#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
“ነገ ማታ እደውልልሃለሁ በመጭው ሦስት ቀናት
አልኖርም:: ጓደኛዬን ለመጠየቅና እግረ መንገዴን ለመሰናበት ባርሴሉና እሄዳለሁ... መልካም ጊዜ ለማሳለፍ ሞክር አሁን
መተኛት እፈልጋለሁ ኦርቫ" ብላው ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች:
በተቀመጠበት ህሊናው የስሜት ግጭት ተንቆራቆሰበት...
የሐሳብ ልዩነት.. ውሃና እሳት ትኩሳትና ብርድ... የስሜት
ጩሕት... የማይታኘክ ጉርሻ..
ከጥቁርና ነጭ ቀለም የተውጣጣው የቀይ ዳማ ቀለሟ ዞማ ፀጉሯ ከለግላጋ ቁመናዋ ጋር ፈጣን አስተሳሰቧ ሁሌም ጎልታ
እንድትታይ ያደርጋታል።
መርከበኛው አባቷ ፍራንሲስኮ ፔሶ ቤኒ በስራው ምክንያት
ከናቷ ከሎካዬ ጋር ለብዙ ወራት ተለያይቶ ሲቆይ ከህፃንነቷ ጀምሮ ናፍቆት ቢንጣትም እንኳን የተሟላው ኑሯቸው
ጨዋታ ወዳዱ አባቷ በየመዝናኛው ከናቷ ጋር ይዟት ስለሚዞር አብሯት
ስለሚቦርቅ ደስተኛ ሆና ለማደግ አስችሏታል።
በተማሪነቷ የስካውት አባል የነበረችውና በስካውትነቷ ብዙ ጉዞዎችን ከእድሜ እኮዮችዋ ጋር ያደረገችው ቅርፀ ማራኪዋ ኮንችት
ጊታር መጫወትን በጋራ ማዜምንና ከእስፔናውያን ባህላዊ ዳንስ በተጨማሪ የምዕራባውያንን ውዝዋዜ በስልት አጣጥማ የማቅረብ
ተሰጥኦዋ ተደጋጋሚ አድናቆትን ስላተረፉላት ከዘጠኝ ዓመት እድሜዋ ጀምሮ ጊዜዋ “የፋሽን ሾው" ስራ እየሰራች የራሷ ገቢ
እስከማግኘት አስችሏት ነበር።
አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከፈፀመች በኋላ በባልትና ሳይንስ ትምህርት ሰልጥና ከሙያዋ ይልቅ በሞዴሊስትነት
ሥራ በመሰማራት በጂምናዚዬም አካላዊ እንቅስቃሴ በማድረግ
ለሚስስ ካታሉንያነት ሁለት ጊዜ ተወዳድራ በሶስተኛው ሚስስ ካታሉንያ በመባል የቁንጅና ዘውዷን ደፍታለች።
ኮንችት በህፃንነት ያየችው አፍሪካዊ አያቷ ኤድዋርድ ሎካዬ ብቸኝነቱ ዝምታውና ደስታ አልባ ሆኖ ኖሮ ከሚናፍቃቸው ዘመዶቹ
ተገናኝቶ ያሰበው ሳይሳካለት ማለፉ እንደ እግር እሳት ሁሌም
ያቃጥላታል። አይቶት በማያውቀው እንደ ሰማይ በተዘረጋ ውቅያኖስ ላይ ጭነው ፖርቶሪኮ ውስጥ ኗሪ ለነበረው ለኤድዋርድ ጃኒፌር የተሸጠው አያቷ ከአንዱ አለም ወደ ሌላ ዓለም ከተወሰደ በኋላ
በቋንቋም በአስተሳሰብም ልዩ ሆኖ ፖርቶሪኮ ውስጥ በተነሳው የርስ በርስ ጦርነት እንደ አባቱ የሚቆጥረው ጌታው ኤድዋርድ ጃኒፈር
ወደ አሜሪካ ሜሪላንድ ሸሽቶ በመሄዱ እንግሊዘኛና እስፓኒሽ ቋንቋ
አፍንጫውን ተይዞ ተምሮ የዕለት ፍላጎቱን ለማርካት የታክሲ ሾፌር ሆነ።
ከዚያ ከኮንችት ሴት አያት ከራሚሬዝ ኦርኔዝ አኜስ ጋር
በአጋጣሚ ተገናኝተው የኮንችት አያት አኜስና ሉካያ እናቷን ከሪናን በመውለድ ስፔን ውስጥ አ ብረው መኖሩ ጀመሩ። ሎካዬ በተለያየ ጊዜ በአፍሪካ ጉብኝት አድርጎ ዘመዶቹን ፈልጎ ለማግኘት ቢሞክርም
