አትሮኖስ
282K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
492 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

ቀናት ገሠገሡ። ሳምንታት አለፉ። አሮጌው ሄደ፡፡ አዲሱ መጣ፡፡ የጊዜ
ዑደት ሕግ ሥርዓቱን ጠብቆ በአንድ አቅጣጫ ወደፊት ያመራል።
ህይወት ግን በዝብርቅርቅና በውጣ ውረድ ቀለበት ውስጥ እየተዟዟረች
ትህትና ድንበሩና ሻምበል ብሩክ በላይ በከንፈር ማህተም ያፀደቁትን ቃል
ኪዳን ጠብቀዋው ስለወደፊቱ የትዳር ህይወታቸው በሰፊው መወያየቱን
ከጊዜ ጋር ትራመዳለች::
ቀጥለዋል።
ሻምበል ብሩክ በቤተሰቡ ልብ ውስጥ ዘልቆ ከገባና ዝምድናውን ካጠናከረ በኋላ ያ ቤት ድሮ የትህትና አባት መቶ አለቃ ድንበሩ እያለ የነበረውን የህይወት ሙቀት ቀስ በቀስ መላበስ ጀምሯል፡፡
ይህ አባት አከል የወደፊት የትዳር ጓደኛዋ፤ ወድቆባት የነበረውን የህይወት ሸክም አቀለለላት፤ “አለሁልሽ” እያላት ነው፡፡ ለእናቷ የተጠየቀውን ገንዘብ ከፍሎ ሆስፒታል ተመልሳ እንድትገባ ያደረገ
ዕለት...
“ ለምን ሌላ ሆስፒታል አናስተኛትም ብሩኬ?” ስትለው፡፡
“የመጀመሪያው ሆስፒታል ምን አለን ትሁት?” አላት፡፡
“እሱማ ምንም አላለን፤ አማራጭ እስካለን ድረስ ለምን ሆስፒታል አንቀይርም ለማለት ፈልጌ ነው እንጂ” አለችው መልሳ።
“እንደኔ፤ እንደኔ፤ መጀመሪያ ሲከታተላቸው የቆየው ዶክተር
ቢያክማቸው ውጤቱ ያማረ ይሆናል ባይ ነኝ፡፡ አዲስ ዶክተር ማለት አዲስ ህክምናን ሀ ብሎ እንደመጀመር ነው የሚሆነው፡፡ ይሁን ካልሽም እሺ” አላት ዐይን ዐይኖቿን በፍቅር እያየ።
ከዶክተር ባይከዳኝ ሙሉ ለሙሉ ለመራቅ እንጂ፤ በህክምናው በኩል ተደናቂ ሀኪም መሆኑን ዘንግታው አልነበረም፡፡ ሻምበል ብሩክም ልክ አዜብ እንዳለቻት ሁሉ ህክምናውን የመጀመሪያው ሀኪም
እንዲቀጥል ሀሳብ ሲያቀርብላት ጥያቄዋን አነሳች፡፡
በዚህ ሰዓት ሆስፒታል በመቀየር ከምታገኘው ጥቅም ይልቅ የእናቷን ጤንነት ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲከታተል በቆየው ዶክተር ህክምናውን መቀጠሉ የሚያስገኘው ጥቅም አመዝኖ ታያትና...
“እንግዲያውስ ይሁን” በማለት ተስማማች። ዕድሜ ለሱ። ዛሬ የሰላምና የንፁህ አየር እየተነፈሰች የወደፊት የትዳር ህይወቷን ትልም በመንደፍ ላይ ነች ፤ እናቷ ተገቢውን ህክምና እንድታገኝ የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው። በሻምበል ብሩክ ከፍተኛ ምክርና ጥረት አንዱአለም
ችላ ብሎት የነበረው ትምህርቱን በሚገባ መከታተል ጀምሯል።
ይህ ውጣ ውረድ የበዛበት ህይወቷን ለማስተካከል እንድትችል ማካካሻ ያገኘችበት መልካም እድል
ሊሆንላት፤ የዶክተር ባይከዳኝና
