አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
502 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...በዲላ ከተማ ዜሮ አምስት ቀበሌ ውስጥ ስምንተኛ መንገድ ላይ ፊቱን ለማታ ፀሃይ ሰጥቶ በተገነባው በወይዘሮ ዘነቡ አሰግድ ግቢ ውስጥ በስተጓሮ በኩል ያለው የሽዋዬና የሔዋን መኖሪያ ቤት ከጣሪያና ግድግዳው በስተቀር በውስጡ ይታይ የነበረ ትዕይንት ሁሉ ዛሬ መልኩን ቀይሯል፡፡ የሁለት የእትማማች
ጣውንቶች መኖሪያ ሆኖ ደስታ ርቆታል፡፡ በፍቅር ተስፋ ለምልመው የነበሩ ልቦች ዛሬ የሀዘን ድባብ ጥሎባቸዋል፡፡ በሳቅ ይፍለቀለቁ የነበሩ ጥርሶች ዛሬ ተከድነዋል።
ፏ ብለው ይታዩ የነበሩ ፊቶች ዛሬ ግን አኩርፈው እንደ ኩልኩልት
ተንጠልጥለዋል። የአስቻለው እግሮች ተሰብስበው ቤቱ እንግዳ ናፍቆታል።
ሽዋዬ ፣ ሔዋንና አስቻለው በየራሳቸው የሀሳብ ጎዳና ይነጉዳሉ፡፡ የሽዋዬ ግን
ከሁሉም በተለየ ሁኔታ እንቅፋት የበዛበት ሆኗል፡፡ የሚቆጫት አስቻለውን ማጣቷ ብቻ አይደለም፤ በእሷ እምነት አስቻለውን የነጠቀቻት እህቷ በመሆኗ ከዚሁ ጋር ተያይዘው ይመጣሉ ብላ የምታስባቸው ማህበራዊ ቀውሶች ከወዲሁ ያስጨንቋት ይዘዋል። አስቻለውን በማፍቀሯና ከግንኙነታቸው መጥበቅ የተነሳ የኔ ነው ብላ
ለሌላ ሰው ያወራችም ይመስላታል። ዛሬ በእህቷ ተነጠቀች የሚል አሉባልታ
የሚነሣ እየመስላት ትሳቀቃለች:: ምናልባት አስቻለውና ሔዋን ወደፊት ቢጋቡ
“ትልቋ እያለች ትንሿ፣ ሥራ ያላት እያለች ተማሪዋ አገባች የሚል የዘመድ አዝማድ ሹክሹክታም ሲነሳባት ይታያታል፡፡ ወደፊት በሚፈጠር ቤተስባዊ ግንኝነት ሁልጊዜ እያየችው በቅናት እየተቃጠለች ልትኖር ነው። ዛሬ የገጠማትን የስሜት ሰቀቀን ሁልጊዜ እያስታወስች እንዴት መኖር እንደምትችል ይቸግራታል።
አዕምሮ ደግሞ ትንሽ የሀሳብ ቀዳዳ ከከፈቱለት ያቺነ በማስፋት የጭንቅ ተባይ እየፈጠረ ያቅበጠብጣልና የሽዋዬ መንፈስ በስጋት ተወጠረ፡፡ ቀኑን ያለ ዕረፍት
ሌሊቱን ያለ እንቅልፍ ታቀያይረው ጀመር፡፡

ከዚህ ሁላ ጭንቅ የሚገላግላት ብቸኛ መንገድ አስቻለውና ሔዋንን
ማለያየት ብቻ መሆኑ ታያት፣ ጨለማ የሆነባት ግን ማለያያው ዘዴ፡፡ አንዳንዴ ሔዋንን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ መፍትሄ የሚሆን መስሎ ይታያታል፡፡ ነገር ግን አስቻለው ሔዋንን፣ ሔዋን ደግሞ አስቻለውን እስካሉ ድረስ ከዚያስ ሄዶ ቢያመጣት? ወይም አስቻለው ከቤቷ ድርሽ እንዳይል ማድረግ ብትሞክርስ? ያም
አያዋጣ፡፡ ሔዋን ራሷ ወደ እሱ ቤት ልትሄድ ትችላለች። እንደ በግ አትዘጋባት፣ እንደ ጥጃ አታስራት፡ ወይ ደግሞ ስራዋን ትታ እሷን ስትጠብቅ አትውል! ሁሉም
መንገድ የማይጨበጥ ህልም ሆኖባታል::

