አትሮኖስ
280K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
477 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዝግመተ_ለውጥ


#በአሌክስ_አብርሃም


...እንዲሁ ስለመምሬ እና ለትዳር ስላሰቡልኝ ልጅ እያሰብኩ የያዝኩትን ጋዜጣ መቃኘት ጀመርኩ፡፡.

በደማቅ ጥቁር ቀለም፣ “በማኅበር ተደራጅተው ጫት የሚያመርቱ አርሶ አደሮች ኑሯችን
ተለውጧል አሉ...” ይላል፡፡

ወረድ ብሎ፣ “አንዳንድ የማኅበሩ አባላት “ጫት በመሸጥ አይሱዙ መኪና ገዝተናል፣ ልጆቻችንንም
ከተማ ልከን እያስተማርን ነው ሲሉ ገልፀዋል” ከጽሑፉ ስር አይሱዙ መኪና ተደግፈው ፎቶ
የተነሱ አርሶ እደር ምስል ይታያል፡፡

ወረድ ብሎ ሌላ አርዕስት፣

አንድ አይሱዙ መኪና ሃያ ሜትር ጥልቀት ያለው ገደል ውስጥ ገብቶ ከላይ ጭኗቸው የነበሩ
ሰባት ሰዎች ሞቱ፡፡ ከሟቾቹ አራቱ ከገጠር ከተማ እየተመላለሱ የሚማሩ ተማሪዎች ሲሆኑ
ፖሊስ የአደጋው መንስዔ ሹፌሩ ጫት እየቃመ ማሽከርከሩ ነው ብሏል !"

ጋዜጣውን እጥፌ ሰፈራችንን ማየት ጀመርኩ፡፡ ቅድስት ቀይ የእራት ልብስ ለብሳ እቃ ታጥባለች፧እያንጎራጎረች፣ “በሰባራ ፎሌ ውሀ አያጠለቅም" አይ ቅድስት ! እንደኛ ሰፈር ሴት የባከነበት መንደር ያለ አይመስለኝም፡፡ ቆንጆ ናት 'ሞዴል' የመሆን ፅኑ ፍላጎት ነበራት፡፡ እንደውም የሰፈር ልጆች ሲፎግሯት፣ “ውበት ውጪያዊና ውስጣዊ ነው' ሲሉ ሰምታ ውስጣዊ ውበቷን ለማየት
እልትራሳውንድ ተነሳች” ይሏታል፡፡ ሰታንጎራጉር እየሰማኋት የድምጿ ማማር ተገረምኩ፤
“ወይ ይህቺ አገር ዘፋኞቿ በየማጀቱ እቃ እያጠቡ እቃ አጣቢዎቿ በየአደባባዩ እንዝፈን እያሉ ያደነቁሩናል" አልኩ ለራሴ፡፡ የቄሳርን ለእግዜር፡ የእግዜርን ለእግዚሃር፡፡

የመንደራችን የአንድ እሁድ ውሎ ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ነው:: ከጧቱ 12፡00 ሰዓት
አልማዝ የምትባለው ጎረቤታችን በሯ ላይ ስለተጣለው ድግምት ታማርራለች፣ ትራገማለች፡
ጠበል ታርከፈክፋለች፡፡ ድግምት በመጣል የሚጠረጠሩ ጎረቤቶቿን ታሸሙራለች፣ “እችኑ ኑሮ
ብለዋት...” እያለች፣ ብዙ ጊዜ የሞተ እይጥ ነው በሯ ላይ ተጥሎ የሚገኘው:

ከ 12፡30 እስከ ጧቱ 2፡00 ሰዓት እማማ ዘብይደሩ ጭንቅሎ የተባለውን የልጅ ልጃቸውን
ይረግማሉ፣ ይሳደባሉ፣ ይውገራሉ፡፡ አንዳንዴ ወገራው ሲበዛ ገላጋዮች ይገባሉ፡፡ “ባጭር ቅር….ይሉትና ሲታመም ሆስፒታል ለሆስፒታል አዝለውት ይዞራሉ፡፡
ከሁለት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት የመንደሩ ልጆች እኔ ቤት ፊት ለፊት ያለች (ሰርቪስ ቤት እንኳን
የማታቆም) ቢጢቃ ሜዳ ላይ ኳስ ይራገጣሉ፡፡ የሚያስነሱት አቧራ ልጆቹን ስለሚሸፍናቸው
እንደ ህልም ነው ብዥ ብለው የሚታዩት፡፡

