#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....መርማሪ ፖሊስ ሚክ ጆንሰን የክንዱን ቆዳ ቀይ እስኪሆን ድረስ እያከከ
በዴንከር ጎዳና ላይ ከሚገኘው የትሬይቮን ሬይሞንድ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት በር ላይ ቆሟል፡፡ ገና ከመኪናው እንደወጣ ነበር እንግዲህ ክንዱን ማሳከክ የጀመረው። ምናልባትም ለዚህ አስቀያሚ እና “ቴስቲሞንት” የሚባለው ሰፈር በመጣ ቁጥር አለርጂኩ ይነሳበታል፡፡ በእርግጥም ደግሞ ይኼ ትሬይ
ሬይሞንድ ያደገበት መንገድ ላይ አሰቃቂ ወንጀሎች፣ አመጸኛ ድርጊቶች፣
አደንዛዝ ዕፆች፣ ሙስናዎች እና ግማቶችን ሲያስተናግድ የኖረ መንገድ
ነው፡፡
ብዙ ሰዎች ሚክ ጆንሰንን ዘረኛ ነው ይሉታል፡፡ ይህንን በእሱ ላይ በዚህ
ጉዳይ የሚደርሰውን ወቀሳ ሲቃወም ኖሯል። ግን እዚህ ሰፈር ሲመጣ
በዘረኝነቱ ዙሪያ የሚቀርቡበትን ወቀሳዎች ልክ ናቸው ብሎ ያምናል፡፡ ለምን ቢባል ሁለት በጣም የሚቀርባቸው የሥራ ባልደረባዎቹ እና ጓደኞቹን
በተጨማሪም ባለፈው ጊዜ ከእሱ ጋር አጋሩ ሆኖ ይሠራ የነበረው ዴቭ
ማሎንም ጨምሮ እዚሁ መንገድ ላይ ነው እንግዲህ በወጣት ጥቁር የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በጥይት የተገደሉት። ግድያዎቹ የተፈጸሙት በጠራራ ፀሐይ ቢሆንም አንድም ሰው ቢሆን ጥይቱን ተኩሰው የገደሉትን ሰዎች አይተናል ብሎ ምስክርነት አልሰጠም፡፡ ብቻ ዴቭ ዳሽ ቦርዱ ላይ ከሚያስቀምጠው ካሜራ ላይ የገዳዮቹ ማንነት ስለታወቀ እነዚህ ሁለት
ጥቁሮች በሳን ኮንቲን እስር ቤት የሞት ፍርዳቸው እስኪፈጸምባቸው ድረስ
ተራቸውን በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
ጓደኞችህን የገደሉብህንና የዋሽህ ህብረተሰብ ላይ ምንም ዓይነት ቂም
አለመያዝ በራሱ አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ በደቡባዊ እና ማዕከላዊ ሎስ አንጀለስ
ላይ ሁልጊዜም ጦርነት አለ፡፡ በትሬቨን ሬይሞንድ እድሜ ላይ የሚገኙት
የአደንዛዝ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ጠላቶች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንደ
ዶውግ እና ኒክ ሮበርትስ ያሉ ነፃ አሳቢ እና ለዘብተኛ ልብ አውልቅ ሰዎች
ደግሞ ከአደንዛዥ ዕፅ የማገገሚያ ክሊኒኮች ሃሳብ መልሶ መክሰስ አለበት፡፡
ጥቁሮቹ በጣም ድህነት ውስጥ ስለሆኑም ነው በተስፋ መቁረጥ ውስጥ
ገብተው አደንዛዝ ዕፆችን የሚጠቀሙት፡፡ በሀገሪቱ ሲስተም ደካማነት የተነሳ
ወጣት ጥቁር አሜሪካውያንን እዚህ ችግር ውስጥ ለመክተት ችሏል እያሉ
ይበጠረቃሉ፡፡ እነርሱ እኮ እንደ ኤል.ኤ.ፒ.ዲ. ፖሊሶች ምሽግ ውስጥ ሆነው ጦርነቱን እየተዋጉ አይደለም፡፡ ደግሞም ሲስተሙ አይደለም ዴቭ ማሎንን የተኮሰበት እና ደሙን ሲያዘራም እያየ ቆሞ የሳቀበት፡፡
ጆንሰን ሬይሞንድ ቤተሰብ መኖሪያ ቤትን በር በኃይል እየደበደበደ ማንኳኳት ጀመረ።
“ክፈቱ! ይህን የተረገመ በር ክፈቱ! ፖሊስ ነኝ” ብሎ በጣም ቁጣ በሚነበብበት ድምፅ ተቆጥቶ አዘዘ፡፡
ከውስጥ በኩልም ቀጭን የሴት ድምፅ “እሺ እየመጣሁ ነው! እየመጣሁ
ነው!”
