#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል
....የማለዳዋ የጥር ወር ፀሐይ በመሬት ወለል አካባቢ ከየሚዳው! ከየተራራው፣ ከየዛፉ፣ ከየቤቱ፣ ከየጉራንጉሩ ቀዝቃዛ አየር ጋር ትንቅንቅ ገጥማለች። ተፈጥሮ ራሷን በራሷ የምታስተካክልበትና የምትለዋውጥበት ተፈራራቂ ኃይል ስላላት ቀዝቃዛው አየሩ ቀስ በቀስ ተረታ። ለውጥ የተፃራሪ ኃይሎች የግብግብ ውጤት ነው::
በእኔ ሕይወት ውስጥ ግን ጎልቶ የሚጠቀስ ለውጥ ባለመገኘቱ ሕሊናዩ
እየቀዘቀዘ ከመሔድ በቀር የብርታት ለውጥ አልታየብኝም፡፡ ከመኝታዬ ተነሥቼ
ልብሴን ስለባብስ ሰውነቴ ቀነቀነኝ፡፡ እውነተኛዎቹ የሐሳቤ ቅንቅኖች ግን አንጎሌ ውስጥ ይርመሰመሳሉ። የሥራ ቀን ነበር፡፡
መንገዱ የሚያልቅልኝ ስላልመስለኝ ቀደም ብዬ ተነሣሁ፡፡ ወደ ሕጋዊ ፍርድ ቤት ሳይሆን ወደ ግፈኞች የመከራ ሽንጎ የምገሠግሥ መሰለኝ፡፡ ከአራት ኪሎ እስከ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያለውን ርቀት በሁለት ታክሲ አጠቃለልኩት፡፡
ጠበቆች፣ ዳኞች፣ ጸሐፊዎች፣ ነገረ ፈጆችና ወኪሎች፣ ተሟጋቾችና አማላጆች፣ “ጫማ ጠራጊዎችና ሥራ ፈቶች፣ እንደየ ኑሮ ደረጃቸው ለብሰው ተራ በተራ ሁለትና ሦስት እየሆኑ በመምጣት የፍርድ ቤቱን አካባቢ የበጋ ወራት ገብያ
አስመሰሉት፡፡ አንዳንዶቹ ሰዎች የለበሱት ነጠላና ጋቢ በጣም ከመቆሸሹ የተነሣ
ዳግመኛ ታጥቦ የሚነጣ አይመስልም፡፡ ጥለቱ የተንዘለዘለ፣ ዐልፎ ዐልፎ አይጥ
የበላው ይመስል የተቀዳደደ፣ እንደ አረጀ ሻሽ አለቅጥ የሳሳ ልብስ፣ በተለያየ
የጨርቅ ዐይነት የተጣጣፈ ኮትና ሱሪ፣ ከታጠበ ብዙ ዓመታት ዐልፈውት እድፉ
እንደ ማሰሻ የተላከከበት ሱፍ ኮት፣ ከተወለወለ ወራት ያለፉትና የቆዳው ቀለም የተገጣጠባ ከወደ አፍንጫው በእንቅፋት አልቆ ቀዳዳው የደረቀ የዓሣ አፍ የመሰለ፡ ከወደ ተረከዙ ወይም ከወደ ጎኑ ባንድ ወገን ተበልቶ የተንጋደደ ጫማ፣
በፀሐይ ሐሩርና በውርጭ፣ በአቧራና በእንክርት ቀለሙ ጠፍቶ የነተበ ባርኔጣ፣
የለበሱ ያደረጉና የደፉ ሰዎች በተስፋ መቁረጥ ስሜት እዚህም እዚያም
ቆመዋል፡፡ ለአያሌ ወራትና ዓመታት የተንገላቱና የተጎሳቆሉ ባለጉዳዮች ናቸው::በረሃብና በጥማት በርዛትና በንዴት በመጎዳታቸው አብዛኛዎቹ ውርጭ ላይ ያደረ አንጋሬ ይመስላሉ፡፡ ሕይወታቸው በትካዜ በመሞላቱ የገጽታቸው ፈገግታ ደርቋል፡፡
