አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_አራት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ሲልቪ
ላይ ላዩን


..ተመስገን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ ስሰራ አንዳንዴ ውቢቱ ሲልቪ ትመጣና «Salut Castro noire» ትለኛለች። («ሰላም፣ ጥቁር ካስትሮ») (ፂም ስላለኝ ነው፡፡)

«Que la paix soit avec toi Scheherazade Blanche» እላታለሁ
(«ሰላም ላንቺ ይሁን፣ ፃእዳይቱ ሻህራዝድ ሆይ»)

ትስቃለች። በምስራቃውያን አነጋገር እንቀጥላለን። ቀልድ
ነው። ከሲልቪ ጋር ሁልጊዜ ቀልድ ነው:: እውነተኛ ፈረንሳዊት ናት፣ ስለምንም ነገር ቢሆን «Moi je men fous!» ነው የምትለው
(«እኔ ስለዚህ ነገር ደንታ የለኝም»)
ታድያ ደስ ትላለች። ሰፊ አፏ
ሳሙኝ ሳሙኝ ይላል፡፡ አብረሀት ስትሆን ሳቅ ቀልድ ታበዛለህ፣

«ዠማንፉቲዝሟ» ይጋባብሀል፤ ስለምንም ነገር ደንቴ አይኖርህም
አንድ ቀን ግን
«ምንድነው ሁልጊዜ ስትፅፍ የማገኝህ?» አለችና ደብተሬን
አየችው:: የምን ፅህፈት ነው ይሄ? ያገራችሁ ነው?» አለችኝ
«አዎን»
«ምኑም አይገባም»
«ቀላል ነው፡፡ ሁለት መቶ አርባ የሚሆኑ ፊደላት አሉት»
«Quel horreur! (ኧረ የጉድ ያለህ!) እንግዲያው አታስረዳኝ
ይቅርብኝ .. ምንድነው ምትፅፈው?»
«ምንም አይደለም»
«ልብወለድ ነው?»
«ብጤ ነው»
«እንዴት ማለት ብጤ?»
«እንዴት ልበልሽ? ልብወለድ ነው፣ ግን ፈጥሬው አይደለም፣
ያየሁትን የሰማሁትን ነገር ሰብስቤ ቅርጹን እለዋውጣለሁ እንጂ፣
ላንባቢ እንዲጥም»

«ቆይ ቆይ፡፡ አሁን መፃፍ አለብህ ወይስ ለጊዜው ልትተወው
ትችላለህ»
«ልተወው እችላለሁ»
«እንግዲያው ከዚህ እንሂድና ቡና ልጋብዝህ:: እና ስለድርሰት
እናውራ። ይስማማሀል?»