“ቶሎ ነይ እና በሩን ክፈቺ!” አላት ጆንሰን በትዕዛዝ ድምጽ፡፡
በዚሁ መንገድ ላይ በመቶ ያርድ ርቀት ላይ በኒሳን አልቲማ መኪናው ውስጥ ቁጭ ያለው ዴሪክ ዊሊያምስ መርማሪ ፖሊስ ጆንሰን የሚያደርገውን ነገር ሲመለከት ተበሳጨ፡፡ ቀጭን እና ትንሽ ሰውነት ያላት አሮጊት ሴት
(ምናልባትም የትሬቮን አያት) ልትሆን የምትችል ናት በሩን ከፍታ ቆማ
በጆንሰን የሚደርስባትን ማመናጨቅ በፀጋ እየተቀበለች ያለችው፡፡ ችላ ዝም
ማለቷም አሳዝኖታል፡፡ እነዚህ የሟች ቤተሰቦች ምንም ዓይነት ወንጀል
ሳይፈጽሙ እንኳን እንደ ወንጀለኛ ነው እየተቆጠሩ ያሉት ለዚያውም በገዛ
ቤታቸው ውስጥ፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በቆዳቸው ቀለም እና በመርማሪ
ፖሊስ ጆንሰን ዘረኝነት የተነሳ ነው፡፡ ይህንን ነው እንግዲህ ኤል.ኤ.ፒ.ዲ
“ማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ብሎ የሚደሰኩርበት፡፡ ለዚህም ይመስለኛል የዚህ ሰፈር ነዋሪዎች ኤል.ኤ.ፒ.ዲን በሙሉ የሚጠሉት፡፡
ዴሪክ ዊሊያምስም ቢሆን ኤል.ኤ.ፒ.ዲን ይጠላዋል፡፡ የጥላቻው ምክንያቱ ግን ከጥቁሮቹ ጋር አይመሳሰልም፡፡ ዴሪክ በድምሩ ለሦስት ጊዜያት ያህል የኤል.ኤ.ፒ.ዲ አባል ለመሆን ማመልከቻ አስገብቶ ነበር፡፡ የአካል ብቃት ፈተናዎቹን በጥሩ ውጤት አልፎ የነበረ ቢሆንም እንኳን ፊታቸውን በማያውቃቸው ቅጥሩን በሚወስኑ ሰዎች አልተቀበልንህም የሚል
መልስን የያዘ ደብዳቤ ለሦስት ጊዜ ያህል ተጽፎለታል፡፡
ይኼ እንግዲህ ከ20 ዓመታት በፊት የተከሰተ ጉዳይ ቢሆንም እስከአሁን
ድረስ ነገሩን ሲያስበው ያንገበግበዋል፡፡ በተለይ ደግሞ የተዛባ ሃሳብ ያላቸውን
እንደሚክ ጆንሰን እና እንደ አጋሩ ጉድማን ያሉ ቀሽም የመሃይም መርማሪዎችን ሲመለከት በጣም ይበሳጫል፡፡
ጄንሰን ሬይሞንድ ቤተሰብ ቤት ውስጥ ለአርባ ደቂቃ ያህል ቆይቶ ሲወጣ ፊቱ ቀልቶ እና ወደቤቱ ከመግባቱ በፊት ከነበረበት የንዴት ስሜት በላቀ ንዴት ውስጥ ሆኖ ነበር ከቤቱ የወጣው፡፡ ዊሊያም ጆንሰን መኪናውን አስነስቶ ከአካባቢው በራቀ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከመኪናው ወርዶ ወደ ሬይሞድ ቤተሰብ ቤት አመራ፡፡ የቤቱ በርንም ክብርን በማያሳይ መልኩ አንኳኳ።
“አሁን ደግሞ ምን ቀረህ?” አለ የቅሬታ ድምጸት የሚሰማበት የሴት ድምጽ እኛ የምናውቀውን ነገር ሁሉ ነገርንህ አይደል! ለምንድነው የማትተወን ብላ ደስ የምትል ጥቁር በአርባዎቹ አጋማሽ ላይ የምትገኝ
