አትሮኖስ
281K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
482 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


ከቶሎሳ ጋር በስልክ ካወራ በኋላ የአብዱላሂ ፊት አልፈታ አለ፡፡ሊያሳይ የሚሞክረው ፈገግታ ሁሉ የውሽት መሆኑ እያስታወቀበት መጣ፡፡ ጌትነት ግራ ተጋባ፡፡ ተጨነቀ። ከሽመልስ አይዞህ ባይነት በስተቀር የሚተማመንበትና ተስፋ የሚያደርግበት ነገር አጣ፡
"ወይ ፈጣሪዬ አብዱላሂም ሰለቸኝ ማለት ነው? ምን አባቴ ባደርግ ይሻለኛል? ምነው አልሰማህ አልከኝ የአባቴ አምላክ? የሱን አደራ ለመወጣት ነውኮ የምጨነቀው። የዚያች ምስኪን እናቴ አምላክ እባክህ እርዳኝ ይህንን በሃሳቡ ማውጣትና ማውረድ የጀመረው በዚህ ሁለትና ሶስት ቀን ውስጥ የአብዱላሂ ፀባይ ሙሉ ለሙሉ ስለተቀየረበት ነው።

የስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ የማታ ትምህርት ፕሮግራም ክፍል አመልካ
ቾች የማትሪክ ውጤቶቻቸውንና ትራንስክሪፕቶቻቸውን በማቅረብ እንዲ
መዘገቡ ማስታወቂያ ለጥፏል። በዚሁ መሃል ሽመልስ የጀመረው ክርክር
የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥበት ዕለት እየደረሰ ነበር፡፡ ያ ቀን ለጌትነት
የሞት ወይም የሽረት ቀን ነበር፡፡ የምሥራች ወይንም የመርዶውን ዜና
የሚሰማበት ዕለት። ክርክሩ ሲጧጧፍ ሽመልስ አስመላሽ አንድ እውነትን ይዞ፣አቶ አባይነህና አቶ ማንአየህ ደግሞ አድልዎንና ሃስትን ተገን አድርገው ሲያፋልማቸው የቆየው ጉዳይ የሚቋጭበት ቀን መጣ፡፡

አቶ ሽመልስ ያንን ግትር አቋሙን እንዲለውጥ አቶ አባይነህ ብዙ ጥረት
አድርገው ነበር። ሲጨንቃቸው በመለማመጥና በመለመን ትንሽ ፋታ
ሊያገኙ ደግሞ በዛቻና በማስፈራራት ሊያንገዳግዱት ሞክረው ነበር፡፡
ሊወድቅላቸው ግን አልቻለም፡፡ በአማላጅ ብዙ ሞከሩ። ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ! አቶ አባይነህ ካደረጓቸው በርካታ ሙከራዎች መካከል በአንዱ ይሸነፍልኛል ብለው ገምተው ነበር። ግን በቀላሉ የሚሸነፍ እጁን የሚሰጥ ሆኖ አልተገኘም። ባቀረበው አቤቱታ መሰረት የድርጅቱ የበላይ ሃላፊ ስለጌትነት መኩሪያና ስለ ፀሃይ አስፋው ቅጥር ጉዳይ የሚያጣራ ሶስት አባላትን የያዘ ኮሚቴ አቋቋሙ። ኮሚቴው ማስታወቂያው ከወጣ በት ቀን ጀምሮ ፀሀይ አስፋው የቅጥር ፎርማሊቲ እንድታሟላ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሂደት ማጣራት ጀመረ።

ኮሚቴው የመጀመሪያውን የፅሁፍ ፈተና ውጤትና ለመጨረሻ ጊዜ በተካሄደው የቃለ መጠይቅ ፈተና የተያዘውን ቃለ ጉባኤ በዝርዝር በማጥናት የውሳኔ ሃሳቡን አጠናቅሮ አቀረበ፡፡ ኮሚቴው የመጀመሪያ የፅሁፍ ፈተና የወሰዱትን የስድስቱንም ተፈታኞች የፈተና ወረቀቶች የመረመረ ሲሆን ፀሃይ አስፋው ዶሮ የጫረው ከሚመስለው የእጅ ጽሁፉ ጀምሮ በይዘቱ