«በደምብ ነዋ! ቆንጆ ሴት ቡና ስትጋብዘኝ ሁልጊዜ
ይስማማኛል»
«Malin Castro noir va!» («ሂድ ወድያ! ፎሌ ጥቁር ካስትሮ!»)
Deux Chevaux መኪናዋ ውስጥ ከገባን በኋላ
«ኤክስ ውስጥ የምወደው ካፌ የለኝም፡፡ ማርሰይ እንሂድ?»
አለችኝ
እየቀለድን እየሳቅን ደጋግማ «Moi, u sais je m en fous!»
እያለች፣ በሆዴ ውበቷን እያደነቅኩ፣ ማርሰይ ደረስን፡፡ የንግድ ሳይሆን የግል የመደሰቻ ልዩ ልዩ አይነት ጀልባዎች ከተደረደሩበት ወደብ አጠገብ አንድ ካፌ ገብተን ቢራ ካዘዝን በኋላ፣ ጉልህ ሰማያዊ
አይኖቿ በፈገግታ እያዩኝ
«ንገረኛ ስለምትፅፈው» አለችኝ
«ምን ልንገርሽ?»
«ስለሰዎቹ፣ ስለጊዜው፣ ስለግንኙነታቸው፣ ማን ማንን እንደ
ሚወድ፣ ማንስ ማንን እንደሚጠላ፣ መፅሀፍህ አንዴት እንደ ሚጀመር፣ አሁን የት እንደደረሰ፣ በኋላ እንዴት እንደሚያልቅ፣
ምን ምን ነገር እንደሚያስቸግርህ፣ መፅሀፍህ ምን እንዲል እንደ
ምትፈልገው፣ ሁሉን ንገረኝ
ቆንጆ ስለሆነች ይሁን፣ አጠያየቁን ስላወቀችበት ይሁን ወይ ሌላ ያልተገለፀልኝ ምክንያት ይኑር እንጃ፣ ስለመፅሀፌ ሁሉን
ነገርኳት። ለማንም ነግሬ የማላውቀውን ለሷ አጫወትኳት፡፡ ችግሩን ደስታውን፣ ብስጭቱን፣ የድል አድራጊነት ስሜቱን፣ ምንም
ሳልደብቅ አዋየኋት። ፈረንሳይኛው ሲያስቸግረኝ ልክ ልናገረው
የፈለግኩትን ቃላት ታቀብለኛለች፣ ምክንያቱም ሀሳቤ ቃላቱን
ቀድሞ ደርሷት ይቆያል። አንዳንድ ቦታ አንድ ሀሳብ ተናግሬ
ጨርሼ ሌላ ሀሳብ አልመጣልህ ሲለኝ አንድ ጥያቄ ትጠይቀኛለች
እሱን ጥያቄ ስመልስ፣ ሌላ ሀሳብ ይመጣልኝና እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ ብዙ ካወራሁ በኋላ

«ይገርምሻል፣ ይህን ለማንም ነግሬ አላውቅም» አልኳት
«Jen suis lattee» አለችኝ (ክብር ይሰማኛል።)
«እኔ እውነቴን ነው»
«እኔም እውነቴን ነው»
«አሁን ተራሽን አውሪልኝ
«ቆይ» አለችና ከያዘችው የመፃህፍት ቦርሳ አንድ አስር የሚሆኑ ባንድ በኩል ብቻ በታይፕ የተፃፈባቸው ነጠላ ወረቀቶች ሰጠችኝ።
አንብበው አለችኝ፡፡ አነበብኩት፡፡ አጭር ልብ ወለድ ታሪክ ነው።
ስጨርስ ምን ይመስልሀል?» አለችኝ
«አንቺ ነሽ የፃፍሽው?» አልኳት
«አዎን» አለችኝ
«አዝናለሁ። ጥሩ ታሪክ አይደለም»
«ምንድነው የጎደለው?»
«እርግጠኛ አይደለሁም። አየሽ፣ አንድ ሰው የሚወዳትን ሴት
ሊገድል ይችል ይሆናል፡፡ ግን ባስር ገፅ ውስጥ ይህን መናገር
የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ሁለት መቶ ገፅ
ያስፈልገዋል»
«ይህንንም አንብብ እስቲብላ ሌላ አስራ ሶስት ገፅ ሰጠችኝ።
አነበብኩት። ግሩም ታሪክ ነበር፡፡
«ይህንንም አንቺ ነሽ የፃፍሽው?»
«አዎን»
«ታሪክ ይሉሻል ይሄ ነው! ይህን ጊ ደ ሞፓሳን ራሱ ነው የፃፈው ቢሉኝ አምናለሁ» አልኳት
ጉልህ ሰማያዊ አይኖቿ ልዩ አስተያየት ሰጡኝ፣ እንደማቀፍ ያለ
አስተያየት፣ ሙቀት ያለው አስተያየት

