አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
493 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...አሁን ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ባለው ሚስጥር ላይ ቆሻሻና የሚሸቱ ጨርቆች በሻንጣዎቹ ውስጥ በመክተት ሌላ ሚስጥር ጨመርንበት.

ስለ ሁኔታው አብዝተን ባለማውራታችን ከነገሩ እጅግ አስፈሪ መሆን አመለጥን:
ጠዋት እንነሳና ፊታችን ላይ ውሀ ረጨት እናደርጋለን። ጥርሶቻችንን በባዶ ውሀ እናፀዳለን፤ ጥቂት ውሀ እንጠጣና ትንሽ ወዲያ ወዲህ እንላለን፡ ከዚያ ጋደም ብለን ቴሌቭዥን እናያለን ወይም እናነባለን፡

መንትዮቹ ምግብ ፈልገው ሲያለቅሱ መስማቴ ህይወቴን ሙሉ ልቤ ላይ የሚኖር ጠባሳ አስቀመጠልኝ፡ አያታችንን እንዴት እንደጠላኋት። ያቺ አሮጊት እና እናታችን ይህንን ስላደረጉብን ጠላኋቸው።

የመመገቢያ ሰአታችን ያለ ምግብ ሲያልፍ እንተኛለን፡ ለሰዓታት እንተኛለን::እንቅልፍ ሲወስደን የርሀብ ወይም የብቸኝነት ወይም የምሬት ስቃይ አይሰማንም በእንቅልፍ በውሸት የደስታ ስሜት ውስጥ እንሰምጣለን ከዚያ
ስንነቃ ስለምንም ነገር ግድ አይኖረንም።

እንደ ፈዘዝኩና እንደደከምኩ ጭንቅላቴን ዞር አድርጌ ክሪስንና ኮሪን እያየሁ ነበር ከዚያ ክሪስ ከኪሱ ሰንጢ አውጥቶ የእጁን አንጓ ሲቆርጥ ያለምም
ስሜት ጋደም ብዬ እየተመለከትኩ ነው። የሚደማ እጁን ወደ ኮሪ አፍ አስጠጋና ኮሪ ቢቃወምም እሱ ግን ደሙን እንዲጠጣ አደረገው: ከዚያ የኬሪ ተራ ሆነ ሁለቱ ምንም ነገር ያልበሉ በመሆናቸው፣ የትልቁ ወንድማቸውን ደም ጠጥተው፣ በደበዘዘ፣ በፈጠጠና በተቀባይነት አይን አተኩረው ተመለከቱት።

ማድረግ ባለበት ነገር የማቅለሽለሽ ስሜት ተሰምቶኝ ፊቴን አዞርኩ። ያንን በማድረጉ አድናቆት ተሰምቶኛል። ሁልጊዜ ከባባድ ችግሮችን ማቃለል
ይችልበታል።

ከዚያ ክሪስ ወደኔ አልጋ መጣና፣ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጦ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ሲመለከተኝ ከቆየ በኋላ አይኖቹ ወደተቆረጠው አንጓው ዝቅ
አሉ አሁን መድማቱን አቁሟል። እኔም ደሙን ጠጥቼ ረሀቤን እንዳስታግስ ሌላኛውን ደም ስሩን ለማድማት ሰንጢውን አወጣ እንዳያደርገው ነግሬ ሰንጢውን ቀምቼ ወረወርኩት። ብርታት ለማግኘት ስል የእሱን ደም
እንደማልጠጣ ምዬ ተገዝቼ ብነግረውም መሀላዬን ከቁም ነገርም ሳይቆጥር ሰንጢውን በአልኮል ማፅዳት ጀመረ።

“ተመልሳ ባትመጣ ምንድነው የምናደርገው ክሪስ?" ስል ጠየቅኩት አያታችንን ለሁለት ሳምንት አላየናትም: አይጥ ለማጥመድ ወጥመዱ
ላይ ያደረግነውን ቺዝ የሚላስ የሚቀመስ ባጣን ጊዜ በልተን ጨርሰነዋል።ምግብ የሚባል ሳንቀምስ ሶስት ቀናችን ሆኗል፡ መንትዮቹ እንዲጠጡት
የተውንላቸው ወተትም ካለቀ አስረኛ ቀን ሆኖታል።

