አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
480 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


.....አምናን ካቻምናን ከዚያ በፊት የተቆጠሩ ዓመታትን ጨምሮ ለብዙ ጊዜ የደከሙበት ትምህርት የሚቋጨው ዘንድሮ ነው። ጌትነትና አማረች ከጓደኞቻቸው ጋር በቡድን በቡድን ሆነው እያሽመቁ ጥናታቸውን ሲለበልቡ የከረሙበት ላለፉት ረጅም አመታት ትምህርታቸውን በመከታተልና የሚሰጣቸውን አድካሚ የቤት ስራዎችን ከመደበኛ ሥራቸው ጋር አጣምረው በመስራት ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉበት የነዚያ ሁሉ አመታት ልፋት ድምር ውጤት የሚደመደምበትና የሚመረቁበት አመት ዘንድሮ ነው።
ሁለቱ ፍቅረኛሞች በአዋሳ ላንጋኖ ሃይቅ ውስጥ ተክለው ያለመለሙት ፍቅራቸው የሚያስቀና ሆኗል። ጌትነት የመልካሙ ተበጀ አዋሳ ላንጋኖ
ዘፈን አስቀድሞ የሚወደው ቢሆንም ለሱ የተዘፈነለት እስከሚመስለው ድረስ በይበልጥ የወደደውና አብሮ ማቀንቀን የጀመረው ከላንጋኖ ሽርሽር
በኋላ ነው።
አዋሳ ላንጋኖ ለሽርሽር ሄጄ ያየሁሽ፣
የሲዳሞ ቆንጆ እንዴት ነሽ?
ሽንጥና ተረከዝ ዳሌና ጡትሽ...
አዲስ አበባ ውስጥ ለሁለት አመታት ሲመኛት ቢኖርም በፍቅር ያወቃት በአዋሳ ላንጋኖ ሀይቅ ውስጥ ነበረና ያንን ዘፈን ሲሰማ የአዋሳ ላንጋኖው ሃይቅና ያ ውብና ምንጊዜም ከህሊና የማይጠፋ አስደሳች ዓለም ከነሙሉ
ጓዙ ተጠቅልሎ በሃሳቡ እየመጣበት ዘፈኑን ነፍሱ ምንጥቅ ብላ እስከምትወጣ ድረስ ወደደው። በዚህ የተነሳ የሲዳሞ ቆንጆ በሚለው ምትክ የአዲስ አበባ ቆንጆ እንዴት ነሽ በሚል ተክቶ ከዘፋኙ ጋራ አብሮ ሲያቀነቅን የሚሰማው ስሜት የተለዬ ነበር፡፡ አማረች ለሁለት አመታት ስትመኘው የነበረው ጉዳይ በመሳካቱ እጅግ ደስተኛ ከመሆኗ በላይ ከምትወደው ልጅ ጋር በትዳር ተሳስራ በመኖር የወላጆቿን ፍላጎት ለማሟላት
የሚያስችላት መልካም አጋጣሚ መፈጠሩ በአንድ ጠጠር ሁለት ወፍ ሆኖላታል። ወላጆቿ ልጃቸው ትዳር እንድትይዝላቸው ከፍተኛ ጉጉት አላቸው፡፡ “መቼ ይሆን የአያትነት ወግ ማእረግ የምታሳይኝ ልጄ? እንግዲህ ጀርባዬ ሳይጎብጥ ጉልበቴ ሳይዝል ጥሩ እስክስታ እንድመታልሽ ከፈለግሽ ይሄን ጊዜ ነው ጉልበቴን መሻማት” እያሉ የሚወተውቷት አባቷ
ይህንን ውሳኔዋን ሲሰሙ ደስታቸው ወደር እንደማይኖረው ጥርጥር አልነበራትም፡፡እናቷ አማረችን የሚያይዋት እንደ ልጃቸው ሳይሆን እንደ ታናሽ እህታቸው ነው። አማረችም እናቷን እንደ ታላቅ እህት እንጂ
እንደ እናት አይደለም የምታያቸው፡፡ ታሪኩን ያጫወተቻቸውም እሳቸው
በነገር ወጋ አድርገዋት ነው፡፡