ወዛቸው እንደ ቅቤ ቅል የሚቅለጠለጥ ፊታቸው በዶሮ ጮማ እንደተወለወለ የወይራ በትር የሚያበራ፣ ቦርጫቸው የመንፈቅ ርጉዝ መስሎ ሱሪያቸው መታጠቂያው ላይ የሪቅ አፍ የሚያህል፣ አለባበሳቸው ሁሉ በጣም ያማረና የተዋበ ደንደሳሞች፣ በየደቂቃው በሚረባና በማይረባው ሁሉ የሚሥቁ በጣም መሠሪ ሰዎች ከየቢጤዎቻቸው ጋር ሰብሰብ ከምችት ብለው አፍ ለአፍ
ገጥመው ያወራሉ። የያዙት የሰነዶች መያዣ ኮሮጆ እንደ ባለቤቶቹ የፀዳ ሲሆን
የልፋት እንክርት አልነካውም፡፡ የተሰበሰበውን ሰው በዝርዝር ሲያዩት እያንዳንዱ ብቻውን ቆሞ እጁን እያወራጨ ከራሱ ጋር ይሟገታል።
አብዛኛው ጨርቅ ለባሽ በሌላ ሰው ወረቀት እያስነበበ ይኽ ልክ ነው
የለም ይኽ ሐሰት ነው! ለዚህ በቂ ነቃሽ አለኝ! ያያት የቅድመ አያቴ ነው ይግባኝ እላለሁ፡ ከዳኛው ጋር ተዋውለው ነው። ወላዲተ አምላክን!” እያለ እሰጥ
አገባ ይላል። ሁሉም ከሕይወት ወዲያ ማዶ በውሸት ዓለም ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እንጂ በርግጠኛ ሕይወት በእውነተኛ ዓለም የሚኖሩ አልመሰሉኝም
የመጥፎ ነገር ጥቀርሻ በጥብጠው የጋቱኝ ይመስል አእምሮዩ ተጨነቀ፡፡
የማያቋርጠው የጊዜ ጎርፍ እየጋፈረ መጓዙን ቀጠለ። ደቂቃ የደቂቃ ርካብ ረግጣ እየተፈናጠጠች ላትመለስ ትጋልባለች።
ጎነ ረጂሙ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ግዙፍ ሕንፃ ታላቅ የመከራ ተራራ መስሎ ፊት ለፊት ተገትሯል። የማደርገውን ጥንቃቄ አሟልቼ አካባቢዬን ገልመጥ እያልኩ እያየሁ መለስ ቀለስ አልኩ፡፡ ጭንቀቴና ጥበቴ እንደ ሐምሌ ጥቁር ደመና ከብዶ አንጎሌ ውስጥ አንዣሰሰ። በውስጤ የነበረው ሥጋት በድኃ ገበሬዎች አዋሳኝ እንዳለ የከበርቴ እርሻ መስፋቱን ቀጠለ። ረፈደ።
በወታደሮች ታጅበው በእግራቸውና በመኪና የመጡ አያሌ እስረኞች
በተለየ ቦታ ሰብሰብ አጀብ ብለው ቆሙ። ገር ገጭ ገጭ ገጭ፣ ሲጢጢጢጢጢ !
ካካካካካኪ! የሚል ድምፅ የምታሰማ ቮልስዋገን መጥታ አጠገቤ ቆመች፡፡ ጉልላት ነው። የየወዲያነሽ ቀነ ቀጠሮ በመሆኑ እኔና እርሱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት
ለመገናኘት ተነጋግረን ነበር። ድክምክም ባለ እንቅስቃሴ የመኪናይቱን ቋቋቲያም
“በር ከፍቶ ወጣና ጨበጠኝ፡፡
ለአራት ሰዓት ሩብ ጉዳይ እኮ ሆኗል እስካሁን አላመጧትም እንዴ?»
