አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

...እንዲህ እንዳይመስሉሽ። ኸግር እስተራስሽ እያገላበጡ ነው ሚያዩሽ።ቄንጥ ሲያወጡ አይጣል ነው” ሲሉ መከሯት።

“እሚታዬ ልቤ ፈራ” አለቻቸው፣ እጆቿን እያፍተለተለች።

“ምን ሚያስፈራ ነገር አለ?” አሉ፣ ቆጣ ብለው። ለራሳቸው፣ እንደዛ
ቆፍጣና ምትመስለኝ ልዥ ምን ሆነች? ማታውቀው ቦታ ስለምትኸድ ነው? አሉና ለእሷ፣ “አብሬሽ ማዶል እንዴ ምመጣው? ንጉሥ የሆኑ እንደሁ ልዣችንን እንዳው ዝም ብለን ምንሰድ ይመስልሻል? ጐንደርንም ቢሆን አገላብጨ ነው ማውቃት። ጃንሆይ ሳይነግሡ በፊት... ነፍሳቸውን ይማርና ኸነእንኰዬ አባት ጋር ኑረናል። ጃንሆይ ኸነገሡ በኋላ አልኸድኹም እንጂ” አሏት።

“አብረሽኝ ምትመጪ ባትኾኚ ምን ይውጠኝ ኑሯል?” ብላ፣አንገታቸው ሥር ገብታ ሳይታሰብ ተንሰቀሰቀች። ውስጥ ውስጡን
ያስለቀሳት ግን ከጥላዬ መለያየቷ ነው።

“ደሞ ለክፉ ሆነ ለደግ ግዝየ ሚሆን ወልደልዑልን የመሰለ ወንድም አለሽ። ስንኳን ላንቺ ለእህቱ፣ አላየሽም እንዴ ላገር ሲተርፍ? አርከሌድስም አለ። ልዤ ነው ብዬ ማዶል ። አንቺም ብትሆኚ ታውቂያሽ እንዴት ብርቱና ታማኝ እንደሆነ። እንደ ኒቆላዎስስ ቢሆን... ጋሻና መከታ እንደሚሆንሽ አንቺም ታቂያለሽ” አሉ፡ ደረታቸውን መታ፣ አንገታቸውን ነቀነቅ አድርገው።

ምንጊዜም ቢሆን ስለሚወዱት ታናሽ ወንድማቸው ስለኒቆላዎስ
ሲያወሩ ደስ ይላቸዋል፤ ይኮሩበታል ። ቀጠለና፣ “አጎትሽ እሽቴም አለ። ደሞስ ያጎቶችሽ ልዦች ጌታ፣ አውሳቢዮስና፣ ነጮ አሉ ማዶል እንዴ? የወገን ጥላ አያሳጣኝ ማለት ነው” እያሉ እንባዋን በነጠላቸው ከፊቷ
ላይ ጠራረጉላት።

“ግና የቤተመንግሥት ወግ ኸየት አባቴ አውቄ?” አለች።

“አንቺ ደሞ ያልቸገረሽን። ወጉንስ እኼው እያስተማርሁ ማዶል
እንዴ? ሌላውን ደሞ ግዝየው ሲደርስ ትማሪያለሽ።”

“እሚታዬ፣ ቤተመንግሥት ልገባ?”

“ቤተመንግሥት ለመግባት ምን ያንስሻል? አጥንተ ጥሩ... ያውስ
የንጉሥ ዘር ማዶለሽ? አባትሽስ ቢሆኑ የደንብያው ባላባት የአቤቴ
ተክለሃይማኖት ልዥ ማዶለ? መልክስ ቢሆን ማን ደረሰብሽ? ቀይ ሰው መልክ አይፈጅም ይላሉ፤ አንቺ ፈጅተሻል። ቅላትሽ እኮ የኔና የናትሽ ነው። እንዳባትሽ ጠይም ብትሆኚ ኑሮኮ ምን የመሰለች ጠይም አሳ መሳይ ትሆኚ ነበር። ምግባርና ብሩህ አይምሮም አክሎልሻል።
ለዝህም እኮ ነው ጃንሆይ የመረጡሽ። እቴ ኸንግዲህ ማቄን ጨርቄን የለም፤ መኸድ ብቻ ነው።”

