#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
....ወይዘሮ እንኰዬ የእናታቸውን ንግግር ሲሰሙ ከሐሳባቸው መለስ አሉና በኩራት የነጠላቸውን ባለ ደማቅ ጥልፍ ጥለት አስተካክለው፣ “ሰማህ?” በሚል ሁኔታ ኢሳያስን ተመለከቱት።
ኢሳያስ ግን እጥር ምጥን ያሉትን ዮልያናን እያየ፣ “ጃንሆይም እኮ
ያጤ ሚናስ ነገድ መሆናችሁን አውቀዋል። ልዣችሁን የመረጡበት ዋናው ምክኛት ግን እሱ ማዶል። ባይናማነቷ፣ በጠባይዋና በብሩህ አይምሮዋ ደስ ተሰኝተው ነው” አላቸውና በራፍ ላይ የቆመውን አገልጋይ፣ “ያነን ማሙየን ሴቶቹ ዕቃውን ይዘው እንዲመጡ ንገራቸው
በለው” አለው።
አሳላፊው ቀልጠፍ ብሎ ወጥቶ ሲመለስ አብረውት ሁለት ደንገጡሮች የቀርከሀ ሰንዱቆች ይዘው ገቡ። ኢሳያስ ሰንዱቆቹን እንዲከፍቱና ዕቃዎቹን እንዲያሳዩ በእጁ ምልክት ሰጣቸው። ለጥሎሽ የመጡትን
የሐር ቀሚሶች፣ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ካባ፣ ቆዳ ጫማ፣ ከወርቅ የተሰሩ ያንገትና የጆሮ ጌጦች፣ እንዲሁም አምባሮች በእቅፋቸው አድርገው
ለተሰበሰበው ሰው አሳዩ።
እነግራዝማች ትንፋሻቸውን ውጠው ተመለከቱ። ተነሥተውም
በአክብሮት እጅ ነሡ፤ የምርቃት መዓት አዥጎደጎዱ።
ወለተጊዮርጊስ ጥሎሹን ለማየት ዐይኗን ከወዲያ ወዲህ አዘዋወረች።እንደልብ ማየት አቃታት። ቤተሰቦቿ ፊት ላይ ከሚንፀባረቀው የኩራትና የደስታ ስሜትና ከአዘነቡት የምስጋና ቃላት ግን የመጣላት ጥሎሽ ቀላል እንዳልሆነ ተገነዘበች።
እንዳው ሰውየው... አረ ንጉሥ ነው ሚባሉ... ንጉሡ ኸኛ ጋር ምን
አገጣጠማቸው? ንዳድ እንዲህ ጉድ ታምጣብን እያለች ስትገረም
ቆየችና ንጉሠ ነገሥቱ እነሱጋ፣ በነበሩ ጊዜ እሷን ለማግባት ማሰባቸውን የሚጠቁም ነገር እንዳው ፍንጭ አኸገኝ እንደሆን ብላ፣ ሐሳቧ ወደ ኋላ ሽምጥ ጋለበ።
ጨታመው በመጡ ማግስት እናቷ አዘዋት ፊታቸውን በጨርቅ ስታብስ ንጉሠ ነገሥቱ ዐይናቸውን ገለጥ አደረጉ፤ እንደደነገጡ አስተዋለች። ለምን እንደሆነ አልገባትም። እሳቸው ዐይናቸውን ከድነው በስመአብ አሉ። ዐይናቸውን ድጋሚ ሲከፍቱ፣ እነዚያው ይዘዋቸው የመጡት
ሰዎችና እነግራዝማች ናቸው የከበቧቸው። ቅዠት ኑሯል? ትኩሳቱ ነው ሴት ልዥ ያየሁ ያስመሰለኝ ብለው ዐይናቸውን መልሰው ከደኑት።
ወለተጊዮርጊስ አጥሚት ይዛ ተመልሳ መጥታ፣ በለሰለሰ አንደበት፣ “እስቲ ትንሽ ይቅመሱ” ስትላቸው በድንገት ከእንቅልፋቸው እንደባነኑ
