#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
...ጥላዬ ፊቱ ጥላሸት ለብሷል።
አብርሃ፣ የጥላዬን ፊት መለዋወጥና ለምንም ነገር ፍላጎት ማጣት አስተዋለና ስሜቱ ከየት እንደመጣ ተመራመረ። ኸቤቱ የወጣ..ናፍቆት ይሆናል አለ፤ ለራሱ።
በፋሲል ቤተመንግሥት በስተግራ በኩል ወደ ላይ ሲወጡ፣
ሰዎች ከላይ ወደእነሱ አቅጣጫ ሲመጡ፣ ወንዶች ቆባቸውን፣ ሴቶች ክንብንባቸውን እያወረዱ እጅ እየነሱ ሲያልፉ፣ ጥላዬ እርስ በርሳቸው ሰላምታ የሚሰጣጡ መስሎታል። ጥቂት እንደተራመዱ፣ አብርሃ የተማሪ
ቆቡን አውልቆ እጅ ሲነሳ አየው።
መንገዱ ላይ ካለሁለቱ በስተቀር
ማንም የለም።
ጥላዬ፣ “ማነን ነው እጅ ምትነሳ? ኸኔና ኻንተ በቀር ማነም የለ
በምንገዱ” ሲል ጠየቀው።
“ማነነም! ሰዎቹስ እጅ ሲነሱ አላየህም እንዴ? እኼን ምንገድ አየህ?”አለው፣ አገጩን ወደፊት ቀደም አድርጎ፣ ሰፊውን የእግር መንገድ እያሳየው። “የንጉሡ መኸጃ ነው። እሳቸው ሲወጡ ማንም በዝኽ አያልፍም። አየኸው ያን ደጋን የመሰለ የደንጊያ ግንብ መተላለፊያ?ንጉሡ ወደ ራስጌ
አጤ ፋሲል ያሠሩት የራሶቹ መኖሪያ ነው...ኸዝኸ ከፍ ብሎ ነው ያለ... ወይ ደሞ ወደ ሌላ ቦታ ሚሄዱበት ነው።እሳቸው ባይኖሩም ቆብ አውልቆ እጅ መንሳት ደንብ ነው። ቦታው
እስተስሙ ቆብ አስጥል ነው።”
“እንደቤተክሲያን ነው በለኛ!” አለ ጥላዬ፣ ፈገግ ብሎ።
“ንጉሥ እኮ ፊታቸው ተሸፍኖ ነው ሚሄዱ። አሁን ታቦት ትኩር
ብለህ ታያለህ? አታይም! እሳቸውንም ፊታቸውን ጨርሶ አታይም።
አብረዋቸው ሚኸዱት ስንኳ ኸጎናቸው ሲራመዱ መሬት መሬቱን
እያዩ ነው። ደሞም አለልህ ሊቀመኳሱ... ንጉሥ አሳሳች ሚባለው። ልክ
እንደሳቸው ሁኖ ይወጣል። ንጉሡ ኸቤት ተቀምጠው እሱ እሳቸውን
መስሎ ይወጣል። ያን ግዝየ ሰዉ ንጉሡ መጡ ብሎ ይሰግዳል።
እንዲህ ዋዛ መስሎሀል! ወሬ ስሰማ እቴጌዎቹ ደሞ ሲወጡ ምንግዝየም
በጃንደረሳ እየተጠበቁ ነው።”
“ጃንደረባ ደሞ ምንድርነው? ስለምንስ ይጠበቃሉ?”
“ጃንደረባማ ... እቴጌዋን ሚጠብቀው... ስልብ ነው። ሚጠብቀው
ያው እቴጌዋ ኸሌላ እንዳይኸዱ ነዋ!” አለ፣ ሳቅ ብሎ።
ጥላዬ ለራሱ፣ ወለቴ
ጉድ ፈላባታ አለና ለአብርሃ፣ “እኼ
ቤተመንግሥት ሚባል ነገር ብዙ ጣጣ አለው” አለው።
“ወጉ እንግዲህ እንደዝኸ ነው። እኼ ምታየው... ኸቤተመንግሥቱ
አጠገብ ያለው ሁሉ ደሞ የባለርስቶቹ ምንደር ነው።”
ጥላዬ ዞር ብሎም አልተመለከተ።
አብርሃ፣ ጥላዬ ለሚያየው ነገር ሁሉ እምብዛም ትኩረትና ፍላጎት
የሚያሳይ አልመስል አለው። ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገባው።
“ትመለስ ይሆን?” አለው።
“እረገኝ ስለምን?”