ከሚጫወቱት ልጆች መሃል ጭንቅሎ (የእማማ ዘብይደሩ የልጅ ልጅ)፤ ሃይለሚካኤል 'አረቡ'
(የእማማ የውብዳር የልጅ ልጅ)፣ ሙስጠፋ (የእማማ ዘሃራ የልጅ ልጅ)፣ ሲቲና ወንዳወንድ ሰለሆነች 'ከቤ' ይሏታል (የነማማ ትርሃስ የልጅ ልጅ ናት)፤ ከላይ ከተዘረዘረው የዘር ሃረግ
እንደሚታየው መንደራችን አንድ እናት' የሚባል ትውልድ ገድፏል፣ አባት የሚባል ሃረግ ዘሏል
ሕፃናቱ ከአያቶቻቸው ጋር ነው ያደጉት፡፡ ያውም አቅም ከሌላቸው ደሃና እቅመ ደካሚ ባልቴት
አያቶቻቸው ጋር! እናቶቻቸው የት ሄዱ? አባቶቻቸውን ምን በላቸው?' ቢባል መልሱ ከሁለት
ጉዳዮች አያልፍም፡፡ እንድም ወልደው ለእናቶቻቸው እየሰጡ አረብ እገር ሄደዋል፡ አልያን
በኤችአይቪ አልቀዋል፡፡ የመንደራችን እውነታ ነው ይሄ !! ደግሞ ሕፃናቱ የተመካከሩ ይመስል በየምክንያቱ ሲጣሱና ሲነታረኩ የሁሉም መሃላ አንድ ዓይነት፣ እናቴ ትሙት !” የሚል ነው፡፡

ልክ ከአራት ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት፣ ሁላቱ የመንደራችን እንጀራ ሻጮች ሙሉና ዝናሽ. ዱላ ቀረሽ ስድድብ ይጀምራሉ፡፡ በደንበኛ መቀማማት ነው የሚጣሱት፣

“ለማያውቅሽ ታጠኚ..ደግሞ ሙያ እንዳለው ሰው:: ማየት የተሳነው እንጀራ እየጠፈጠፍሽ.
እኩል ታወሪያለሽ…"

“ኤጅ እባከሽ…እኔ ሙሉ በወፍጮ ቤት ጥራጊ አይደለም ደንበኞቼን የማስተናግደው፣ ጥርት
ባለ ጤፍ ጥር…ት”

“ሂሂሂሂሂ መጣፈጡ ቀርቶ እጄን በሰቀቀኝ አሉ እትዬ አሰለፍ፣ ጥራቱ ቀርቶብሽ ቡሃቃሽን
በወር እንዴ እንኳን ባጠብሽው:: ሰዉን ሁሉ በሆድ ቁርጠት ጨረሽው” ትላለች ዝናሽ። የሙሉ
ደንበኛ ስለሆንኩ በዚህ ኣባባሏ ሆዴ ይጮሃል፣ ..ኡ... ወር ሙሉ የማይታጠብ ቡሃቓ እቺ
ስድድብ ደንበኛን ለማስከዳት ወሳኝ የቃላት ጦርነታቸው ናት፡፡

ልክ አምስት ሰዓት ሲሆን እማማ መጣፈጥና ስንቅነሽ ቡና ይጠራራሉ፡፡ ወደ ስድስት ሰዓት
ጀሚላ የቅንድቧን ኩል ጆሮና ጆሯዋ ጥግ ድረስ ተኩሳ በስልኳ እያወራች ወደላይ ትጣደፋለት፡
ሃቢቢ መጣሁ ወጥቻለሁ” እያለች፡፡ ኣፍንጫ የሚሰነፍጥ ሽቶዋ መንደሩን ያውደዋል፡፡ ጀሚላ ስታልፍ ጥርኝ ያለፈች ነው የሚመስለው:: የታከከችው ነገር ሁሉ ሽቶ ሽቶ፣ መቼም ሃቢቢዩ
የአፍንጫ መሸፈኛ ማስካ ያደረገ ሰው መሆን አለበት፡፡

