አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


....ከቤተሰቦቼ ጋር የነበረኝ ግንኙነት እምብዛም ሳያፈነግጥና ሳይቀርብ፣
ሳይጥምና ሳይሆመጥጥ ቀጠለ የወዲያነሽ አንድ ዓመት ከመንፈቋ እንደ አንድ የደስታ ቀን ፈጥኖ ዐለፈ፡፡ አንድ ቀን እሑድ ከሰዓት በኋላ ከአንድ ጓደኛዬ
የተዋስኩትን መቅረፀ ትርዒት (ካሜራ ወይም ፎቶ ማንሻ ይዤ ወደ ዕጓላ
ማውታ ሄድኩ

ከዚያ ቀደም ሲል ከወሰድኩለት ልብሶች መካከል ጥሩዋን ልብስ አልብሽ አነሣሁትና እንዴት እንደሚደርሳት ቀደም ብዪ ጨርሼ ስለነበር በሳምንቱ እሑድ
የልጇን ፎቶ ይዤ በጉልላት መኪና ወህኒ ቤት ሄድኩ። እንደ ተለመደው !
፣አስጠራኋት፡፡ የአጥሩን አግዳሚ ዕንጨት ተደግፋ ጥቂት አወራራን ድንገት !ሳታስበው ፎቶግራፉን ከኪሴ መዥረጥ አደረግሁና «በይ እስኪ በቃሽ እዪና ጥገቢው፡ ነጋ ጠባ፣ ልጄ! ልጄ ስትይ!...» ብዬ በወታደሪቱ ኣስተላላፊነት
አቀበልኳት፡፡ የወረቀቱን ግራ ቀኝ ጠርዝ በሁለት እጆቿ ይዛ ትኩር ብላ
ተመለከተችው:: ፊቷ ላይ ስታሸበሽብ የቆየችው ኮስማና ፈገግታ ደብዛዋ ጠፋ።

ወዲያው ብርሃኗ በጥቅጥቅ ጭጋግ እንደ ፈዘዘ ጨረቃ ፈዘዘች። እንባዋ
በዐይኖቿ ዙሪያ ግጥም አለ፡፡ አቀረቀረች። በሰንበሌጥ ላይ እየተንኳላላች እንደምትወርድ ጠፈጠፍ እንባዋ ጉንጯን ሳይነካ ከትንሿ ወረቀት ላይ ተንጠባጠበ።

ከሩኅሩኅ የእናትነቷ ባሕሪ የመነጨ የፍቅር ኩልልታ ስለነበር ለመጪው
ጊዜ የሚቀመጥ የትዝታ ጥሪት አስቀመጥኩ፡፡ ደግማ ደጋግማ ሥዕሉን ሳመች።እምብዛም ነገሬ ሳትለኝና እህ! ብላ ሳታዳምጠኝ ተሰናብቻት ተመለስኩ።

ከሌላ ስድስት ወር በኋላ የወዲ ያነሽ ሁለት ዓመት ሞላት።

እሑድ ከሰዓት በኋላ ነበር፡፡ የዕለቱን ጋዜጣ እያነበብኩ እንግዳ መቀበያ
ክፍል ውስጥ ተቀምጬ ሳለሁ የውብነሽ አጠገቤ ተቀመጠች። የያዘችውን
የአማርኛ ሰዋሰው መጽሐፍ እንደተገለጠ አጭሯ ክብ ጠረጴዛ ላይ ዘረጋችው።

ዐይኔ ተወርውራ የጊዜ ተውሳከ ግሥ የሚለውን ርዕስ አየች። ለነገርና
ለወሬ ማነሣሻ ይሆነኝ ዘንድ «ይልቅስ የአኳኋንና የሁኔታን ተውሳከ ግሥ
አታጠኚም» ብዬ መጽሐፉ ውስጥ የማነበው ያለኝ ይመስል አገላብጬ
አስቀመጥኩት። «እኔ የጊዜ ተውሳከ ግሥ አልዘለቅ ብሎኛል። አንተ ደግሞ
ሌላውን ትለኛልሀ» አለችና እጄ ላይ የነበረውን ጋዜጣ ወስዳ የመጀመሪያን ገጽ አርእስቶች በለሆሳስ አነበበች፡፡