ሴት በሩን ከፈተችለት፡፡ ድምጹን ልታወጣ የቻለችውም መርማሪ ፖሊስ ጆንሰን ተመልሶ የመጣ ስለመሰላት ነበር፡፡ በሩ ላይ የቆመው ሰው መሆኑን ስታይም የቅሬታ ፊቷ ወደቁጣ ተቀየረ፡፡ ዓይኗን አጥብባ እየተመለከተችውም
“አንተ ሌላኛው መርማሪ ነህ? ጓደኛህ አሁን ነው ከዚህ የወጣው፡፡ እዚህ
መጥታችሁ ከወንጀል ነፃ የሆኑ ሁለት ሴቶችን ከምታበሻቅጡ ለምንድነው
ይኼንን ገዳይ ይዛችሁ ለፍርድ የማታቀርቡት” ብላ በቁጣ ጠየቀችው::
“እኔ ፖሊስ አይደለሁም” ብሎ የቢዝነስ ካርዱን አውጥቶ እየሰጣትም “እኔ የግል መርማሪ ነኝ ሚስስ ሬይሞንድ፡፡ እኔ የትሬይን ገዳይ አድኜ ለማግኘት ነው በኒክ ሮበርትስ የተቀጠርኩት፡፡ ወደ ውስጥ መግባት እችላለሁ?” አላት ዊሊያምስ፡፡
ቤቱ ውስጥ ከገባ ከአስር ደቂቃ በኋላ ዊሊያምስ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ
ኩባያው ውስጥ የሚገኘውን ቡና ፉት እያለ ነው፡፡ ከእሱ በተቃራኒ ደግሞ
ሁለት መደገፊያ ባላቸው ወንበሮች ላይ የሬይሞንድ እናት እና አያት ቁጭ
እንዳሉ በትህትና እያናገሩት ነው፡፡
“ስለዚህ አንተን የቀጠረችህ ደ/ር ሮበርትስ ናት?” ብላ የሬይሞንድ እናት
ጠየቀችው እና “በጣም ጥሩ ሰው ናት፡፡ ምንም እንኳን ቀለል ያለች እና ልታዋራት የምትችል ሴት ብትሆንም በእውነት ጥሩ ናት፡፡ ሟች ባሏ ደግሞ በጣም ቅዱስ ሰው ነበር”
“አዎን ቅዱስ ነበር” ብላ የሬይሞንድ አያት ተናገረች፡፡
“ለትሬይ ሥራ ሰጠችው፡፡ ሁሌም ደግሞ ለእሱ ደግ ነበረች፡፡ እናመሰግናታለን፡፡ እና እሷ ናት የቀጠረችህ?”
ዊሊያምስም ራሱን በአዎንታ ከነቀነቀ በኋላ “ፖሊሶቹ የትሬይን ገዳይ
ለመያዝ በበቂ ሁኔታ እየሠሩ እንዳልሆነ ነው የሚሰማኝ፡፡ እሷም ላይ የግድያ ማስፈራሪያ ደርሶባታል፡፡” አላት ዊሊያምስ፡፡
ሁለቱ ሴቶችም እርስ በርስ ከተያዩ በኋላ “ይህንን ነገር አላወቅንም ነበር፡፡ በእውነት እንደርሱ ከሆነ መጥፎ ነገር ነው፡፡”
“ሊዛ ፍላንገን የተባለች ሌላ የተገደለች ወጣት ነበረች”
ይኼኔም የትሬይ እናት መሃረቧን አውጥታ ዓይኗን እየጨመቀች
“ይህቺን ሴት ትሬይ ይወዳት ነበር፡፡ የዶክተር ሮበርትስ ታካሚ ነበረች
አይደል? ምስኪን ሴት በተለይ ደግሞ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር ስላላት ግንኙነት
በጋዜጦች ላይ የሚፃፉት ነገሮች ትክክል

