#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
«በፍፁም» አለ ዶክተር ደጀኔ እርግጠኛ ስለመሆኑ ለመግለፅ ጭንቅላቱንም እየወዘወዘ"ቀድሞ ነገር ውድድር አልተካሄደም ነገሩ ከላይ ተወስኖ ነው የመጣው አለው»
«ከላይ ማለት?» ሲል ጠየቀ አስቻለው በእርግጥ የቃሉ ትርጉም ጠፍቶአልና አልነበረም።
ነገር ግን ከዚያው ከአውራጃው ወይስ ከክፍለ ሀገር አለያም ከማዕከል ለማለት ፈልጎ እንጂ።
«ብቻ ከላይ ሌላው ምን ያደርጋል።»ካለ በኋላ ዶክተር ደጀኔ ድንገት ወደ ሌላ ሐሳብ ውስጥ ገባና መሬት መሬት እያየ
ይተክዝ ጀመር አስቻለው በበኩሉ በንዴት አንጀቱ ተቃጥሎ በእግሩ መሬቱን መታ መታ ያደርግ ጀምር።
«ግን አስቻለው» ሲል ዶክተር ደጀኔ ለራሱ አለና አስቻለውንም አነቃው።
«አቤት ዶክተር»
«ለመሆኑ እዚህ ሆስፒታል ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ ሰራህ ?»
«ሰባት አመት አለፈኝ!»
«ዝውውር ሞክረክ አታውቅም?»
«አልሞከርኩም»
«አሁንስ ለመሞከር አታስብም?»
«ይሳካል ብለህ ነው ዶክተር?»
«እርግጠኛ ነኝ በዚህ ከተማ ውስጥ የምትጦራቸው አሮጊትና ሽማግሌ የለህም።»
«ምንም » አለ አስቻለው፡፡ ግን ደግሞ ወድያው ሔዋንን ጨምሮ ታፈሡ በልሁና መርዕድ ትዝ አሉት፡፡ ከእናትና አባቱ ባልተናነሰ ሊለያቸው የማይፈልጋቸው የፍቅር ቤተሰቦች ናቸውና።
እንደኔ እንደኔ ከዚህ ሆስፒታል ወደሌላ ብትዛወር የተሻለ ርምጃ መስሎ ይታየኛል፡፡ ለምን መስለህ አስቻለው!»
«እሺ ዶክተር »
አስቻለው በጽሞና እያዳመጠው "መሆኑን የተረዳሁ ዶክተር ደጀኔ ሀሳቡን ቀየር አደረገና በቅድሚያ አንድ ነገር ልጠይቅህና አንተም ትክክለኛውን ንገረኝ::ሲል ፈገግ እያለ በማየት አሳሰበው::
«ምንም አልደብቅም ዶክተር፣»
«ለመሆን እዚህ ከተማ ውስጥ 'የሴት ጓደኛ አለች» ሲል አሁንም ፈገግ ብሎ እያተ ጠየቀ። አስቻለው ድንግጥ ብሎ ድንገት ስሜቱ ሲለዋወጥ አይቶ
ዶክተር ደጀኔ አሁንም ፈገግ እያለ “ምነው ደነገጥክ?» ሲል ደግሞ ጠየቀው፡፡
አስቻለው የምንተነፍረቱን «አይ …ማለት» አለና እንደ መርበትበት
ከአደረገው በኋላ «መኖር አለችኝ ግን ምነው?» ሲል ዶክተር ደጀኔን መልሶ ጠየቀው።
«እስከገባኝ ድረስ አልጅቷ ጋር አብራችሁ አይደላችሁም፡፡ ልጅቷ
ምትኖረው ከእህቷ ጋር ነው። ልክ ነኝ?»