«ሥራ አለብሽ እንዴ የውቢ? ከሌለብሽ አንድ ቦታ ደረስ ብለን እንምጣ» ብዬ ጸጉሬን አሻሸሁት፡፡ ጋዜጣውን አጣጥፋ አስቀመጠችው:: «እሺ እንሂድ፡፡ ይህን ማታም ቢሆን ልፈጽመው እችላለሁ» ብላ ከንፈሯን በምላሷ እያራሰች።
«ምንም እንኳ ለጊዜው አሳዛኝ መስሎ እንደሚታይሽ ባውቅም የኋላ ኋላ
ግን ያስደስትሽ ይሆናል» ብዩ ኩራትን ለመግለጽ በሚያስችል ወፍራም ደርባባ
ድምፅ ተናገርኩ። ካንተ ጋር ከሆንኩ ምን ያሳዝነኛል? በመጨረሻ የሚያስደስተኝ
ነገር ሁሉ ደስ ይለኛል፡፡ እንሂድ ካልክ ልብሴን ልቀያይርና እንሂድ» ብላ ተነሣች፡፡ እንዲሁ ገባ እንዳለች ዘርፈጥ ብላ የተቀመጠችበት ቀሚሷ ከበስተኋላዋ
ልሙጥነቱ ጠፍቶ ወደ ልዩ ልዩ አቅጣጫ የተሰበጣጠረ ጭምድ መስመሮች
ሠርቷል። ልብሷን ለመቀያየር ወደ መኝታ ቤት ስትገባ እኔም ጸጉሬን ለማበጠር
ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡

የልብሴን መስተካከል በመስተዋት ከተመለከትኩ በኋላ ጸጉሬን በደረቁ
እበጥሬው ወጣሁ፡፡ ደረጃውን ወርጀ እንደ ጨረስኩ ደረሰችብኝ።

ምንም እንኳ ወዴት እንደምንሄድ ባታውቅም «የምንሔድበት ቦታ ብዙ
ሰዎች አለበት እንዴ?» ብላ ጠየቀችኝ፡፡ «ማንም የለም። የምንሄደው አንድ እሳዛኝ
ሰው ለማየት ነው» ብዬ አለባበስና አረማመዷን እያየሁ መንገድ ገባን፡፡ ደማም ወጣትነቷና እንስታዊ ውብ ቅርጺ ማራኪነት ሰጥቷታል፡፡ ፈገግ ስትል ፍልቅቅ የሚሉት ነጫጭ ውብ ጥርሶቿ ከደም ግባቷ ጋር የአተር አበባ አስመስለዋታል፡፡

እግረ መንገዳችንን ልዩ ልዩ የሚባሉ ነገሮች ገዛሁላት። ዐሥር ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በታክሲ ዕጓለ ማውታ ደረስን፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት
አስከትዩ በመሄዴ ያ ዘወትር ብቻዬን ስመላለስ የሚያየኝ ዘበኛ የውብነሽን
በማየቱ የመገረም ፈገግታ ታየበት።

አብዛኛውን ጊዜ ከቤቱ ታዛ አካባቢ ከብዙ ከልጆች ጋር ተቀምጦ ሲጫወት ከሩቁ የማውቀው በልብሱ ስለነበር ሜዳው መኻል ቆም እያልኩ የቢቶቹን የፊት ዙሪያ ተመለከትኩ፡፡ ብዙ ልጆች ጨዋታቸውንና ልፊያቸውን እየተዉ አዩን፡፡ ወደ መኝታ ክፍሉ ይዣት ገባሁ። እሱኑ ከሚያካክሉ ሁለት ልጆች ጋር ወለሉ ላይ ተቀምጦ እየተኮላተፈ ይጫወታል። ሁለቱ ልጆች መለስ ብለው ካዩን በኋላ ጨዋታቸውን ቀጠሉ፡፡ የእኔ ልጅ ዐይኖች ግን እኔ ላይ
ተተከሉ፡፡ ጎንበስ ብዪ አነሣሁት፡፡

አባባና እማማ የሚባሉ ቃላት የማያውቀው፣ የወላጅ ፍቅር ያልቀመሰው
ልጄ እንደ ወፍ ዘራሽ የመስክ አበባ ያምራል። ለምን ወደ ዕጓለ ማውታ እንደ
መጣች ግራ የገባት የውብነሽ በመጠኑ ደንገጥ አለች፡፡ ወደ እርስዋ ዞሬ ትከሻዋን
ቸብ ካደረግሁዋት በኋላ እስኪ ይህን ልጅ ተመልከችው የውብነሽ ቆንጆ ልጅ
አይደለም እንዴ? ብዬ ጠየቅኋት። እ..ብላ ዝም አለች።

ሰውነቷ በጥርጣሬና በሐሳብ የተጠመደ መሰለ፡ ድንገት ከእንቅልፏ ነቅታ ባጋጣሚ ያየችው ይመስል ሁለት እጆቿን ዘርግታ «እውይ እማምዬ ማማሩ! ደስ ማለቱ?» ብላ ከእጁ ላይ ወስዳ ታቀፈችው፡፡