ሊሳካለት አልቻለም ነበር:
በስተ እርጅናው ጣልያን ሮም ላይ የተደረገውን የማራቶን ውድድር ለመመልከት ሄዶ ግን ባጋጣሚ የአገሩ ፍንጭ ቢታወቅም ሽምግልናውና ጤና ማጣቱ ተዳምረው
ምኞቱን አሰናከለባት።
ኮንችት አያቷ ለመሞት ቀናት ሲቀሩት ጠርቷት ወደ
አታክልቱ ቦታ ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ወስዷት ትክ ብሎ እያያት።
“ለሰባት ዓመት ልጅ አደራ መተው ምንኛ ይከብዳል
መሰለሽ” አለና አፉን በመሀረብ ይዞ ሲስል ቆይቶ፡
“አሁ ካንች ሌላ ማንስ አደራዬን ሊቀበል ይችላል-" ሲል ኮንችት የሚለውን ነገር ስላልገባት ግራ ገብቷት ስትቁለጨለጭ፡-
“የዘመዶቼን አገር አላውቅም ነበር። ጠንካራነቴ አሁን
የነበረውን ፍንጭ የዛኔ ቢኖረኝ ኖሮ ምን ነበረበት ግን አልሆነም
የኔ ልጅ ይህች ትንሽ ባንዲራ በልጅነቴ አሁን ስሙን ከማላውቀው
የገጠር ከተማ ከአባቴ ጋር ሄጄ አይቻት ነበር። በህፃንነት ልቦናዬ ያን
ጊዜ ስትውለበለብ ያየኋት ባንዲራ ሮም ላይ ሯጩ ይዟት አየኋት እና እንኪ ያዣት በጥንቃቄም አስቀምጫት! ሲሆንልሽ ግን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ | ባንዲራ ወደ አለባት ኢትዮጵያ ወደሚሏት
ሃገር ሂጂ።
"ይህም መቀመጫ ስንተራሳት ስቀመጥባት ምንድናት?' እያልሽ የምትጠይቂኝ መቀመጫዬም 'በርኮቶ' ትባላለች በኮዬጉዎች።
“ምን?” አለች ኮንችት
ኩዬጕ ኩዬጉዎች… የኔ ዘመዶች የሚቀመጡባት
መቀመጫ ናት" ሳሉ እንደገና አሳለው ላቡ በግንባሩ ተንቆረቆረ
ወደ ሰማይ ቀና ብሎ፦
“ልዑል እግዚአብሔር! እባክህ ትንሽ ትንሽ ጊዜ ስጠኝ አለና እግዚአብሔርን ተማፅኖ፣ “አጠገባቸው ትልቅ ወንዝ አለ::
ሱርማዎች ኦሞ ይሉታል: ከወንዙ ተሻግረሽ ትንሽ ስትሄጂ ኩችሩ የሚባል መንደር አለ፡፡
ሰላም ሲሉ አሹቃ ይላሉ። አሳ አጥማጆች አትክልተኞች ከዱር ማር ሰብሳቢዎች ናቸው" እንደገና ሳለ፤ ቀና ብሉ ሰማዩን ተመለhተ።
ኮንችት የሚለው አልገባትም በጨቅላ ህሊናዋ ግን ስቃዩ
አሳዝኗታል።
“ሁሉንም ፅፌልሻለሁ ባንዲራዋን ከዘነጋኋት ዘመዶቼም ከመኖሪያቸው ለቀው ከሆነ ልፋትሽ መና ይቀራል። ወለላዬ እስቲ
እነዚያ ቆንጂዬ ጣቶችሽ? አላት ድንገት:: ሁለቱንም እጆችዋን ዘረጋችለት:: ጊዜ አልነበረውም መጣደፍ ነበረበት፡፡
ጳ..ጳ አርጎ በጥቁሩ ከንፈሩ በየተራ ሳማቸው: ጉንጯን
ሊስማት ፈለገ¦ ግን ፈራ ሳሉ ቢተላለፍባትስ:
“እንኪ በላስቲኩ
አሮጌ ካርቶን ውስጥ ይኸው ከትቼልሻለሁ። የኔ ልጅ እኒያን ዘመዶቼን ቀንቶሽ ካገኘሻቸው
እዘኝላቸው እንዳንች ንፁሆች ናቸው፡፡ ሎካዬ ናፍቋችኋል ሰላም
ብሏችኋል! በያቸው: ሞቷል አትበያቸው: ስንት ጊዜ በእኔ ይዘኑ ለእኔ ያልቅሱ አለ በያቸው ሲረጋጉ ደግሞ እኔ ነኝ ሎካዬ በያቸው እንደ ህፃን ያምኑሻል መጠራጠር አያውቁም ፤የሚጠራጠር ራሱ ሌባ ነው ይባል የለ! እነሱ ግን እንደ ዶሮ እየጫሩ