ከመዋል ከማደር አንድ የተስፋ ብልጭታ ብቻ ማየት ጀመረች፡ ለዚያውም ይህ ነው ብላ የምትጠብቀው ግልጽ ውጤት ሳይኖር፡፡ ያም ቢሆን ከራሱ ከአስቻለው ያገኘችው ፍንጭ ነው። ከጥቂት ወራት በፊት አንድ ቀን እሷና አስቻለው በአንድ
ቡና ቤት ውስጥ ይዝናናሉ፡፡ የተቀመጠበት ቦታ መስኮት አጠገብ ስለነበረ መንገዱ
ይታያቸዋል። አስቻለው ድንገት ባርናባስን መንገድ ላይ ያየውና ሽዋዬን ጎሽም አድርጎ «ያን ሰውዬ ተመልከች» ይላታል፡፡
«የቱን?»
«ደማቅ ስማያዊ ካኪ የለበሰውን፡፡
«እሺ አየሁት»
«ዲላ ሆስፒታል ውስጥ ድርብ ስልጣን ያለው ሰው ነው፡፡» ካለ በኋላ በእሱና በባርናባስ መሀከል ያለውን ያለመግባባት የመነሻ ጀምሮ አሁን እስካሉብት ጊዚ ድረስ ያለውን ሁኔታ እንደ ቀልድ ያጫውታታል። ይህ ነገር በሸዋዬ ልብ ውስጥ አለ።

ግን ደግሞ አስቻለው አላወቀም እንጂ ሸዋዬና ባርናባስ በደንብ
ይተዋዉቃሉ፤ ያውም ከስምንት ዓመታት በፊት ጀምር፡፡ ሰበቡ ሸዋዩ ትምህርቷን እንደ ጨረሰች መምህርነት ተመድባ ወደ ያቤሎ መሄዷና ባርናባስ ደግሞ በወቅቱ
የግሉ ጤና ጣብያ የአስተዳደር ክፍል ኃላፊ ሆኖ ይሰራ የነበረ መሆኑ ነው። ሸዋዬ ያቤሎ ደርሳ ከመኪና እንደ ወረደች ማረፊያ የት እንደምታገኝ ስትጠይቅ የመኪና
ተራ ልጆች ወደ አንድ የማረፊያ ቦታ ይወስዷታል፡፡ ቤቱ ሆቴል ቤት አልነበረም፤ ነገር ግን ግቢው መስክ በርካታ በአልቤርጎ ዓይነት የተስሩ ክፍሎች አሉት።
ድንገተኛ እንግዳም ያርፍባቸዋል። ለወር ኮንትራትም ይሰጣል፡፡ ባርናባስም ከእነዚያ ክፍሎች እንዷን በኮንትራት ይዞ" ብቻውን ይኖር ነበር::

ሸዋዬ ከእነዚያ ክፍሎች በአንዷ ውስጥ አድራ በማግስቱም እዚያው ትደግማለች። በሦስተኛ ቀንም እንዲሁ። በኋላም ከዚያ የተሻለ መኖሪያ እንደማታገኝ
ሲገባት ልክ እንደ ባርናባስ ክፍሏን በኮንትራት ይዛ ትቀመጣለች፡፡ ከመዋል ከማደር ከየባርናባስ ጋር ይተዋወቃሉ፡፡ ቀስ በቀስ ይተራረባሉ። ይግባቡና ይፋቀራሉ፡፡መጨረሻ ላይ ልክ እንደ ደባል ሆነው አብረው መኖር ይጀምራሉ፡፡ ባርናባስ
በዕድሜው ጠና ያለ ቢሆንም ለሽዋዬ ግን ይመቻታል። እሷም ላእሱ ትሞቀዋለች።ያ ሁሉ ሲሆን ባርናባስ ባለ ትዳርና የልጆች አባት መሆኑን እንዲሁም ቤተሰቦቹ ዲላ
ከተማ ወስጥ እንደሚኖሩ ሸዋዬ አታውቅም ነበር። በእርግጥ ወደ ዲላ አዘውትሮ እንደሚሄድ ታውቃለች፡፡ ነገር ግን ለስራ ጉዳይ እያለ ስለሚያታልላት እሷም
አትጠረጥር ነበር።