የእንደሻው ጥላ ደግሞ በሄደችበት እየተከተላት፤ ሀሳቧን ጠቅለል አድርጋ
እንዳትተኛ እንቅፋት ከመሆን አልቀረላትም፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ በፍቅሯ እንደተቃጠለ ነው። እንዲያውም እስከመጨረሻው የሱ ሆና እድትቀር የነበረው ምኞቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ልዩ ልዩ ስጦታዎች ያበረክትላት ጀምሯል። የዶክተር ባይከዳኝ ጥርስ የሌለው አንበሳነት፤ በህይወቷ ላይ ችግር የማያስከትል በመሆኑ እናቷ ሙሉ ለሙሉ ከበሽታዋ ድና እስከምትወጣ የተለመደውን ከልብ ያልመነጨ ፍቅር እያቀመሰችው ለመቆየት ወስናለች።
ይህንን የወሰነችው ደግሞ ብቻዋን አልነበረም፡፡ ከአዜብ ጋር በደንብ አድርገው ከተወያዩበትና ከተማመኑ በኋላ ነው።
“አዜቢና ለምን ቁርጡን አልነግረውም?” በማለት ስሜቷን ለጓደኛዋ ስትገልጽላት።
“ምን ብለሽ ትሁት?” ስትል ጠየቀቻት።
“በቃ እጮኛ እንዳለኝና እንዲተወኝ ብጠይቀውስ?”
“ሞኝ ሆንሽ እንዴ ትሁት? እንደሱ ብለሽ ብትነግሪው የሚያምንሽ ይመስልሻል? ጠልተሽው የደረብሽበት ነው የሚመስለው፡፡
በዚህ ላይ ይሄ ሁሉ የስጦታ ግርግር ፍቅር መሆኑን አትርሺ!!
ምን ቸገረሽ ለትንሽ ጊዜ ብትታገሺ? ፍቅር የያዘው ሰው ፍቅሩን ለሌላ አሳልፎ መስጠት ስለማይፈልግ ሌላ አፈቀርኩ ብለሽ ብትነግሪው ጥሩ አይመጣም፡፡ ያፈቀረ ብዙ ነገር ከማድረግም ወደኋላ አይልም፡፡ አቅሙን እንደሆነ የምታውቂው ነው፡፡ ጉዳት እስካላስከተለብሽ ድረስ ማሚ ድነው እስከሚወጡ እየሸወድሽው ብትቆዪ ምናለበት? በዚህ ላይ ታዋቂ ሀኪም ነው” ስትል አማከረቻት።
እሱን በአሁኑ ሰዓት ማጣት ጉዳት እንጂ ጥቅም ስለሌለው ከሻምበል ብሩክ ጋር ጋብቻቸውን እስከሚፈጽሙ ድረስ ግንኙነታቸው እንደነበረ እንዲቀጥል ተስማሙ።
በተቻላት መጠን ግን ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማርገብ ጥረት እንድታደርግ፤ ቀስ በቀስ የግንኙነት ገመዱን ለማላላት እየቀጠሩ መጥፋት፤ ሲገናኙ መለማመጥና ምክንያት እየሰጡ
በአጭር ጊዜ ውስጥ ላለመገናኘት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ በዚህ
ውስጥ እንዲጠቃለሉ በስፋት ተማከሩበት። በዚሁ መሠረት ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ለረጅም ጊዜ ሳይገናኙ
ቀሩ። ለረጅም ጊዜ ያለመገናኘታቸው ደግሞ እንደግምታቸው ተስፋ የመቁረጥና የመረሳሳትን አዝማሚያ ከማሳየት ይልቅ ' ዶክተር በናፍቆት
ተጠብሶና፤ በፍቅር ተቃጥሎ፤ እንዲጠብቃት አደረገው፡፡ሻምበል ብሩክ አስፈላጊውን ክፍያ ሁሉ ፈጽሞ እናቷን
ሆስፒታል ባስገባችበት ዕለት ተገናኙ። እናቷ በገንዘብ እጥረት ምክንያት
ከሆስፒታል እንድትወጣ ሲደረግ! ስለገንዘብ ከሆነ አለሁልሽ ብሏት
