#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
... እሷ የሽማግሌዎቹ ቁርጥ ሳይታወቅ፣ ከጥላዬ ሌላ ለማንም እንድትሰጥ አትፈልግም። ብቻ አባባ ለዝኸ ትኩር ብሎ ሲያየኝ ለነበረው ሰውየ እንዳይሰጡኝ አለች፣ ኢሳያስን እያየች።
ተጨነቀች፤ ተጠበበች፣ ብረሪ ብረሪ አላት። ኸጥላዬ ጋር ተያይዘን እንጠፋለን እንጂ እሱን አላገባም አለች።
እሷ ይህንን ስታሰላስል አባቷ አላስችል ብሏቸው እንግዶቹ
ተመልሰው የመጡበትን ምክንያት በዘዴ ለማወቅ፣ “ኸጐንደር ነው
ኸሌላ የመጣችሁ?” ሲሉ ጠየቁ።
የወለተጊዮርጊስ ጀሮዎች ተነቃቁ።
“ኸጐንደር ነው የመጣን” አለ ኢሳያስ። ትንሽ ካመነታ በኋላ፣
“እንግዲህ እንንገርዎ እንጂ” አለና አብረውት የመጡትን ተመለከተ።
የተግባቡ መሰለው። ፊቱን ወደ ግራዝማች መልሶ ፈገግ አለ። ዐይን ዐይናቸውን እያየ፣ “ግራማች… የዛን ዕለቱ እመምተኛ እኮ ንጉሡ ራሳቸው... አጤ በካፋ ነበሩ” አላቸው።
ግራዝማች ከመደቡ ላይ ተወርውረው ተነሡና፣ “በወፍታው!” አሉ፤ ሰንበት የሚሳለሙትንና በየዓመቱ የሚዘክሩትን ደብራቸውን ወፍታ
ጊዮርጊስን ጠርተው።ራሳቸውን በሁለት እጆቻቸው ይዘው፣ “ጃንሆይ ራሳቸው? እኛ እንደ
ዋዛ ኸዝኸ ተኝተው የነበሩቱ?” አሉ፣ ተቀምጠውበት የነበረውን መደብ በሌባ ጣታቸው እያመለከቱ።
ግራዝማች በህመምና በሐዘን ምንክንያት የንጉሠ
ነገሥቱ የንግሥ ሥርዐት በተከበረበት ወቅትና በበዓል ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱን በዐይን ለማየት ዕድል አግኝተው አያውቁም ነበርና ንጉሠ ነገሥቱን ባለማወቃቸው አዝነው ራሳቸውን ነቀነቁ።
“ምነዋ እንደዝኸ ጉድ ትሠሩኝ? እንዲያው እንዴት ያለ ፌዝ ነው
ምትነግሩኝ? እንዳው በወፍታው ምን ጉድ ነው ምትነገሩኝ?” እያሉ
ራሳቸውን በሁለት እጆቻቸው እንደያዙ ቆመው ቀሩ። ሰውነታቸው ብርክ እንደያዘው ተንቀጠቀጠ፤ ትከሻቸው ላይ ያጣፉት ጋቢ ወርዶ መሬት ነካ።
የተነገራቸው ቀልድ መሆኑን የሚያረጋግጥላቸው የፈለጉ
ይመስል ዐይኖቻቸውን ከአንዱ እንግዳ ወደ ሌላው አፈራረቁ።
እንግዶቹ በሁኔታቸው ተደናገጡ። እንኰዬ ባላቸውን እንባ ቀረሽ
ተመለከቱ፤ ተነሥተው ጋቢያቸውን ሊያስተካክሉላቸው ፈልገው
መነሣት አቃታቸው።
“በተክልየ ይቀመጡ ግራማች” አላቸው ኢሳያስ፣ ሁኔታቸው
አስደንግጦት።
ግራዝማች ራሳቸውን እየነቀነቁ ለመራመድ ዐቅም እንዳነሳቸው
ሁሉ ጋቢያቸውን ሰብሰብ አድርገው ቆም አሉና ጉልበታችው