“በረሀብ አትገድለንም” አለ ክሪስ አጠገቤ ተኝቶ በደካማ ክንዱ እያቀፈኝ። “እሷ ያንን እንድታደርግ ከፈቀድንላት ደደቦች ነን ማለት ነው ነገ ምግብ ይዛ ካልመጣች ወይ ደግሞ እናታችንም ብቅ ካላለች አንሶላ ተልትለን መሰላል
እንሰራና ወደ መሬት እንወርዳለን” አለ፡

ጭንቅላቴ በደረቱ ላይ ስለሆነ ልቡ ሲመታ ይሰማኛል። “ምን እንደምታደርግ ታውቃለህ? ስለምትጠላን እንድንሞት ትፈልጋለች። መወለድ የማይገባን
የሰይጣን ልጆች መሆናችንን ስንት ጊዜ ነው የነገረችን?

ካቲ፤ ያቺ ጠንቋይ አሮጊት ደደብ አይደለችም: እናታችን ካለችበት ከመምጣቷ በፊት ምግብ ይዛ ትመጣለች::”

የተቆረጠ እጁን ላሽግለት ተንቀሳቀስኩ ከሁለት ሳምንት በፊት እኔና ክሪስ ለማምለጥ መሞከር ይገባን ነበር። የዚያን ጊዜ ሁለታችንም ጥንካሬ ነበረን
አሁን ብንሞክር ግን በእርግጠኝነት ወድቀን እንሞታለን፡ መንትዮቹን
በጀርባችን አዝለን ከሆነ ደግሞ የበለጠ ከባድ ይሆንብናል።

በማግስቱ ጠዋት ምንም ምግብ እንዳልመጣ የተመለከተው ክሪስ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል እንድንሄድ አስገደደን፡ እኔና ክሪስ ለመራመድ እጅግ ደክመው
የነበሩትን መንትዮች ተሸከምናቸው የመማሪያ ክፍሉ ጥግ ላይ ስናስቀምጣቸው አቅማቸው ስላልቻለ እንደመተኛት
እያሉ ግድግዳውን ተደግፈው ቁጭ አሉ። ክሪስ መንትዮቹን ጀርባችን ላይ የምናስርበትን ገመድ እያዘጋጀ ነው

“በሌላ መንገድ እናደርገዋለን” አለ ክሪስ እንደገና እያሰበ “በመጀመሪያ እኔ እሄዳለሁ መሬት ስደርስ ኮሪን ታስሪውና ቀስ እያልሽ ወደታች ትለቂዋለሽ
ቀጥሎ ኬሪንም እንደዚያው ታደርጊያለሽ: በመጨረሻ አንቺ ትመጫለሽ ስለ እግዚአብሔር ብለሽ የምትችይውን ጥረት ሁሉ አርጊ! አደጋ በሚደርስበት
ወቅት ከፍተኛ ንዴት ከሰው በላይ የሆነ ጥንካሬ እንደሚፈጥር ሰምቻለሁ።"

“አንተ የበለጠ ጠንካራ ስለሆንክ እኔ መጀመሪያ ልሂድ” አልኩት በድካም ስሜት “አይሆንም! ድንገት ፈጥነው ከመጡ ለመያዝ ታች መሆን አለብኝ ያንቺ ክንዶች የኔን ያሀል ጥንካሬ የላቸውም: ክብደቱ ሁሉ አንቺ ላይ
እንዳይሆን ገመዱን ጭስ መውጫው ላይ አስርልሻለሁ እና ካቲ ይvህ የአደጋ ጊዜ ነው!”