«Merci»አለችኝ

«Je ten prie (ኧረ ምንም አይደለም) ይህን የመሰለ ለመፃፍ
ስትችዪ፣ እንዴት አርገሽ የቅድሙን ፃፍሽው?» አልኳት
መሳቅ ጀመረች (ጥርሶቿ ትክክል ሆነው ነጫጭ ናቸው። ነጭ
የፈረንጅ ጥርስ ብዙ እይታይም) «እኔ እንጃ አለችኝ «በምፅፍበት
ሰአት ሁሉም እኩል ጥሩ ሆኖ ይሰማኛል። ካንድ ሁለት ወር በኋላ
ሳነበው ነው እውነተኛው ዋጋው የሚታየኝ»
«ይሄ መጥፎው መቼ ነው የተፃፈው?»
«ካንድ አመት ተኩል በፊት
«እንግዲያው መጥፎ መሆኑ
ድሮ ገብቶሻል። ለምን
እስነበብሽኝ?»
«ላውቅህ ስለፈለግኩ። ማንም ሰው ቢሆን፣ እንደምፅፍ ካወቀ
ወይም እንዲያውቅ ከፈለግኩ፣ መጀመሪያ መጥፎ ታሪኬን
አስነብሰዋለሁ። አንብቦት ጥሩ ነው ካለ በቃው። ሁለተኛ እኔ
የፃፍኩትን አያነብም። እስካሁን ለአንድ ስምንት ሰው አስነብቤያለሁ።
አንተና አንድ የፓሪስ ጓደኛዬ ብቻ ናችሁ መጥፎውን መጥፎ
ያላችሁት። ስለዚህ ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ ጥሩውን ያነሰሳችሁ»
«ሌላ የፃፍሽው አለ?»
«ሃያ ሶስት አለኝ፡፡ አስራ አንዱ ጥሩ ይመስሉኛል። ሰባቱ
በጣም መጥፎ ነው:: አምስቱ ግን ጥሩም አይደል፣ መጥፎም
ኣይደል እንደኔ እስተያየት። ስለዚህ አንተ እነዚህን አምስት
አንብበህ ምን እንደሚመስልህ ብትነግረኝ፣ ተስፋ የሌለውን
እጥለውና ተስፋ ያለውን እየመከርከኝ አሻሽለዋለሁ»

«ክብር ይሰማኛል፣ ግን ልመክርሽ መቻሌን እንጂ
«ትችላለህ። ታግዘኛለህ? »
«ከቻልኩማ በደስታ! አሁን ስለራስሽ ንገሪኝ፡፡ ቅድም እኔ
እንደነገርኩሽ»
ነገረችኝ፡፡ የምንፅፍበት ቋንቋ ተለያየ 'ንጂ ሙከራችን፤
ችግራችን፣ አስተያየታችን በጣም ይመሳሰላል፡፡ ስንወያይ መሸ፡፡
«እማውቃት ጥሩ ርካሽ ምግብ ቤት አለች» ብላ ሳን ሻርል
ባቡር ጣቢያ አጠገብ ወስዳ እራት ጋበዘችኝ። በፈረንሳይ ደምብ ከምግቡ ጋር አንድ ጠርሙስ ወይን ጠጣን፡፡ ሲኒማ ላስገባሽ አልኳት፡፡ ሁለታችንም እንደዚህ ልንጨዋወት የምንችልበት ጊዜ
መቼ ተመልሶ እንደሚመጣ አይታወቅም አለችኝ፡፡ እውነትሽን ነው አልኳት
ወደ ወደቡ ተመልሰን በእግር እየተዘዋወርን ወሬያችንን ቀጠልን። በተርታ የቆሙ ጀልባዎች የሚወዛወዙበት ውሀ ውስጥ የማርሰይ መብራት ይጫወታል። የባህር ሽታ ይዞ ከባህር በኩል የሚመጣው ነፋስ ቅዝቅዝ ያለ ሆኖ ይለሰልሳል። እንደኛው እያወሩ
የሚዘዋወሩ ሰዎች አሉ፤ አብዛኛዎቹ ተቃቅፈዋል፡፡ መንሽራሽር ሲበቃን አንድ ካፌ ገብተን ቁጭ ብለን ቢራ አዘዝን
👍271👏1