የከዳቸው ይመስል፣ በሁለት እጃቸው ደግፈውት ተመልሰው መደቡ ላይ ተቀመጡ። የሚሉትን ቀርቶ የሚያስቡትን ማወቅ ተስኗቸው፣ ግንባራቸውን ኩምትር አድርገው፣ ዐይኖቻቸውን መሬት የተነጠፈው አጎዛ ላይ ተክለው ቀሩ።
ወይዘሮ እንኰዬና እናታቸው ትኩረታቸው ግራዝማች ላይ ነበርና
መቀመጣቸውን ተከትለው ዐዲስ እንደሰማ፣ “በቁስቋሟ!” አሉና
እርስበርስ ተያዩ። ወለተጊዮርጊስም በቁስቋሟ ብላ አማተበች። አያቷ ሆኑ ቅድመ
አያቶቿ የሚያከብሯትን፣ የሚማጸኗትን፣ የሚዘክሯትን፣ ባለውለታቸውን፣ በዕለተ ቀኗም ብዙ ድል የተቀዳጁባትንና እሷ ራሷም ብትሆን “ግጥሜ”
የምትላትን ቁስቋም ማርያምን ጠርታ። በግራ እጇ ኣፏን ይዛ፣ ንጉሡ ራሳቸው እኛ ኸዝኸ ኸመደብ ላይ ተኝተው የነበሩቱ? እኛ ፊታቸውን ሳጥብ፣ አጥሚት እየሠራሁ ሳጠጣ... እጃቸውን ሳስታጥባቸው የነበሩቱ
እንዴት ብለ? ንጉሡ ራሳቸው? ጉድ ጉድ! የዛሬውስ ቀን ምንያለውን ጉድ ይዞ መጣ እናንተዬ? አለች፣ መጋረጃውን ለቃ፣ ራሷን በሁለት እጆቿ ይዛ። ጥቂት ቆይታ መጋረጃውን እንደገና አጋጥማ ይዛ ወደ እንግዶቹ ተመለከተች፤ ያወጋሉ። የሚሉትን ለመስማት ሞከረች።
ሐሳቧ ግን አልሰበሰብ አለ።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሕመምተኛ የነበሩት፡ የአሁኑ ንጉስ። ፊቷ ላይ ድቅን እያሉ አስቸገሯት። መላ ቤተሰቡ ንጉሥ መሆናቸውን እንዴት ሳያውቅ፣ ሳይጠረጥር እንደቀረ ገረማት። ነገሩን በቅጡ ለመመርመር ሐሳቧ ወደ ኋላ ነጎደ።....
የመጡ ቀን፣ እንደ ልማዷ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ተቀምጣ የእነዚያን
የአስታራቂ ሽማግሌዎች መምጣት ትጠባበቃለች። ግቢው መግቢያ ላይ ሰዎች ስታይ ብድግ አለች። “እረ የታመመ ሰው ነው መሰል ይዘው የመጡ” አለች፣ ዛሬ ከመጡት እንግዶች ውስጥ ሁለቱና ሌሎች ሁለት ሰዎች አንድ ሰው ደግፈው ድንገት ግቢው ውስጥ ሲገቡ አይታ።
“እነማ?” እያሉ እናቷ፣ አባቷና አያቷ ከውስጥ በችኮላ ወጡ።
በርግጥም የታመመ ሰው እንደመጣ ሲያውቁ ደነገጡ፣ “ግቡ! ግቡ!” እያሉ መንገድ ለቀቁ። ነፍጥ የያዙ፣ ፈረስና በቅሎ ሳይቀር ያስከተሉ በርካታ ሰዎች እየተገፋፉ ገቡ። ሁሉም የመረበሽ መልክ ይታይባቸዋል።
እምብዛም ግርግር የማያውቀው ግቢ ትርምስምስ አለ። የተረጋጋው
የእነግራዝማች ቤት ለወከባና ለድንጋጤ ቦታ ለቀቀ።
አራቱ ሰዎች ወደ ቤቱ ውስጥ ገብተው፣ አቅፈው ደግፈው ያመጧቸውን ሕመምተኛ መደብ ላይ አሳረፏቸው። ወለተጊዮርጊስ፣ እኚህ መሣሪያ የያዘ ወጀብ የተከተላቸውና በጽኑ የታመሙ የሚመስሉት ሰው ማን መሆናቸውን ለማወቅ እጇን ደረቷ ላይ አድርጋ ተመለከተች፤ ግንባሯ