ይሄን ሁሉ ሳይ ይከፋኛል። ብቸኝነት ይጫጫነኛል፡፡ ከወንዙ ተገንጥሎ ኩሬ ውስጥ እንደተኳታሪ ውሃ እዛው የምሻግት አልያም የተቀመጥኩበት በትነት የማልቅ ነገር መስሎ ነው የሚሰማኝ

ይሄን…የተረገመ እሁድ ወደዛ አልቆ ሥራዩ በገባሁ ! ለነገሩ ከእሁድ ይሻላል ብዬ እንጂ ሥራዬም ሠልችቶኛል፡፡ የባንክ ሠራተኛ ነኝ፡፡ ብዙ ሰዎች የባንክ ሠራተኛ መሆኔን እንደትልቅ እና አስደሳች ሥራ እድርገው ሲያወሩ ይገርመኛል፡፡ ለእኔ የባንክ ሥራ በምድር ላይ ካሉ አስከፊ ሥራዎች
ሁሉ አስከፊው ይመስለኛል፡፡ እንደውም ለሰው ሳይሆን ለሮቦቶች የሚስማማ ሥራ ቢኖር የባንክ ሥራ ነው እያልኩ አስባለሁ፡፡

አንድ አይነት ቅርፅ ያላቸው ብር ዮሚባሉ መርገምቶችን መቁጠር፡፡ አራት ዓመት ሙሉ
ቆጠርኳቸው..ኤጭ ድፍን አገር የሚራኮትለት ብር ለእኔ አንዳች ቆሻሻ ነገር መስሎ ነው
የሚታየኝ፡፡ ብር ይሸታል፡፡ ካላመናችሁ ወደ ኣፍንጫችሁ አስጠጉና ሞክሩት፡፡ እንደ ብር
መጥፎ ሽታ ያለው ነገር ምን አለ ? ለነገሩ የዘንድሮ ብር ላሸትተውም ብትሉ አፍንጫችሁ ላይ
ላይደርሰ ያልቃል ሰላቢ ነገር ነው::

ምስላቸው ብር ኖት ላይ ያሉት ሰዎች ከመኖር ብዛት የቢሮ ባልደረባ መስለውኛል፡፡ ደግሞ
አልወዳቸውም፡፡ ለምሳሌ አንድ ብር ኖት ላይ ምስሉ ያላውን ሰው መንገድ ላይ ባገኘው ገላምምጬው የማልፍ ይመስለኛል፡፡ አስር ብር ላይ ያለችው ሴትማ ስታበሳጨኝ፤
የሆነች ነገረኛ ነገር፡፡ በደንብ አይታችኋታል? ስፌት የምትሰፋ ትመስላለት እንጂ ጆሮዋን አቁማ
ነገር የምትሰማ እኮ ነው የምትመስለው፡፡ ደግሞ ፊቷ ላይ የአሽሙር ፈገግታ አለ፡፡ ከሁሉም
ከሁሉም የሚያበሳጨኝ ነገር ደግሞ ከንፈሯ ! የከንፈሯ ማማር የሰብለን ከንፈር እኮ ነው
የሚመስለው !! ከነስፌቷ እጎኗ ላለው አንበሳ ነበር መስጠት !!

ባንክ ቤት ስትሰሩ ስጋችሁ በሱፍ ተጀቡኖ ወሩ መጨረሻ ላይ የሱፍ ቆሎ መግዣ እንኳን የማይተርፋችሁ መናጢ ደሃ መሆናችሁን ብዙ ሰው አይረዳም፡፡ ቁጥርና ስጋት ባንድ ላይ
የሚኖሩት ባንክ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ብር ስትቆጥሩ በስጋት ነው:: አንዱን የብር ኖት ሌላ የተደራረበ እየመሰላችሁ በፍትጊያ ፍዳውን ታበሱታላችሁ፡፡ በዛ ላይ ሰው ለብር ያለውን ሟችነት፣ ስግብግብነት፣ ደግነትም ጭምር ትታዘባላችሁ፡፡
👍321👎1👏1🎉1
#ፈንዲሻ_ሲቆሎት_ድምፅ #ሲሰሉት_ድምፅ