“አማሩዬ? እኔ የምለው? እኛ የምናመጣልሽ ባል እንደማይኖር
በጠዋቱ አስጠነቀቅሽን
አንቺ የምታመጭውን ብንጠብቅ ደግሞ የማሚታይ ነገር ጠፋ።
ምን ይሻላል ልጄ? የሁልጊዜ ምክንያትሽ ትምህርቴን ልጨርስ ነው። ትዳር ተይዞ መማርን ምን ይከለክለዋል? አባትሽ ትዳር ትዳር እያልኩ ስጨቀጭቃት ሸክም ሆንሽብኝ ያልኳት እንዳይመስላት እንዳትሳቀቅብኝ እያለ እየፈራ እንጂ ከኔ የበለጠ የቸኮለ እሱ ነው፡፡ እንዲያው ለጤናው ያድርግለት ችኩል ብሏል”
የትዳሯ ነገር ያጓጓቸው፤ የሰርጉ ቀን የናፈቃቸው መሆኑን አጫወቷት።አማረች ቀኝ ክንዷን በቀኝ ጉልበቷ ላይ አገጯን በመዳፏ ደገፍ አድርጋ
በፍቅር ዐይን ዐይናቸውን እየተመለከተች ነበር የምታዳምጣቸው፡፡

ፊቷ ወይን ጠጅ መስሏል፡፡ ከረጅም ጊዜ ሚስጥር በኋላ እጮኛ ያላት መሆኑን ወላጆቿ ያላወቁት የትዳር ጥንስስ በልቧ ውስጥ ተጠንስሶ መቆየቱን ልትነግራቸው ፈለገች። ከዘንድሮ ምረቃ በኋላ ለትዳር የወጠነቸው
ጓደኛ ያላት መሆኑን ለእናቷ ለማብሰር ፈለገችና ጥርት ያለው ፊቷ በእፍረት ሲቀላባት የወይን ጠጅ መልክ እየያዘ ሄደ።

ከአማረች የመኝታ ክፍል ውስጥ ሆነው ነበር የሚጨዋወቱት፡፡ አማረች ስለፍቅረኛዋ ማስረዳቱን ቀጠለች፡፡ የዐይነ ህሊናዋ ካሜራ በጌትነት ላይ አነጣጥሮ ያሳለፉትን ጣፋጭ የፍቅር ጊዚያት አንድ በአንድ እንደ ፊልም
እየቀረፀና የአዋሳው ትዝታ ፊቷ ላይ ድቅን እያለ፡ “ትንሽ ነው የቀረኝ በጣም ትንሽ ጊዜ፡፡ በጣት የሚጠለቀውን ቀለበት አላጠለኩም እንጂ ታጭቻለሁ። ለረጅም ጊዜ የተዋወቅኩት የምወደው ፍቅረኛ አለኝ፡፡ እስከ አሁን በደንብ ተጠናንተናል። ተግባብተናል። ተዋደናል። ያንቺና የአባዬ ብቻ ሳይሆን በትዳር የመኖሩ ጉጉት በኔ ብሷል። ዩኒቨርስቲ አብሮኝ የሚማር
ልጅ ነው፡፡ ላንቺም ለአባዬም የማስተዋውቅበት ጊዜው ደርሷል። ሁላታችንም በዚህ ዓመት እንመረቃለን፡፡ እስከዛሬም የደበቅኩሽ ትምህርቴን
ከመጨረሴ በፊት ሠርጉ ይፋጠን የሚል ጥያቄ እንዳታቅርቡልኝ ነው።አሁንም ቢሆን ላንቺ ብቻ ነው የምነግረው፡፡ ለአባዬ ጊዜው ሲደርስ አንቺ ትነግሪዋለሽ” የአማረች እናት ልባቸው በደስታ ዘለለች። እንኳን የተማረ! እንኳን ያፈቀረችውን ይቅርና ሱሪ ይልበስ እንጂ እሷ ተመችቶኛል ትዳር
መያዝ እፈልጋለሁ ብላ ፈቃደኝነቷን ከገለፀች ከማንም ጋር ቢሆን ድል ባለ ሠርግ ሊድሯት ሁሌም የሚቃዡበት ምኞታቸው ነበረና፣ እንደ
ዕድሜ እኩዮቻቸው “ልጃችንን ዳርናት” እያሉ አፋቸውን ሞላ አድርገው ለመናገርና እርጅና ከመምጣቱ በፊት የአያትነት ወግ ማእረግ ሊያገኙ ነውና የሰሙት የምስራች እንደ ትንሽ ልጅ እያስቦረቃቸው የባለቤታቸውን ደስታ ጭምር አገላብጠው ሳሟት፡፡