በአይጥ መያዣ ወጥመዱ ላይ አራት የሞቱ አይጦችን በድንጋጤ ተመለከትኩ።“ትንሽ ጥንካሬ እንድናገኝ እነዚህን አይጦች መብላት አለብን፡” አለ ኮስተር ብሎ፡ “ማድረግ ያለብንን ሁሉ ማድረግ አለብን::''

እነዚያን የሞቱ ትንንሽ ወፍራም ነገሮች በመጠየፍ እየተመለከትኩ “ጥሬ ስጋ? ጥሬ አይጥ? አይሆንም!" አልኩ በቀስታ:
በጣም ተናዶና አስገዳጅ በሚመስል አይነት መንትዮቹንም ሆነ ራሴን በህይወት ለማቆየት የሚያስፈልገውን የትኛውንም ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ነገረኝ፡ “ተመልከቺ ካቲ፣ መጀመሪያ እኔ ሁለቱንም እበላለሁ ገመዶቹን
በደንብ ለመቋጠርም የልብስ መስቀያ ስለሚያስፈልገኝ ላምጣ… ታውቂያላሽ ኬቲ እጆቼ አሁን በደንብ አይሰሩም” አለ፡

ሁላችንም በጣም ከመድከማችን የተነሳ የምንንቀሳቀሰው የግዳችንን ነው::

አየት አደረገኝና “በእውነት አይጦቹ በጨውና በበርበሬ በጣም የሚጣፍጡ ይመስለኛል” አለ፡፡

ጭንቅላታቸውን ቆርጦ ቆዳቸውን ገፈፈና አንጀታቸውን አወጣው: ትንንሽ ሆዳቸውን በመሰንጠቅ ረጃጅምና ቀጫጭን አንጀቶቻቸውን እንዲሁም ትንንሽ
ልቦቻቸውንና ሌሎች የውስጥ እቃዎቻቸውን ሲያወጣ እየተመለከትኩት ነበር ሆዴ ባዶ ባይሆን ኖሮ ሊያስመልሰኝ ይችል ነበር።

ክሪስ ጨውና በርበሬ ሊያመጣ ሲሄድ አይኖቼ ቆዳቸው ተገፍፎ ለምግብነት የተዘጋጁት አይጦች ላይ ተተክለው ቀሩ። አይኖቼን ጨፍኜ የመጀመሪያውን
ጉርሻ ለመጉረስ ሞከርኩ እርቦኛል ግን ይህንን ለመብላት የሚያክል አይደለም ረሀቤ።

ወዲያው እጅ ለእጅ ተያይዘው፣ ግንባራቸውን አጋጥመውና አይናቸውን ጨፍነው ጥጉ ላይ የተኙትን መንትዮች አሰብኩ በእናታችን ማህፀን ውስጥም እንደዚህ ተቃቅፈው የነበሩ ይመስለኛል: ምስኪን ልጆች! በአንድ ወቅት በጣም የሚወዷቸው እናትና አባት ነበሯቸው።

እነሱን በደህና መሬት ለማድረስና ከጎረቤት ምግብ ለማግኘት አይጦቹ ለእኔና ለክሪስ በቂ ጥንካሬ እንደሚሰጡን ተስፋ አድርገናል።

ክሪስ ቀስ እያለ ወደኛ ሲመለስ ሰማሁ። በሩ ላይ ቆም ብሎ አመነታ።ሽራፊ ፈገግታ እያሳየ ነው ሰማያዊ አይኖቹ ወደኔ እየተመለከቱ አንፀባረቁ።
በሁለት እጆቹ በደንብ የምናውቀውን ትልቅ የሽርሽር ቅርጫት ይዟል። ቅርጫቱ መክደን እስከሚያስቸግር ድረስ በምግብ ተሞልቷል ሁለት ትልልቅ
ፔርሙዞች አወጣ አንደኛው ውስጥ የአትክልት ሾርባ፣ ሌላኛው ውስጥ ወተት ነበረበት በማየው ነገር ግራ ተጋባሁ። እናታችን አምጥታልን ነው?
ከሆነ ታዲያ ለምን ወደታች እንድንሄድ አልጠራችንም? ለምንስ ደግሞ እኛን ፍለጋ ወደዚህ አልመጣችም?
👍252👏2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የመንግስተ ሰማያት ጣዕም