በፊቱ ላይ አንዳችም ሌላ ለውጥ ሳይታይና ፈገግታው ሳይቀንስ ዝርግፍ
ብሉ ወደ እርሷ በመሄዱ በጣም ደስ አለኝ፡፡ እንዲያውም እዚያች ጠባብ ደረቷ
ላይ ልጥቅ አለ፡፡ ነገር ግን ልጄን ለመጀመሪያ ጊዜ ያቺ የማፈቅራትና
የምንሰፈሰፍላት የወዲያዬ ሳትሆን እኅቴ አቅፋው በማየቴ በፋይዳ የለሽ ጥላቻ
ተናደድኩ፡፡ ጉንጮቹን ሳም ሳም ካደረገች በኋላ ፊቷን ወደ እኔ መለስ አድርጋ
<<የማን ልጅ ነው ?» ብላ በጓጓ ስሜት ጠየቀችኝ። የምናገረው እውነተኛና ርግጠኛ እንዲመስል ለመመለስ የማሰላሰያ ጊዜ አልወሰድኩም፡፡ «አንቺ የማታውቂው አንድ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ የዚህ ልጅ አባት ማለቴ ነው። ትዝ እይልሽም ይሆናል እንጂ እኛም ቤት አንድ ሁለት ቀን ያህል መጥቶ ነበር» ካልኩ በኋላ የነገሩን
ድምጥማጥ ይበልጥ ለማጥፋት «ነገር ግን ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት
በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሞቷል፡፡ ልጁ ግን ለጊዜው አሳዳጊ ዘመድ በማጣቱ
ይኸው እዚህ በምታይው ሁኔታ በማደግ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ልጅ አባት በጣም
ግሩም ሰው ስለ ነበር እሱን በማሰብና ለልጁ በማዘን ብቻ አልፎ አልፎ ብቅ
እያልኩ እጠይቀዋለሁ፡፡ ጉልላትም አንዳንድ ቀን እየመጣ ያየዋል» ብዬ ዋሸኋት፡፡ግንባሩን ሁለት ጊዜ ያህል ስማ ውብ ዐይኖቹን ባንጸባራቂ ሸጋ ዐይኖቿ ትኩር ብላ ተመለከተቻቸው::

«ምነው አንተም እንዲህ የሚያምርና የሚያስጐመዥ ልጅ በነበረህ» ብላ
እንደ ወይን እሽት የሚያስጐመዡትን ጉንጮቹን ሳመቻቸው:: ንግግሯ ለጊዜው
ረግቶና በርዶ የቆየውን የሕሊናዬን ባሕር በብስጭት ማዕበል አረሰው፡፡

“ምናልባት ሚስት ባገባ ማስቴን በርግዝናዋ ወራት ከቤት አታባርሯት
እንደሆነ ነዋ እንዲህ ያለ ልጅ ማግኘት የሚቻለው» ብዩ በሽሙጥ መለስኩላት።
ድንገተኛው የንግግሬ ይዘት ፊቷን አስቀጨመው:: ልጁን ከሰጠችኝ በኋላ
አንገቷን ስብራ አቀረቀረች። ከጥቂት ዝምታ በኋላ ከወለሉ ላይ ቃላት
እየለቃቀመች ትናገር ይመስል ወለሉን እያየች «ያ ያለፈው ሁሉ ሌላ ጉዳይ
ነው፡፡ የማይገናኙ ነገሮች አታገናኝ እኔን ምን አድርጊ ትለኛለህ? አንተ ከእኔ
የበለጠ ብልህ መሆንህን ዐውቃለሁ አባታችን ቢሰማ ኖሮ በአንተና በእርሱ
መካከል ትልቅ ጠብና ማለቂያ የሌለው
👍41
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


