አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#በክፍለማርያም

...ወረቀቱን ፍለጋ ወደ ዉስጥ ተመለሰ
ፍቃዱ ወረቀቱን እያነሳ ድል እንዳረገ ሰው ኮራ እና ጀነን እያለ
"አገኘኋችሁ"
ሲል አጉተምትሞ የወረቀቱን አቅጣጫ ተከትሎ መሄድ ጀመረ።

እማማ ስንቅነሽ ቁርስ ሰራርተዉ ዉጪ ተገትራ የቆመችዉን ቤዛዊትን ወደ ቤት ዉስጥ ገብታ
እንድትበላ ጠሯት አልሰማቻቸዉም ልቧ ከአሁን አሁን መጣ አልመጣም ብላ የምትጠብቀዉ ፍፁም ላይ ነዉ።

ቀረብ ብለዉ እየነኳት
"ልጄ የምትጠብቂዉ ሰዉ አለ እንዴ"
እማማ ስንቅነሽ በሁኔታዋ ተጠራጥረዉ ጠየቋት
"አዎ ግን አሁን አልነግሮትም"
ፈጠን ፈጠን እያለች እያወራች
የእማማን ልብ ለማንጠልጠል አስባ
ነገር ግን እማማ ስንቅነሽ ምንም አልመሰላቸዉም እንደሚያማት ስለሚያዉቁ አብዳ ለይቶላት
ጨርቋን ጥላ ሳይፀየፉ ሰዉ ናት ብለዉ ስላቀረቧት አሁን አሟት ቢሆን እንኳ ሰዉ የምትጠብቀዉ ሊጫኗት አልፈለጉም።

እዉነተኛ ወዳጅም እንደዚህ ነዉ ጥፋትህን ስህተትህን ካወቀ በስህተት በጥፋትህ ተጠቅሞ
ሊጎዳህ አይሞክርም
ያግዝሀል ያበረታሀል እንጂ
እማማ ስንቅነሽም የቤዛዊትን እጅ በፍቅር ይዘዉ ሳብ እያረጉዋት
"በይ ነይና ቁርስሽን በልተሽ ትጠብቂዋለሽ"
ለእሳቸዉ የእሷ ቁርስ መብላት እንጂ ታማ ዉጪ መገተሯ ወይ በጤነኛ አይምሮዋ ሰዉ ቀጥራ
እየጠበቀች መሆኑ ብዙም ትኩረት አይሰጣቸዉም
ቤዛዊት የቀጠረችዉ ሰዓት ሳይደርስ መጨነቋ እየገረማት እና ፍፁምን ምን ያክል እንደምትወደዉ እያሰበች ወደ ቤቱ ዉስጥ ከእማማ ስንቅነሽ ጋር ተከታትለዉ ገቡ።

እጇ ላይ ያሰረችዉ ሰዓት ይቆጥራል እርግጠኛ ስላልመሰላትም በእማማ ስንቅነሽ በር በኩል
የሚያልፉ እና የሚያገድሙ ሰወችን
"ይቅርታ ሰዓት ስንት ነዉ?"
በሚያሳዝን አስተያየት ትጠይቃለች
"ሶስት ተኩል፣አራት ስዓት .."
እያሉዋት የጠየቀቻቸዉ ሰወች ያልፉሉ
እሷም ያሰረችዉ ሰዓት ግን ትክክል ነበር የሚሰራዉ።

ቤዛዊት ስልኳን ይዛ ባለመዉጣቷ ተበሳጨች ይዛዉ ብትጠፋ ቤተሰቦቿ እየደወሉ የሚጨቀጭቋት ስለመሰላት ነበር ትታዉ የወጣችዉ አሁን ግን ብይዘዉ ኖሮ ስትል
ተመኘች የፍፁም መዘግየት እያሳሰባት ስድስት ስዓት ሊሆን ተቃርቧል።
እማማ ስንቅነሽ በጠራራ ፀሐይ ዉጪ የቆመችዉን ቤዛዊትን ቤት እንድትገባ ለመለመን ከጉዋዳቸዉ ወጡ
"አይ ልጄ ፀሀዩ በረታብሽ እንዳያምሽ ወይ ወደ ቤት ግቢ አልያም በረንዳ ላይ ጥላ ቦታ ተቀመጪ"
"ቀረብኝ እኮ ሶስት ሰዓት ተባብለን ስድስት ሰዓት ሞላ"
"እኮ ይመጣል ብቻ ከፀሐይዋ ራቅ በይ"
እንደዚህ ሲልዋት ቤዛዊት በደስታ ፈገግ እያለች
"የሚመጣዉ ማን እንደሆነ ልንገሮት?"
በእሺታ እማማ ስንቅነሽ ጭንቅላታቸውን ነቀነቁ
"ጉዋደኛዬ ፍቅረኛዬ ባሌ"
ቀጠል አድርጋም
"ፍፁም ይባላል ሲመጣ አስተዋዉቃችሁዋለሁ"
እማማ በእሷ ደስተኛ መሆን እየተደሰቱ እና እያዋሩ ቤዛዊትን ከፀሀዩ ወደ ጥላ ወስደዋት ነበር።