ክሪስ በቀስታና በጥንቃቄ እጁን ከእጁ ስር፣ እግሩን ከእግሩ ስር እያደረገ ወደ መሬት ወረደ እኔ ደግሞ ጣሪያው ጠርዝ ላይ በደረቴ ተኝቼ ወደታች ሲወርድ እያየሁ ነው እጁን አንስቶ ሲያውለበልብልኝ ጨረቃዋ ወጥታ ብሩህ ሆና እያበራች ነበር፡ እንድወርድ ምልክት እየሰጠኝ ነበር። ክሪስ
እንዴት እንደወረደ አይቻለሁ: ዥዋዥዌ ከመጫወት የተለየ አይደለም ብዬ
ለራሴ ነገርኩት። ቋጠሮዎቹ ትልልቅና ጠንካሮች ናቸው: በዚያ ላይ በበቂ ሁኔታ አራርቀን ነው የሰራናቸው አንድ ጊዜ ጣሪያውን ከለቀቅኩ በኋላ ወደ
ታች እንዳልመለከት አስጠንቅቆኛል መጀመሪያ አንደኛውን እግር ካሳረፍኩ
በኋላ በሌላኛው እግሬ የታችኛውን ቋጠሮ መፈለግ ላይ እንዳተኩር ነገረኝ።
እንዳለኝ እያደረግኩ ከአስር ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መሬት ላይ ከክሪስ አጠገብ ቆምኩ።

“ዋው!” አለ ወደሱ አስጠግቶ እያቀፈኝ ከእኔ በተሻለ አደረግሽው”

የፎክስወርዝ አዳራሽ የጓሮ አትክልት ቦታ ውስጥ ነን፡ ክፍሎቹ በሙሉ ጨለማ ውጧቸዋል። የሠራተኞቹ መኖሪያ መስኮቶች ሁሉ ደማቅ ቢጫ ናቸው፡ ዝቅ ባለ ድምፅ “በል መንገዱን ካወቅከው ወደ መዋኛው ምራኝ አልኩት:

በእርግጥም መንገዱን ያውቀዋል እናታችን እሷና ወንድሞቿ ከጓደኞቻቸው
ጋር እንዴት ተደብቀው ወደ ዋና እንደሚሄዱ ነግራናለች:
እጄን ይዞ በጣቶቻችን እየተራመድን ከትልቁ ቤት ወጣን በሞቃታማው
የበጋ ምሽት ውጪ መሬት ላይ መሆን ለየት ያለ ስሜት አለው መንትዮቹን ብቻቸውን የተቆለፈ ክፍል ውስጥ ትተናቸዋል፡ ትንሽዬዋን ድልድይ ስናቋርጥ አሁን ከፎክስወርዝ ግዛት ውጪ መሆናችንን ስላወቅን ደስታ ተሰማን:: ነፃ የሆንን መሰለን፡ ቢሆንም ማንም እንዳያየን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። ወደ ሜዳውና እናታችን ወደ ነገረችን ሀይቅ ሮጥን።

ጣሪያው ላይ ስንወጣ አራት ሰዓት ነበር: በዛፎች የተከበበውን ትንሽ የውሀ
አካል ስናገኝ አራት ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር። ሌሎች ሰዎች እዚያ ኖረው ምሽታችን ይበላሽብናል ብለን ፈርተን ነበር። ነገር ግን የሀይቁ ውሀ ፀጥ ያለና
በንፋስ እንኳን የማይንቀሳቀስና የሚዋኙም ሆኑ በጀልባ የሚቀዝፉ ሰዎች የሌሉበት ነበር።

በጨረቃ ብርሃን በኮከቦች በደመቀ ሰማይ ስር ሆኜ ሀይቁን እየተመለከትኩ እንደዚህ አይነት የሚያምር ውሀ አይቼ እንደማላውቅና እንደዚህ በሀሴት
የሞላኝ ምሽት ኖሮ እንደማያውቅ አሰብኩ።