ኩምትር፣ አፏ ከፈት ብሏል። እናቷ፣ “ወለቴ እስቲ ውሃ” ሲሏት
በፍጥነት ወጥታ በቅምጫና አምጥታ አቀበለቻቸው።
ያን ሰዐት፣ ዙርያውን በቆሙት ሰዎች መሃል፣ ባለ ንቅሳት አንገቷን
ሰገግ አድርጋ ሕመምተኛውን አየች። በጽኑ እንደታመሙ አስተዋለች፤
ይቃዣሉ፤ ይቃትታሉ፤ ይወራጫሉ፤ ብርክ እንደያዘው ይንዘፈዘፋሉ።
ሮጥ ብላ ከመጋረጃው ጀርባ ቡሉኮ አምጥታ ደረበችላቸው።
ሰውየው የመጣላቸውን ውሃ መጠጣት ቀርቶ ዐይናቸውን መግለጥ ሆነ አፋቸውን መክፈት አልቻሉም። ግራዝማች መንበር ተደናግጠው፣
“ምንን ሁነው ነው? እመማቸው ምንድር ነው? እያሉ ከወተወቱ በኋላ፣ አንደኛው እንግዳ፣ “ንዳድ ሳትሆን አትቀርም። ቆላ ሲወርዱ ነድፋቸው ፊት ታመው ያቃሉ። ኸናንተ ዘንድ ይዘነ መጣነ” በማለት መልስ ሰጡ፣ ንጉሠ ነገሥቱን ይዘው ማንም ሰው ቤት ስለማይገቡ፣ ቋራ ውስጥ
የታወቁት ባላባት ቤት የትኛው እንደሆነ ጠይቀው የመጡት መሆኑን ሳይናገሩ።
ግራዝማችም፣ “ኧረ ደግ አረጋችሁ፤ ስንኳንም መጣችሁ። ቤት የአብርሃምም ማዶል?” ብለው አደግድጎ የቆመውን አሳላፊ፣ “እስቲ ኸድና ያነን በሪሁንን ተሎ ይዘህ ና” አሉት፡
መድኃኒተኛው በሪይሁን ከመቅጽበት መጥቶ አንድ እጁን
ሕመምተኛው ግንባር ላይ አስቀምጦ ራሱን ነቀነቀ። ጉንጫቸውን ዳበስ፣ እጆቻቸውን ጨበጥ፣ ጨበጥ አድርጎ መልሶ እጁን ግንባራቸው ላይ አሳረፈና፣ “ንዳድ ነች” አለ።
“ተሎ በልና መዳኒት አርግላቸዋ” አሉ፣ አንደኛው እንግዳ።
በሪሁን ለሰውየው መልስ ሳይሰጥ በቅዎጫና ተቀምጦ የነበረውን
ውሃ ደጅ ወጣ ብሎ ቀነሰለት። ይዞት ከመጣው ከረጢት ውስጥ
የደቀቀ ቅጠል መሳይ ነገር ቆንጠር አድርጎ በውሃው በጠበጠና በርከክ ብሎ የሕመምተኛውን ጭንቅላት በአንድ እጁ ቀና አድርጎ በመዳፉ
ጋታቸውና ቆሞ ተመለከታቸው።
ይህ ሁሉ ሲሆን ሰውየው ዐይናቸውን አልከፈቱም፤ አንገታቸው ወደ አንድ ወገን ዘንበል ብሎ ተኝተዋል። የሚሆነውን ሁሉ የሚያውቁ
አይመስሉም።
“በሪሁን ሁሉም አልገባም። ኸመዳኒቱ ትጨምርላቸው?” አሉ
ግራዝማች መንበር፣ ከሰውየው አፍ ቀስ እያለ የሚንጠባጠበውን ፈሳሽ እያዩ።
በሪሁን፣ “ግድ የለም የገባው ይበቃል” ሲል ሰውየው አስመለሳቸው።
ወለተጊዮርጊስ ፈጠን ብላ ንፁህ ሀጨርቅና ውሃ አምጥታ የሰውየውን አፍ ጠራረገችላቸው፤ አካባቢውንም አጸዳች።
“መዳኒቱ ወጥቷል። እንደገና አርግላቸዋ” አሉ ግራዝማች፣ በሪሁንን።
“ትንሽ ይርጋላቸውና አረግላቸዋለሁ።”
መድኃኒቱን እንደገና ግቷቸው በርከክ ብሎ ተጠባበቀ፡፡ ሰውየው
አላስመለሳቸውም።

👍11❤1