አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_ሰባት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ባህራም
ከቅርብ


ማክሰኞ ነበር አስታውሳለሁ፡፡ ከምሳ በኋላ Le Monde ጋዜጣዬን ገዝቼ ካፌ ዶርቢቴል ገብቼ እንደ ልማዴ petit creme አዝዤ ካርታ የሚጫወቱት ሀበሾች አጠገብ ቁጭ አልኩ። ትንሽ ቆይቶ ባህራም መጣ፡፡ ሳየው የተለወጠ መሰለኝ፡፡ ልማዱ በፍጥነት እርምጃው ከተፍ ብሎ ሲያበቃ፣ ሀበሾቹን «እናትክን! ሀለላሴ ሙት! Je veux jouer
aux cartes.» («ካርታ አጫውቱኝ») ብሎ ቁጭ ማለት ነበር፡፡ ዛሬ ግን በቀስታ እርምጃ መጣ። እንደ ድሮው አልቀለደም፡፡ እንደ አጋጣሚ ለካርታ ጨዋታው አንድ ሰው ጎድሏቸው ስለነበረ «ባህራም! ና ካርታ እንጫወት አሉት

«ካርታ ጨዋታ አላሰኘኝም» አለና ዝም ብሎ ቁጭ አለ።

የተበሳጨ ይመስላል
«ምን ሆነሀል?» አለው ሉልሰገድ
«በፈተና ወደቅኩ» አለ
ሁሉም የሚሉትን አጡ
እንግዲህ በፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲዎች ደምብ፣ አንድ ተማሪ የሰኔ ወር ፈተናውን የወደቀ እንደሆነ በእረፍት ጊዜው ሲያጠና
ይከርምና፣ በጥቅምት (ትምህርት ቤት ሲከፈት) እንደገና
ይፈተናል። ስለዚህ ተመስገን
«አይዞህ በጥቅምት ፈተና ታልፋለህ» አለው ባህራም አልተፅናናም፡፡ ሁሉም ዝም አሉ። ካርታ ጨዋታቸውን ቀጠሉ።