በጣም ደካማ ለነበረው ሥራዋ የተሰጣት ከፍተኛ ውጤት አድሎአዊነትን
የሚጠቁም ሆኖ አግኝቶት ነበር። የቃለ መጠይቆቹ ፍሬ ሃሳቦችና የተሰጡት ነጥቦች አቶ ሽመልስ የያዘውና እነ አቶ አባይነህ የያዙት ፍፁም የማይመሳሰል ከመሆኑም በላይ ፀሀይ አስፋው በብርቱ ክንድ እንደተደገፈች የሚያሳዩ በርካታ ጠቋሚ መረጃዎች ተገኙ። ከዚህ በመነሳትም የመጨረሻውን ውሳኔ ለመስጠት እንዲያስችል በሁለተኛነት ደረጃ ተመዝግቦ ወድቋል የተባለው ጌትነት መኩሪያና ፀሀይ አስፋው ብቻ በድጋሚ ተጠርተው ሌላ የመመዘኛ ፈተና እንዲሰጣቸው ኮሚቴው የውሳኔ አስ
ተያየት አቀረበ፡፡ የበላይ ሃላፊውም የኮሚቴውን ሃሳብ አፀደቁት። የኮሚ
ቴውንና የዋና ስራ አስኪያጅን ውሳኔ በሰማበት እለት ሽመልስ የተሰማውን ደስታ የተመለከተ ጉድ ይል ነበር ለእውነት ሲል ተከራክሮ ለሀቅ ሲል ታግሎ የድል ፍንጭ ያየበት ዕለት በመሆኑ ደስታው ልዩ ነበር።ሀቅ ከሃሰት ውቅያኖስ ውስጥ ብትወድቅም ትሟሟ እንደሆነ እንጂ እን
ደማትጠፋ አምኖ በልቡ ተስፋን አሳደረ፡፡ “ዘመዱ ስለሆነ ነው። በእናቱ በኩል የባሌ ሰው ነው፡፡ የአጎቱ ልጅ ነው..." እያሉ አንዳንዶቹ ማስወራት ጀምረው ነበረና በእርግጥም ጌትነትን ያለችሎታው ሊረዳው ጥብቅና የቆመለት መሆን አለመሆኑ የሚታወቅበት፣ እሱ ወይንም እነ አቶ አባይነህ የሚጋለጡበት፣ እንክርዳዱና ስንዴው የሚለይበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በመድረሱ ደስታው ገደብ አልነበረውም፡፡ በዚሁ መሰረት ጥሩ የብቃት መለኪያ ፈተና በገለልተኛ ወገን እንዲዘጋጅ ተደረገ፡፡ ፀሀይ ውሳኔው ከተ
ሰጠበት ቀን ጀምሮ የሞላችው የቅጥር ፎርማሊቲ ዋጋ የሌለው መሆኑ
ተገልፆ ለአዲሱ ፈተና ራሷን እንድታዘጋጅ በተነገራት ጊዜ ከድንጋጤዋ የተነሳ ዕቃ ሰበረች።

እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል አይዞህ ተስፋ አትቁረጥ በማለት ሞራል ሲስጠው የቆየው ሽመልስ የክርክሩ ውጤት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያሳውቀው እንደነገ ሆኖ ዛሬ አብዱላሂና ቶሎሳ በያዙት ቀጠሮ መሠረት ተገናኝተው አምሽቶ መግባቱ ነበር። አብዱላሂ ለንቦጩን ጥሏል። ፊቱ እንደ ፊኛ ተነፍቷል። ጌትነት ደነገጠ፡፡
“እንደምን አመሸህ ጋሼ አብዱላሂ?" አለው ፈራ ተባ እያለ፡፡
"ደህና ነኝ!" መልስ አሰጣጡ እንደምንስ ባድር ምናባክ አገባህ? የሚል
ትርጉም ነበረው፡፡ እንደ ውሻ ቡፍ! አለበት።
“ምነው ጋሼ አብዱላሂ ያስቀየምኩህ ነገር አለ እንዴ? ለትንሽ ጊዜ እንጂ
አላስቸግርህም እኮ ቁርጤን እስከማውቅና ጋሼ ሽመልስ የመጨረሻውን ውጤት እስከሚያሳውቀኝ ድረስ ብቻ ብትታገሰኝ ምን አለበት? ሸክም እንደሆንኩብህ ይሰማኛል"
“ወሬውን ተዋ! ወላሂ እኔ ስው እንደዚህ ወሬኛ ሲሆን አልወድም፡፡ሁሉ ነገሬ ፊት ለፊት ነው፡፡ ግልፅ ነኝ፡፡ ግልፅ ሁን!"
