አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

ኬድሮን ካደረገቻቸው ሀገር አቋረጭ ጉዞዋች ውስጥ በጣም ድንቁና በህይወቷ መቼም የማተረሳው ወደታንዛኒያ ያደረገችው ጉዞ ነው ፡፡15 ዓመት ስትደፍን ሙሉ ወጣት ሴት ሆነች..የሰውነቷ ግዝፈትና የቁመቷ መመዝ ብቻ ሳይሆን የውበቷም መድመቅና መጉላት በሰፈሯም ብቻ ሳይሆን በከተማዋም በቀላሉ ሚለይና ልክ እንደሰንደቅ ምልክት ሆና መታየት ጀመረች…ከንስሯ ጋር ያለት መናበብና ቁርኝት በቃላትም የሚገለፅ አይነት አይደለም፡፡በተለይ የፈለገችውን ቦታ ወስዶ ስለሚያዝናናትና ስለሚሳያት በጣም ደስተኛ ብቻ ሳይሆን ስለአለም ያላት ግንዛቤና ስለተፈጥሮ ያላት ዕውቀት በጣም ጥልቅና በመገረም የተሞላ ሆነ ፡፡በትምሀርቷም በቀላሉ በሳምንት ሶስትና አራት ቀን ብቻ ክፍል ገባታ እየተማረች በትምህርት ቤቱ ታሪክ ታይታ የማታውቅ ኳከብና ተወዳጅ ተማሪ ሆነች፡አንደኛ ሴሚስተር ፈተና እንደተፈተነችና ትምህርት ቤት ለሳምንት እንደተዘጋ ረዘም ያለ ጉዞ ልትሄድ አሰበች፡ብዙ ቦታ በእምሮዋ መጥተው ነበር፤መጨረሻ ግን የአፍሪካ ጣሪያ በመባል ሚታወቀው ኪሊማንጀሮ ተራራን ሄዳ ለማየት ወሰነች፡፡ለእናቷ ለሶስት ቀን እንደማትኖር ተናገረችና በአነስተኛ ሻንጣ አንድ ሁለት ቀሚስና ፎጣ ነገር ያዘች… ዝግጁ ሆና ተነሳች..እናትዬው ወ.ሮ በሬዱ በመካከለኛ መጠን ባለው አገልግል የተጠቀጠቀ ጩኮ አስያዘቻት፡፡
‹‹እማ አሁን እኔና ንስሬ የምንራብ ይመስልሻል?››

‹ገራ ኮ እንደማይርባችሁ አውቀለሁ… .ግን ደግሞ ከእሱ ጋር ስጋ እየተናጠቁ መመገብ ብቻ ጤነኛ አመጋገብ አይሆንልሽም..አንቺ የእኔ ልጅ ነሽ …ሰው ነሽ እና እህልም  በመጠኑም ቢሆን ሰውነትሽ ማግኘት አለበት፡››

