አትሮኖስ
281K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
483 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...«አስቻለው የሔዋን አባት መሆኑን ማን ነገረሽ አንቺ?» ስትል ጠየቀቻት።
«ነዋ! እንዴ ሆእ!» አለች ሕጻኗ አሁንም፡፡
ሸዋዬ የበለጠ ግራ ገባት፡፡ ህጻኗ ያለ አንድ መነሻ ያን ንግግር
እንዳልተናገረች ገመተች፡፡ ወይዘሮ ዘነቡንና ሰራተኛ'ቸውን አስበቻቸው፡፡ ለጊዜው
ግን «እንዴ! እንዴ.! እንዴ.! እያለች ቤቷን ከፍታ ገባች። አልጋዋ ላይ ቁጭ አለችና
«እንዴት ነው ይኸ ነገር? በማለት ቁና ቁና እየተነፈሰች ለረጂም ጊዜ ቆየች።
ሔዋን የገዛቻቸውን የወጥ ቅመማ ቅመሞች በዘንቢል ይዛ ወደ ቤት ስትገባ የሽዋዬ ዓይን ፈጥጦ አገኘችው፡፡ ሁኔታዋ አላማራትም'ና
«እት አበባ አለቻት ዘንቢሏን እንደያዘች ከፊቷ በመቆም። ሸዋዬ ግን ገልመጥጥ ከማድረግ በቀር ምላሽ ሳትሰጣት ቀረች::
«ምነው?» አለቻት ሔዋን አሁንም፡፡
«አትተይኝም? አለቻት ሽዋዬ ቁጣ በተቀላቀለበት አነጋገር፡፡ ወዲያው ወደ አልጋዋ በመውጣት አንሶላና ብርድ ልብስ ውስጥ ገብታ ሽፍንፍን ብላ ተኛች።
ሔዋን የእህቷ ሀኔታ ግራ አጋባት፡፡ በዚያው ልክ ፈራች፡፡ ድንጋጤም
ተሰማት፡፡ ወደ ጓዳ ገብታ ዘንቢሏን ከአስቀመጠች በኃላ ጓዳው በር በኩል አንገቷን ብቅ እያረገች የሸዋዬን ሁኒታ ትከታተል ጀመር፡፡ አይታ አይታ ምንም ለውጥ
ልታገኝ ባለመቻሏ የምሣሤ ወጥ ስራዋን ጀመረች፡፡
ሽዋዬ ከተኛች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀስቀስ ያለችው የወይዘሮ ዘነቡ የቀትር ቡና ሲወቀጥ ነው፡፡

ወትሮም ቢሆን በተለይ ቅዳሜና እሁድ ከምሳ በኋላ ለሚጠጣው ቡና ሽዋዬ ወደ ወይዘሮ ዘነቡ ቤት ትጠራ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ገና ሳትጠራ ለመሄድ ብድግ አለች፡፡ ያቺ ህጻን በዚያ ቤት ውስጥ ሲወራ ያልሰማችውን ነገር
ከየትም ከምጥታ ልትነግራት እንዳልቻለች ገምታ የወሬዉን ምንጭ ከስሩ ለመጎርጎር ወስነኝ፡፡ ፒጃማ ዓይነት ጀወለል ቢጤ የቤት ልብስ እንደለበሰች ነጠላ
ጫማ አድርጋ ወደዚያው አመራች በጓሮ በኩል ወደ ሳሎን በሚያስገባው የወይዘሮ
ዘነቡ ቤት በር በኩል እየገባች፡-
ደህና ዋላችሁ» አላቻቸው፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ነጭ በነጭ የሆነ የሐገር ልብሳቸውን ለብሰው ሶፋ ላይ ጉብ ተብለዋል ፡፡ ቀይ ናቸው:: የአንገታቸው ንቅሳት ከቅላታቸው ጋር አለላ መስሎ ይታያል። የአገጭ ስር ጅማቶቻቸው ገተር ገተር ማለት የዕድሜያቸውን መግፋት ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ጥቁር መነፅራቸው ከቀይ ፊታቸው ጋር ደምቆ ሲታይ ዕድሜያቸውን ወደ ኋላ ለመመለስ የሚታገል ይመስላል፡፡ ኑሮአቸውን የቤታቸው
ሁኔታ ያመለክታል፡፡ በዘመናዊ ዕቃ የተሞላ ነው። የሳሎኑ ስፋት ፈረስ ያስጋልባል የሚባል ዓይነት ነው፡፡ በቡና ንግድ የናጠጡ ሀብታም የነበሩት ሟቹ ባለቤታቸው
ያደራጁላቸው ንብረት ነው።
‹ደህና ዋልሽ የኔ ልጅ!» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ «ይኸውልሽ፣ የጎረቤት ደንቡ ይኸ ነው፡፡ ጥሪ የሚፈልግ ከሆነ ግን ንፉግነቱን ያመለክታል፡፡» እሷት ሸዋዬ
ሳትጠራ በመምጣቷ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ::
«አንዳንዴም ቀላዋጭ ያሰኛል!»