ተዛዝነው ያገኙትን ሲለቅሙ ይውሉና የኩችሩ ጫካ ክንፍ ውስጥ እንደ ጫጩት እየተሰገሰጉ ሙቀታቸውን እየተጋሩ ይተኛሉ…"
አሳለው! ሰውነቱ ራደ ላቡ ወረደ።
በይ ሄጂ ተጫወቺ እ..ኔ
ደ.ግ.ሞ እ ..ሁ ልረፍ” አላት ተስፋ በቆረጠ አስተያየት እያያት የአደራ ካርቶኗን ታቅፋ ስትሄድ ፈገግ ብሎ ከኋላዋ ለመጨረሻ ጊዜ ተመለከታት።

👍20
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
“…ሶራ- የባህል ትንሽ ትልቅ አለው ብዬ ላነፃፀር
አልሻም። ልምዴና እውቀቴ ገና ውስን ነው: የባህል ልዩነት ግን አኗኗር ልዩነት እንደሚያመጣ አውቃለሁ፡፡
“ሁሉም ሰው ያለበትን አካባቢ ከሌላው በተሻለ ያውቃል! ይጠቀማል አያቴም ከለመደው ባህል ወጥቶ ካለፍላጎቱ ወደ
አለመደው ባህል ከመጣ በኋላ አስተሳሰቡ ከዘመነው ህብረተሰብ አንፃር ያነሰ ቢሆንም ከዚህኛው ህብረተሰብ የተሻለ ትዕግስትና ጨዋነት የነበረው ከዚህኛው የነበረው በመሆኑ ሴት አያቴን አስባውና
አልማው ያልነበረውን በጥቁር ፍቅር እንድትንቦራችና አያቴ ከዚህ
ዓለም በሞት ከተለየ በኋላም ፍቅሩ ጥቁር ድመት አቅፋ እንድትውል አድርጓታል፡
“ወንድ አያትሽን በመልክ ታውቂያቸዋለሽ? ሶራ ጠየቃት:
“ልጅ ነበርኩ እንጂ አስታውሰዋለሁ። ከእንጨት ጠርቦ የሰራት ትንሽና ልዩ በርጩማው ላይ ቁጭ አንዳንዴም ጋደም ብሎ
ይንተራስና ሽቅብ ሽቅብ እያየ ሰማዩ ላይ ማፍጠጥ ይወዳል:
“እኔም ከሌሎች ጋር ስሆን መዝለልና መጫወት
እንደማልወድ ሁሉ እሱ ደረት ወይ ትከሻ ላይ ሆኜ ግን ለረጅም ጊዜ
ከሚቆዝመው ጥቁርና ልዩው አያቴ ጋር ፀጥ ስለምል ሴት አያቴ፡-
“ሎካዬ! ካንተ ጋር ስትሆን ለምን ዝም እንደምትል
ታውቃለህ?" ስትለው ዘወር ብሎ ወይም አይኖቹን ከሰማዩ ላይ መልሶ ያያታል።
“ስለምትፈራህ ነው አንተ ስ
ለህፃንም ለአዋቂም ዝግ ነህ አዕምሮህ የዕድሜ ልዩነትን አይገምትም! መሣቅ መጫወት ለልጆች
ምን ያህል ጠቃሚ መሆኑን አታስብም…” ትለውና ለመውሲድ እጅዋን ስትዘረጋልኝ በእንቢታ ደረቱ ውስጥ ድብቅ እላለሁ፡
“ወለላዬ! ሂጂ፤ አብረሽኝ መሆንሽን እየዘነጋሁ በዝምታ እኔ የምፈራው አንሶኝ አንችንም አስፈራሁሽ ውሰጃት :ኜስ
ላጫውታት አልታደልሁም" ይላታል። ያን ጊዜ በትናንሽ እጆቼና እግሮቼ ቁልፍ አድርጌ እይዘውና “አልሄድም' እላለሁ
“ያኔ ሴት አያቴ ትኩር ብላ ታየንና ቀስ ብላ መጥታ
ትከሻውን ተደግፋ! …ሎካዬ ለምን ደስተኛ አትሆንም እወድሃለሁ እኮ መሣቅ መጫወት ግን ልትለምድልኝ አልቻልክም: ለምን
ታሳቅቀናለህ! ስትለው ዝም ብሏት ይቆይና፡-
"አኜስ እባክሽ ተይኝ" ይላታል:
ከኔ በላይ የሚቀርብህ ማን ሊመጣ ይችላል፡፡ ጭንቀትህ ውስጣዊ ብሶትህ ጊዜ የማይሽረው ዝምታህ ምንድነው?” ስትለው፡-
“የአባቴ ልማድና ወግ ከብቶቼ…"ሃሳቡን ሳይጨርስ
አይኖቹን ይጨፍናል
“የአንተ አገር ከብቶች ከኛ ይለያሉ?"