‹እሺ እማ..ብላ የእናቷን ጉንጭ ስማ ንሰሯን አቅፋ ሻንጣዋን በአንድ ትከሻዋ አገልግሏን ደግሞ በሌላዋ ትከሻዋ በማንጠልጠል ንስሯን ከደረቷ አስጠግታ በጡቶቾ መካከል ለጥፋ ከሰፈር ወጥታ ሄደች…  የያዘችው አቅጣጫ ወደምትሄድበትን የሚያመራ አይደለም….ስለዛ የምትጨነቅበት ምንም ምክንያት የለም…እሷ ሰፈሯን ለቃ ጭር ወደ አለ ጫካ ስፍራ ለመድረስ ነው እቅዷ.. ከዛ ንስሯን በአየር ላይ ለቀቀችው …ተርገፍግፎ ወደ ላይ በረረና አየሩን እየሰነጠቀ የተወሰነ ርቀት እየተገለባበጠ ለህዝቡ ትሪኢት እንደሚያሳይ የአንድ ሀገር አየር ኃይል ጀቶች የመከረባት ትርኢት አሳየና ወደእሷ እየተምዘገዘገ መጣ‹‹…ሰውነትህን እያሞሞቅክ መሆኑ ነው ›ስትል ፈገግ አለች…እሷ ግን ለእሷ ፈገግታ ምላሽ ሳይሰጥ በተለመደው ሁኔታ ማጅራቷ አካባቢ የለበሰችውን ልብስ ያዘና ከተሸከመችው ሻንጣና አገልግል ጋር አንድ ላይ በአየር ላይ አንጠለጠላትና ሽምጥ ወደላይ ተመነጠቀ…ከዛ በተለመደው ዘዴ ወደ ላይ ወርውሮ እየተምዘገዘገች ወደታች ስትወርድ ከኃላዋ ዞረና ጀርባዋ ላይ ተጣበቀባት…ከዛ ክንፍ ሆናት ማለት ነው፡፡ ከዛ በኃላ አቅጣጫውን ወደ ደቡብ  አስተካክላት እሷም  በተዝናኖት መብረር ጀመረች ፤መዳወላቡን ፤ነጌሌ ቦረናን፤ ሞያሌን በሩቁና በጭልጭልታ እያየች የኢትየጵያን ድንበር አቆርጠው ኬንያ ገቡ..የተወሰነ እንደተጎዙ በጣም ቀልብ ሚስብ ቦታ እይታዋ ውስጥ ገባ፡፡
ጀግናዬ እዛ ቦታ አረፍ ብንል ምን ይመስልሀል? ስትለው ከፍታውን እየቀነሰ ወደጎን እየተጎዘ ሄደና 20 የሚሆኑ ዝሆኖች ጀርባ ላይ ቁጭ አደረጋት ከጀርባዋ ተገንጥሎ ተለየና በራሱ መብረር ጀመረ .ደነገጠች.እሱ ከጭንቅላቷ በላይ በአምስት ሜትር እርቀት እየዞራት ነው፡፡ዝሆኑ እላዩ ላይ ዝንብ ያረፈበትም ሳይመስል ተረጋግቶ ከመሰሎቹ ጋር ወደፊት ጎምለል ጎምለል እያለ ይጓዛል…እሷ መረጋጋት አልቻለችም.. ዘላ እንዳትወርድ  ከግራም ሆነ ከቀኝ መአት ዝሆኖች ናቸው ያሉት መሬት አርፋ ተስተካክላ ከመቆሞ በፊት በግዙፈ እግሮቻቸው ሚጨፈልቋት መስሎ ተሰማት...እራሷን በጣም ግዙፍና የሰማይ ስባሪ አድርጋ ትቆጥር ነበር.አሁን ከከበቧት ዝሆኖች ጋር እራሷን ስታነፃፅር ግን በዳዴ ሚሄድ ህጸን ልጅ የሆነች መስሎ ተሰማት፡፡

‹‹ጀግናዬ ና አንሳኝ ብዬሀለው. ና››
ንሰሯ ላይ ጮኸችበት …እየተመዘገዘገ ወደእሷ መጠና ትከሻዋን በክንፎቹ ቸብ አድርጎት መልሶ ወደላይ ተነሳ
‹‹አንተ ጫወታ ነው እንዴ የያዝከው ?ስወድህ….?የእኔ ጀግና በእኔ ትጨክናለህ….አላሳዝንህም››ተለማመጠችው፡፡