“አልገባኝም?" በጭንቀት።
“ከቶሎሳ ጋር በምንድነው የተጣላችሁት?!" ቱግ! አለበት።
"በም.ም. . .ምን. . ነው የተጣላነው?" አፉ ተንተባተበ፡፡
“ውሽታም!! ውሽታም ነህ አንተ! ወላሂ! ውሸታም ነህ፡፡ አምንህ ነበር ታማኝነትህ ግን በገንዘብ ላይ ብቻ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ በቂ አይደለም፡፡
ከሌላው ልክስክስ ሌብነት የገንዘብ ሌብነት ይሻላል። ቶሎሳ ወንድምህም
አባትህም ነው ሸዋዬ ደግሞ እህትህም እናትህም ነች አይደለም?!"
"ልክ. . ልክ ነው ጋሼ አብዱላሂ ልክ ነው" በጭንቀት ዐይኑ ቁልጭ ቁልጭ አለ፡፡አብዱላሂ ለምን እንደዚህ በሃይለ ቃል እንደተናገረው ወዲያውኑ አወቀ። በልቡ ሸዋዬ እግዚአብሔር ይይልሽ አለ፡፡ የአልኮል ትሩፋት አይ ስካር? በዚህ አይነት ስንቱ በስካር ቤት ንብረቱ ፈርሷል? ሲል ራሱን ጠየቀ። ወስዋስ ሸዋዬ ወስውሳ ወስውሳ ባስፈፀመችው ድርጊት ምክንያት ጦሱ በየሄደበት ቦታ ሁሉ እየተከተለው ነው። ከሷ ቤት አምልጦ ሲመጣ ይኸውና ዛሬ ደግሞ ጣጣው ተከትሎት አብዱላሂ ቤት እየደረሰ ነው፡፡
ወይ ፍርጃ! ያ ቀን ምን ዓይነት ቀን ነው? ያንን ጠላ ጠጥቶ ድርጊቱን የፈፀመበትን ቀን በጥላቻ አስታወሰው። አብዱላሂ የጌትነት ፊት መለዋወጡን አፉ መንተባተቡን ሲመለከት ቶሎሳ ያጫወተው በሙሉ ትክክል መሆኑን አረጋገጠ፡፡

ንጂስ የሆንክ ሰው ነህ! ሀራም ሥራ! በጣም ብልግና ነው የፈፀምከው።
በል ከነገ ጀምሮ ቤቱን ልቀቅልኝ! ዐይንህን ማየት አልፈለግም! ጓዝህን ጠቅልለህ ወደምትሄድበት ሂድ! እስከዛሬ ያገለገልክበት ዋጋህን ያውልህ!"ሁለት ባለ አሥር ብር ኖቶች ከኪሱ አወጣና ወደ እጁ ዘረጋለት።
“የለም! የለም ግድ የለም ጋሽ አብዱላሂ" ዐይኖቹ እንባ አቀረሩ። ልሳኑ ተዘጋ፡፡ እንደምንም ጉሮሮውን ጠራረገና
“እስከዛሬ ድረስ የዋልክልኝ ውለታ ቀላል አይደለም፡፡ የሰራሁት ተቀጥሬ
ሳይሆን በችግሬ ምክንያት እንድታስጠጋኝ ላምኜህ ነውና ልትከፍለኝ አይገባም፡፡ ውለታህን እግዚአብሔር እንጂ እኔ ልከፍለው የምችለው አይ
ደለም። አንድ የምለምንህ ነገር ቢኖር ግን አሁን አንተ የምትለኝ ሁሉ በፍፁም እኔነቴን ነፃ አእምሮዬን የሚመለከት አለመሆኑን እንድታውቅ ልኝ ነው። ሰው የሚከስሰውና
👍3