ባህራም «ዘላለም ካርታ ጨዋታ ምን ያረጋል? እንውጣ ትንሽ
እንንሽርሽር» አለ። ማንም መልስ አልሰጠውም፡፡አብረውት
መውጣት ፈርተዋል። ካርታ ጨዋታቸውን ቀጠሉ ለጨዋታው
ብቻ ሳይሆን ከባህራም ብስጭት ለማምለጥም ጭምር። ገባው::
ተነስቶ ብቻውን ወጣ፡፡ ተከትዬው ወጣሁ። ወደ መናፈሻው በኩል
እያመለከትኩ
«ወደዚያ እንሂድ?» አልኩት፡፡ መልስ ሳይሰጠኝ ወደዚያው
አመራ። ትንሽ እንደተራመድን
«ያውና ተካ። ወደኛ በኩል ይመጣል» አለኝ «አደራህን አብሮን እንዳይመጣ። ዛሬ እሱ ሁለት ቃላት ቢያናግረኝ አብዳለሁ»
«አትስጋ» አልኩት
ተካ አቆመንና በፈረንሳይኛ
«ከየት ነው የምትመጡት?» አለን
«አሁን ከየትም ብንመጣ ደንታ የለህ። ለምንድነው የምትጠ
ይቀን?» አልኩት በአማርኛ
«ከዶርቢቴል ነው የምትመጡት?» አለኝ ባማርኛ
«አዎን» አልኩት ባህራም እጁን ኪሱ ከቶ ወደዚያ ይመለከታል
«ወዴት ነው የምትሄዱት?» አለኝ ተካ
«ወዴትም፡፡ ምን ያረግልሀል?»
«ወደ ሲቴ ነው የምትሄዱት?»
«ምነው? ከኛ ጋር ሲቴ መሄድ አማረህ?»
«አይ! እኔ ለራሴ ከዛ መምጣቴ ነው። ቡና አምሮኛል»
«እንግዲያው ሂድና ቡናህን ጠጣ»
«ጋዜጣህን አሁን አታነበው እንደሆነ ስጠኝ»
ጋዜጣዬን ሰጠሁትና መንገዳችንን ልንቀጥል ስንል
«ይሄ አቃጣሪ ገንዘብ እንዳያጭበረብርህ ተጠንቀቅ» አለኝ
«ሂድ ቡናህን ጠጣ» እልኩት። ሄደ
እኔና ባህራም አንድ ቃል ሳንነጋገር መናፈሻው ደረስን፡፡ ዛፎች
ጥላ ስር አንድ አግድም ወምበር ላይ ቁጭ አልን ፈተና መውደቅ የተለመደ ነገር ነው:: በጥቅምት ታልፋለህ» አልኩት
በተገማመደ ፈረንሳይኛው፣ በወፍራም ልዝብ ድምፁ መናገር
ጀመረ መውደቄ አይደለም የሚያበሳጨኝ፣ አወዳደቄ ነው።
ትምህርቱን በደምብ ይዤዋለሁ። በምን እንደጣሉኝ ታውቃለህ?
በፈረንሳይኛዬ ጉድለት: አያስቅህም? ፈተናውን የወደቅኩት እኔ ራሴ ባልሆን ያስቀኝ ነበር
«እኔንና ፈረንሳዮቹን የክፍሌን ልጆች አስተያየን እስቲ፡፡
ትምህርቱን እኩል እናጠናቀው። ፈተና እንግባና ጥያቄው ይሰጠን።
መልሱን እኔም እነሱም እኩል እንወቀው። እነሱ ምን ያረጋሉ?
መልሱን በፍጥነት ይፅፋሉ፡ አሰካኩንና አገባቡን ያማርጣሉ፡፡
ጥቃቅኗን ነገር ጭምር ያስገቧታል፡፡ ሀያ ሀያ አንድ ገፅ ፅፈው ይወጣሉ፡፡ ያልፋሉ፡፡ እኔም መልሱን ከነሱ እኩል አውቀዋለሁ፡፡
ታድያ ፈረንሳይኛው ከየት ይምጣ? ከሱ ጋር ስታገል የጊዜዬን
ግማሽ አጠፋለሁ:: ለዚያውም አምጩ የማመጣው ፈረንሳይኛ አንካሳ ሽባ ስለሆነ፣ በደምብ የማውቀውን መልስ ልክ እንደማላውቀውና
በግምት ወይም በነሲብ እንዳገኘሁት ያስመስልብኛል። ዘጠኝ አስር ገፅ ፅፌ እወጣለሁ፣ በመጥፎ ፈረንሳይኛ፡፡ ትምህርቱን እያወቅኩት ፈተናውን እወድቃለሁ

«ፈረንሳዮች ደሞ ታውቃቸዋለህ። በቋንቋቸው የመጣ በጣም
አንጎለ ጠባብ ናቸው። ለምሳሌ አስተውለህ እንደሆነ በፍጥነትና ያለ ስህተት ያነጋገርካቸው እንደሆነ ያከብሩሀል፣ «Intelligentይሉሀል።
እየተንተባተብክ ያነጋገርካቸው እንደሆነ ግን ምንም ቁም ነገር
ብትናገር መሃይም ነህ ማለት ነው። በቋንቋህ ብታናግራቸው እንደ ቂል አፋቸውን ከፍተው እንደሚቀሩና፣ የነሱም ቋንቋ ላንተ ያንን ያህል እንግዳ እንደነበረ፣ የሚሉት ሁሉ «ዠቨሹቪ» ይመስልህ እንደነበረ፣ በስንት ልፋት በመጠኑ ልታውቀው እንደቻልክ፣ በቋንቋቸው መንተባተብ ስለቻልክም ሊያመሰግኑህ እንጂ ሊንቁህ
እንደማይገባቸው፣ ይህን ለመገመት ያህል ሰፊ አንጎል የላቸውም።ተራውስ ሰው እንዲህ ቢሆን አልፈርድበትም፡፡ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮቹ እንዲህ ሲሆኑ ግን በጭራሽ አይገባኝም፡፡ እንግዲያውኑ የነሱ ትምህርት የታል? እቺን ያህል ቀላል ነገር ማመዛዘን ካልቻሉ አንጎላቸውስ ትምህርታቸውስ ምን ትርጉም ይኖረዋል?