መልሶ ተከርብቶ መጣና ማጅራቷን ይዞ ወደ ላይ ተነሳና ከዝሆኖቹ መንጋ 20 ሜትር ያህል ራቅ አድርጎ ለምለም ሳር መካከል ቁጭ አደረጋት፡፡ግራና ቀኝ ትከሻዋ ላይ ያለውን ሻንጣዋንና አገልግሏን ከላዮ ላይ አውልቃ ጥላ በጀርባዋ ተዘረረች…ወደ ውስጧና ወደውጭ ደጋግማ አየር እየሰባች ወደውጭ በመልቀቅ ውስጧ በንፅህ አየር ብቻ ሳይሆን መረጋጋትም እንዲነግስባት መሞከር ጀመረች…ንስሯ ከጎኗ መጥቶ ተረጋግጦ ተቀመጠ
ለመረገጋጋት 10 ደቂቃ ያህል ከወሰደች በኃላ 
አሁን ያረፉት መርሳቤት ብሄራዊ ፓርክ ነው፡፡ፓርኩ  ከናይሮቢ 540ሜትር  በስተሰሜን  አርቆ ሚገኝ አጠቃላይ ስፋቱ 600 ሜ.እስኬር ስፋት ያለው በመርሳቤት ተራራ ማሀከል አድርጎ በሰሜን ኬንያ  የሚገኘው ድንቅ ቦታ ኬድሮንና ንስሯ ከዚህ በፊትም አዘውትረው የሚጎበኙት  በጣም ተመራጭ ስፍራቸው ነበር.ይህ ከእኛው ሞያሌ በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኘው ፓርክ በልዩ ተፈጥሮ የበለፀገ ስፍራ ነው፤፤ቦታው በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነ፤ 3 ሀይቆች ያሉት በተለይ  ወፎችን በተመለከተ መነኸሪያቸው ነው ማለት ይቻላል.. ብዛታቸው የማይቆጠር ቀለምና አይነታቸው አስደማሚ ብቻ ሳይሆን ልብንም ስልብ የሚያደርግ ነው፤ከወፎች ቀጥሎ ዝሆኖች በብዛትና  በምቾት የሚንጎማለሉበት ስፍራ ነው፡: 
ልክ ስምንት ሰዓት ሲሆን አካባቢውን ለቀው ወደ ደቡብ ኬንያ ጉዞቸውን ቀጠሉ…የሚገኙበት በሌላ ጎን በአፍሪካም ሆነ በሀገረ ታንዛኒያ ሁለተኛው ረጅሙ ተራራ ከባህር ጠል በላይ 4566 ኪ.ሜት የሚረዝመው ሜሩ ብለው ሚጠሩት ተራራ የሚገኝበት የሚንዠቀዠቁ ያዶትን እና ዋቤ ሸበሌን መሰል ወንዞች የሚገኙበት የተፈጥሮ ገፀበረከት ቢፌ የሆነ ቦታ ነው ግን በመጠን ብዙም ሰፊ ያለሆነ አርሻ የሚባል ብሄራዊ ፓርክ ነው ከዛ ድንገት ኪሊ ማጀሮ ተራራ ትዝ አላት
አካባቢውን እስኪበቃቸው ከጎበኙና በኃላ ንስሯ እስከፈለገው ጥግ ያለማቆርጥ የመጓዝ ችግር ባይኖርባትም እሷ ከድካሟ የተነሳ ሰውነቷ ስለዛለ ከዛ በላይ መጓዝ አልፈለግችም..በአካባቢው ቅርብ ወደአለ ከተማ ሔደው  ማደር ቢችሉም ግን ደግሞ በተለየ ለንስሯ ደህንነት አሳሳቢ ከመሆኑም በተጨማሪ ለእሷ ለራሷም  ወደሰው ሀገር ለመግባት የሚያስችል ምንም አይነት ቢዛም ሆነ ፍቃድ ስሌላት እንደዛ ማድረግ አልመረጠች፣  
‹‹ጀግናዬ እዚሁ ነው የምናድረው… ዞር ዞር ብለህ እራትህ ፈልግና  ና.. እኔ የእናቴን ጩኮ  በዚህች ምንጭ ውሀ እያወራረድኩ እበላለሁ›› አለችው…ትዕዛዟን አክብሮ በረረ …እሷም በያዘችው ኮዳ እየተንኳለለ ከሚወርደው የምንጭ ውሀ ቀዳችና በአካባቢው ከሚገኝ ግዙፍ ዛፍ ስር ተጠግታ አረፍ በማለት አገልግሏን ከፈተች…ውስጡ በባለው ማንኪያ እየቆረሰች በቂቤ ተነክሮ የተሰረራውን የእናቷን ተወዳጅ ምግብ በደስታ እያጣጠመች በልታ..ሳትጨርስ ንስሯ የራሱን ግዳይ  በመንቁሩ አንገቱን አንቆ ይዞ መጣና  ሰሯ  አረፈ …ከዛ መሞቱን ካረጋገጠ እየዘነጣጠለ እስፈሪ በሆነ መንገድ መብላት ጀመረ