የደከመ ዐይናቸውን ከፈት ሲያደርጉ፣ የተኙበት መደብ አጠገብ ሴት ልጅ ሸብረክ ብላለች። ቀደም ብለው ያይዋት ወጣት እንደሆነች ሲገነዘቡ፣ ዐይኖቿ እንደ ኮከብ እሚያበሩ፣ ቆዳዋ የማር ወለላ የመሰለ፣ እንዴት ያለች ዐይናማ ናት በሩፋኤል? አሉ፣ አንድም ቀን
ስለታቸውንና ጥያቄያቸውን አስተጓጉሎባቸው የማያውቀውንና እሳቸው ጐንደር ውስጥ የተከሉትን ሩፋኤልን ጠርተው።
ወለተጊዮርጊስ ፈገግታ ለገሠቻቸው። ዐይኗ ላይ ያዩት ርህራሄ መጽናናትን ሰጣቸው። ልባቸው በደስታና በአድናቆት ከቦታው ተነቃነቀ። አጥሚት የያዘውን የሸክላ ጽዋ ወደ አፋቸው ስታቀርብላቸው፣ ወይዘሮ እንኰዬ፣ “እስቲ ይቅመሱ፣ እሷው ናት የሠራችልዎ” አሏቸው። የምግብ ፍላጎት ባይኖራቸውም፣ እንደ ኩበት የደረቀ አፋቸውን ታግለው ከፈቱላት። አንገታቸውን በአንድ እጇ አቅንታ ከአጥሚቱ
አስጎነጨቻቸው። ከበዋቸው የተቀመጡት፣ “ተመስገን፣ ለሱ ምን ይሳነዋል?” ብለው ወደ ላይ አንጋጠጡ።
በሚቀጥሉት ቀናት ከበሪሁን መድኃኒት በተጨማሪ ወለተጊዮርጊስ ከምትኖርበት ከአያቷ ቤት ማልዳ እየመጣች ምግብ እየሠራች፣ እያጎረሰች፣ አጥሚት እያጠጣችና እየተንከባከበቻቸው ራሳቸውን
ሲችሉም፣ እጅ እያስታጠበችና ምግብ እያቀረበች፣ ደከመኝ ሳትል
አስታመመቻቸው። እሳቸውም በሩፋኤል እንዴት ያለች ዐለላ...ሰንደቅ የመሰለች ናት ትትናዋስ? እያሉ ተስተናገዱ።
በተኙበትም ሰው ውልብ ባለ ቁጥር እሷ እየመሰለቻቸው ዐይናቸው ሲባክን፣ ሲያይዋት ልባቸው ከአፎቱ ተመንጥቆ የወጣ ሲመስላቸው፣ፊታቸውን በውሃ ስታብስ የእጇ ልስላሴ ሊያስተኛቸው ሲቃጣው፣
ትንፋሿ በሽታቸውን ከላያቸው ሲገፍላቸው፣ ሕዝኸ ወድያ ጥድቅ
ኸየት ይገኛል? አቤት አቤት እንዴት ያለች መልከ መልካም ናት?
ደም ግባቷ የተደራጀ፣ ጠጉሯ እንደ ሜላት የተፈተለ፣ ወገቧ እንደ ንብ
ንግሥት የቀጠነ፣ እንደ እርጎ የረጋች በምግባር የታነጠች እያሰኘ አከረማቸው።
እንኳንስ አይተዋት፣ ሳያይዋት ስለእሷ ማሰቡ ብቻ በወባ የዛለ
አካላቸውን ዘና ሲያደርግላቸው፣ ከዐይናቸው ስትርቅ ምግብ፣ ውሃ
ወይንም አጥሚት ይዛ የምትመጣበትን ሰዐት ሲናፍቁ፣ ጀንበር መጥለቂያዋ ላይ ወደ አያቷ ቤት ስትመለስ ሆድ ሲብሳቸው፣ ጠዋት ስትመጣ ከእናቷና ከአያቷ የወረሰችውን እንደ ውሃ የጠሩ ዐይኖቿን
ከብለል እያደረገች የወደዱትን እየመረጠች የሠራችውን፣ “እስቲ ትንሽ ይቅመሱ፣ እኼኛው ይሻልዎ ይሆን?” ስትላቸው፣ ጆሯቸው የተዋበ ዜማ የሰማ ያህል ወደ እሷ ዘመም ሲል፣ ልባቸው ለማራኪ ዐይኖቿ ሲገዛ ቀናት አለፉ።