አለኝ፡፡ ከንፈሬ ተጣብቆና ምላሴ አልላወስ ብሎ ቢያስቸግረኝም የለም እስካሁን አላመጧትም» ብዬ ዝም አልኩ። ውካታ በበዛበት አካባቢ ጥቂት ዝም ብለን ቆምን። ትላንት ማምሻዬን ሦስት ባለሙያ ጠበቆች አነጋግሬ ነበር። ሁሉም የሰጡኝ መልስ በጣም ተቀራራቢ ነበር፡፡ ቢበዛ አምስት ዓመት” አሉኝ። እንተስ ምን ይመስልሃል?» ብሎ ዐይኔን ማየት ጀመረ።
«እኔ ምን ዐውቃለሁ፡፡ ማንም ቢሆን ከራሱ ላይ ይልቅ በሌላው ላይ
መፍረድ ይቀልለዋል። የፍርድ ሰጪዎቹን ማንነት ስታየው ግን አምስት ዓመት
የሚበዛ አይመስልም፡፡ ቢሆንም ለእኔና ለእርሷ እያንዳንዱ ደቂቃ የሕይወታችን
ማሻከሪያ ክፍለ ጊዜ መሆኗ ነው» ብዬ ዝም አልኩ፡፡
«መቼም ቢሆን» አለ ጉልላት ወደድክም ጠላህም ምን ጊዜም ቢሆን ሕግ አለ። በሕጉም የሚጠቀሙና ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ አሉ። አህያና ጅብ
ባንድ ላይ ሕግ አያረፉም፡፡ ለጨቋኝና ለተጨቋት በአንድ ጊዜ በእኩልነት
የሚያገለግል ሕግ የለም፣ አልነበረምም፡፡ ሕግ ስለተፃፈ ብቻ ሕጋዊ አሠራር አለ
ማለት አይቻልም። እኔና አንተ ባለንበት ሥርዓተ ማኅበር ውስጥ እጀግ በጣም
አያሌ ባለሥልጣኖችና አጫፋሪዎቻቸው በልዩ ልዩ የእሠራር ስልትና ሥልጣን
ፈጠር ከለላ ከሕግ በላይ የሆኑበትና የሚሆኑበት ሁኔታ እንዳለ መዘንጋት
የለበትም፡፡ ስለሆነም ሕግ በትክክለኛው መንገድ በሥራ ላይ እስካልዋለ ድረስ
የሌለ ያህል ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በስፋት የሚያነጋግግር ስለሆነ አሁን ከመጣንበት
ጉዳይ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት የለውም። ወደ መጣንበት ጉዳይ እንመለስ፡፡
ስለዚህ በሚሰጠው ፍርድ እንዳትገረም፡፡ የበዛ ወይም ያነሰ ሊሆን ይሆናል» ብሎ
ወደፊት ተራመደ፡፡ ርምጃዬን ከርምጃው ጋር አስተካክዩ ተከተልኩት።
ከእኛ ትንሽ ራቅ ብሎ አንድ ብረት ሽፍን ባለ ጥቁር ሰሌዳ አረንጓዴ መኪና ቆሟል፡፡ ጉልላት መኪናውን አሻግሮ እየተመለከተ «ለምንድን ነው አልመጣችም ያልከኝ? ያ እኮ ነው የወህኒ ቤቱ መኪና» ብሎ ጥሎኝ ሔደ፡፡
አልተከተልኩትም፡፡
መኪናው ውስጥ ከተቀመጠው ሰው ጋር ምን እንደተባባሉ ባይሰማም ጉልላት ትንሽ ራቅ ብሎ ተነጋገሩ። ወዲያው ወደ እኔ ዞር ብሉ ና ቶሉ በሚል አኳኋን ጠቀሰኝ እና ሄድኩ፡፡ እስረኞቹ ወደሚገኙበት አካባቢ እንደ ደረስን ዐይኔ
ያካባቢው የብርሃን መጠን ያነሣት ይመስል የውበት ሃያ መስኮቶቿ ተሸጎሩ።
አጠርጠር ያሉና በሰፊ የካኪ ጨርቅ ስልቻ ውስጥ የቆሙ የሚመስሉ
የወህኒ ቤት ሴት ወታደሮች እያንዳንዳቸው አጠር ያለ ዱላ ይዘው ቆመዋል። በአቅራቢያቸው አምስት ሴቶች ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል። የትካዜ እሳት ያነኮታቸው ይመስላሉ። ንዳድ እንደ ተነሣበት ሰው መላ ሰውነቴ ጋየ፡፡