ነበር፡፡ በክፍያ ችግር ምክንያት መሆኑን ልትገልጽለትና በሽንፈት እጇን
ስላልፈለገች... “ለገንዘቡ አይደለም ዶክተር፤ እናቴ ከሆስፒታል ወጥታ በቤት ውስጥ ለመታከም ስለፈለገች ነው
” በማለት ነበር መልስ የሰጠችው::
አሁን እናቷን ሆስፒታል መልሳ ማስተኛቷን ሲያውቅ ቶሎ ቶሎ ለመገናኘት እድል ይፈጥርለታልና በጣም ተደሰተ፡፡ እሷ ግን ይህንን አልወደደችውም።ሻምበል ብሩክ ግንኙነታቸውን እንዳይደርስበት ሰጋች።
ሆኖም እሱን ከማንኛውም ጥርጣሬ ነፃ የምታደርግበት የራሷ ማረጋገጫ
አላትና፧ ተጽናናች። ሁሌም ለእሷ ንፁህ የመሆን ማህተሙ አብሯት እስካለ ድረስ ዶክተር ባይከዳኝ የእናቷ ሀኪም ከመሆኑ ባሻገር ሌላ ጉዳይ ይኖራቸዋል ብሎ እንደማይገምት ተማምና፤ ከዶክተር ጋር ያላትን ቀዝቃዛ ግንኙነት ቀጠለች።
ይህ ሁኔታ በዚሁ ቀጥሎ ሳለ፤ አንድ ቀን ሻምበል ብሩክ በፖሊስ መምሪያ የተካሄደውን ስብሰባ ተካፍሎ፤ ምሳውን ከበላ በኋላ፤ ወደ ቢሮው ለመመለስ የያዛትን የመንግስት መኪና በሚያሽከረክርበት ወቅት አዲስ ነገር ተፈጠረ።
ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሆኗል።
ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ነው። የትራፊክ መብራት ይዞትእንደቆመ፤ በስተቀኝ በኩል ከፊት ለፊቱ ቀደም ብላ የቆመችውን ነጭ
ኦፔል መኪና እንደዋዛ በዐይኖቹ ገረፍ አደረጋት።
በዚያች መኪና ውስጥ እንደዋዛ ያየው ነገር የትኩረት ስሜቱን ሳበውና፤ መኪናውን ቀስ ብሎ ትንሽ ወደፊት በማንቀሳቀስ ተጠጋ፡፡ፍጹም ሊሆን የማይችል ነገር ነው። አእምሮው ሊጠረጥረው የማይችለውን
ነገር በማየቱ፤ አይኖቹን ተጠራጠረ። የሚያየውን እውነታ ህሊናው በቀላሉ ሊቀበልለት ስላልቻለ፤ ቀይ መብራት በርቶ
መኪኖች ሲለቀቀቁ እንኳ አልታወቀውም ነበር። የሚያየው ነገር እውነት መሆኑን፤ አይኖቹ የሚያሳዩት የሌለ ነገር ሳይሆን፤ ያለውን ሀቅ መሆኑን፤ ሲረዳ ግን፤ ጭንቅላቱ በከባድ ነገር እንደተመታ ሁሉ፤ ክው ብሎ ደርቆ ቀረ።
በሚያየው ነገር ምክንያት ሰውነቱን ማተኮስ ስለጀመረው! የመኪናውን የበር መስታወት ወደታች ዝቅ አድርጎ ንፋስ አስገባ፡፡ በዚያች መኪና ውስጥ ያለቸው ትህትና ድንበሩ መሆኗን
ሲያረጋግጥ፤
መኪናውን የሚያሽከረክረውን ሰው ማንነት ለመለየት ፈለገና አተኩሮ
ተመለከተው፡፡ ያውቀዋል። ዶክተር ባይከዳኝ ነው።ጉድ ፈላ! ስራውን ትቶ የዚህን ተአምር ማብቂያ ሊከታተል
ወሰነ። መብራቱ አረንጓዴ በርቶ ሲለቀቁ ነጫን ኦፔል መኪና ተከትሎ ያሽከረክር ጀመር ክትትሉ እንዳይታወቅበት
🔥2👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....ሶስና ነበረች የመለመለቻት…አንድ በአንድ ይታወሳታል... ጓደኛዋ ሶስና ነበረች የመለመለቻት፡፡

