እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እስከማስታውሰው ድረስ ለበርካታ ቀናት ምንም አይነት መድሀኒት የወሰድኩ አይመስለኝም፡፡››
‹‹ይሄ የፓብሎ ተግባር ነበር፡፡ግን እሱ ራሱ የት እንደገባ ምንም የሚታያውቅ ነገር የለም፡፡ቆይ መጣሁ›› ብላ ሔደችና ከሁለት ደቂቃ በኃላ ሁለት ኪኒኒ ከእሽግ ውሀ ጋር ይዛ መጣች፡፡ኪኒኖቹን ከእሽጉ ፈልቅቃ አቀበለችው….‹‹ውሀውን ከፈተችና በል ዋጥና ለአንድ ሰዓት ያህል ጋደም በል… ስትነሳ ሰላም ትሆናለህ….››
‹‹አልገባሽም ..አመመኝ ስልሽ እኮ ህመም አይደለም..ምንም የማስታውሰው ነገር የለም እያልኩሽ ነው..አንቺን ጭምር ማንንም አላስታውስም››የተረዳችው ስላልመሰለው ፍርጥ አድርጎ እውነቱን ነገራት፡፡
‹‹ገባኝ የእኔ ፍቅር ..ሁሉ ነገር ይስተካከላል… ብቻ ያልኩህን አድርግ… መድሀኒቱን ዋጥና ከልጅህ ጎን ተኛ፡፡››እንዳለችው መድሀኒቱን ተቀበላትና ዋጠ፡፡ጫማውን አወለቀና ቀስ ብሎ አልጋው ላይ ወጣና ከልጁ ጎን ተኛ፡፡ፊት ለፊት ካለው የልብስ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ አልጋ ልብስ አወጣችና አለበሰችው፡፡ ቀስ ብላ ክፍሉን ዘግታለት ወጣችና ከጠባቂዎቹ ራቅ ብላ የጀልባዋ በረንዳ ላይ ባላ ወንበር ተቀምጣ ከወንዙ ባሻገር ያለውን ጥቅጥቅ የአማዞን ደን በተመስጦ መመልከቷን ቀጠለች፡፡
ኑሀሚ ያለችበት ጎጆ የተወታተፈ በራፍ ሲከፈት ሰማችና የጨፈነ አይኗን ከፈተች፡፡ከአጋቾቾ መካከል አንዱ ነው፡፡፡አሁን እጆ ላይ ተጣብቆ ከወዲህ ወዲያ በተንቀሳቀሰች ቁጥር ቅጭልቅል እያለ የሚረብሻትን ሰንሰለት ተቆራኝቷት የነበረው ልጅ ነው፡፡በእጁ የሚበላ ነገር በሰሀን እና የሚጠጣ ውሀ በላስቲክ ኩባያ ይዞል፡፡ወደእሷ ተጠጋና በርከክ ብሎ ምግብን አስጠግቶ አስቀመጠላትና የስፓንሽ ቋንቋ ዘየ በተጫነው ግን ደግሞ ባልተደነቃቀፈ እንግሊዘኛ፡፡‹‹ተነሽ ይሄን ምግብ ብይ…ከጥቂት ጊዜ በኃላ በእግር ረጅም መንገድ መጓዛችንን ስለምንቀጥል ጥንካሬው ያስፈልግሻል፡፡››አላት፡፡
ጎኑ ላይ የያዘውን አብረቅራቂ ኮልት ሽጉጥ በጎሪጥ እየተመለከተች‹‹ወደየት ነው የምትወስዱኝ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እሱን ለአንቺ ለመናገር ፍቃዱ የለኝም፡፡››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹እባክህ…እህት የለህም..እኔ እኮ በጣም ከሩቅ አህጉር የመጣው ምስኪን ወጣት ነኝ…ምን ላደርግላችሁ ነው እንዲህ ከእኔ ጋር የምትሰቃዩት?››አሳዛኝ መስላ ለመቅረብ ሞከረች፡፡
‹‹እህት አለኝ ….ግን ላደርግልሽ የምችለው ነገር ቢኖር አንድ ምክር ላንቺ መስጠት ብቻ ነው፡፡››
‹‹ምንድነው? እባክ ንገረኝ፡፡››
‹‹ፈፅሞ የሞኝ ስራ እንዳትሰሪ…››
ያልጠበቀችው የምክር አይነት ስለነበር‹‹ምን ማለት ነው?››በማለት ጠየቀችው፡፡
‹‹ጥዋት በምንጓዝበት ጊዜ በየመሀከሉ ሁኔታሽን ስከታተለው ነበር… ለማምለጥ ወይም ለመፋለም የመፈለግ አዝማሚያ አይቼብሻለው፡፡ በእርግጠኝነት ትንሽ እንቅስቃሴ ወይም ሙከራ ካደረግሽ ከመሀከላችን አንድ ወዲያው ነው የሚደፋሽ… እመኚኝ ሌሎቹ እንደእኔ ልስልስ እና ደካማ ነገር አይደሉም፡፡ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠና ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ጭካኔም ያላቸውና ሰውን በመግደልና ድመት በመግደል መካለከል ምንም ልዩነት የማይታያቸው ገዳዬች ናቸው..እንደውም አጋነንከው ከላልሺኝ ለእነሱ ወሲብ ማድረግና ሰውን መግደል ተመሳሳይ አይነት እርካታ ነው የሚያጎናፅፋቸው፡፡››ሲል መስማት ከምትፈለገው ተቃራኒ የሆነ አስቀያሚ ዜና ነገራት፡፡
‹‹እና መጨረሻዬን ምንም ሳላውቅ ልክ እንደፋሲካ በግ ዝም ብዬ ልነዳ ?››
‹‹እኔ እንግዲህ እንደዛ የሚሻል ይመስለኛል፡፡በህይወት ነገ ተነገ ወዲያ ምን እንደሚከሰት አይታወቅም፡፡ነገ ይዛ የምትመጣውን እድል ለመጠበቅ ደግሞ ዛሬ በህይወት ቆይቶ ነገ ላይ መገኘት ያስፈልጋል፡፡በይ እንዳልኩሽ የቀረበልሽን ብይ… የእግር ኮቴ እየተሰማኝ ነው፡፡
‹‹ልሂድ››ብሎ ቁጢጥ ካለበት ምንጭቅ ብሎ ተነሳና በራፉን ከፍቶ እንደአመጣጡ ተመልሶ ሄደ፡፡

👍82❤7👎1👏1😱1