“እርቃናችንን እንዋኛለን?” ሲል ክሪስ ለየት ባለ ሁኔታ እያየኝ ጠየቀኝ፡

“አይ የውስጥ ሱሪያችንን ለብሰን ነው የምንዋኘው” አልኩት።

ችግሩ አንድም የጡት መያዣ የሌለኝ መሆኑ ነበር። አሁን ግን እዚህ ደርሰናል: አጉል የሆነው የጨዋነት ጥያቄ በዚህ በጨረቃ ብርሀን በደመቀ ውሀ ከመደሰት አያስቆመኝም። ልብሴን አውልቄ የመርከብ ማቆሚያ ወደ
ሆነው ጥልቀት የሌለው ጥግ ጋ ሮጥኩ። ስደርስ ግን ውሀው እንደ በረዶ ይቀዘቅዝ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ በመጀመሪያ እግሬን ነከር አድርጌ አረጋገጥኩ እውነትም በጣም ቀዝቃዛ ነው! ክሪስን ሳየው ሰዓቱን ከእጁ ላይ ፈትቶ ወደጎን
በማስቀመጥ ወደ እኔ እየሮጠ መጣና ደፍሬ ወደ ውሀው ከመግባቴ በፊት ጀርባዬ ጋ ደርሶ ገፈተረኝ: ውሀው ውስጥ በደረቴ ወደቅኩና ሙሉ በሙሉ
ውሀ ውስጥ ጠለቅኩ።

ከውሀው ስወጣ እየተንቀጠቀጥኩ ነበር። ወደ ክሪስ ተመለከትኩ ከፍ ያለ ድንጋይ ላይ ቆሟል ክንዶቹን ወደ ላይ አነሳና ወደ ሀይቁ ተወርውሮ ገባ፡ በድንጋጤ አቃተትኩ። ውሀው በቂ ጥልቀት ያለው ባይሆንስ? መሬቱ
መትቶት አንገቱ ወይም ጀርባው ቢሰበርስ?

ክሪስ ወደ ላይ አልተንሳፈፈም: አምላኬ! ሞቷል ሰምጧል!

“ክሪስ!” እየጠራሁትና እያለቀስኩ ገብቶ ወደተሰወረበት ቦታ መዋኘት ጀመርኩ።

ድንገት የሆነ ነገር እግሬን ያዘኝ! ጮህኩና ወደ ውስጥ ገባሁ የጎተተኝ ክሪስ ነበር፡ በጥንካሬ እግሮቹን እያወራጨ ወደምንስቅበትና ውሀ ወደምንረጫጭበት ወጣን

“እዚያ የተረገመ የሚሞቅ ቤት ውስጥ ከመዘጋት ቅዝቃዜው አይሻልም? ሲል ጠየቀኝ፡ ልክ እንደ እብድ ዙሪያውን እየዞረ ሲጮህ ላየው ይህች ትንሽ ነፃነት እንደ ጠንካራ የወይን ጠጅ አናቱ ላይ ወጥታ ያሰከረችው ይመስል
ነበር። ዙሪያዬን እየዞረ ዋኘና እግሬን ይዞ ወደታች ሊጎትተኝ ሞከረ: አሁን
ግን አልቻለም:

ውሀ እየተረጫጨንና እየዘፈንን፣ ከዚያ ደግሞ አቅፎኝ ስንስቅና ስንጮ ነበር። ልክ እንደገና ልጆች የሆንን ይመስል ታገልን… አበድን ውሀ ውስጥ በጣም ጎበዝ ነው ልክ እንደ ዳንሰኛ: እየዋኘን እያለ በድንገት ደከመኝ::በጣም ከመድከሜ የተነሳ እንደ እርጥብ ፎጣ ሆኜ ነበር። ክሪስ በክንዱ ደግፎ ወደ ዳር እንድወጣ አገዘኝ።

ሁለታችንም ሀይቁ ዳር ላይ ያለው ሳር ላይ በጀርባችን ተጋድመን ማውራት ጀመርን።

“አንድ ጊዜ እንዋኝና ወደ መንትዮቹ እንመለስ” አለ ሁለታችንም
የሚያብረቀርቁና የሚጣቀሱ የሚመስሉት ኮከቦች ላይ አተኩረናል። ደስ የምትል ግማሽ ጨረቃ ደመናው ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያለች ድብብቆሽ
የምትጫወት ትመስላለች፡ “ምናልባት ወደ ጣሪያው መውጣት ባንችልስ?” አልኩ