የሕይወቴ ክፋይ የሆነችውና የማፈቅራት የወዲያነሽ አንገቷን ሰበር አድርጋና ጀርባዋን ለረፋዷ ፀሐይ ሰጥታ መሬት ትቆረቁራለች። ጉልላት ከሴቷ ወታደር ትንሽ ራቅ ብሎ በትሕትና እጅ ነሣ ራመድ ብዬ ከጎኑ ቆመኩ
በተከዘ ፊቱ ላይ ለማስደሰት የሚፍጨረጨር ፈገግታ እያሳየ «ከነዚህ

👍3❤1
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
አአድን
....ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት አካባቢ መርዕድ ከአንድ የሥራ ባልደረባው ጋር በመሆን በቀድሞው የዲላ ከተማ አውቶብስ መናኸሪያ ፊትለፊት ጥቂት ሜትሮች ወረድ ብሎ ከሚገኝ (አባይ ፏፏቴ ተብሎ በሚታወቅ ሆቴል በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ሻይ ይጠጣሉ። ፊታቸውን ወደ መናኸሪያው አድርገው ስለተቀመጡ አካባቢ ወለል ብሎ ይታያቸዋል፡፡ በጨዋታቸው መሀል ዓይንና
ቀልባቸው ወደ መናህሪያው ወርወር ሲያደርጉ አካባቢው ለየት ያለ ሁኔታ እየተፈጠረ መሄዱን፣ ሁለቱም በየግላቸው ያጤኑ ኗሯል ሰው በርከትከት እያለ መሄዱን ወንዶች ጋቢ ፣ ሴቶች ደግሞ ነጠላ እየለበሱ እጅብ እጀብ እያሉ መቆማቸው ያያሉ።
«ዛሬ ምን ችግር አለ?» ሲል የመርዕድ ጓደኛ ጠየቀ፡፡
እኔ እንጃ! ምናልባት ከሌላ አገር የሚመጣ አስክሬን ይኖር እንደሆነ፡፡» አለ መርዕድ ወደ መናኸሪያው እየተመለከተ፡፡
ከትንሽ ቆይታ በኋላ ከርቀት የሚሰማ የለቅሶ ድምፅ ከጆሮአቸው ጥልቅ አለ። የድምጹ አቅጣጫ ከተቀመጡበት ሆቴል በስተጀርባ ነው፡፡ መርዕድ
ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ የለቅሶ ድምጽ ወደተሰማበት መንገድ ወጣ በማለት ቁልቁል ሲመለከት አንዲት ሴት በሌሎች በርካታ ሰዎች ታጅባ ክንፏን ዘርግታ እያለቀሰች ወደ ላይ ወደ መናኸሪያው ስትገሰግስ አያት፡፡ወንድሜ ወንድሜ! እኔ
አፈር ልብላ! ወንድሜ እኔ ልደፋ! ወንድሜ…!» ስትል ይሰማዋል።
«አረ ወደዚህ ወደ መናኸሪያው እየመጣች ነው» ሲል መርዕድ ያየውን ሴትዮዋ ብዙም ሳትቆይ እነመርዕድ የነበሩበትን ሆቴል አልፋ ወደ መናኸሪያው ተጠጋች፡፡ በአካባቢው የነበሩ ስዎችም እየተላቀሱ ሲቀበሏት መርዕድና
ጓደኛው ተመለከቱ፡፡ «እስቲ ጠጋ ብለን እንጠይቅ!» ተባባሉና መርዕድና ጓደኛው ወደ መናኸሪያው አቀኑ። የመርዕድ ጓደኛ ወደ አንድ ትክዝ ብሉ ቆሞ የነበረ ሰው ጠጋ በማለት ችግር አለ እንዴ የኔ ወንድም?» ሲል ጠየቀው፡፡
«ስው አለቀ ይላሉ።» አለው ስውየው እዝን ባለ አነጋገር።
«ምን ሆኖ?
«በመኪና አደጋ፡፡
«የት?»