“ለምን የፈለገው አይሆንም አማሩዬ? ይህችን አሁን ያሰማሽኝን የምስራች ይቺን እኔ የሰማኋትን ሚስጥር እሱም ቢሰማ ኖሮ በደስታ አስር
ዓመት ወደ ኋላ ያስቆጥር ነበር” በዜናው እጅግ ተደስተው ወደር የማይገኝለት የእናትነት ፍቅራቸውን እቅፍ አድርገው በመሳም ገለፁላት።አባቷ የሚወዷት የመጀመሪያ ልጃቸው ትምህርቷን ጨርሳ በዲግሪ ተመርቃ
የምትወደውን ፀባየ ሸጋና ጠንበለል ልጅ ይዛላቸው ከተፍ ስትልሳቸው ከደስታቸው የተነሳ ቦሌ አካባቢ ያሰሩትን አምስት ክፍል ቪላ ቤት ጀባ እንደሚሏቸው ጥርጥር የለውም፡፡ ይህንን ጠንቅቃ ስለምታውቅ ጌትነትና ስለመኖሪያ ቤት እያነሳ ሲጨናነቅ በልቧ ትስቅ ነበር። አማረች የምስራቹን ለእናቷ ባደረሰችበት በመመረቂያቸው ዓመት ላይ ጌትነትና እሷ የዓመት ዕረፍት ፈቃዳቸውን ወስደው ለመጨረሻው ፈተና እየተዘ
ጋጁ ነበር።

ትናንትና ለእናቷ የነገረቻቸውን ልትነግረው ፈለገች። አሁንም እንደ
አማረች በሆነ ባልሆነው “ጌትሽ ድረስ!” ሆኗል ዜማዋ፡፡ ዕቃ ሲሰበር አዲስ ፊቷ በእፍረት እየተለወጠ እየቀላ ሄደ፡፡ አሁን አሁን ደግሞ “ጌትዬ ድረስ!" ሆኗል ዜማዋ ምናምን ካስደነገጣት ጌትሽ” ብቻ ለሁሉም ነገር "ጌትሽ
ነጠላ ዜማ ሆኗል፡፡ ይሄ ነገር እናቷንም ግራ ሲያጋባቸው የኖረ ጉዳይ ነበር፡፡ በመጨረሻው ላይ እቅጩን ነገረቻቸው እንጂ ደጋግመው ስምተዋታል "ጌትዬ! ጌትዬ" ስትል፡፡

በዩኒቨርስቲው የመማሪያ ክፍል ውስጥ ከሁለቱ በስተቀር ማንም አልነበረም፡፡ባዶ ነው።ኃይለኛ ንፋስ መስኮቱን ጓ! አደረገና አላጋው። እንደልማዷ”ጌትሽ ድረስ!” በማለት ሄዳ ልጥፍ አለችበትና” ለማዘር ነገርኳት እኮ!"
አለችው እየተፍነከነከች።የመስኮቱ ጩኸት እፍረቷን አቡንኖታል።
“ምኑን?" ፈገግ እንዳለ ዘቅዝቆ እየተመለከታት፡፡
“በቃ ላስተዋውቅህ መሆኑን? እና እንትኔ መሆንህን፡ ባሌ መሆንህን!" አንገቱን እቅፍ አድርጋ ከንፈሩን ሳመችው። ቅብጥ ስትል ያለማጋነን ደስ ትላለች። የአንዳንዱ ቅብጠት ያስጠላል። አማረች ግን የቅብጠት ቅመሙን ጣል አድርጐባት ነው መሰል ቅብጥብጥ ስትል የበለጠ
👍31
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በትክክል_ገና