“እንችላለን፡ ምክንያቱም ማድረግ አለብን” ክሪስቶፈር ሁልጊዜ እንደሚቻል የሚያምን ልጅ ነው: ሰውነቱ በውሀ ረጥቦ፣ ፀጉሩ ግንባሩ ላይ ተጣብቆ አጠገቤ ተጋድሟል። አፍንጫው እንደ አባታችን አፍንጫ ቀጥ ያለ ነው: ከንፈሮቹ የሚያምር ቅርፅ አላቸው:: አገጩ አራት ማዕዘን ሲሆን ደረቱ መስፋት ጀምሯል። እያደገ ያለው ወንድነቱ በጠንካራ ጭኖቹ መሀል ማበጥ ጀምሯል። ስለ ወንዶች ሳስብ አንድ ነገር ይማርከኛል
ያም ጥሩ ቅርፅ ያላቸው ጭኖች ናቸው፡ ጥፋተኝነት ሳይሰማኝና ሳላፍር ቁንጅናውን በአይኖቼ ለመመገብ ባለመቻሌ አዝኜ ጭንቅላቴን አዞርኩ።

ፊቱን አዙሮ አይኖቼን ተመለከተ: እኔም አየሁት። ሌላ ቦታ መመልከት
የማንችል እስኪመስል ድረስ እይታዎቻችን ተቆላለፉ ለስላሳ የደቡብ ነፋስ ፀጉሬ ውስጥ እየተጫወተና ፊቴ ላይ ያለውን ውሀ
እያደረቀው ነው፡ ምሽቱ በጣም ጣፋጭና በጣም ደስ የሚል ቢሆንም ፍቅርን የመራብ ከፍተኛ ስሜት ውስጥ ባለ ዕድሜ ላይ ያለሁ በመሆኔ ብቻ ምንም
ምክንያት ሳይኖረኝ ማልቀስ ፈለግኩ: ከዚህ በፊት እዚህ የነበርኩ አይነት ስሜት ተሰማኝ፡ ከሀይቁ አጠገብ ሳሩ ላይ እንደተጋደምኩ እንግዳ የሆነ
ሀሳብ በመጀመሪያ እንደ ተሳዳጅ ወደዚህ ወደመጣንበትና ከማይፈልገን አለም ወደተሸሸግንበት ወደዚያ ምሽት መለሰኝ።

ክሪስ፣ አሁን አስራሰባት አመት ሊሆንህ ነው፣ አባቴ እናቴን በመጀመሪያ ሲያገኛት የነበረበት እድሜ ማለት ነው”

አንቺ ደግሞ አስራ አራት፤ ልክ በእሷ እድሜ” ድምፁ ጎርነን ብሎ ነበር።

መጀመሪያ እይታ በሚፈጠር ፍቅር ታምናለህ?”

“በዚህ ርዕስ ላይ ጠቢብ አይደለሁም ትምህርት ቤት እያለሁ፣ አመነታ አንዲት የምታምር ልጅ አይቼ ወዲያው ፍቅር ይዞኝ ነበር ስናወራ ግን የሆነች ደነዝ ነገር ሆና ሳገኛት ለሷ የነበረኝ ስሜት ጠፋ፡ ግን ውበቷ በሌሎች
ነገሮች ከተደገፈ በመጀመሪያ እይታም ፍቅር ሊይዘኝ ይችላል ብዬ አስባለሁ ነገር ግን እንደዚያ አይነት ፍቅር አካላዊ መሳሳብ ብቻ እንደሆነ አንብቤያለሁ።

“እኔስ ደነዝ እመስልሀለሁ?”

“በጭራሽ! እንደሆንሽ እንደማታስቢ ተስፋ አለኝ፡፡ ምክንያቱም አይደለሽም።ፈገግ ብሎ ፀጉሬን ሊነካ እጁን እየዘረጋ ችግሩ ካቲ፣ ብዙ ተሰጥኦዎች ስላሉሽ ሁሉንም መሆን ትፈልጊያለሽ ያ ደግሞ የማይቻል ነው:"

“ዘፋኝም ተዋናይም መሆን እንደምፈልግ እንዴት አወቅክ?”
👍332