"ዝዋይ ያሜዳ በረሃ ላይ::» አለና «ከዚህ ከዲላ ወደ አዲስ አበባ ይሄድ የነበረ አንደኛ በራሪ አውቶቡስ ከሌላ መኪና ጋር ተጋጭቶ ነው አሉ። አለ ጉንጩን በመዳፉ ደግፎ ዘመም በማለት፡፡
«እንዴ!» አለ መርዕድ፡ ጓደኛው ዞር ብሎ መልከት ሲያደርገው የመርዕድ ፊት ልውጥውጥ ብሏል።
«የሄደ ዘመድ እለህ እንዴ?» ሲል ጠየቀው::
አንድ ጓደኛዬ ሄዷል፡፡
«በአንደኛው በራሪ?»
«እሱን እንኳ አላውቅሁም ጠዋት የሸኘው ሌላው ጓደኛችን ነው።» አለና መርዕድ እንዴት ይሻለኛል?» ሲል ጠየቀ ለጊዜው ምላሽ ባይጠብቅም::
«ጠዋት የሸኘውን ጓደኛህን ጠይቀዋ!» አለው ጓደኛው::
«ለመስክ ሥራ እንደሚሄድ ማታ ነግሮኛል። አሁን ከተማ ውስጥ
አይኖርም፡፡» አለ መርዕድ። ትናንት ምሽት ላይ የአስቻለውንም የበልሁንም የወጪ ግብዣ ጠጥቷልና በልሁ ከተማ ውስጥ እንደማይኖር ያውቃል።
አካባቢው በፍጥነት እየተለዋወጠ ሄደ:: ከዲላ ከተማ አራቱም ማዕዘን ወደ መናኸሪያው ሰው ይጎርፍ ጀመር፡፡ የዚያኑ ያህል አልቃሹ በዛና ጩኸት በረከተ
ድብልቅልቁ ወጣ፡፡ እንዳንዶቹ የዘመዶቻቸውን ዕጣ ፈንታ አውቀው አስከሬን ለማምጣት የኮንትራት መኪና ፍለጋ ይሯሯጡ ጀመር። አብዛኛው ግን ከአዲስ አበባ ወደ ዲላ በሚመጣው አውቶቡስ የሚመጣውን ሰው ይጠባበቃል፤ ሁኔታውን አይቶ
ወይም አውቆ ከሆነ ብሎ መረጃ ለማግኘት።
ወደ አስር ሠዓት አካባቢ ድንገት የአውቶብስ ጡርንባ እሩቅ ተሰማ። ልክ "አልቅሱ" የሚል ፊሽካ የተነፋ ይመስል ያ ሁሉ ሰው በአንዱ ጮኹ፡፡ እሪታና ኡኡታው ቀለጠ። በዚያ አላበቃም፣ ወደ አውቶብሱ መምጫ መንገድ ሩጫና
እሽቅድምድም ተጀመረ፡፡ አውቶቡሱ ከታች ከአዲስ አበባ መግቢያ በሆነው አስፋልት
መንገድ ላይ ገስግሶ ወደ መናኸሪያ መታጠፊያ በሆነችው አደባባይ ላይ ሲደርስ በህዝብ ተከበቀ፡፡ መሄጃ አጥቶ ቆመ:: በተሳፋሪና በጠባቂው ህዝብ መካከል መጯጯህ ተጀመረ። መኪና ወስጥ ያለው አንገቱን በመስኮት እያወጣ ምነው?