«እማናውቀው አገር መጥተን፣ በማናውቀው ቋንቋ
የማናውቀውን ህዝብ ባህልና ታሪክ ለመማር ስንታገል፣ ለምን
አስተያየት አያደርጉልንም?»

“ምን አይነት አስተያየት ሊያደርጉልን ይችላሉ?» አልኩት

«ፈረንሳይኛችን ትንሽ የተጣመመ እንደሆነ፣ የቋንቋውን መጣመም ችላ ብለው የፍሬ ነገሩን እዚያ መገኘት ለምን አያስቡልንም? አገራችን ስንመለስ በራሳችን ቋንቋ ነው የምንmቅመው፣ ስለዚህ ፈረንሳይኛውን አንደነሱ ቻልነው በመጠኑ ተንተባተብንበትስ ምን ያህል ልዩነት ያመጣል? እንግዳ ስንሆን፣ ፈረንሳይኛውን በሀያ ሶስት፣ በሀያ አራት፣ በሀያ አምስት
አመታችን ስንጀምረው፣ እንዴት ከናታቸው ጡት ጋር ሲጠቡት
ካደጉ ሰዎች እኩል ካልሆነ ተብለን እንቀጣበታለን? ቅጣት መሆኑ
ይታይሀል? ፍሬ ነገሩን እንደማውቀው ግልፅ ሳለ፣ የተጠቀምኩበት ፈረንሳይኛ የተቀመመ ፈረንሳይኛ ባለመሆኑ ፈተናዬን ስወድቅ፣አንድ አመት ሙሉ የለፋሁበትን ስከለከል፣ ይሄ ቅጣት ነው እንጂ ምንድነው? ፍትህ የሌለው ቅጣት

«አንድ አመት ምን ያህል እንደሆነ ይገባሀል? አስበው፡፡ የዘጠኝ
የአስር አመት ልጆች ሳለን ክፍል በመድገም አንድ አመት ብናጠፉ
ምንም አይደለም፡፡ በህያ ስድስት፣ በሀያ ሰባት አመታችን አንድ
አመት ማጥፋት ግን ሌላ ነገር ነው:: ምክንያቱም እነዚህ አመታት
ከሀያ አምስት እስከ ሰላሳ አምስት ሰፈር ያሉት አመታት የሌሎቹን አመታት ሶስት አራት እጥፍ ዋጋ አላቸው። አሁን ነው ህይወታችንን ለመጨረሻ የምንቀርፀው:: አሁን ነው ያለ የሌለንን ለሀገራችን ልናበረክትላት የሚገባን። አሁን ነው የኑሮ ስራችንን የምንመርጥበት የምንጀምርበት ጊዜ። አሁን ነው የኑሮ ጓደኛችንን
የምንመርጥበት፣ ትዳራችንን የምንቆረቁርበት ጊዜ፡፡ አሁን ነው።
አሁን! አሁን! አሁን ነው ልጅነትም የማያታልለን፣ እርጅናም የማይ
ጫጫነን፡፡ አሁን ነው ፍሬ ለመስጠት ዋጋ ለማስገኘት የምንችለው» ረጋ ባለ ድምፅ

«አሁን ነው ፈረንሳዮች "ለምን ቋንቋችንን ከኛ እኩል
አልቻላችሁም?' ብለው ወርቅማ አመታችንን የሚያጠፉብን
👍175😁1