(ከሰዓታት በፊት)
ፍፁም ሁለት ስዓት ተኩል አካባቢ ከተባለዉ አድራሻ በታክሲ ተሳፍሮ እንደወረደ እና ባለችዉ አቅጣጫ ጥቂት ከተራመደ በኋላ ቦታዉን ለማረጋገጥ ፈልጎ ቤዛዊት የሰጠችዉን ወረቀት ኪሶቹ ዉስጥ ሲፈልግ ስላጣዉ እየተበሳጨ
የት ሊጥለዉ እንደቻለ ማሰብ ጀመረ።
ቤቱ እየወጣ ለአከራዩ ብር ሲሰጥ ሊሆን እንደሚችል ገምቶ የቦታዉን እርግጠኝነትን ለማረጋገጥ
ጭንቅላቱን መጠየቅ ተያያዘ
አልተሳሳተም ያለችዉ ቦታ ላይ ደርሷል ነገር ግን እሱ ከቆመበት መንገድ ተሻግሮ ነበር
አንገቱን ቀና አርጎ ለማየት ሞከረ ቤዛዊትን በርቀት አያት
በእድሜ ገፋ ካሉ ሴትዮ ጋር ቆማ ታወራለች
ስላያት እየተደሰተ ግዜ ሳያጠፋ መንገዱን ሊሻገር ሲል በቅርብ እርቀት ከቅድም ጀምሮ ከጀርባዉ
የነበረ የመሰለዉ ሰዉ ስላየ መሻገሩን ተቶ የሰዉየዉን ፊት ለማየት በቀስታ ዞሮ በጨረፍታ አይቶት
መሻገሩን ወደ ቤዛዊት መቅረቡን ትቶ ቀጥታዉን መንገድ ይዞ እየተናደደ እያጉተመተመ መራመድ ጀመረ።

"ከቤት ጀምሮ ሲከተለኝ ነበር ወይስ እንዴት እዚህ ድረስ ሊመጣ ቻለ"
ፍፁም እራሱን እየጠየቀ ከኋላዉ የሚከተለዉን ሰዉዬ ለማምለጥ እየሞከረ ነዉ
"አይ ፍቃዱ ምን አርግ ነዉ ግን የሚለኝ ምን በደልኩት ምን አሰቀየምኩት
ይሄን ያህል የጎን ዉጋት የሆነብኝ"
ፍፁም ከፊት ሲራመድ ፍቃዱ አድፍጦ ከኋላው እየተከተለዉ ነዉ ፍፁም እሮጦ ማምለጥ
ተመኘ ነገር ግን እግሮቹ ለመሮጥ ብቁ አደሉም
ፍፁም እያነከሰ ፍቃዱን ለማምለጥ ክራንቹን ተጠቅሞ ፈጠን ፈጠን ለማለት እየታገለ ነዉ
ከጀርባዉ ያለዉ ፍቃዱ ግን ዘና ብሎ እየተራመደ በፍፁም አረማመድ አነካከስ እየሳቀ እየተከተለዉ ነበር።

አንዳንዴ በህይወት መስመራችን ዉስጥም ከእኛ በብዙ እጥፍ የሚበልጡን በብዙ እጥፍ
የተሻሉ ሰወች አሉ
ነገር ግን አብዛኞቹ ስለበለጡን የሚኮፈሱ ስላነስን የሚንቁን ናቸዉ
ህየወትንም ከባድ የመያረጋት መሮጥ የሚችል ሰዉን በታመመ እግር በክራንች ታግዘዉ ማምለጥ መቻል ነዉ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
2👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