‹‹አረ ቀስ በል…..የት ትሄዳለህ?››አለችው፡፡
 
ይቀጥላል
👍1496🥰3🔥2😁2
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

..ሁለቱም የሚያጠግባቸውን እህልም በልተው ካጠናቃቁ በኃላ እሷ የተረፋትን ከድና ለነገዋ ስታስቀምጥ አሱ ደግሞ በመንቁሩ ነከሰና አሽቀንጥሮ ወደጫካው ወረወረው…በአካባቢው የነበሩ ሌሎች አውሬዎች ሲሻሙበት ተመለከተች፡፡

‹‹እንግዲህ እንደዛ አትየኝ እኔ ብወረውርላቸውም ጩኮ የሚበላ አውሬ የለም››
‹‹እውነቴን ነው ደግሞ ቢኖርስ እናቴ ወዟን ጠብ ያደረገችበትን ጣፋጭ ምግብ ለሌላ በሊታ የምሰጥ ይመስልሀል…?አሁን በል እዚህ ዛፍ ላይ ልውጣ ወይስ አንተ ታወጠኛለህ፡፡?››

ከተቀመጠበት አለት ድንጋይ ተነሳና በአየር ላይ ሆኖ ክንፉን በማርገፍገፍ የሻንጣዋን ማንጠልጠያ በመንቁሩ ይዞ በአየር ላይ ተንሳፈፈና ወደላይ ወደዛፉ ጫፍ በመሄድ ተደላድሎ ተቀመጠ፡፡

ሳትወድ በግዷ አሳቃት‹በቃ እንዲህ ተንኮለኛ ሆነህ ቀረህ…ይብላኝ ላንተ እኔስ ይህቺን መውጣት አያቅተኝም›› አለችውና አገልግሉን በአንገቷ  አጥልቃ የጫማዋን የተፈታ ማሰሪያ በማጠባበቅ እንደለመደችው እየቧጠጠች ዛፍን መውጣት ጀመረች.. እሱ ያለበት ለመድረስ 5 ደቂቃ ፈጀባት..፡፡
‹‹ይሄው በጣም ደክሞኛል ደስ አለህ?›አለችውና ከጎኑ ተመቻችታ ተቀመጠች፡፡ ካለበት ተነስቶ ተፋዋ ላይ ዘፍ ብሎ ተደላድሎ ተቀመጠ፡፡ ሻንጣውን ተንጠራርታ ወደራሷ ሳበችና ውስጡ ያለውን አልጋ ልብስ አውጥታ እራሷንም እሱንም አለበሰችና ጋደም አለች፡፡
ለሊት 11 ሰዓት ነው ከእንቅልፍ የነቃችው፡፡.ያው ንስሯ  እሷ በምትነቃበት በማንኛዋም ሰዓት እሱም ይነቃል..እና ጊዜ ሳያባክኑ ነበር ጉዞ የጀመሩት… 5 ሰአት ሲሆን የአፍሪካ ጣሪያ ላይ ተፈናጣ በሁለት እግሮቾ መቆም ቻለች፡፡ኪሊማጀሮን ለመጎብኘት ያደረገችው አስደማሚ ጉዞ በውስጧ ኩራት ፈጠረባት፡ አካባቢውን ስትቃኘው እጅግ ግራ ሚያጋባና አስደማሚ ነው፡፡
፡፡ኪሊማንጀሮ ተራራ በአመት ከግማሽ ሚሊዬን በላይ ቱሪስቶች የሚጎበኙት ተአምራዊ ቦታ ነው።በአለም ላይ ተጠቃሽ ከሆኑት 5 ተራሮች መካከል አንዱ ሲሆን ለተራራ መውጣት እስፓርት ከሁሉም የተሻለ ተመራጩና ምቹ ነው።