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


«በፍፁም» አለ ዶክተር ደጀኔ እርግጠኛ ስለመሆኑ ለመግለፅ ጭንቅላቱንም እየወዘወዘ"ቀድሞ ነገር ውድድር አልተካሄደም ነገሩ ከላይ ተወስኖ ነው የመጣው አለው»
«ከላይ ማለት?» ሲል ጠየቀ አስቻለው በእርግጥ የቃሉ ትርጉም ጠፍቶአልና አልነበረም።
ነገር ግን ከዚያው ከአውራጃው ወይስ ከክፍለ ሀገር አለያም ከማዕከል ለማለት ፈልጎ እንጂ።
«ብቻ ከላይ ሌላው ምን ያደርጋል።»ካለ በኋላ ዶክተር ደጀኔ ድንገት ወደ ሌላ ሐሳብ ውስጥ ገባና መሬት መሬት እያየ
ይተክዝ ጀመር አስቻለው በበኩሉ በንዴት አንጀቱ ተቃጥሎ በእግሩ መሬቱን መታ መታ ያደርግ ጀምር።
«ግን አስቻለው» ሲል ዶክተር ደጀኔ ለራሱ አለና አስቻለውንም አነቃው።
«አቤት ዶክተር»
«ለመሆኑ እዚህ ሆስፒታል ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ ሰራህ ?»
«ሰባት አመት አለፈኝ!»
«ዝውውር ሞክረክ አታውቅም?»
«አልሞከርኩም»
«አሁንስ ለመሞከር አታስብም?»
«ይሳካል ብለህ ነው ዶክተር?»
«እርግጠኛ ነኝ በዚህ ከተማ ውስጥ የምትጦራቸው አሮጊትና ሽማግሌ የለህም።»
«ምንም » አለ አስቻለው፡፡ ግን ደግሞ ወድያው ሔዋንን ጨምሮ ታፈሡ በልሁና መርዕድ ትዝ አሉት፡፡ ከእናትና አባቱ ባልተናነሰ ሊለያቸው የማይፈልጋቸው የፍቅር ቤተሰቦች ናቸውና።
እንደኔ እንደኔ ከዚህ ሆስፒታል ወደሌላ ብትዛወር የተሻለ ርምጃ መስሎ ይታየኛል፡፡ ለምን መስለህ አስቻለው!»
«እሺ ዶክተር »
አስቻለው በጽሞና እያዳመጠው "መሆኑን የተረዳሁ ዶክተር ደጀኔ ሀሳቡን ቀየር አደረገና በቅድሚያ አንድ ነገር ልጠይቅህና አንተም ትክክለኛውን ንገረኝ::ሲል ፈገግ እያለ በማየት አሳሰበው::
«ምንም አልደብቅም ዶክተር፣»
«ለመሆን እዚህ ከተማ ውስጥ 'የሴት ጓደኛ አለች» ሲል አሁንም ፈገግ ብሎ እያተ ጠየቀ። አስቻለው ድንግጥ ብሎ ድንገት ስሜቱ ሲለዋወጥ አይቶ
ዶክተር ደጀኔ አሁንም ፈገግ እያለ “ምነው ደነገጥክ?» ሲል ደግሞ ጠየቀው፡፡
አስቻለው የምንተነፍረቱን «አይ …ማለት» አለና እንደ መርበትበት
ከአደረገው በኋላ «መኖር አለችኝ ግን ምነው?» ሲል ዶክተር ደጀኔን መልሶ ጠየቀው።
«እስከገባኝ ድረስ አልጅቷ ጋር አብራችሁ አይደላችሁም፡፡ ልጅቷ
ምትኖረው ከእህቷ ጋር ነው። ልክ ነኝ?»