..“ይሸጣል እንዴ?” ከመካከላቸው አንዱ፡፡
“አሉልህ እኮ አሁን ወጣ ብለን ብንፈልግ ደማቸውን እንደ ጭማቂ ለመሸጥ የሚንጐራደዱ አይታጡም" ”ሌላው፡፡ ይሄ ደግሞ የገንዘብ መስዋዕትነትን ጠየቀ፡፡ አሁንም ተፋጠጡ፡፡
“አቦ ትጠራ ምን ትሆናለች” ባዩ በዛና ትህትና ይሄንን መርዶ በጠዋቱ እንድትረዳ ፈረዱባት፡፡ ከዚያም ልጁ ሊጠራት እየበረረ ከሆስፒታሉ ወጣ፡፡
እሷ በዚያን ሰዓት አገር ሠላም ነው ብላ ለእናቷ የምትወስደውን ምግብ እያዘጋጀች ነበር፡፡ ወንድሟ ለሷ ለሚወዳት እህቱ ብሎ በዚህች
ስዓት በሕይወትና በሞት መካከል ይገኛል፡፡
በጠዋቱ የተንኳኳውን በር ሄዳ ከፈተች፡፡ ለምን እንደሆነ አላወቀችም ልቧ ሽብር ሽብር አለባት፡፡
“አንዱአለም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ገብቷል” አላት ጭክን ብሎ።
“ኡ ይ!” ምን ሆኖ!” ጮኸች።
“ሰው ደብድቦት፡፡ አሁን በአስቸኳይ ደም ተጠይቋል” ቁርጡን ነገራት። ከዚያ በኋላ ያደረገችውን አታውቅም፡፡ የሞተ ነው የመሰላት፡፡
የውጭውን በር በርግዳ....
“ኡኡ.... አንዱዬ ...! አንዱዬ....! ወንድሜን!... ወንድሜን!”
ሩጫዋን ቀጠለች። ልጁም ከኋላ ከኋላዋ እየተከተለ ተያይዘው ቁልቁል ይሮጡ ጀመር፡፡ እንደዚያ ራሷን ስታ እየጮኸች ስትሮጥ የሚያያት ሰው በጣም ነበር ያዘነላት፡፡ እንባዋ እንደጉድ ይፈሳል፡፡
ከጥቁር አንበሳ ት/ቤት ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለመሻገር ከላይም ከታችም መኪና ማየት ሲገባት፤ እንደዚሁ ግብኗን እየበረረች ግማሹን አስፋልት ተሻግራ ደሴቱን አቋረጠችና ወደ ሁለተኛው አስፋልት ጥልቅ ብላ ገባች፡፡
ከዚያ ከላይ ከቴዎድሮስ አደባባይ ቁልቁል እየበረረች የምትመጣው ውይይት ታክሲ በድንገት ጥልቅ ብላ የገባችውን ልጅ ለማዳን ሹፌሩ ፍሬኑን በሃይል ሲረግጠው፤ መኪናዋ ወደጐን ዞረችና ደሴቱ መሐል ገብታ ተቀረቀረች፡፡
እዚያ ታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች በድንጋጤ ውሃ ሆነዋል፡፡ ትህትና የዚህ ሁሉ መንስኤ እሷ መሆኗን አታውቅም፡፡
ሩጫዋን አላቆመችም፡፡ ልጁ በተፈጠረው አደጋ ተደናግጦ ጭንቅላቱን
በሁለት እጆቹ ይዞ ቀረ፡፡ ከዚያም ሮጦ ደረሰባትና! እጇን ይዞ ይማፀናት
ጀመር፡፡ አልሰማ አለችው፡፡ ያለው አማራጭ ከኋላ ከኋላዋ መሮጥ ብቻ
ነበር፡፡ ተያይዘው ሆስፒታል እንደ ደረሱ፤ እነዚያ የሆያ ሆዬ ጓደኞቹ ተሰባስበው! ተቀበሏት፡፡