«እሱም የስስታም ሰው አባባል ነው፡፡ በእኛ ቤት ደሞ እንደዚያ ብሎ ነገር የለም፡፡ ለወደፊቱም ይልመድብሽ፡፡» ብለው ፊታቸውን ከሶፋው አጠገብ በነጭ ረኮበት ላይ ወደ ተደረደረው ሲኒ መለስ አደረጉ ሰራተኛቸው ፋንትዩ ቡናውን ጀበና ውስጥ እየጨመረት ናት፡፡
ጉዳይ ስላለኝም ነው ቀድም ብዬ የመጣሁት፡፡» አለች ሽዋዩ በወይዘሮ ዘነቡ ፊትለፊት ሶፋ ላይ ተቀምጣ ዓይን ዓይናቸውን እያየች፡፡
"ምነው" ድህና አሏት ወይዘሮ ዘነቡ ፊታቸውን ወደ ሽዋዩ መለስ
አድርገው
«ተቀይሜብዎታለሁ::»
«ውይ ነኔ ልጅ!ድንግል ትባርክሽ ቅያሜሽን ፊት ለፊት ተነገርሽኝማ
ድንግልም ትወድሻለች፡፡» አሉና «ግን ሳላውቅ ምን እጥፍቼ ይሆን ሲሉ አንገታቸውን ዘመም አድርገው እያዩ ጠየቋት።
«አንድ ነገር እያወቁ ደብቀውኛል።»
«ምን ይሆን የኔ ልጅ»
«በኔ ሰበብ ግቢዎት ሲደፈር እያዩ ዝም ማለትዎ!»
«ምን ያገባው ሰው ነው ግቢዩን የሚደፍረው?»
ብልግና ከተፈጸመበት ያው ተደፈረ ማለት አይደል?»
«የምን ብልግና?»
«አይዋሹኝ እማማ ዘነቡ!»
«ድንግል ትመስክር ምንም የምዋሽው ነገር የለም፡፡ ከንቺ ግን ምን ሰምተሸ ነው?» ሲሉ መነፅራቸውን ወለቅ አድርገው እያዩ ጠየቋት::
«ይቺ የኔ እህት ከዚያ አስቻለው ከሚባል ልጅ ጋር እየባለገች መሆኑን ሳያውቁ ቀርተው ነው?» ስትል ጠየቀቻቸው አንገቷን ጠመም አድርጋ በጎ አስተያየት እየተመለከተቻቸው::
«ውይ! ይኼ ነው እንዴ ነገሩ?» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ ቀለል አድርገው
«ለመሆኑ አንቺ እስተ ዛሬ ምንም የምታውቂው ነገር አልነበረም?» ሲሉ ጠየቋት፡፡

«ምኑን?» አለች ሸዋዬ እንደ አዲስ፡፡ ነገሩ እርግጥ መሆኑ ሲገባት በድንጋጤ ሰውነቷ ሁሉ ክፍልፍል ያለ መሰላት።
«ስለ ሁለቱ ልጆች ፍቅር ነዋ!»