#በአሌክስ_አብርሃም


የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት አድርገን እንደተቀመጥን፤ ፕሮግራሙ ቶሎ እንዲያበቃ ሌላ የህሊና ጸሎት ጀመርኩ፡፡ ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን ለማከበር የክፍለ ከተማው የሴቶች ሊግ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ተገኝቻለሁ፡፡

ሊጉ በመሥሪያ ቤታችን በኩል ግዳጅ የተቀላቀለበት ጥሪ አቅርቦልን አለቃዬ ሂድ !" ስላለኝ
የቀበሌው አዳራሽ ውስጥ ተገኝቻለሁ። ያውም ቅዳሜን በሚያክል ቀን ከሰዓት!! ሰኔና ሰኞ
ገጥሞብኝ፡፡

አሁን ደግሞ የከፍለ ከተማችን የሕፃናትና ሴቶች ፑል ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ደርባቤ በላቸው
እንስራውን ሰብሮ ወሰዳት ልጅቱን የሚል ምርጥ ግጥም ያቀርቡልናል…" አለ ጉጉት የመሰለው መድረክ አስተዋዋቂ፡፡ አፉ ላይ የደቀነውን ማይክሮፎን ድምፅ ማጉላቱን የተጠራጠረ ይመስል በጣም እየጮኸ ነው የሚናገረው::

ቀጠለ "ወ/ሮ ደርባቤ ለክፍለ ከተማችን፣ ብሎም ለከተማችን፣ ብሎም ለኢትዮጵያ ሴቶች፣
ብሎም ለአፍሪካ ሴቶች ታላቅ ምሳሌ የሚሆኑ የዘርፈ ብዙ ሙያዎች፣ ተሰጥኦዎች፣ ትምህርቶች፣ስልጣኖች ባለቤት ናቸው” አለና፣ “…እስቲ ወ/ሮ ደርባቢን ወደ መድረክ…”

...ቿ..ቿ...ቿ..

ጥልፍ ቀሚስ የለበሱትና አንዳንድ ልማታዊ ዝግጅቶች ላይ ልማታዊ ግጥም በማቅረብ የሚታወቁት
ወ/ሮ ደርባቤ መድረክ ላይ ቆመው በፈገግታ ለሕዝቡ ጎንበስ ቀና እያሉ ምስጋና ይሁን ሰላምታ
ያለየለት ግማሽ ስግደት አቀረቡ፡፡ ግጥሙን ሊያቀርቡ ነው ብለን ፀጥ ስንል አስተዋዋቂው
ማዋደዱን ቀጠለ፣ “….ብታምኑም ባታምኑም ወ/ሮ ደርባቤ ይሄን ዝግጅት አስመልከቶ ግጥም
እንድትፅፍልን የነገርናት (አንች አላት) ትላንት ዘጠኝ ሰዓት ነው፡፡ ይገርማችኋል ሌሊቱን ስትፅፍ
አድራ ጧት ስደውልላት በስልክ ግጥሙን አነበበችልኝ…'ወይ መባረክ' ነው ያልኩት።( በሕዝብ
ስልክ ስምንት ገፅ ግጥም እያነበቡ አላየንም ባርኮት)፡፡

“...የግጥሙን ጥልቀት እና ውበት ራሳችሁ ታዘቡት እስቲ ለዚህች ብርቱ ሴት ሞቅ ያላ ጭብጨባ…" ብሎ ጭብጨባውን ራሱ ጀመረው፡፡ ማይኩን በሌላኛው እጁ ሲጠፈጥፈው አዳራሹ ጓጓጓ.. በሚል ልጆሮ የሚቀፍ እስቅያሚ ድምፅ ተሞላ፡፡ ከታዳሚው የተንቦጫረቀ ደካማ ጭብጨባ ጋር ተዳምሮ ጓጓታው በቀላል የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች የታጀበ የከባድ መሳሪያ ድምፅ ነበር የሚመስለው፡፡