ሌሎች ውበቷን አይተው እጇን ሲጠይቁ እሳቸው ከመልኳ ባሻገር
ለጋሥ መንፈሷን፣ አስተዋይነቷን፣ ሠናይ ምግባሯንና ትሕትናዋን
አስተውለው ወደዷት። በአኳኋኗና በልባዊ መስተንግዶዋ ልባቸው
ተነካ። ተወዳጅ ገፅታዋ፣ አነጋገሯ፣ ርጋታዋ፣ ወደ ሙሉ ሴትነት
በመሻገር ላይ ያለው ዳሌዋና ለግላጋነቷ በወባ የተንገላታችው ልባቸው ላይ ነፍስ ዘሩበት።
ድኘ እጐንደር ስገባ ይችን ልዥ አገባለሁ እያሉ ደጋግመው ዛቱ።
እሳቸው እንደዚህ እያሉ ይዛቱ እንጂ፣ ወለተጊዮርጊስ ወደዋት
እንደነበር የሚያሳይ አንዳችም ፍንጭ አላገኘችም። እሳቸውም በግልጽ ያሳይዋት ነገር አልነበረም።
የሚሄዱ ቀን፣ ግራዝማችንና ቤተሰባቸውን ከታላቅ ምስጋና ጋር
ተሰናብተው፣ ውድ ንብረት ወደ ኋላ የተዉ ያኸል እየተገላመጡ፣ ያችን “የአጥቢያ ኮከብ የመሰለች” ሲሏት የከረሙትን የአስራ ስድስት ዓመት ጉብል በዐይናቸው ፈልገው አመሰገኑ። ወለተጊዮርጊስ በተለይ ለእሷ ለቀረበው ምስጋና እጅ ነሥታ ቀና ስትል ዐይኖቿ ከሰውየው ዐይኖች ጋር ተጋጩ።
ከእሳቸው ዐይነ ብሌን ባሻገር ግን ከቋራ እስከ ጐንደር የሚወስደው
መንገድ እንደተቃና አላስተዋለችም።
ከሐሳቧ ስትመለስ ጨዋታው ቀዝቀዝ ብሏል። እንግዶቹም የተዳከሙ መስለዋል። ቤቱም ጨለምለም ብሏል። ሥራ ቤት በየበኩሉ ማሾ ሊያበራ ሽር ብትን ይላል።
ኢሳያስ፣ “እንግዲህ ልዥቱን ይዘን ነገ ጐንደር እንዝለቃ” አለ፣
ግራዝማችን፣ እንኰዬንና ዮልያናን በየተራ እየተመለከተ።
ነገ አለች፣ ወለተጊዮርጊስ። በረጅሙ ተነፈሰች፣ ወላጆቿና አያቷ የሚሉትን ለመስማት ጆሮዋን አቀናች።
“ባይኾን ኸነገ ወዲያ ይሁን፣ ጥቂትም ቢኾን ልዣችንን እንድናዘጋጅ” አሉ፣ አያቷ።
“እንዳላችሁ ይሁን” አለ፣ ኢሳያስ።
ጐንደር መሄዷ ነው! ተጨነቀች። ተርበተበተች። ኸጐንደር ልኸድ? አለች። ንጉሥ ላገባ ጥላዬስ?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ወለቴን ንጉሥ ኸወሰዳት እኔ የሥዕል ንጉሥ ማልሆን”
ጥላዬ፣ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ተቀምጦ ስለራሱና ስለወለተጊዮርጊስ ዕጣ
ፈንታ ያስባል። እናቱ ወይዘሮ ጌጤነሽ የምሽቱን ግብር ውሃ ወጥተው ሲመለሱ አየት አደረጉት። “አምሽተህ ነው?” አሉትና ለራሳቸው ሰምቶ
ይሆን? አሉ። ዛሬ ከልባቸው አዝነውለታል። ወደ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት፣ “በምሽት እንኳ ዕረፍት አይኖርህ ልጄ?” አሉት፣ መሬት ላይ የሚጭረውን አይተው።

👍14