«እንዴት ልታውቅ ቻልክ ዶክተር»
ዶክተር ደጀኔ በያዘው እስርቢቶ ጠረጴዛጠን መታ መታ አደረገና እንደገና ወደ አስቻለው ቀና በማለት «ቅድም በቤታችንና በግቢያችን ወስጥ የሚከናወነውን እንኳ አናውቅም ብዬህ ተማምነንስ እልነበረም!» እለው፡፡
«ልጅቷ ገና በልቤ ወስጥ ነው ያለችው»
ዶክተር ደጀኔ ድንገት ሃ..ሃ..ሃ...ሃ ብሎ ሳቀና አየህ! ግማሽ አካሏ ከውጭ ቀርቶ ኗሯል አለና አሁንም ሃ ሃ ሃ ሃሃ
«የ'ሷን ነገር ለምን አነሳኸው አለው አስቻለው ዶክተሩ ሳቁን ሲጨርስ፡፡
«ግን እንደው አርግዛብህ ታዉቃለችን።?»
«በፍጹም ዶክተር እንዲያውም አታምነኝ እንደሆነ እንጂ ልጅቷ ገና ድንግል ናት።»
ዶክተር ደጀኔ እንደ መደነቅ ብሎ «ድንግል! ድንግል!»
«ከልቤ ነው የምነግርህ ዶክተር»
ዶክተር ደጀኔ በመገረም ዓይነት ፍዝዝ ብሎ አስቻለውን ሲመለከት ቆየና ራሱንም ወዘወዘ «ገና ብር አምባር ሰበረልዎ እንላለና»
«እዚያ ካደረሰን! አለና አስቻለው ግን የእሷን ነገር ለምን እንዳነሳህ
አለገባኝም ዶክተር አለ አሁንም ዓይኑን በዶክተር ደጀኔ ላይ እያንከራተተ፡፡
«ምክንያት አለኝ!»
«ምን?»
«ያልተወለደ ገዳይ የሆንከው ከእሷ ጋር በተገናኘ ሁኔታ ነው፡፡
እኔ ግን ነገሩ አሉባልታ ስለመሆኑ በትክክል ገብቶኛል፡፡» አለው፡፡
«ምኑ ከምን ጋር ተገናኝቶ?»
አሁን አሁን እየተበሳሽ ነው::
«ምኑም ከምንም!» አለና ዶክተር ደጀኔ በአጭር ቃል መለሰለትና ራሱ ቀጠለ፡፡ «እንደሚመስለኝ የአንተና የልጅቷ እህት ግንኙነታችሁ ጥሩ አይደለም፡፡
የልጅቷ እህትና ባርናባስ እንደሚግባቡስ ታውቃለህን?»
«ሰሞኑን ሲደንቀኝ የሰነበተው ይህ ነው ብትነግረኝ ይከብድህ ይሆን?"
«ብዙ የማውቀው ነገር የለም፡፡ አንድ ቀን ግን እኔና ባርናባስ ከተማ ውስጥ አብረን ስንዘዋወር መንገድ ላይ ከአንዲት ሴት ጋር ተነጋግሮ ወደኔ እንደመጣ
«ህቺ ሴት መምህርት ናት፡ ያቤሎ በነበርኩበት ወቅት እሷም እዚያ ስለነበረች እንተዋወቃለን፡፡ ብቻ ነው ያለኝ አለው ዶክተር ደጀኔ፡፡ አስቻለው የሁለቱን የትውውቅ መሠረት በማውቁ ሳይሆን አይቀርም አንገቱን ደጋግሞ ነቀነቀና «አሁን ብዙ ነገር ገባኝ ዶክተር፡፡» አለው::
«አዎ እስቻለው! የጓደኛህ እህትና ባርናባስ ከፈጠሩት ግንኙነት በመነጨ ነው ያልወሊደ ገዳይነትህ የተወራብህ፡፡ ይህን ደግሞ የነገረኝ ራሱ ባርናባስ ነው!