“ልጄ ዕድል ነው። ተሰጥቶሽ ነው። ደግ ሁኖልሻል፤ ሁሉን
አብዝቶልሻል” አሏት፣ እስከዛ ድረስ እናታቸው የሚሉትንና
የሚያደርጉትን በፀጥታ ሲታዘቡ የቆዩት እናቷ።

“የምን ዕድል ነው ምትይ? ዕድል ከሰማይ ይወድቃል? እንዲሁ
ነው እንዴ ንጉሡ ልዣችንን ሊያገቡ የፈለጉ? ልዣችን ሚገባትን ነው ያገኘችው። በደም ግባቷ፣ በብሩህ አይምሮዋ፣ በመልካም ምግባሯና
ጎንበስ ቀና ብላ ስላስታመመቻቸው ነው ንጉሡ ለንግሥትነት የመረጧት፣ ንግሥትነት እንደሚገባት አይተው መዝነው ነው እንጂ እንደ መደዴው ለውበቷ ወይም እንደገበሬ ለሙያዋ ብቻ ብለው
አይደለም።” ዮልያና ልጃቸውን ቆጣ አሉ።

“መቸም ደመ ግቡ ሁሉ... ያስታመመ ሁሉ ንጉሥ ባል አያገኝም። እንዳው የዕድል ነገር ይገርማል። እኼን ማን አሰበው?” አሉ፣ የእናታቸውን አፍ ብዙም የማይዳፈሩት ወይዘሮ እንኰዬ።

“የኔ ልዥ ገና ንግሥት እሌኒን አረግሻለሁ” አሉ፣ አያትየው።

“እሳቸውን መሆን እንዴት ይቻለኛል?”

“አንቺ ደሞ... እሌኒን ትሆኛለሽ ስልሽ እኮ ልክ እንደሳቸው ሁኚ
ማለቴም ማዶል። እንዴት እንደምኖሪ ማወቅ ያንቺ ፈንታ ነው። ሁሉ እየቅል ነው።”

ለጊዜው የአያቷ ምክር በመጠኑም ቢሆን አረጋጋት።

በነጋታው መንገደኛ ናትና ጥሩ እንቅልፍ እንድታገኝ እናትና አያት
ትኩስ ወተት በማር አጠጥተው አስተኟት። እሷ ግን እንደ ትናንቱ
ሁሉ ዛሬም እንቅልፍ በዐይኗ ሳያልፍ ፍርሐት፣ ጥላዬን ለመጨረሻ ጊዜ ሳታየው የመሄድ ጭንቀት፣ ብሎም ቀስ እያለ ውስጧ እየተጫረ የመጣው ቤተመንግሥት የመግባት ጉጉት መሳይ ነገር ሲፈራረቁባት
ሌሊቱ እንደመንጋት አለ።

ዶሮ ሲጮህ ቀሰቀሷትና ተጣጠበች። ቁርስ ብዪ ብለው ሲያቀርቡላት ግን ተናነቃት። እናቷ፣ “ትንሽ አፍሽ አርጊ፤ ምንገድ ባዶ አፍ አይከድም” እያሉ ሊያግባቧት ሞከሩ። እሷ ግን እንኳን እናቷን፣
አባቷን፣ ወንድሟን፣ ጥላዬንና የቤት አገልጋዮቹን ቋራን ራሱን ጥላ መሄዱ ዳገት ሆነባት።

ዐይኗ እንባ አቀረረ።

የእናቷን ፊት የተጫጫነውን ሐዘን ስታይ፣ ዐይኖቿ ጥግ ተጠልሎ
የነበረው እንባዋ ወደ ጉንጮቿ ኮለል አለ። እናቷ እስከዛ ሰዐት አምቀውት የነበረውን እንባ እንደ ድንገተኛ ዝናብ አወረዱት። ጉልበታቸው ላይ ተደፍታ፣ “እነየ መተሽ አታይኝም?” ስትላቸው፣ ትከሻዋ ላይ ተደፍተው
እዬዬ ሲሉ እሷም ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።