በግራ በኩል ለብቻው እንደግድግዳ የተዛረጋ ውበቱ ልብን የሚያርድ ግግር በረዶ ይታያል። ከፊት ለፊቷ እንድ አነስተኛ የእግር ኳስ ሜዳ በሚመስል ስፍራ አመድና አፈር የሞላበት እንቅስቃሴው የተገታ  እሳተጎመራ  ይታያል፡፡፡  ይሄንን አይነት መልካ ምድርን ስትመለከት ሀገሯ ምድር ላይ የሚገኘውን  ኤርታሌ  ዘወትር የሚንቀለቀል እና ሲፍለቀለቅ የሚውል ከዚህኛው በጣም በተለየ ሚደንቅና  ውበት ብቻ ሳይሆን አስፈሪነት  የተጎናፀፈ ልዩ ነው. አሁን ከፊቷ ያለው በዛ ልክ ባይሆንም ግን የራሱ የሆነ ውበት አለው፡፡ ወደሌላ አለም መሽሎኪያ  ሚስጥራዊ በር ነው የሚመስለው ..
ወደፊቷ  የተወሰነ ተራመደችና ቁልቁል ጭው ወደለው የተራራው መነሻ መስረት ለማየት ሞከረች ፤ ከእይታዋ አቅም  በላይ ሆነባት፡፡ ከእሷ  5 ሜትር ያህል ራቅ ብሎ የሾለ ድንጋይ ላይ ጉብ  ብሎ የተቀመጠውን ንስሯን ተመለከተች ።
‹‹እባክህ እርዳኝ›› ስትል ጠየቀችው ።ፍቃደኛ ሆኖ አዕምሮውን ከፈተላት… የንስሯ  እይታ ያው እንደሚታወቀው 5 ኪ.ሜትርም የራቀ ስለሆነ ሰፊ ስፍራን ያካለለ እይታ አገኘች  ..ድንገት የሰው ድምፅ ሰማች..ትኩረቷን ሰበሰበችና ለማዳመጥ ሞከረች … እንደውም ባህላዊ የጋራ ዘፈን ነው እየስማች ያለችው… በርከት ያሉ ስዎች በህብረት የሚዘምሩት ዝማሬ ድምፅ
… ወደእሷ እየቀረበ እንደሆነ አውቃለች ..እንደውም ሰው አየች …ከሆነ ሽለቆ ከመሰለ ከለላ ውስጥ ቀስ በቀስ በየተራ እየወጡ በቀጭኑ  ጠመዝማዛ መንገድ እሷ ወዳለችበት እየመጡ እንደሆነ ገባት ለመቀመጫ የሚሆን ጠፍጣፋ ድንጋይ ፈለገችና ተቀምጣ ትጠብቃቸው ጀመር  ፡፡በአስር ደቂቃ ውስጥ ስሯ  ደረሱ.. ስምንት የሚሆኑ የጓዝ ሻንጣና ሌሎች እቃዎችን የተሽከሙ የሀገሬው ስዎችና  5 የሚሆኑ ፈረንጆች ናቸው። የሀገሬው ስዎች ወገብ የሚያጎብጥ ሽክም የተሽከሙ ቢሆንም አሁንም ተጨማሪ መንገድ የመጓዝ አቅሙ እንዳላቸው በሁኔታቸው መገንዘብ ይቻላል።ፈረንጆቹ ግን ያንጠለጠሏቸው እቃዎች አነስተኛና ቀላሎች አንዳንዶችም ባዶቸውን ቢሆንም ስሯ ሲደርሱ ትንፍሽ እጥሯቸውና ድካም አዝሎቸው በየቦታው ተዘረሩ...የሀገሬውን ስዎች ጨምሮ ፈረንጆቹም  በዛ የኪሊማንጀሮ ከፍታ ላይ አንድ ሴት ከአንድ ንስር አጠገብ ያለፍርሀት እና ድካም ቁጭ ብላ ሲያዮት መገረም ውስጥ ገብ….አብዛኞቹ በአካባቢው ሌላ ሰው ካለ  በማለት ለማየት ዙሪያ ገባውን ቢያማትሩም ምንም የስው ዘር  ማየት አልቻሉም፡፡ ከፈረንጆቹ መካከል አንድ በግምት  35..40 የሚሆነው መልከ-መልካምና ፈርጣማ ሰው ትንፋሽ ለመሰብሰብ እየጣረ … ከተዘረረበት እንደምንም ተነስቶ ወደእሷ ቀረበና… የአሜሪካ አክስንት በተጫነው እንግሊዘኛ ‹‹አንድሪው እባላለሁ"አላት፡፡
 
"ኬድሮም እባላለሁ..."በአጭሩ መለሰችለት...ሲጠጋት የሆነ ነገር እየተሰማት ነው ፡፡ልትገልፀው የማትችል ከዚህ ቀደም ተሳምቷት የማያውቅ አይነት ስሜት …ምክንያቱንም  ማወቅ አልቻለችም፡፡

"ጓደኞችሽ...የት ሄድ?"