ምናልባት እኩያሞች ስለሆኑ ነው መሰል የእነሱን ፍቅር ልቤ
ይወደዋል፡፡»
«እማማ ዘነቡ!» ስትል ጮኸች ሸዋዬ ድንገት። ዓይኗ በወይዘሮ ዘነቡ ላይ ፍጥጥ አለና መላ ሰውነቷንም ያንቀጠቀጣት ጀመር።
«ወይ የኔ ልጅ!»
«ምን እያወሩ እንደሆነ ያውቃሉ?»
«ዘባርቄ ይሆን እንዴ ልጄን» አሉና ወይዘሮ ዘነቡ እውነትም ድንግጥ
ብለው ሽዋዬን ትኩር ብለው ያዩዋት ጀመር።
«ቀላል!»
«ምን አልኩኝ?»
«ሊያጋቧቸው እስበዋል እንዴ?»
«ኧረ ምን ቁርጥ አድርጎኝ ልጄ! ቢሆን አይከፋም ማለቴ ነው
እንጂ!»
ሸዋዬ ውስጧ ተቃጠለ፡፡ አረረች። በወይዘሮ ዘነቡ ሀሳብ ከመበሳጨቷ የተነሳ ያን ከሰል ላይ የተጣደ ጀበና ብድግ አድርጋ በመሀል እናታቸው ላይ
ብትከስክሰው እየተመኘች «የሚሉት ነገር ሁሉ ሊገባኝ አልቻለም!» አለቻቸው
ዓይኗን ፍጥጥ፣ ጥርሷን ግጥጥ አድርጋ እያየቻቸው፡፡
ግልጥልጥ አድርጌ እየነገርኩሽ! እንዴት እይገባሽም?» አሏት የሸዋዬ የወስጥ ስሜት ያልገባቸው ወይዘሮ ዘነቡ፡፡
«ቆይ ግን አለችና ሸዋዪ ንዴት ያወላከፈውን ጉሮሮዋን «እህህ» ብላ ሞረደችና የሁለቱን መፋቀር እንዴት አወቁ?» ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
«ድንግል ምስክሬ ናት፤ በበኩሌ ክርና መርፌ ሆንሁ በዓይኔ አላየሁም፡፡ ግን መቸም ትንሽ ሳይያዝ ብዙ አይወራም ብዬ ነው፡፡» ብለው ፊታቸውን ወደ
ረከቦቱ መለስ አደረጉ፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ አንድ ነገር በሆዳቸው አለ። አንድ ቀን አስቻለውና ሔዋን ተዘናግተው ሳይሆን አይቀርም በሩን መለስ እንኳ ሳያደርጉት ቆመው ሲሳሳሙ
ሰራተኛቸው ፋንዩ በበር በኩል አለፍ ስትል አይታቸው ኖሯል። ወይዘሮ ዘነቡ በአቅራቢያዋ ስለነበሩ ወደ ጆሮትእው ጠጋ ብላ በሽንሹክታ ዓይነት እማማ ሂዱ
ወደ እታ አበባ በር አጠገብ፤ የሚያዩት ነገር አለ ብላቸው ነበር፡፡ እሳቸውም ሌላ ነገር መስሏቸው ቤቱን ሰለል እያረጉ በበሩ አጠገብ አለፍ ሲሉ ፋንትዩ ያየችውን
ያያሉ፡፡ በእርግጥ በወቅቱ በፋንትዪ ድርጊት ተቆጥተው ነበር፡፡ ግን ደግሞ ያዩትን
ማመን ችለዋል፡፡

«ለመሆኑ ይህን ወሬ የሚያወራው ማነው?» ስትል ሽዋዬ ጠየቀቻቸው፡፡
ሠፈር ሙሉ ነዋ! እኔ እንደውም የስማሁት በወይዘሮ እልፍነሽ ቤት
ውስጥ ሲወራ ነው፡፡» አሏት።
👍3