አያትየው ልጃቸውን፣ “እንደማበርታት ጭራሽ ታባቢያታለሽ?” ብለው ቆጣ አሉና፣ ወለተጊዮርጊስን ትከሻዋን ነካ አድርገው፣ “ተይ እኮ የኔ ልዥ፣ በቅጡ እንዳልተኛሽ ስንኳ ያስታውቃል። ምንገደኛ ነሽ። ገና
ምንገዱ ሚያጠወልግሽ ይበቃል። ፊትሽን አታበላሺ። የቀባሁሽንም
ኩል እንባሽ አጠበው። በቃ እንድች ብለሽ እንዳታለቅሺ። በይ ነይ” አሉና ፊቷን በእጃቸው አባብሰው፣ እንደገና ሥር ኩል ዐይኗ ላይ አደረጉላት።

እንግዶቹ እህል አፋቸው ካደረጉ በኋላ፣ ለመሄድ ወደ ውጭ ሲወጡ በአቅራቢያ ያለ ቤተዘመድ፣ የወለተጊዮርጊስን ጐንደር መሄድ የሰማ
ጎረቤትና ጓደኞቿ ተሰብስበዋል። ወለተጊዮርጊስ የአያቷን ረጅም የሐር ቀሚስ ለብሳ፣ ከቀሚሱ ሥር በሐር ክር ጫፉ የተጠለፈና ተረከዟን ጠበቅ አድርጎ የያዘ ሱሪ ታጥቃ፣ በአያቷ ወርቅ አሸግና ብቅ ስትል፣እንግዶቹ ትንግርት እንጂ እውን ሰው የሚያዩ አልመስል አላቸው።

ዘመድና ጎረቤት ግቢውን በዕልልታ ሲያደምቀው፣ የወለተጊዮርጊስ ጓደኞች ዐይናቸው እያየ በጓደኛቸው ሕይወት ውስጥ ያልገመቱት
ዓይነት ለውጥ መምጣቱ፣ ካጠገባቸው ተነስታ ለንግሥትነት መታጨቷ አስደነቃቸው። በዓመት መለወጫ ቀን አደይ አበባ እያስቀጠፈች፣ከቤት ቤት በድፍረት ይዛቸው እየዞረች፣ የምታስተባብራቸውና እንደ
መሪያቸው የሚቆጥሯት ጓደኛቸው ከመሃከላቸው በመለየቷ አዘኑ፤
በታላቁ ዕድሏ ቀኑ፣ ተደሰቱ። በዚኹም ድብልቅልቅ ስሜት መሃል ግን በመለያየታቸው አለቀሱ።

ግራዝማች የልጃቸውን ውበት ገና ያን ቀን ያዩ ይመስል ዐይናቸው
ውሃ አቆረ። እሷን ለመሰናበት ማልደው የመጡት ታላቅ ወንድሟ
ወልደልዑል፣ አጎቷ አርከሌድስ፣ የዮልያና ወንድም ኒቆላዎስ፣ አጎቷ
እሽቴና የአጎቷ ልጆች አውሳቢዮስ፣ ጌታና ነጮ በኩራት ተመለከቷት።
ንጉሥ ቤት ነውና የምትገባው በልባቸው ዙርያ የተስፋ ድር አደራችበት።

እናትና ልጅ በሠሩት ጥበብ ተደንቀው ዐይን ለዐይን ተያዩ።
አያትየዋ ያ ሁሉ እንባ ምልክት ስንኳ አልተወም፡፡ ድንቅ እኒያ
ደርሰው ትከሻ ሚሰጡ የጐንደር ወይዛዝርት እንግዲኽ ዐይናቸው
ይደፍርስ አሉ።

ለሱ አይቅርበት አሉ እናትየው፣ እንባቸውን በነጠላቸው እየጠራረጉ።

ጎረቤትና ቤተዘመድ ምርቃት ሲያዘንብላት፣ ዕልል ሲልላት፣ ጓደኞቿ የደስታ እንባ ሲራጩላት፣ ምቀኛው ግን፣ “ታመው የተኙ ግዝየ መዳኒት አርጋባቸው እንደሁ እንጂ ውነት አሁን ንጉሡ…” እያለ ወሻከተ።
👍111