“እንዴታ! ይለያሉ እንጂ።"
“በምን?”
“በማእረግ ፧ አኜስ! ከብት ከስጋና ወተቱ ይልቅ ቅሩ
ያጠግባል። በምላሱ ሲልስሽ በሽንቱ ስትታጠቢ እነሱ እያገሱ አንች
እያንጎራጎርሽ ስትከተያቸው
ስትውይ የሆዳቸውን
ጩኸት እያዳመጥሽ
ትንፋሻቸውን እየሞቅሽ
አብረሻቸው ስትተኝ…
የህይወት ቁርኝቱ የተፈጥሮ ሰንሰለቱ በፍቅር የተገመደ ነውር ።
“እዚህ ግን ከብቶችና እኔ አረም ነን። የምግብ ክምር
ይሰጠንና ታስረን የምንውል ማግሳትና ማንጎራጎር የማንችል…"ሲላት ሴት አያቴ በወንድ አዬቴና ላይ ያለ የሌለ እርግማን ታወርድበታለች፡፡
“ምንም ሳይመልስላት አይኖቹን አድማስ ላይ ይተክላል። የእጅ ጣቶቹ ግን የሰራ አካላቴን ሳይታክቱ
ስለሚደባብሱኝ የመጨረሻውን ሳላውቅ እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ይወስደኛል፡፡
“እና! የሴት አያቴ ዘመዶች ሴት አያቴን፡
“አፍሪካዊው ሎካዬን በማግባቷ ብዙ ነር ጎድሏታል እያሉ
ኢያቴን ለምን አብራው እንደምትኖር ሲጠይቋት-
ዝምታው ልቤን በፍቅር የባህር ጨው አድርጎታል::
የፍቅር ነፃነቴም ያስደስተኛል ሎካዬን እንለያይ ብለው እሺ እህትና ወንድም እንሁን 'እንዳልሽ' ከማለት ሌላ ታቃውሞ ግዴታዬ መለማመጥ ፍርሃት ስለማላይበት ከእሱ መለየት የማይታሰብ ነው ብላ አፋቸውን ታሲዛቸዋለች:
“ወንድ አያቴ ሎካዬ በግር መጓዝም ይወዳል! በተለይ
በረፍት ቀኑ ከተማው መሃል ካለው መናፈሻ የተወራረደ ሰው ሄዶ አያጣውም እፅዋት ስር ይገባና አላፊ
አግዳሚውን ሳያይ እንደ ስነ
ፍጥረት ተመራማሪ አይኑን ሰማዩ ላይ ሰክቶ በርጋታ ለብዙ ጊዜ ይቀመጣል።
ሶራ ወንድ አያቴ ማንም ሊረዳው ከሚችለው በላይ ውስጡ ናፍቆት ትዝታ የቦረቦረው ነበር ዘመናዊነት ደስታን ሊፈጥርለት አልቻለም በረጅሙ ህይወቱ ካገኘው ልምድ ይልቅ
የልጅነት ዘመነ ትዝታ እሱነቱን ሽፍኖለታል: ድሮ ስለ አያቴ ባሰብኩ ቁጥር የሱን ትውልድ ቦታ እንደ ገነት እቆጥረው ነበር።
እናቴ ግን አፍሪካ ድህነት ችግር….የተከመረባት ሰዎቹም እርስ በርሳቸው የሚበላሉ እንደሆኑና ሲኦል እንጂ ገነት እንደሊለባት
ስትነግረኝ ሌላ ሃሳብ በአእምሮዬ መፈጠር ጀምሮ ነበር። ይህች አለም ጥቁርና ነጭ አምላክ ያላት ሁለት ገነት የሚገኝባት ሆና
አንዱ የሌላው ጠላት እንደሆነ ይስማኝ ነበር፡፡
"አያቴ ስለ ወንድ አያቴ ሁለት ተቃራኒ እምነቶች ነበሯት በአንድ በኩል ዝምታውንና ጅንነቱን የምትወድለት ቢሆንም በሌላ በኩል ደግሞ አብረው ለመዝናናት ለመወያየት ስለማይችሉ ፀጉሯን እየነጨች ትበሳጫለች ያም ሆኖ ግን እናቴ እንደነገረችኝ ከሆነ