ብዙው ታዳሚ በየእጁ ፈንዲሻ እና ለስላሳ ይዞ ስለነበረ ማጨብጨብ አልቻለም እንጂ በጭብጨባማ የእኛን ኮፍለ ከተማ ሴቶች ሊግ ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች ማን ብሏቸው::በተለይ እጃቸው ባዶ ሲሆን የሚያጨበጭቡት ጭብጨባ ቢሾፍቱ ይሰማል፡፡ እጃቸው ባዶ ሲሆን ለዜና ያጨበጭባሉ፣ ለሪፖርት ያጨበጭባሉ፣ የቀበሌው ሊቀመንበር ሲያስነጥሱ ሁሉ
ያጨበጭባሉ፣ እጃቸው ሞላ ካለች ግን ጠቅላይ ሚንስትራችን ቢዘፍኑም አያጨበጭቡም
እንዳንዴ ታዲያ ጭብጨባዎች ሲቀንሱ ኢኮኖሚያችን ያደገ ይመስለኛል፡፡

ቀጠለ አስተዋዋቂው (ወ..ይ ዛሬ) "ወ/ሮ ደርባቤ.ገጣሚ ብቻ አይደሉም፤ የታሪክ ተመራማሪም
ናቸው፡፡ (ወ/ሮ ደርባቤ ቆመው በቁማቸው ገድላቸው ሲለፈፍ በፈገግታ ያዳምጣሉ )..ከፍተኛ
አድናቆት ያተረፈውንና የከፍላ ከተማችን የእድገት ማራቶን ሩጫ ከዘመነ ደርግ ውድቀት ቀኋላ' የሚለውን መጽሐፍ ጨምሮ አራት የግጥም መጻሕፍትን አሳትመዋል፤ ይሄን ያህል
ካልኩ እንዳላሰለቻችሁ ወደ ወ/ሮ ደርሳቤ ልምራችሁ...” ብሎ ማይኩን በአክብሮት ለሴትዬዋ
አቀበላት፡፡ (እፎይ! አንድ አዛ ለቀቅ ይላሱ እማማ ሩቅያ ሲተርቱ)

..ማይኩን ተቀብላ ጓ...ጓ አደረገችና (የፈረደበት ማይክ ተጠፍጥፎም፣ ያወሩትን ሁሉ ተቀብሎ አጉልቶም እሳዘነኝ)፡፡ እ..እኔ እንኳን የተባለውን ያህል ነኝ ብዬ አላምንም.፣ ምከንያቱም እንደ እኔ ዕድሉን ቢያገኙ እንኳን ኢትዮጵያን ዓለምን ጉድ የሚያስብሉ ሴቶች ከእናንተ መሀል አሉ ብዬ ስለማምን ነው…" አለች ወይዘሮ ደርባቤ፡፡

ጭብጨባ…! ቿቿቿቿቿቿቿቿቿ (ፈንዲሻው አለቀ ባአንዴ ጭብጨባው ደመቀኮ)
ከጎኔ የተቀመጠች ሴት “እውነት ነው" ብላ ጮኸት፡፡ (ዓለምን 'ጉድ' ከሚያስብሉት ሴቶች
መሐል እንዷ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ዞር ብዬ ሳያት በግራ እጇ ሞባይል ስልኳን፣ በቀኟ፣ መዳፏ
እስኪወጣጠር የዘገነችውን ፈንዲሻ ይዛ በስሜት ወደ መድረኩ እያየች ቁጭ ብድግ ትላለች፡፡
..ከፈንዲሻው ኮርሽም አደረገችለት፡፡)

ሴትዮዋ ግጥሟን ከማቅረቧ በፊት ሰላሳ ደቂቓ አወራች፡፡…እንዴት የወንዶችን ተፅዕኖ ተቋቁማ ታላቅ ገጣሚ' ለመሆን እንደበቃች፣ ሴቶች የርሷን ፈለግ ይዘው እንዲከተሏት፣(ብትወዱስ እኔን ምስሉ ዳርዳርታ)ይሄን ሁሉ አወራችና “እንዳላሰለቻትሁ” በማለት ወደ ግጥሟ ተሸጋገረች
(ገና ድሮ የሰለቸንውን !?)