«እንዴት ልታውቅ ቻልክ ዶክተር»
ዶክተር ደጀኔ በያዘው እስርቢቶ ጠረጴዛጠን መታ መታ አደረገና እንደገና ወደ አስቻለው ቀና በማለት «ቅድም በቤታችንና በግቢያችን ወስጥ የሚከናወነውን እንኳ አናውቅም ብዬህ ተማምነንስ እልነበረም!» እለው፡፡
«ልጅቷ ገና በልቤ ወስጥ ነው ያለችው»
ዶክተር ደጀኔ ድንገት ሃ..ሃ..ሃ...ሃ ብሎ ሳቀና አየህ! ግማሽ አካሏ ከውጭ ቀርቶ ኗሯል አለና አሁንም ሃ ሃ ሃ ሃሃ
«የ'ሷን ነገር ለምን አነሳኸው አለው አስቻለው ዶክተሩ ሳቁን ሲጨርስ፡፡
«ግን እንደው አርግዛብህ ታዉቃለችን።?»
«በፍጹም ዶክተር እንዲያውም አታምነኝ እንደሆነ እንጂ ልጅቷ ገና ድንግል ናት።»
ዶክተር ደጀኔ እንደ መደነቅ ብሎ «ድንግል! ድንግል!»
«ከልቤ ነው የምነግርህ ዶክተር»
ዶክተር ደጀኔ በመገረም ዓይነት ፍዝዝ ብሎ አስቻለውን ሲመለከት ቆየና ራሱንም ወዘወዘ «ገና ብር አምባር ሰበረልዎ እንላለና»
«እዚያ ካደረሰን! አለና አስቻለው ግን የእሷን ነገር ለምን እንዳነሳህ
አለገባኝም ዶክተር አለ አሁንም ዓይኑን በዶክተር ደጀኔ ላይ እያንከራተተ፡፡
«ምክንያት አለኝ!»
«ምን?»
«ያልተወለደ ገዳይ የሆንከው ከእሷ ጋር በተገናኘ ሁኔታ ነው፡፡
እኔ ግን ነገሩ አሉባልታ ስለመሆኑ በትክክል ገብቶኛል፡፡» አለው፡፡
«ምኑ ከምን ጋር ተገናኝቶ?»
አሁን አሁን እየተበሳሽ ነው::
«ምኑም ከምንም!» አለና ዶክተር ደጀኔ በአጭር ቃል መለሰለትና ራሱ ቀጠለ፡፡ «እንደሚመስለኝ የአንተና የልጅቷ እህት ግንኙነታችሁ ጥሩ አይደለም፡፡
የልጅቷ እህትና ባርናባስ እንደሚግባቡስ ታውቃለህን?»
«ሰሞኑን ሲደንቀኝ የሰነበተው ይህ ነው ብትነግረኝ ይከብድህ ይሆን?"
«ብዙ የማውቀው ነገር የለም፡፡ አንድ ቀን ግን እኔና ባርናባስ ከተማ ውስጥ አብረን ስንዘዋወር መንገድ ላይ ከአንዲት ሴት ጋር ተነጋግሮ ወደኔ እንደመጣ
«ህቺ ሴት መምህርት ናት፡ ያቤሎ በነበርኩበት ወቅት እሷም እዚያ ስለነበረች እንተዋወቃለን፡፡ ብቻ ነው ያለኝ አለው ዶክተር ደጀኔ፡፡ አስቻለው የሁለቱን የትውውቅ መሠረት በማውቁ ሳይሆን አይቀርም አንገቱን ደጋግሞ ነቀነቀና «አሁን ብዙ ነገር ገባኝ ዶክተር፡፡» አለው::
«አዎ እስቻለው! የጓደኛህ እህትና ባርናባስ ከፈጠሩት ግንኙነት በመነጨ ነው ያልወሊደ ገዳይነትህ የተወራብህ፡፡ ይህን ደግሞ የነገረኝ ራሱ ባርናባስ ነው!