አያቴ ለወንድ አያቴ በተደጋጋሚ በፍቅር ስትናዘዝለት ሰምታታስች
ለምሳሌ እንድ ቀን አያቴ ከሁዌልቫ በስተምእራብ አስራ አምስት ኪሎሜትር ላይ ከሚገኘው የብርቱካን ማሳቸው አያቴን ይዛት
ትሄዳለች እዚያ ሲደርሱ ግን ወንድ አያቴ አልነበረም፡
“ስለዚህ እናቴ ከሪና ሁሌም እንደምታደርገው ወደ ብርቱካን ማሳው ገባ ብላ ብርቱኳን እየላጠች ስትበላ የቀሚሷ ጫፍ እየያዘች
ስትዘፍንና ስትዝናና ቆይታ አያቴን ወደተለየችበት ቦታ ስትመጣ አያቴን ታጣታለች።
“ደጋግማ ተጣርታ ወይ የሚላት ሲጠፋ የትም አትሄድም በሚል እራሷን አረጋግታ አያቴን አኜስን ስትፈልጋት እመስኖው
ውሃ ቦይ ትደርስና ውስጡ
ገብታ እየተንቦጫረቀች ስትሄድ የመስኖውን ውሃ ከሚስበው ሞተር ቤት ደረሰች፡፡
የሰው ድምፅ የሰማች መስሏት ፀጥ ስትል ድምፁ
ጠፋባት፡ ልትጣራ ፈለገች
ከመጣራቷ በፊት ግን ቀርቦ የራቃት ድምጽ ተመልሶ መጣ! ከሞተሩ ቤት የሚመጣውን ድምጽ በጆሮዋ ያዘችው። የሚያቃስት ሰው ድምጽ ነው የእናቷ! ደነገጠች ወደ
ሞተሩ ቤት ሄዳ በፍርሃት በጭላንጭል አየች እናቴን ከእግር ጥፍሯ እስከ ጸጉሯ አንዳች ነገር ነዘራት፡፡ ድምፁ እንደገና ቀሰቀሳት
አያቴ አኜስ ናት! ድምፅዋ ቁርጥርጥ እንደሚቀጣ ህፃን ትንፋሽዋን በሲቃ ውጥር ይልና ደሞ ይጠፋባታል፤
በመጨረሻ ድምፁ
መጠኑን ጨምሮ መጣ
የሁለት ሰው ድምፅ የሉካዬና አኜስ ጨመረ ድምፁ እናቴ ተጨነቀች። ልትሮጥ ዘወር ስትል
የፎይታ ድምጽ ሰማች። ከዚያ አያቴ ተረጋግታ ስትናገር ሰማቻት፡
“አመሰግናለሁ ሎካዬ የልቤን ነው ያደረስከው ከከሪና ጋር ወደ አንተ ስገሰግስ እንዲህ አንጀቴን እንደምታርሰው እርግጠኛ
ነበርሁ። የውጭ በግ…
የልጋ ላይ ግን አንበሳ ነህ. ብላ ስትናዘዝላት እናቴ አያቴን ሰምታታለች።
“ይህ ደግሞ ሴት አያቴ
ወንድ አያቴን የምታፈቅረው
በዲፕሎማሲያዊ አነጋገር በዝምታው ነው ትበል እንጂ ጌታውን እንዳዬ ውሻ እግሩ ስር የሚያልወሰውሳት ሚስጥሩ ሴላ ነው፡፡
ሶራ የሚገርምህ ግን እናቴ ያችን ቀን ፆታዬን
ያወቅሁበትና ረሃቤን ለማዳመጥ ትእግስት የጎደለኝና የተመኘሁትን
ያጣሁበት ቀን ናት' ብላ ታስታውሳለች፡፡
ይህ በሆነ ከአምስት ዓመት በኋላ ግን እናቴ ከአባቴ
ከፍራንሲስኮ ፔሶ ቤኒ ጋር ከሁዌልቫ ወደ ሊዝበን ለጉብኝት ስትሄድ
ተዋውቀው ግንኙነታቸውና መግባባታቸው እየጨመረ ሲሄድ የብርቱካን ማሳቸውን ልታሳየው ቀጠረችው፡፡

👍32