#ክፍል_ሰላሳ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....ከግንባሯ እና ከብብቷ ስር ላቧን እየጠረገች አኔ ቤታማን ከሶል ሳይክል
የዳንስ ትምህርቷ ወደ ብሬንት ውድ ፀሃያማ ቀን በጥሩ ስሜት ውስጥ ሆና
ወጣች፡፡
የስትራንቨስኪ ኮንሰርት ላይ ባሳየችው ብቃቷ የተነሳ በሁሉም ቦታዎች ላይ ቫዮሊን እንድትጫወት ግብዣዎች እየቀረቡላት ይገኛሉ። በዚህም የተነሳ
ምንም የገንዘብ ችግር እንደማይገጥማትና ቀጣይ ሥራ አላገኝ ይሆን ከሚል ሃሳብ ወጥታለች፡፡
በግላዊ ህይወቷም ቢሆን ሁሉም ነገር ሰላም የሆነ ይመስላል።ምክንያቱም ባሏ በስልክ መልዕክቶች፣ በስልክ ጥሪዎች እና ስጦታ አበባዎች እሷን ማስጨነቁን ትቶታል፡፡ በዚህም የሃዘኔታ ስሜት ቢሰማትም በመጨረሻ ግን ልቧ እረፍት ሊያገኝ ችሏል፡፡ አሁንም ቢሆን የሆነ የልቧ ክፍል እሱን ያፈቅረዋል፡፡ ግን ደግሞ ኒኪ ትክክል ናት፤ የሁለቱ መፋቀር
ብቻ በቂ አይደለም፡፡
አሁን ጥሩ ስሜት እንዲስማት ያደረገው ሌላ ነገር ከኒኪ ጋር መስማማት መቻላቸው ነው፡፡ ኮንሰርቱን ባቀረበችበት አዳራሽ የመልበሻ ክፍል ውስጥ እያሉ ባሏ በላከላት ብዙ አበቦች የተነሳ የማይገባ ነገር ከተነጋገሩ በኋላ አኔ መልሳ ኒኪን ማየት አፍራለች፡፡ ስለሆነም ከኒኪ ጋር ያላትን የህክምና ቀጠሮ ደውላ ሳታሳውቅ ሰረዘችው፡፡ ቀጣዩንም የህክምና ቀጠሮ ሳትሄድ ቀረች፡፡ ቀጠሮውን ሳታሳውቅ በመሰረዟ ከኒኪ የስልክ ጥሪ ወይም ደግሞ በኢ-ሜይል ቀጠሮውን ሳታሳውቅ በመሰረዟ የቀጠሮዎችን ክፍያዎች እንደምትከፍል የሚያስጠነቅቅ መልዕክትም አልተላከላትም፡፡ኩራቷን ውጣ ለኒኪ ልትደውልላት እና ባለፈው ምሽት ስላሳየቻት ያልተገባ ባህሪ ይቅርታ ልትጠይቃትም ነበር። በዚያ ላይ ደግሞ በጣት የሚቆጠሩ ጓደኞችን እያጣች ነው፡፡ እና ብቸኝነት እየተሰማት ነው በዚህ ስሜት ውስጥ እያለች በነበረችበት ወቅት ነበር እንግዲህ የኒኪ በወረቀት ላይ የተፃፈ ይቅርታን ያዘለ መልዕክት አፓርትመንቱ ድረስ የመጣው፡፡
ሌላ አዲስ ቴራፒስት ጋ ብትሄጅ እረዳሻለሁ፡፡ ምንም ዓይነት መጥፎ
ስሜትም አይሰጠኝም፡፡ ነገር ግን ሌላ ቲራፒስት ጋር እንዳልሄድሽ ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም አብረን ስንሠራቸው የነበሩ ነገሮች እየረዱሽ እንደሆነም አስባለሁ፡፡ አንቺም በውስጥሽ ይሄ እንደሚሰማሽ እርግጠኛ ነኝ ይላል መልእክቱ፡፡ አኔ ምን እንደሚሰማት እርግጠኛ አይደለችም፡፡ ማለትም ኒኪ ወደ እሷ ስለተመለሰች ደስ ብሏታል፡፡
የሆነ ያልተለመደ ነገር እየተሰማት እንደሆነ ይገባታል፡፡ ለዚህ ደግሞ