“የት ነው ያለው? ወንድሜ የት ነው? አንዱዬ የታለ? ሞቶ እንደሆን ንገሩኝ” ትለፈልፋለች፡፡ ከስንት ልመና በኋላ እንደምንም ብለው ሊያረጋጓት ሞከሩ፡፡ ከዚያም ሀኪሞች “አይዞሽ ደህና ነው” ብለው ካጽናኗት በኋላ ደም እንድትሰጥ ተደረገ፡፡
“ወንድሜን ዐይኑን ልየው እባካችሁ?” እያለች ፤ እያለቀሰች ብትለምንም “ሪከቨሪ” ስለሆነ መግባት አይቻልም ተባለች፡፡
ቀስ በቀስ ነፍሷን መግዛት ስትጀምር፤
ለአዜብ ስልክ አስደወለችላትና አዜብ መጣች፡፡ አዜብ ሁኔታውን እንዳረጋገጠች...
“ምን መዘዘኛ ነኝ?” የሚል መጥፎ ስሜት ተሰማት፡፡ ሚስጥሩን ስትነግረው በፍፁም የዚህ አይነቱ አደጋ ይደርስበታል ብላ አልገመተችም ነበር። ትንሽ እዚያ አካባቢ ዞር፤ ዞር፤ እያለች ከቆየች በኋላ፤ ሹልክ ብላ ሳትነግራት ወደ ቤቷ ሄደች፡፡
ትህትና ጨንቋት፤ አጽናኝ በምትፈልግበት ሰዓት ላይ ጓደኛዋን ብትፈልግ አጣቻት፡፡ ወዲያና ወዲህ ተዘዋወረች፡፡ ተዟዟረች፡፡ አዜብ ግን የለችም፡፡ በመጨረሻ ላይ እቤት ስልክ ደወለች፡፡ “የለችም” አስባለች፡፡ እየመሸ መጣ፡፡ እንደገና ስልክ ደወለች፡፡ አሁንም የለችም ተባለች፡፡
ክው ብላ ደነገጠች፡፡ “ምነው? ምን አደረኳት አዜቢናን?” ሽምቅቅ ብላ፤ ስልኩን አስቀምጣ፤ ብቻዋን ጭር ያለ ቦታ ፈልጋ ተቀመጠችና፤ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ እናቷ የካቲት አስራ ሁለት
ሆስፒታል፣ ወንድሟ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ምን ዓይነት ስቃይ
ነው? እንደተመኘችው ሳታየው መሸ፡፡ በማግስቱ እናቷን ጠይቃ፤ ወደ
ወንድሟ መጣች፡፡ ልታየው አልቻለችም፡፡ ፀጉሯን እንኳን ማበጠር አቁማለች፡፡ እንደዚያ የምታምረው ልጅ ነገሮች ተደራርበውባት፧ ማስፈራሪያ እየመሰለች ነው፡፡ እንደዚህ ሆና መከራዋን ካየች በኋላ ወንድሟን ያገኘችው፤ በሶስተኛው ቀኑ ነው፡፡
አንዱአለም ድንበሩ ከሞት ድንበር ደርሶ ተመለሰ፡፡ በሶስተኛው ቀን፤ በሶስተኛ ማዕረግ ከቀዶ ጥገና በሽተኞች ጋር ተቀላቀለ፡፡ እንደዚያ ፊቱ አብጦና፤ ጠቁሮ፤ ስታየው የምትሆነውን ነበር ያጣችው፡፡
“አንዱዬ ምንድነው የሆንከው?” ቀስ ብላ ጠየቀችው። ከትንፋሹ
ጋር እየታገለ....
“እንደሻው... አስደበደበኝ” ብሉ ነገራት፡፡ በዚህ ጊዜ የተሰማትን ስሜት መግለጽ ያስቸግራል፡፡ አዜብ የሸሸችበት ሚስጥር አሁን ገና ወለል ብሎ ታያት፡፡ ሰውነቷን የሆነ ነገር ውርር አደረጋት :: እንደሻው
በግንባሩ ላይ ብዙ ጠመዝማዛ ቀንዶች አብቅሎ፣ ጥርሶቹ ተስለውና፤
አንደመጋዝ ሾለው፣ ጥፍሮቹ እንደ ጃርት እሾህ ተንጨፍርረው፣ ታይዋት፡፡ .