መምህርቷ ነገረችኝ ብሎ። ግን ደግሞ ይህን ሁሉ የምነግርህ ብዙ ጊዜ አካሄድ ፊትለፊት ስለሆነ ድንገት ሳታውቀው እንዳትጠለፍ ለጥንቃቄ ይረዳሃል ብዬ ነውና
አስብበትት፡፡ የዝውውሩንም ጉዳይ ችላ ባትለው መልካም
ይመስለኛል።» አለው፡፡
እስቻለው በረጅሙ ተንፍሶ ጥቂት ካሰላሰለ በኋላ
«የሰሞኑ እንቆቅልሽ ገና ዛሬውኑ ተፈታልኝ ዶክተር» ብሎ ከንፈሩን ነክሶ ጣሪያ ጣሪያ እያየ በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ሄደ፡፡ የዶክተር ደጀኔን የዝውውር ሃሳብ በቀላሉ አልተመለከተውም፤ እንዲያውም በርካታ ነገሮች በተዘዋዋሪ መንገድ ይህንኑ ጉዳይ ሲያሳስቡት ሰንብተዋል። በልሁና መርዕድ ታፈሡና ሽዋዬን ለማስታረቅ ከሞከሩ በኋላ
ተመልሰው የገለፁለት ነገር ሔዋን በሃሳብ ምን ጊዜም ከአንተ ጋር ናት። ሸዋዩ ባለችበት አካባቢ ግን እንጃ….” የሚል ፍሬ ሃሳብ የነበረው ነው። ከዚያም በላይ
የእርቅ ሙከራ በተደረገ ሶስተኛ ቀን ረፋዱ ላይ ሔዋን ሳያስባት ለዚያውም ፊቷ በእንባ ረስርሶ ወደ ቤቱ መጥታ ነበር።
«ምነው ሔዩ» ነበር የአስቻለው ጥያቄ።
«እንካ ይኸን ወረቀት አንብብ ብላ አንዲት ወረቀት ሰጠችው።
አስቻለው ወረቀቷን ገለጥ አድርጎ ሲያነብ የሚከተለውን መልዕክት
አገኘባት።

«ለተከበራችሁ አባትና እናቴ ለአቶ ተስፋዩ ይርጋ እና ለወይዘር ስንዱ በላቸው፣ለጤናችሁ እንደምን አላችሁ። እኔ ግን በጣም ተቸግሬያለሁ። እናንተንም እሷንም
ለመርዳት ስል ሔዋን የተባለች ልጃችሁን ወደ ዲላ ይዣት መጥቼ ነበር። እሷ ግን ትምህርቷን እርግፍ አድርጋ ትታ ሥራዋ ወንድ ማባረር ብቻ ሆኗል። እንዲያውም
መዘዟ ለኔ ተርፎ ችግር ላይ ወድቄአለሁ።ከመቸገሬ የተነሳ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከቤቴ ላባርራት ነው ።ምናልባት ልጃችን ባክና መቅረት የለባትም የምትሉ ከሆነ ከሁለት አንዳቹ መጥታችሁ ውሰዷት። መጥተን እንወስድም ካላችሁ ውርድ ከራሴ።

ልጃችሁ ሽዋዬ ተስፋዬ

አስቻለው ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ በኋላ በንዴት እሳት ለብሶ እሳት ጉርሶ ፈጠን ባለ አነጋገር ሴትዮዋ ምን እያለች ነው?» ሲል ሔዋንን ጠየቃት፡፡
«እኔ እንጃ አስቹ፣ ግራ ገባኝ» ሔዋን እያለቀሰች፡፡
«የት አገኘሽው?»
«ዛሬ ጠዋት ሥራ ስትሄድ ረስታው መሰለኝ አልጋዋ ላይ ተቀምጦ አገኘሁት።»
«ቀዳድጄ ልጣለው?»
«ተው አስቹ፣ ነገር ይባባስብኛል። ግን አንድ ነገር ላማክርህ?
👍3