...ፀጉሩን ተላጨና ቁምጣ ሱሪውን አወለቀ! በምትኩ ቀጭን ቦላሌውን ለበሰ፡፡ ከላይ ሸሚዝና ኮቱን ደርቦ ሽክ.. ኳ! ብሎ ሲታይ ያ ጎንቻ! ያ አስፈሪው ጎንቻ! ያ ባለጎፈሬው ሽፍታ! መሆኑን እንኳንስ የማያውቀው የሚ
ያውቀውም ቢሆን ለማመን ይቸገር ነበር፡፡ውስጣዊ እሱነቱ ሳይሆን ውጫዊ ማንነቱ ተቀይሯል። የከተማው ሰው
የሚለብሰውን ልብስ ለብሶ ሰው መሰል አውሬነቱን የሚያሳስት አይነት ሆኗል።

በዚያች ምሽት በጠፍ ጨረቃ ከዓለሚቱ ጋር ተያይዘው ጠፉ... ከኢተያ ከተማ እስከ ዴራ ከተማ በእግራቸው ተጓዙ በሌሊት መኪና ተሳፈሩና ናዝሬት ገቡ፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ወደዚያ የከተማ ጫካ፣ ወደዚያ የከተማ ዋሻ ገብተው ሊደባለቁ በአዲስ አበባ መኪና ላይ ተሳፈሩ። ከእንግዲህ በኋላ ጎንቻን ፈልጎ ማግኘት ከእንግዲህ በኋላ ዓላሚቱን ፈልጎ
ማግኘት ቁና አሸዋ ውስጥ የወደቀች ጤፍ ለማግኘት እንደመሞከር ነው፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ዓለሚቱ ባሏን ያስገደለች እየተባለች ከምትጠበስበት የሀሜት ምላስ ልትድን እፎይ ልትል ነው፡፡ እነኝያ የገደ ቢስ
ልጆች ጨርሰው ከዐይኖቿ ሊርቁላትና ሰላማዊ ሰዎች መስለው ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር ሊቀላቀሉ የቀራቸው በሰዓታት የሚቆጠር ጊዜ ብቻ
ነው፡፡
ከእንግዲህ ወዲያ የጎንቻን ፍቅር ሙቀቱ እስከሚያቃጥላት ድረስ እንደ ልቧ ልትሟሟቀው ሁኔታው ተመቻችቶላታል። ከእንግዲህ በኋላ የልታጌጥ፣ እንደፈለገችው ልትዘል፣ ልትቦርቅ ልጓሙ ተፈቶላታል።
ጎንቻም አንጎሉን ሲያዞረው በኖረው በዓለሚቱ ፍቅር ወፈፍ በሚያደርገው በዓለሚቱ ናፍቆት ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። አብዛኛውን ጊዜ በጫካ ውስጥ ትዝታዋን ብቻ እያቀፈ በማደር ሲሰቃይ ኖሯልና ናፍቆቷ ነፍሱን መንጥቆ ሳያወጣው በፊት ጥሩ ዘዴ ፈጥራ ይዛው በመኮብለሏ አልተከፋም፡፡ያንን ቢያሽተው ቢምገው የማይጠግበው መዓዛዋን በየቀኑ በየደቂቃው ሊያጣጥመው ነውና ኩብለላው ብዙም አላስጨነቀውም ነበር። የተሳፈሩበት ሎንቺና ወስዶ ለገሃር ጣላቸው፡፡