ዋነኛዋ ተጠያቂ እሷ ኒኪ ናት፤ ምክንያቱም የአካሚና የታካሚ የግንኙነት
መስመርን አልፋ እሷም እንድታልፍ ያደረገቻት እራሷ ናት፡፡
ከፊት ለፊቷ ከሚገኘው ካፌ ገብታ ውድ የፍራፍሬ ጭማቂ ጠጣች፡፡ እና መኪናዋ ውስጥ ዘልላ ገባች እና ወደ ኒኪ ቢሮ በሚወስዳት መንገድ ላይ መኪናዋን ማሽከርከር ጀመረች፡፡ የተለመደው የህክምና ቀጠሮዋ ከሰዓት ላይ ቢሆንም አኔ የኒኪን ፊት ለማየት ስለጓጓች ነው በአሁኑ ሰዓት ወደዚያ ለመሄድ የፈለገችው፡፡ ምናልባትም ቢሮዋ ውስጥ ታካሚ ከሌለ ወጣ ብለው ወይንም እዚያው ቢሮ ውስጥ ለጥቂት ጊዜ ያህል እያወሩ ሻይ ቡና ማለት ይችላሉ፡፡
የመኪናዋን ጣሪያ ከፈተችና ንፋሱ ሰውነቷ ላይ ያለውን ላብ እንዲያደርቅላት አደረገች፡፡ የጠራው ሰማያዊ ሰማይንም ቀና ብላ ስትመለከት ሰማዩ የእሷን ደስታ የተጋራት መሰላት፡፡ የኒኪ ቢሮ ከሚገኝበት ህንፃ ስትደርስ ከመኪናዋ ወርዳ ቁልፏን መኪናዋን በተገቢው ቦታ ለሚያቆምላት
ሰው ልትሰጠው ስትል የምታውቀው ድምፅ ከኋላዋ ሲያወራት ሰማች እና
በድንጋጤ ደርቃ ቀረች፡፡
“ሆላ የኔ መልአክ” የሚለው የባለቤቷን ድምፅ ስትሰማ ልቧ በአፏ የሚወጣ እስኪመስላት ድረስ ደነገጠች፡፡ ጥላው ከመጣች ጀምሮ ይሄ ነገር ሊከሰት እንደሚችል ስታስብ ነበር፡፡ በቃ እሷ ያለችበት ቦታ ድረስ በድንገትመጥቶ እንደሚያገኛት ስታስብ ነበር፡፡ በመጀመሪያ ላይ እነዚህ ሃሳቦች
በህልሟ እየመጡ ቅዠት ይሆኑባት ነበር፡፡ በህልሟ ትታው ወደመጣችው ባሏም ተገድዳ ስትመለስ ለብዙ ጊዚያት ስታልም ነበር፡፡ ከጊዜ ብዛት ግን ይሄ ስሜቷ እየጠፋ መጥቶ ነበር፡፡ አንዳንድ ቀን ስለእሱ ስታስብ እንዲህ ባለ ድንገተኛ ሁኔታ እንዳያገኛት የቀን ህልሟን ስታልም ነበር፡፡
ይኼው አሁን ግን እሱ አጠገቧ ይገኛል፡፡ እሷን ሊያገኝም እሷ ያለችበት
ቦታ ድረስ ለመምጣት ችሏል፡፡
ለጥቂት ጊዜ ትቷት የነበረው ሽብርም ከባሏ ጋር ተመልሶ መጣ ማለት
ነው፡፡ “ተወኝ ብዬሃለሁ! ከአጠገቤ ዞር በል!” ብላ የመኪናውን ቁልፍ
ለፓርኪንግ ሠራተኛው ለመስጠት ስብስብ ወዳሉት ጥቂት ሰዎች ተጠጋች::
“እኔ” ብሎ ሉዊስ ሮድሪጌዝ ተወዳጅ ሚስቱን በፍቅሯ በተጎዳው ዓይኑ ተመለከታት፡፡ “ምን ሆነሻል ውዴ፤ ሉዊስ ነኝ እኮ ለምንድነው የፈራሽኝም
አላት፡፡
ድምፁ ውስጥ ንዴት አይሰማም፡፡ ከዚያ በላይ ግን የሃዘኔታ ድምፀት
ይነበብበታል፡፡ ይህንን ስታይ በሃይል ይመታ የነበረው ልቧ እየተረጋጋ
መምታት ጀመረ፡፡