መምህርቷ ነገረችኝ ብሎ። ግን ደግሞ ይህን ሁሉ የምነግርህ ብዙ ጊዜ አካሄድ ፊትለፊት ስለሆነ ድንገት ሳታውቀው እንዳትጠለፍ ለጥንቃቄ ይረዳሃል ብዬ ነውና
አስብበትት፡፡ የዝውውሩንም ጉዳይ ችላ ባትለው መልካም
ይመስለኛል።» አለው፡፡
እስቻለው በረጅሙ ተንፍሶ ጥቂት ካሰላሰለ በኋላ
«የሰሞኑ እንቆቅልሽ ገና ዛሬውኑ ተፈታልኝ ዶክተር» ብሎ ከንፈሩን ነክሶ ጣሪያ ጣሪያ እያየ በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ሄደ፡፡ የዶክተር ደጀኔን የዝውውር ሃሳብ በቀላሉ አልተመለከተውም፤ እንዲያውም በርካታ ነገሮች በተዘዋዋሪ መንገድ ይህንኑ ጉዳይ ሲያሳስቡት ሰንብተዋል። በልሁና መርዕድ ታፈሡና ሽዋዬን ለማስታረቅ ከሞከሩ በኋላ
ተመልሰው የገለፁለት ነገር ሔዋን በሃሳብ ምን ጊዜም ከአንተ ጋር ናት። ሸዋዩ ባለችበት አካባቢ ግን እንጃ….” የሚል ፍሬ ሃሳብ የነበረው ነው። ከዚያም በላይ
የእርቅ ሙከራ በተደረገ ሶስተኛ ቀን ረፋዱ ላይ ሔዋን ሳያስባት ለዚያውም ፊቷ በእንባ ረስርሶ ወደ ቤቱ መጥታ ነበር።
«ምነው ሔዩ» ነበር የአስቻለው ጥያቄ።
«እንካ ይኸን ወረቀት አንብብ ብላ አንዲት ወረቀት ሰጠችው።
አስቻለው ወረቀቷን ገለጥ አድርጎ ሲያነብ የሚከተለውን መልዕክት
አገኘባት።
«ለተከበራችሁ አባትና እናቴ ለአቶ ተስፋዩ ይርጋ እና ለወይዘር ስንዱ በላቸው፣ለጤናችሁ እንደምን አላችሁ። እኔ ግን በጣም ተቸግሬያለሁ። እናንተንም እሷንም
ለመርዳት ስል ሔዋን የተባለች ልጃችሁን ወደ ዲላ ይዣት መጥቼ ነበር። እሷ ግን ትምህርቷን እርግፍ አድርጋ ትታ ሥራዋ ወንድ ማባረር ብቻ ሆኗል። እንዲያውም
መዘዟ ለኔ ተርፎ ችግር ላይ ወድቄአለሁ።ከመቸገሬ የተነሳ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከቤቴ ላባርራት ነው ።ምናልባት ልጃችን ባክና መቅረት የለባትም የምትሉ ከሆነ ከሁለት አንዳቹ መጥታችሁ ውሰዷት። መጥተን እንወስድም ካላችሁ ውርድ ከራሴ።
ልጃችሁ ሽዋዬ ተስፋዬ
አስቻለው ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ በኋላ በንዴት እሳት ለብሶ እሳት ጉርሶ ፈጠን ባለ አነጋገር ሴትዮዋ ምን እያለች ነው?» ሲል ሔዋንን ጠየቃት፡፡
«እኔ እንጃ አስቹ፣ ግራ ገባኝ» ሔዋን እያለቀሰች፡፡
«የት አገኘሽው?»
«ዛሬ ጠዋት ሥራ ስትሄድ ረስታው መሰለኝ አልጋዋ ላይ ተቀምጦ አገኘሁት።»
«ቀዳድጄ ልጣለው?»
«ተው አስቹ፣ ነገር ይባባስብኛል። ግን አንድ ነገር ላማክርህ?

👍3