“እንግዲያማ ተጫወት። እኔኮ ይህ የመጣሁት አገር ላላምድህ ብየ ነው። እኼ አሁን ምንኸድበት ዘመዴ መልካም ሰው ነው። አንዱም እሱን ብየ ነው እጐንደር የመጣሁት።”
አልፎ አልፎ እየተጫወቱ ቁልቁል ወርደው ረጅም መንገድ ተጓዙ።
ጥላዬ ከቦት የነበረው የመጫጫን ድባብ እየለቀቀው መጣ። ያየውን
ሁሉ እያደነቀና እየወደደ የሆዱን ባር ባር ማለት ረሳ።
“ኸዝኸ ወረድ ስትል የዕጨጌው ሰፈር አለ” አለው አብርሃ
ሊያጫውተው ፈልጎ። “ሸማኔውም ወዲያ ነው። ማዶ ደሞ የባለእጌዎች ምንደር አለ። ለብቻቸው ነው ሚኖሩ። መቸም ባለእጌዎቹ ግንበኞች
አናጢዎች፣ ሸማኔዎች፣ ቀጥቃጮችና ሸክላ ሠሪዎች ናቸው ቤተመንግሥትን ሚያስጌጡ እነሱ ማዶሉ? እስላምጌ ደሞ በዝያ ስትዘቀዘቅ አለልህ። የስላሞቹ የነጋዴዎቹ ሰፈር ነው። ብዙ ሰው ይኖራል ኸዛ። በቅሎና ፈረስ ገባያውም ኸዛው ነው።”
ድንጋይጌ ሲደርሱ፣ “እኼ ገባያው ነው። ቅዳሜ ነው ሚቆም። ዛሬ
ጭር ቢል እንዲህ እንዳይመስልህ። ነጋዴውም... ሁሉም ነው ሚወጣ። ነገ ማልደን እንመጣለን” አለው።
ጥላዬ መልስ አልሰጠውም። ወለተጊዮርጊስ ከንጉሥ ጋር ግብር
በምትቀመጥበት ቀን መውጣት አልፈለገም። ከቤተክርስቲያኑ ግቢ እንደማይወጣ ለራሱ አስገንዝቦ ዝም አለ።
አብርሃ ዘመድ ቤት ገብተው መልካም መስተንግዶ ተደረገላቸው።ጥላዬ አልፎ አልፎ የያዘውን ጠላ ፉት ከማለትና ከአብርሃ ዘመድ የሚቀርቡለትን አንዳንድ ጥያቄዎች ከመመለስ በስተቀር አብርሃና ዘመዱ በትግርኛ ስለሚያወሩ በዝምታ ተውጦ፣ ጠላውን እየተጎነጨ፣
አንዳንዴም እየሰለቸው ቆይቶ፣ ከሰዐት በኋላ፣ ተነሥተው ወጡ።
ደብረብርሃን ሥላሤ ሲደርሱ ተለያዩ። ጥላዬ ጠዋት ተቀምጦበት የነበረው ዋንዛ ዛፍ ሥር ተቀምጦ ያየውን ሁሉ አሰበ። ጐንደር ልዩ ቦታ፣ ከግምቱ በላይ ሆነችበት፤ ወደዳት። የገባ ዕለት ዐዲስ ሕይወት ልትሰጠው የገባችለትን ቃል ኪዳን አጸናችለት። ድንገት የፈሰሰ
ሐሞቱ ነፍስ ዘራ። የአለቃ ሔኖክ ምሽት እሑድ ይመለሳሉ ብለው
ነግረውናል። አብርሃ ደሞ ሰኞ ጠዋት እንኸዳለን ብሎኛል። ብቻ አንዴ እሳቸውን ላግኛቸው፣ ኸዝያ ወዲያ ማደርገውን እኔ አውቃለሁ አለ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጐንደርና ቋራ ምንና ምን
ወለተጊዮርጊስ፣ አፄ ፋሲለደስ ቅጥር ግቢ ስትገባ፣ አያቷ