...ስድስት ወራት አለፉ። ጌትነት የስድስት ወር ደሞዙን በላ፡፡ በዚች አጭር ጊዜ ውስጥ ራሱን በብዙ ነገር ቀየረ። አዲስ ልብስም ገዛ፣ ዩኒቨርሲቲ በሶሻል ሳይንስ "አካውንቲንግ ዲፓርትመንት" ትምህርቱን
ጀመረ። በወር ከሚያገኘው ሁለት መቶ ብር ደመወዝ ላይ ለእናቱ ተቆራጭ አድርጎላት ለአባቱ የገባውን የአደራ ቃል ለማክበርና ትምህርቱን በሚገባ በመከታተል በመጀመሪያው ሰሚስተር ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ቻለ። በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ስም ዝርዝር በሚለጠፍበት ሠሌዳ ላይ የጌትነትን ማንነት ለማያውቁት ሁሉ አስተዋወቀ። "እንኳ” ደስ አላችሁ!!" በሚለው ማስታወቂያ ስር ስማቸው ከተዘረዘረው ጥቂት ተማሪዎች መካከል ጌትነት መኩሪያ ግንባር ቀደሙ
ሆነ፡፡ በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች "ኤ" በማገኘቱ ስሙ በግሬት ዲስቲንክሽን ሊስት ውስጥ ተካተተ፡፡ የክፍሉ ተማሪዎች “እሱ ማን ነው?" ብለው ውስጥ ለውስጥ ሲነጋገሩበት ከረሙ:: በኋላም እሱ አንገቱን የደፋው፣ እሱ ትህትና ያልጎደለው፣ እሱ ብቻውን ገብቶ ብቻውን የሚወጣው በመጨረሻ ወንበር ላይ የሚቀመጠው ያልጠበቁት ሰው ሆኖ
አገኙት፡፡ በአብዛኛዎቹ ዘንድ በአድናቆት መታየት ጀመረ። ከሁሉ የበለጠ ስለሱ ማንነት ለማወቅ የተጨነቀችው ግን አማረች ነበረች፡፡ አማረች በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ በሂሳብ ሠራተኛነት ተቀጥራ የምትሰራ በትምህርቱ ጎበዝ የሆነ ስው የምትወድ ቆንጆ ልጅ ናት። ያንን ከፍተኛ ፉክክር ያለበትን የዩኒቨርሲቲ ህይወት ለመምራት ተማሪ እርስ በርሱ
ይፈላለጋል፡፡ በተለይ ጎበዝ ተማሪ አድኖ ለመያዝ ሩጫው ብዙ ነው። ለዚህ ነበር ያንን አመርቂ ውጤት አምጥቶ ለአካውንቲንግ የመጀመሪያ አመት የዲግሪ ተማሪዎች ቁንጮ የሆነውን “እንኳ” ደስ አለህ” የተባለውን የክፍሏን ተማሪ ማንነት ለማወቅ የተጣደፈችው። ብዙ ጊዜ አልወሰደባትም። አወቀችው፡፡አማረች የቀይ ዳማ ናት። ሰውነቷ ሞላ ቁመትዋ ዘለግ ያለ ፀጉርዋ እንደ ስንዴ ነዶ ጀርባዋ ላይ ዘፍ ያለ እንደ ስሟ
መልኳ የሚያምር፡፡ የመጀመሪያው ትምህርት ክፍለ ጊዜ ደርሷል። የዛ
ሬውን 'ሌክቸር የሚስጠው መምህር ዘግይቶ ነበር፡፡ አማረች ሆን ብላ ያንን ጎበዝ ተማሪ፣ ያንን ቁመቱ ዘንከት ያለ የሚስብ ልጅ ልትተዋወቀው ፈለገች፡፡ በቀጥታ ሄደችና ከአጠገቡ ባለው ባዶ ወንበር ላይ ዐይኖቿ” ተከለች።ሌሎቹ ተማሪዎች ደብተሮቻቸውን ገልጠው መምህራቸውን በመጠባበቅ ላይ ነበሩ፡፡
"ሰው አለው?" በጣቷ ባዶውን ቦታ እየጠቆመች በፈገግታ ተጥለቅልቃ
ጠየቀችው፡፡ ቀና ብሎ አያት። ደነገጠ፡፡

"የለው...እ? አለው!" ከሩቁ የሚጠላት ልጅ. በአብዛኛው መልኳ ሸዋዬን

የምትመስለው ልጅ.. ቀድሞውኑ ሲያያት ያልወደዳት ልጅ የምትቀመጥበትን የፊት ወንበር ትታ እሱ አጠገብ ከኋላ ለመቀመጥ መፈለጓ ድንገተኛ ሆኖበት መልሱን ለመስጠት ተደነጋገረው፡፡ የልጁ ሁኔታ አማረችን ገረማት። ሰው የሌለበትን ወንበር አለበት በማለት አሳፈራት። ማንም
እንደዚህ አሳፍሯት አያውቅም፡፡ እየሳቀችና እየተገላመጠች ወደ ቀድሞ
ቦታዋ ሹክክ ብላ ተመለሰች። "እሽ" ብላ አፍራ ምልስ ስትል አሳዘነችውና ተፀፅቶ ራሱን ወቀሰ፡፡ ለምን ያንን ቦታ እንደፈለገችው ገርሞት በዐይኖቹ ተከተላት።