"ያው ጓደኛዬ"መለሰችለት ...እራቅ ብሎ ወደሚታየው ንስሯ  በእጇም  በአይኗም እየጠቆመችው

"ሌሎች ከእሱ ጋር የመጡ መንገደኞች ፈንጠር ፈንጠር ብለው እረፍት ለመውስድ ከተቀምጡበት ሳይንቀሳቀሱ በከፊል እየተከታተሏቸው ነው፡፡

..በምንም አይነት ሁኔታ ብቻዋን ሆና እዚህ ቦታ ድረስ ይሄን ሁሉ እጅግ ፈታኝና ተአምረኛ የሆነ ተራራ መውጣት እንደማትችል እርግጠኛ ሆኖ"እየቀለድሽ ነው አይደል?"አላት

‹‹በፍፅም እውነቴን ነው"አለችው ፍርጥም ብላ፡፡

‹‹መች ነው እዚህ የደረሺው?"
"ከ20 ደቂቃ በፊት"

እንደ አዲስ ከስር እስከላይ አያት ... እይታው ውስጧን እረበሻት

"ምነው ችግር አለው? "አለችው።
"በዚህ ቅፅበት ከድካምሽ እንዴት አገገምሽ...?እኛ ወንዶቹ እንዴት እንደተዝለፈለፍን አታይም።"

"እሱ ሚስጥር ነው"
በዚህ ቅፅበት መንገድ መሪና ጓዝ ተሸካሚ የሆኑት የሀገሬው ስዎች ጉዞቸውን መቀጠል እንደለባቸው አሳስበው ያሳረፍትን ጓዝ እርስ በርስ አንድ አንድን እያሽከመ ከጨረሱ በኃላ ሽቅብ ወደ መጨረሻው  መዳረሻ ጉዞ ጀመሩ …ፈረንጆቹም እነሱን ለመከተል እራሳቸውን አበርታተው ከወዳደቁበት በመነሳት መራመድ ጀመሩ፡፡አንድሪውም  ከኬድሮም መነጠል የፋለገ አይመስልም"ታዲያ አሁን ጓደኛ እንሁንና አብረን እንሂዳ"የሚል ግብዣ አቀረበላት…

አልተግደረደረችም...‹‹ ደስ ይለኛል›› ብላ በቅልጥፍና ከተቀመጠችበት ተነሳችና አገልግሉን ከመሬት በማንሳት በትከሻዋ በማንጠልጠል ለመራመድ ፊቷን ስታዞር እሱ ሻንጣዋን ሊይዝላት ከመሬት ለማንሳት ጎንበስ ሲል...‹‹ተወዉ ይቀመጥ››አለችው፡፡
‹‹ለምን ?ያንቺ አይደለም?››
ወደ ንስሩ በማመልከት"የእኔ ብቻ አይደለም የእኔ እና የእሱ ነው፡፡ ስለዚህ እሱ ይዞ ይመጣል።"አለችው፡፡

  ፍጥጥ ብሎ አያት...በቋንቋም ያልተግባቡ መሰለው፡፡እጁን ያዘችና የነገረችውን አምኖ እንዲከተላት ጎተተችው፡፡ ወደኃላው በመገላመጥ አንዴ ሻንጣውን አንዴ ከተቀመጠበት ንቅንቅ ያላለውን ንስሯን እየተመለከተ ተከተላት….ጎን ለጎን ሆነው እየተደጋገፉ  ጉዞቸውን ቀጠሉ፡የኪሊማንጀሮ የመጨረሻው ጫፍ እንደደረሱ ቀድመዋቸው የደረሱ ከሶስት በላይ የሆኑ ቡድኖች  ድንኳናቸውን ተክለው አገኞቸው ፡እሷም ያለችበት ቡድን  የተሻለ ክፍተት ያለበት ቦታ ፈለጉና ሸክማቸውን አራግፈው አረፍ አረፍ አሉ፡፡አብረዋቸው
👍1005😁1