እርምጃቸውን ገታ አድርገው፣ “እኼ አጤ ፋሲለደስ ያስገነቡት አሁን ጃንሆይ ሚኖሩበት ነው። እንግዲህ አንቺም ኸዝኸ ነው ምትኖሪው”አሏት።
“ኸዝኸ?” ብላ ዐይኖቿ እስከመጨረሻው ተከፈቱ።
የባለሦስት ደርቡ ህንጻ ግዝፈት አስደነቃት። ሰማይ ጠቀስ
መሰላት። በግንቡ ማዕዘኖች የተሠሩትን የእንቁላል ቅርፅ ያላቸውን ግንቦች አይታ ተደነቀች። ሰገነቱ ላይ ያለው ሰቀሰቅ ለመተኮሻ ተብሎ እንደተሰራ መገመት አቃታት። በእንቁላል ግንቦቹ መሃል ወደ ሰገነቱ
የሚወስደውን የዕንጨት ደረጃ ተመልክታ ምን እንደሆነ አልገባ አላት።
ዮልያና ቀጠሉና፣ “ጃንሆይ ኸዚያ ኸሰገነቱ ቁመው ሁሉን ይቃኛሉ፤
አንዳንዴም ኸዚያው ላይ ሁነው አዋጅ ይነግራሉ። አንቺም እንግዲህ ኸዚያ ላይ ምትቆሚበት ቀን ሩቅ አዶለም” አሏት፣ ሳቅ ብለው።
ዝም አለች። ያን መሰል ነገር አይታ ባለማወቋ፣ ከመንገድ ድካም
ጋር ተደምሮ አእምሮዋ ያየችውን ሁሉ መመዝገብ አልሆንለት አለው።
የግንቡ ግዝፈት፣ የንጉሥ ሚስትነት ልኩ ምን ድረስ እንደሆነ
ገለፀላት። ስለዚህ ዓለም ያላትን ግንዛቤ ሁሉ ግልብጥብጡን አወጣባት።ስለራሷ የነበራትን ግምት አዛባባት። “ንግሥት እሌኒን አረግሻለሁ”እየተባለች፣ የአፄ ሚናስ ደም በደምስሯ እንደሚንቆረቆር እየተነገራትና
በእንክብካቤ ያደገችው ልጅ ለእዚያ ለምታየው ግርማ ሞገስ ሁሌ የማትመጥን መስሎ ተሰማት።
ከቋራ መጥታ ያን መሰል ኑሮ ውስጥ መግባት ምን ማለት እንደሆን ማወቅ ተሳናት። እኛ እናት አባቷ ቤት መደብ ላይ ተኝተው የነበሩት ሰው ንጉሥ ናቸው ሲባል ድንገት እንደ ጨረቃ የራቁባትን ያህል ዛሬ ደግሞ የሚኖሩበትን ቤት ስታይና ልትኖር እንደታጨችበት ጭምር
ስታስብ፣ የእሷም ሕይወት ምን መልክ ሊይዝ እንደሚችል ለመጀመሪያ ጊዜ ተገነዘበች።
ጐንደር ታላቅ የሕይወት ግብዣ እንዳቀረበችላት ታወቃት። ሁሉም ካሰበችው፣ ከገመተችውና ካለመችው በላይ ሆነባት::
ፍርሐት ፍርሐት አላት።አካባቢዋን እንደ ዋዛ ታልፍ የነበረችው ወለተጊዮርጊስ፣ ቋራ እንደዚያ ቆማ የምታደንቀው ሰው ሰራሽ ነገር ባለማየቷ ለመጀመሪያ
ጊዜ ያየችውን ውበት አደነቀች። ጐንደርና ቋራ ምንና ምን አለች።
ያየችው ሁሉ የሰው ልጅ የእጅ ጥበብ ውጤት መሆኑን ተጠራጠረች።ያንን የመሰለ ውበት የቀረጹትን ሰዎችና እጆች ማየት ተመኘች።

👍10❤1