እንደሻው ... እንደሻው ... እንደሻው ... አእምሮዋን እንድትስት አድርጉ ከመታት በኋላ ሊከመርባት፤ በሀሳብዋ መጣባት፡፡ ሰውነቷ እንደሻው ምን ያላደረጋት ነገር አለ? የምትወደው ሻምበል ብሩክን ያጣችው በእንደሻው ምክንያት ነው፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ እንደዚያ ውሻ አድርጐ የሰደባት፤ በኋላም ስለእናቷ ክፉ ንግግር የተናገራት፤ እንደሻው በፈጸመባት ወንጀል ምክንያት ነው፡፡ ስራዋንም ያጣችው በሱ
ድርጊት የተነሳ ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ግፍ ምንም የበቀል እርምጃ አልወሰደችም፡፡ እሷ ብትተወውም ግን እሱ ሊተዋት አልፈለገም፡፡
ይሄውና አሁን ደግሞ እንደ ዐይኗ ብሌን የምትሳሳለት፤ አንድና ብቸኛ ወንድሟን እንዳይሞት እንዳይድን፣ አድርጉ! አስደበደበው፡፡ ግን ለምን ይሄን ያክል ጨከነባት?
“የሰው ልጅ አይደለሁም እንዴ? ምነው ምን አደረኩት?” በሚል ጭንቀት ተውጣ ራሷን ጠየቀች፡፡ በሷ እምነት ምንም
አላደረገችውም።የፈጸመችበት በደል አልነበረም፡፡ የማፈቅረው ሰው ስላለኝ
ይቅርታ አድርግልኝ ብላ ለምና ተለማምጣ ልታግባባው ሞከረች እንጂ
አንዳችም ክፉ ነገር አልወጣትም፡፡እሱ ግን ያንን እንደ ጥቃት ቆጥሮ፤ በጭካኔ ደብድቦ፧ ክብረ ንጽህናዋን መድፈሩ ሳያንሰው አሁን ደግሞ እንደገና ,በወንድሟ ላይ የጭካኔ በትሩን አሳረፈ፡፡ግን ለምን?... ለምን?...ለምን?... ለዚህ ጥያቄዋ መልሱ ብዙም ሳይቆይ ወደ አእምሮዋ መጣላት፡፡ አላንገራገረችም፡፡ ይሄ የመጨረሻው ምዕራፍ ነው ስትል ወሰነች፡፡ የሆነውን ሁሉ በተቆራረጠ ድምጽ ነገራት፡፡
አሁን ሁሉንም ነገር ሰምታ ከጨረሰች በኋላ አዜብ አሳዘነቻት፡፡ እሷን ጠልታ ሳይሆን፤ በሷ ላይ በተደጋጋሚ ለሚደርሰው አስጠሊታ አጋጣሚ ሁሉ እጂ ስላለበት፤ መጥፎ ስሜት ተሰምቷት እንደሆነ ስታውቅ፤ “ጓደኛዬን አስጨነኳት፡፡ ጭንቀቴ እንጂ አንድም ቀን ደስታዬ
ተርፏት አያውቅም፡፡ በዚያው ለሷም ግልግል ነው፡፡” የሚል ስሜት
አደረባት፡፡

ታሪኩን በሙሉ አንድ በአንድ ሰምታ ስታበቃም፤ አሞቷ ኮስተር አለ፡፡ ለሁሉም ገደብ አለው፡፡ ትዕግሥትም ልክ አለው፡፡ እንኳንስ በደል፤ ማርም ሲበዛ ይመራል። በደል ሲደጋገም ደግሞ ከምሬት በላይ ነው፡፡ በቃ! እንደሻውን ልትበቀለው ስመ እግዚአብሔርን ጠርታ በልቧ መሀላ
ፈጸመች፡፡

አንዱዓለም የምትወደው ታናሽ ወንድሟ፤ የተፈጸመባት ግፍ አንገብግቦት ሊበቀልላት ሄዶ ጉድ ሆኗል፡፡ እሷ ደግሞ በታናሽ ወንድሟ ላይ ለተፈጸመው ወንጀል ምላሽ መስጠት አያቅታትም፡የመጨረሻው የአባቷ ቅርስ ታያት፡፡ በክብር ተሸፍኖ በሣጥን ውስጥ በድብቅ
የተቀመጠውን፣ እሷና እናቷ ብቻ የሚያውቁትን፣ መቶ አለቃ
👍2