እንደሁልጊዜውም ዝንጥ ብሎ ለብሷል። ምርጥ የሳቪሌ ሙሉ ልብስ፣ የሐር ከረቫትና የጉቺ አፍተር ሼቭ የተቀባው አዲስ የተላጨው ፂሙ እንኳን ሳታስበው ከእግሮቿ መሃል ንዝረትን ፈጠረባት፡፡ በግራ እጇ በደንብ ተደርገው የተሠሩ የእሷ ምርጫ የሆኑ አበቦችን ይዟል፡፡
“እዚህ ምን ትሠራለህ ሉዊስ?” ብላ ጥርጣሬ በማይነበብበት ለስላሳ
ድምፅ ጠየቀችው፡፡
“ኤል ኤ ውስጥ የሆነ ቢዝነስ አለኝ፡፡ እዚህ ለጥቂት ቀናት እቆያለሁ”
አላት፡፡
አኔም ዓይኗን አጥብባ “ወደ አሜሪካ መቼም ተመልሰህ እንደማትመጣ
ነግረኸኝ ነበር፡፡”
“ልክ ነሽ በጣም ሞክሬ ነበር... ግን ይሄ ነገር በጣም አስፈላጊዬ ነገር ነው፡፡”
ሉዊስ ቢዝነስ ሲል እሷን ይሁን ወይንስ የእውነት ለቢዝነስ ነው ወደ እዚህ የመጣው ብላ አስላሰለች እና ለቢዝነሱ ብሎ ወደ ኤል ኤ በመጣ ብላ ተመኘች፡፡ ፊቱንም ትክ ብላ እያየችው እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ስሜቶችን
ማስተናገድ ጀመረች፡፡ ለቢዝነስ ነው እዚህ የመጣሁት ያለው እውነቱን
ነው? ደስ ሊለኝ ይገባል ወይስ ልፈራ?”
“አኔ በጣም እንደናፈቅኩሽ ታውቂያለሽ አይደል?” አላት በተሰበረ የፍቅር
ድምፅ፡፡
“እኔም ናፍቄሃለሁ” ብላ እውነቱን ተናገረች፣ እና በመቀጠልም “
ግን እንደዚህ በድንገት ልታገኘኝ አይገባም... ልትደውልልኝ ይገባ ነበር።
“ስልክሽ እኮ የለኝም”
“እኔ የምሠራበት ኦርኬስትራ ቢሮ በመሄድ መልዕክት ልታስቀምጥልኝ
ትችል ነበር፡፡ ደግሞ እኔን ማግኘት ያን ያህል አይከብድም፡፡ እንደዚህ
በድንገት መጥተህ መንገድ ላይ ከምታገኘኝ ይልቅ አስቀድመህ ብታስጠነቅቀኝ መልካም ነበር” አለችው፡፡
“አስቀድሜ ባሳውቅሽ ኖሮ እኔን ለማግኘት አትስማሚልኝም ነበር” አላት።
“ቢሆንስ እሱ የእኔ ውሳኔ አይደል?” ብላ አኔ ጠየቀችው፡፡
“በእርግጥ ባሳውቅሽ ችግር የለውም ነበር፡፡” አላት እና ፈገግ ብሎ “ይኼ
ደግሞ የእኔ ውሳኔ ነው፡፡ በዚህ
ውስጥ አንቺን ማግኘቴ ደግሞ
ተስማምቶኛል።”
አኔ ምንም ማድረግ ስላልቻለች ፈገግ አለችለት፡፡ ይኼ የሉዊስ አካሄድ
ነው። የለየለት ጥጋበኛነቱን ከጥሩ ስሜት ጋር ቀላቅሎ ስለሚያቀርበው ነገሮች ይሆኑለታል፡፡ እንደርሱ ያለ ወንድ ገጥሟት አያውቅም፡፡ በእርግጥ
ደግሞ ኒኪ እሱን ዳግመኛ እንዳታገኘው ማስጠንቀቂያ ልካ ነበር፡፡
“ምሳ አብረን እንብላ” አላት እድሉን ለመጠቀም በማሰብም አበባውን
እያቀበላት፡፡
አኔ አበባውን ስትቀበለው ጣቶቻቸው ሲነካኩም በጣም ነዘራት፡፡ ያን ምሽት በእሱ ላይ ከጮኸችበት በኋላ በአካል

👍1