በዚሁ ሁኔታ ለአንድ ዓመት ያህል ከቆዩ በኋላ ድንገት የባርናባስ የሰባት ወር ህጻን ልጁ ይሞትና ከዲላ መልዕክት የተቀበሉ የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች
ወርዶው እንዲደርሰው ያደርጋሉ። በወቅቱ ሸዋዬ ማመን ቢያቅታትም ነገር ግን
በማግስቱ ጀምሮ ከባርናባስ ቤት ወጥታ ትሄዳለች፡፡ በዚያው ትቀራለች::ፍቅራቸውም ይቋረጣል።

ባርናባስ ከልጁ መሞት በኋላ በያቤሎ ብዙ አልቆየም፡፡ እድገትና ዝውውር አግኝቶ ዲላ በመግባት ከቤተሰቡ ጋር ይቀላቀላል። ይሁንና የባርናባስና የሸዋዬ
መለያየት የከረረ ጠብ አላስከተለም፤ ቆይቶም ቢሆን የፍቅር ውጭ ያለ ግንኙነት
ማስቀጠል የሚችል እርቅ ፈጽመዋል። ሸዋዬ ዲላ ከመጣችም ወዲሀ ከአለፈ ገደም እየተገናኙ ሰላምታ ይለዋወጣሉ። አስቻለው ስለ ባርናባስ ያወራት በነበረ ጊዜ ሸዋዬ ይህን ሁሉ በሆዷ ይዛለች፡ እሷ ግን ስለ ባርናባስ ለአስቻለው ትንፍሽ አላለችም::

ምን ሊያደርግላት እንደሚችል በውል ባይታወቃትም ሸዋዬ ለዛሬው ጭንቋ መላ ስታፈላልግ ባርናባስ ትዝ ብሏታል፡፡ የአስቻለው አለቃ ነውና፣ በዚያ ላይ አይስማሙምና፣ ለችግሬ መፍትሄ የሚያመጣ መላ ያፈላልግልኝ ይሆን?› እያለች
ለአንድ ወይም በሌላ ጉዳይ በልቧ ታውጠነጥነው ጀመር።
ነጋሪ
የሸዋዬ ሀሳብ በዚህ መልኩ ሲነጉድ ሔዋን ግን ስለ ጭንቀቷ እንጂ ችግሯን ሰለምታቃልልበት መንገድ የሚታያት አንዳች ነገር የለም፡፡ ሆነም አልሆነ ነገሩ ይበርድላት ዘንድ መጓጓት ብቻ ነው። ከዚያ ባለፈ አስቻለው ወደዚያ ግድም ድርሽ እንዳይል የጠበቀ አደራ በታፈሡ በኩል ልካበታለች:: ነገር ግን አደራውን
ስለመቀበሉ እርግጠኛ አይደለችም ድንገት የመጣ እንደሆነ እያለች ከመሳሳቀቅ
አልዳነችም፡፡

እስቻለው ደግሞ ያኮረፈው ወይም የሚያኮርፈው ሰው ስለሌለ ቤቴ ሰላም ይሁን እንጂ እዕምሮው ግን እረፍት አጥቷል። ዓይኖቹም ተለያይተዋል። በአካል አልጋው ላይ ተኝቶ ሀሳቡ ያለው በሸዋዬ ቤት ወስጥ ነው፡፡
በልሁና መርዕድ የነገሩት የሽዋዬና የሔዋን የተበላሸ ግንኙነት የጭንቁ ሁሉ መነሻ ነው። በዚያ ላይ ወደዚያ ቤት ድርሽ እንዳይል ሔዋን በታፈሡ በኩል ልካበት
👍7