ወደ መድረክ ስትወጣ መነፅሯኝ ቦታዋ ላይ ረስታው ስለነበር፣ " አቀብሉኝ”ስትሳቸው የእጅ ቦርሳዋን አራት ሰዎች ግራና ቀኝ ይዘው (ማሸርገዳቸው ስላበሳጨኝ የጨመርኩት ነው) አቀበሏት፡፡ቦርሳዋ ውስጥ አስር ደቂቃ ፈልጋ መነፅሯን ቤቷ መርሳቷን አረጋገጠች፡፡..እናም ወደ ብርሃኑ ቀርባ ግጥሟን ማንበብ ጀመረች፡፡

እንስራውን ሰብሮ ወሰዳት ልጅቱን(ርዕስ)
አረ አያ ደገፋው አንተ ትልቀ ሰው፣
አንዲት ፍሬዋን ልጅ ማስቸገርህን ተው!
ውሃ ልትቀዳ ወንዝ ስትሄድ፡
ቁመሽ አውሪኝ አልካት በግድ፣
ይሄ እልበቃ ብሎህ ሰው ጭር ሲልልህ
ሕፃኗን ደፈርካት እግዜር ይይልህ (ውይ ወንዶች አለች ከጎኔ ያለችዋ ባለ ፈንዲሻ)
ደሟን እያዘራች እቤቷ ስትደርስ፣
እንስራ ሰበርሽ ብለው ጎረፉት አያድርስ.
ደሞ በሌላ ቀን እንደገና አድብተህ..፣
አሁንም ደፈርካት አንተ ምን ዓይነት ሰው ነህ። ('በስማም ጭካኔ.ሌላዋ ሴት)

አዳራሹ ፀጥ ብሎ 'ግጥሙን' እያዳመጥን ድንገት ጎኔ ያለችው ሴት ጎርደምደምደም…ከሻሸሽ…
ስታደርግ ደንግጬ ዞሬ ተመለከትኳት፡፡ ተመስገን ፈንዲሻ እየበላች ነው፡፡…እኔማ በግጥሙ
ተመስጣ በስህተት ስልኳን ቆረጣጠመቻት ብዬ ነበር፡፡
ግጥሙ ለድፍን ሀያ ሰባት ደቂቃ ተነበበ፡፡ የግጥሙ የመጨረሻ ስንኞች

ፊስቱላ ተይዛ ስትንከራተት፣
ጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኛ አግኝታታ!
እዲሳባ በመኪና አመጣቻት.
መንግሥታችን በሠራው ዘመናዊ አስፓልት…?

አመሰግናለሁ !!

ቿቿቿቿቿቿቿቿቿ….(ታዳሚው ፈንዲሻውን ጨርሶ ነበር)

ለመውጣት ሳቆበቁብ አስተዋዋቂው እንዲህ አለ….

“ለሴቶች ቀን ያልሆነ ግጥም ለመቼ ይሆናል' በማለት ወይዘሪት ዘቢደር የወጣቶች ሊግ አትተባባሪ
ለግንቦት ሃያ አንብባው የተደነቀላትን 'ታታሪዋ ሥራ ፈጣሪ' የሚለውን ግጥምን ላቅርብ
ብላለችና እስቲ ወደ መድረክ…”

ተነስቼ ወጣሁ፡፡ ወደ ቤቴ ስሄድ ከኋላዬ የአስተዋዋቂው ድምፅ ይሰማኛል፡፡

"ወጣት ዘቢደር የእንስቷ ጣጣ የሚል በቅርቡ በታተመ የግጥም መድብሏ ከፍተኛ እውቅና
ያተረፈች ብርቱ ሴት ስትሆን...” እያለ ቀጠለ፡፡

ይሄ ቀበሌ ነዋሪው ሳይሰማ ማተሚያ ቤት ከፈተ እንዴ?.. እንዴት ነው ይሄ መድብል ማሳተም እንዲህ የቀሰለው ጎበዝ? ?!

አለቀ
👍24😁12👎1