ምንድነው?» ይላል። ከውጭ ያለው ደግሞ እንዴት ነው? ሰው ተርፏል ወይ! ወዘተ» እያለ ይጮሀል። መሰማማትም መግባባትም አልተቻለም:: እንደ ምንም መግባባት ሲጀመር ደግሞ ለካ መኪኖቹ ተላልፈው ኖሮ ከአዲስ አበባ የመጣው
መንገደኛ ስለ አደጋው ምንም አልሰማም፡፡ እንደውም ከአውቶቡሱ ላይ እየወረደ
ቀድሞ ከነበረው መረጃ ፈላጊ ሕዝብ ጋር እየተቀላቀለ አብሮ ወለሌ ይል ጀመር።
ቀጣዩ አማራጭ በአለታ ወንዶ በኩል የሚመጣውን ሁለተኛ በራሪ መጠበቅ ብቻ መርዕድ በዚያ ጭንቀት ውስጥ ሆኖ መቆየት አልቻለም፡፡ ይህን ሁኔታ ለታፈሡ መንገር እንዳለበት አስበ:: ጊዜ አላጠፋም፣ ወዲያው ወደ ቤቷ በረረ። በሩጫው ወቅት ከቤቷ ስለ መድረሱ እንጂ ታፈሡ ትኑር ወይም አትኑር ምንም
የሚያስበው ነገር አልነበረም:: ብቻ ሲደርስ ምን ብሎ እንደሚነግራት ያስባል፡፡ ከታፈሡ ቤት ሲደርስ ልክ አሥር ሰዓት ሆኗል። ያገኛት ግን ታፈሡን ሳይሆን ያላሰባትን ሔዋንን ነው።
«ታፈሡ የለችም እንዴ?» ሲል እያለከለከ ሔዋንን ጠየቃት።
ምነው? አለችው ሔዋን ከሶፋ ላይ ብድግ ብላ፡፡ የመርዕድ ሁኔታ
አስደንግጧታል፡፡ ከማለክለኩም በተጨማሪ ፊቱን አልቦታል፡፡ ዓይኑም ፈጥጧል።
«አይ ብቻ- ደህና ነኝ::አለና መርዕድ ሶፋው ላይ ቁጭ አለ::
«አትመስለኝም መርእድ!»
ግን አንቺ በአሁኑ ሠዓት እንዴት እዚህ ልትገኝ ቻልሽ?» ሲል ጠየቃት መርዕድ እሱም በበኩሉ የሔዋንን ሁኔታ ሰለል እያደረገ። ሲያያት ሁኔታዋ ሁሉ አላማረውም፡፡ ስታለቅስ እንደ ዋለች ሁሉ ዓይኖቿ ቀልተው እንዲያው ያበጡ ይመስሳአሉ ። ከፊቷም ላይ ደስታ አይነበብም፡፡! ይቺ ልጅ ስለ አስቻለው ምን ሰምታ ይሆን? እያለ በልቡ ያስብ ጀመር፡፡ «ድንገት መጥቼ ነው፡፡» አለችው ሔዋን። ለጊዜው በዚያ ሠዓት እዚያ ቤት የተገኘችበትን ሁኔታ መዘርዘር አልፈለገም።
“ታፈሡ ስራ ሄዳ ነው?» ሲል ጠየቃት።
«አዎ፡፡» አለችና ሔዋን ግን ደህና እትመስለኝም መርዕድ ስትል
ሁኔታውን ሁሉ በዓይኗ እየሰለለች ጠየቀችው፡፡መርዕድም ልክ እንደ ሔዋን የሆዱን ምስጢር መዘርዘር አልፈልገምና የቻለውን ያህል ራሱን እያረጋጋ «ደህና ነኝ ስልሽ!» ዝምብሉ ጣሪያ ጣሪያውን
ይመሐት ጀመር፡፡ በመሀላቸው ፀጥታ ሰፈነ። በየሆዳቸው ግን የየግላቸውን ጉዳይ በመሀል ከውጭ በኩል የሰው ኮቴ ተሰማቸው። ሁለቱም ጆሮአቸውን
አቁመው ሲያዳሃምጡ ኮቴው እየቀረባቸው መጣ፡፡ አሁንም እርስ በእርስ እየተያዩ ሲያዳምጡ ታፈሡ ከቤት ውስጥ ዘው ብላ ገባች። የቸኮለችና የተጣደፈች ትመስላለች፡፡ ያ ብርቱካን የመሰለ ቀይ ፊቷ የባሰ ደም መስሏል፡፡ ዓይኗም ፈጧል።ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። በዚሁ ስሜት ውስጥ ሆና ሳታስበው መርዕድን በዚያ ሠዓት እዚያ ቤት ውስጥ ማግኘቷ የበለጠ እስደነገጣትና
«አንተ መርዕድ!» አለችው ጮክ ባለ ድምጽ።
«ወይ» መርዕድም ደንግጦ ብድግ አለ::
«ምንድነው ከተማ ውስጥ የሚወራው?»
«አደጋ ደረሰ ይላሉ። አንቺም ስማሽ እንዴ?» አላት በድንጋጤ አስተያየት

👍8