ጎንቻ ከጫካ ያመለጠ አውሬነቱ የታወቀው ገና ከመኪና ላይ እንደወረደ ነበር፡፡ ተይዛ ያመለጠች ሚዳቋ መሰለ፡፡ ሽው!...ሽው!... ውር!... ውር
በሚሉት መኪኖች መሀል ሲገባ ሮጦ ሊያመልጥ ሞከረ። እንጣጥ!
እንጣጥ! እያለ የአንዱ መኪና ራት ሊሆን ትንሽ ቀረው። መንገዱ መሀል ሲደርስ ሰግጠጥ.. ሰግጠጥ እያደረገው አንዴ ወደ ፊት አንዴ ደግሞ ወደ ኋላ ለማምለጥ ዓለሚቱን ክፉኛ ታገላት።እሷም መደናበሯ አልቀረም ቆይ ጎንቻዬ እኔን ተከተለኝ፡፡ ቀስ በል። እኔ ወደምሄድበት ረጋ ብለህ ተራመድ። መኪኖቹን አትመልከት። ያዞርሃል ... ቀስ ...አዎ እንደሱ ጎሽ
..እጆቹን ግጥም አድርጋ ያዘችው እንደምንም ብለው እየተጓተቱ አስፋልቱን ተሻገሩ።
“እሺ ...አዞረኝ እኮ…ቆይ ቁጭ ልበል" አላት፡፡ ደገፈችውና ወደ አንድ ህንፃ አጥር ጥግ ሄዱ፡፡ ተረከዙ ላይ እንደ ዝንጀሮ ቁጢጥ አለ፡፡ ጭውው..አለበት። ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ያዘው። ዐይኖቹ ጭፍን ክድን ጭፍን
ክድን አሉ፡፡ መኪና ላይ ያልተሰማው የማጥወልወል ስሜት ተሰማው፡፡

"ርቦህ ይሆናል ጌታዬ ርቦህ ነው። ቆይ እዚህ ጋር የማየው ሆቴል ቤት ነው መሰለኝ" ባሻገር ከሚታየው ቤት ላይ ጣቷን ቀስራ አሳየችው።ቆዳቸው የተገፈፈ በጎች ሳይበለቱ ተሰቅለዋል። የሰንጋ ብልቶች በአይነት በአይነታቸው በስርአት ተዘጋጅተው በወረንጦ ላይ ተንጠልጥለዋል፡፡
ልክ ነው ምግብ ቤት ነው" አለችውና ከተቀመጠበት አስነስታው ተያይዘው
ትደጋግፈው ወደ ስጋ ቤቱ አመሩ....
የሚበላ ነገር አለ?" ብላ ጠየቀች፡፡
“አዎን!” አለ ሻጩ፡፡
“ምን አለ?"
“ሁሉም ነገር አለ፡፡ የፈለጋችሁትን..." ወደ ውስጥ እንደመዝለቅ አለችና የሻጩን ዐይን ዐይን በልምምጥ ተመለከተችው።
“በል እስቲ ቀይ ወጥ በእንጀራ..“ፈራ ተባ እያለች ጠየቀቸው። ዓለሚቱ ከልጁ ጋር ስትነጋገር ጎንቻን እንደ ህፃን ልጅ ግራ እጁን ግጥም አድርጋ
ይዛው ነበር፡፡ ጎንቻ...ያ ወንዱ..ጎንቻ... ያ አስፈሪው ጎንቻ አስፈሪነቱ ጀግንነቱ ከሹሩባው ጋር አብሮ እንደተላጨ ሁሉ ወኔው በኛሮ ጫካ ውስጥ ተጥሎ እንደቀረ ሁሉ ዐይኖቹ ፈጠው ርቦት ሲቁለጨለጭ ቀበሮ
የፈሳባት ጦጣ መስሎ ሲታይ እሱነቱን የማይክድ አልነበረም።
“በሉ ጥፉ ከዚህ! ፋራዎች! ገገማዎች! ይሄ የሥጋ መሸጫ ሉካንዳ እንጂ የእንጀራ መሽጫ ጉሊት መስለሽ?! አይተሽ አትጠይቂም?!” ጮኸባት።
ሽምቅቅ አሉ፡፡ አቤት አደነጋገጥ ወጥቶ ፀብ እንዳይፈጥር ጎንቻም በንዴት እልህ ውስጥ እንዳይገባና ገና አንዱንም ሳይይዙት መዘዝ ውስጥ እንዳይገባ ፈራች ፀብ ከተፈጠረ ፖሊስ ይዞ እንዳያንገላታቸው ስጋት አደረባትና
ዐይኖቹ መቅላት ልቡ የንዴት ደም መርጨት ሰውነቱ መቆጣት
የጀመረው ጎንቻን ሙጭጭ አድርጋ ይዛ የስድብ መዓት ከሚያወርድባቸው ጎረምሳ ሽሹ...ጎንቻ አንድ ቂም በልቡ ቋጠረ፡፡ ርቦት ሆዱ የእህል
ያለህ! በሚልበት ሰዓት ወስፋት የሚቆልፍና ወሽመጥ የሚበጥስ የስድብ መርዝ ቀመሰ። እንደምንም ብለው እየተጓተቱ ሄዱና እንጀራ የሚሽጥበት ምግብ ቤት በጠቋሚ አገኙ። በሉ፣ጠጡ፣ ጠገቡ። ጊዜው እየመሸ
ሲመጣ አሁንም በጥቆማ አልቤርጎ ተከራዩ። ምን ችግር አለ? ብር እንደሆነ ዕድሜ ለጎንቻ! በሽበሽ ነው፡፡ ከሰባት ሺህ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ይዘዋል። ጎንቻን ትንሽ ያስቸገረው መብራቱ ነበር፡፡ ብርሃን በጣም በዛበት። ዐይኑ በአንድ ጊዜ የአምፖሉን ብርሃን መቋቋም አልቻለም፡፡
ሊተኙ አካባቢ አምፖሉን ቀድሞ ለማጥፋት የሞከረው እሱ ነበር፡፡ “ኡፍ ኡፍፍ. ኡፍፍፍ..!" እንደ ኩራዙ ሞከረ። በኋላ ግን ዓለሚቱ በድርጊቱ እየሳቀች ማጥፊያውን ቀጭ... ቋ! አድርጋ አጠፋችውና በችሎታዋ እየተኩራራችበት ተቃቅፈው ተኙ፡፡

ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት አካባቢ ጎንቻ ሽንቱ ወጠረውና የመኝታ ቤቱን በር ቷ! አድርጎ ከፍቶ ወጣ፡፡ የተከፈተውን ድምፅ የሰማው ሽማግሌ ዘበኛ
“ማነው?” አለ በተጎተተ ድምፅ፡፡
"እኔ ነኝ!" አለ ጎንቻ።
"ወዴት ነው?"
ለውሃ ሽንት!"
“የውሃ ሽንት ተሆነ ቦቦው አለልህ አይደለም?! የት ልትሸና ነው? አሁን የሽንት ቤቱ በር ቁልፍ ነው" አለና ዘበኛው ቁጣ ቀረሽ መልስ ሰጠው፡፡
"የምን ቦቦ ነው የምትለኝ ጃል?! ሽንቴ መጥቷል እኮ ነው የምልህ!... "
በዘበኛው ኃይለ ቃል ልክ መለሰለት።
“ጤናም የለው እንዴ ሰውየው?" ዘበኛው ካፖርቱን እላዩ ላይ ጣል
አድርጎ አጭር ዱላውን ይዞ ወጣ፡፡
ሂድ ግባ! ቦቦው የተዘጋጀው ላንተ እኮ ነው!" አለና ጮኹ፡፡
“የት ነው የምሄድልህ?!"
"አልጋው ስር አለልህ እኮ ነው የምልህ!"
“አልጋ ስር ሽና ነው የምትለኝ?!"
እዚህ ደጅ ግን መሽኛ ቦታ የለም! ያንተ ቢጤ ሰካራሞች ናቸው እዚህ እንኳን አልጋ ስር አልጋህም ላይ ሽናው! እሱ የኔ ችግር አይደለም!
ሽንታቸውን እየሸኑ የጉንፋን መጫወቻ ያደረጉኝ!” በንዴት ጮኸ፡ በዚህ በሁለቱ ጭቅጭቅ መሃል ዓለሚቱ ልቧ በፍርሃት ተውጦ እያዳመጠች ና። የውሽማዋን አመል ስለምታውቅ ሽማግሌውን ሲጥ!
👍42