የትምህርቱ ክፍለ ጊዜ አብቅቶ መውጣት ሲጀምሩ አማረች ቀስ ብላ ጭለማውን ተገን አድርጋ የጌትነትን እንቅስቃሴ ትከታተል ነበር። የዩኒቨርሲቲውን ምድረ ግቢ እንደለቀቀ ግራ ቀኝ ሳይል ታክሲውን ይዞ በረረ፡፡ በሚቀጥለውም በወዲያኛው ቀንም ተከታተለችው። ብቻውን እየወጣ ታክሲውን ተሳፍሮ ይከንፋል። ባደረገችው ተደጋጋሚ ጥናት የሴትም ሆነ የወንድ ጓደኛ እንደሌለው አረጋገጠች። አማረች በምቾት ያደገች የሚያምር ተክለ ቁመና ያላት የጠበቃው የአቶ በልሁ ወዳጄነህ
የመጀመሪያ ልጅ ናት። ከሁሉ የበለጠ የሚስበው ውብ ተክለ ቁመናዋ ነው። አነስ አነስ ያሉት ሳቂታ ዐይኖቿ ጉርድ ያለው አፍንጫዋ ከትንሿ ክብ ፊቷ ጋር በህብረት ሲታዩ በትልቅ ሰውነት ላይ የተቀመጠ የህፃን ልጅ ፊት ያስመስላታል፡፡ አማረች ከቁንጅናዋ ይልቅ የደስ ደሷ ከሩቁ ይጣራል። ጉንጮቿ እንጆሪ ይመስላሉ፡፡ ጌትነት እንደዚያ ይጥላት እንጂ ብዙዎቹ ወንዶች ሲያይዋት ጉሮሯቸው እስከሚጮህ ድረስ ምራቃቸውን ይውጣሉ፡፡ አቤት በተለይ ሱሪ ለብሳ የመጣች ዕለት! በዐይኖቻቸው
ሱሪዋን አውልቀው ያንን የሚገላበጥ ዳሌዋን በምናብ እየቃኙ በስሜት
ከወንድነታቸው ጋር ሲታገሉ ይውላሉ። ያያት ወንድ ሁሉ ቢመኛትም አማረች ግን ቁጥብ ነበረች፡፡ በቀላሉ የምትገኝ
አወጣ የተባለ ወንድ ሎተሪ እንደወጣለት ተደርጎ የሚጋነንበት ሁኔታ ነበር፡፡ ሲበዛ ፈታኝ ሰው ነች። ይሄ ሁሉነትዋ ግን በጌትነት ዘንድ ዋጋ አጥቷል። ሰው መስላ አልታየችውም። በሸዋዬነት ውስጥ የበቀለች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ሲል ደምድሟል።ይቺ በመማሯ ሽዋዬ ደግሞ በማይምነቷ መካከል ያለ ልዩነት እንጂ በሴትነት ባህሪያቸው አንድ ናቸው ብሎ የራሱን ድምዳሜ ሰጥቷል። በመልክ በጣም ይቀራረባሉ። በሌላ ፀባያቸውም ያው ናቸው የሚል እምነት ነው ያደረበት፡፡ አማረች አብዛኛው የሀሳብ ክፍሏን ለጌትነት አሳልፋ ሰጠች። ወደ ክፍል ሲገባና ከክፍል ሲወጣ ደጋግማ በስውር ተከታተለችው። ብቸኛ መሆኑን ካረጋገጠች በኋላ "ምን ችግር ቢኖርበት ይሆን?" ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ ቀርባ ልታነጋግረውና ስለማንነቱ በሰፊው ለማወቅ ተንስፈሰፈች። ናቅ ስላደረጋት ነው መስል ምን ሲደረግ? የሚል እልህ ተናነቃት። ሌሎች ለሷ ያላቸውን ግምት በሚገባ ታውቃለች። ታዲያ ጌትነት
የምን ትዕቢት ነው? በትምህርቱ ጎበዝ ስለሆነ? መልከ መልካም ስለሆነ?
እኛ ስላለችው? ወይስ ሰው መስዬ ስላልታየሁት? ራሷን በብዙ ጥያቄዎች ዙሪያ በጭንቀት እንድታሽከረክር አደረጋት። ልቧ ዋተተ። እሱ እሷን በሚሸሽበት፣ በሚጠላበት ልክ እሷ ደግሞ እሱን ለመተዋወቅ ልቧ
ሽፈተ።

ይቀጥላል
👍1