ርብቃ ሶስናን የምታውቃት በዩኒቨርስቲ ዓመቶቿ ነው፡፡ ሁለቱም የቋንቋ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ ከትምህርት ዓለም ተሰናብተው ወደ ሥራ ዓለም ሲሸጋገሩ ሶስና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ርብቃ ደግሞ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሥራ ያዙ፡፡

የሥራ ቦታቸው መለያየት ሊለያያቸው የሚችል ቢሆንም አልተራራቁም፡፡ ቢያንስ በሣምንት አንዴ እየተገናኙ አብረው ጊዜያቸውን ያሳልፉ ነበር፡፡ በመጨረሻም የለያያቸው ሶስና በአንደኛ ፀሃፊ የሥራ መደብ ካይሮ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መሄዷ ነበር፡፡

ባለፈው ዓመት መጨረሻ ገደማ ላይ ነበር፡፡ ከሥራ ሰዓት በኋላ ዘወትር እንደሚያደርጉት ቀጠሮ ተሰጣጥተው ተገናኝተው ሲጫወቱ አመሹ፡፡ ወደ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ሶስና ድንገት ተነስታ ቀጠሮ እንዳላት ስትነግራት ርብቃ አዲስ ነገር ሆነባት።

“በዚህ ሰዓት?” አለች መምሽቱን ተመልክታ፡፡
አዎ ርብቅዬ... ማታ ማታ ነው የምንገናኘው።”
“ማነው ባክሽ?” አለች ርብቃ እየተሽኮረመመች፡፡

“ኦ! ወንድ መስሎሽ ነው እንዴ አይደለም ጓደኞቼ ናቸው፡፡”
“እኔ የማላውቃቸው ጓደኞች! ሂ! ሂ! ሂ!” ርብቃ ሳቀች ጓደኛዋ የደበቀቻት ምሥጢር እንዳለ በማመን፡፡

“ርብቃ ሙች እንዳስብሽው አይደለም፡፡ ምን መሰለሽ በእርግጥ አታውቂያቸውም፡፡ እኔም ቅርብ ጊዜ ነው የተዋወቅኋቸው.. እና አልፎ አልፎ ተገናኝተን በተለያዩ አርዕስቶች ላይ እንነጋገራለን፡፡”

“ምን ልትፈጥሩ?” “ አለች ርብቃ ጓደኛዋ የምትለው መላቅጡ ሲጠፋት፡፡

“የተሻለ ዓለም!” አለች ሶስና ጓደኛዋ ትኩር ብላ እየተመለከተቻት ምን መሰለሽ .. ” አለች የርብቃን መደናገር ስታይ፡፡ “በአንድ ርዕስ ላይ ስትከራከሪ የተለያዩ ሃሳቦችን ታገኝያለሽ፡፡ ጭንቅላትሽ ይሰፋል አስተሳሰብሽም ይዳብራል፡፡”

“እና ለመከራከር ተቀጣጥራችሁ ትገናኛላችሁ ማለት ነው?”

“አዎ አንድ ርዕስ እንመርጥና እንዘጋጅበታለን፡፡ ለምሳሌ ስነጽሁፍ …ወይ…ኋላቀርነት ወይ አፍሪካ በቃ እንድ ርዕስ ከዛ በርዕሱ ላይ እያንዳንዳችን እንዘጋጅና ተገናኝተን የሰበሰብነውን
እንለዋወጣለን! እንከራከራለን፡፡” .

“ጥሩ ነው ሃሳቡ፡፡” አለች ርብቃ ቦርሳዋን እያነሳች:: “በይ ከሄድሽ ቶሎ እንሂድ፡፡ እንዳይመሽብሽ፡፡”

“ለምን አብረን አንሄድም?”
“የት?!” አለች ርብቃ ጓደኛዋ ላይ አፍጥጣ፡፡
“አሁን ያልኩሽ ቦታ ነዋ::”
“አበድሽ እንዴ? ደግሞ እኔ ምንድነኝ? አንቺኮ ጓደኞችሽ ስለሆነ…”
“አይደለም. አይደለም:: ባይገርምሽ አብዛኛዎቻችን የተዋወቅነው
እዛው ነው:: እየሽ እያንዳንዱ አባል ብስለት አለው የሚለውን ሰው መጋበዝ
ይችላል፡፡እና ተጋባዥ እንድ ፕሮግራም ይካፈልና ከጣመው አባል ይሆናል፡፡”

“ሌላ ጊዜ።” አለች ርብቃ የጓደኛዋን ክንድ ይዛ ከነበሩበት ቡና ቤት እየወጡ፡፡

ለምን? ነይና እይው፡፡ ምንም መናገር አያስፈልግሽም፡፡ ዝም ብለሽ ተቀምጠሽ እኛ ስንወያይ ታዳምጫለሽ፡፡ እንዳልኩሽ ፕሮግራሙ የሚጠቅምሽ ከመሰለሽ… እያየሽ ትቀጥያለሽ፡፡ ማን ያውቃል ብዙ ነገር ታስተምሪን ይሆናል፡፡ ጋዜጠኛ መሆንሽን ሲያውቁማ ወጥረው ነው የሚይዙሽ፡፡” ሶስና ገፋፋቻት፡፡

“ጋዜጠኛ ለፍላፊ ነው ለማለት ነው ብሽቅ!” አለች ርብቃ ጓደኛዋ
የወትሮውን ብሽሽቅ የጀመረች መስሏት፡፡
“አይደለም... አየሽ ጋዜጠኞች በተለያዩ አርዕስቶች ላይ ስለምትስሩ ከተራው ሰው የተሻለና ሰፋ ያለ እውቀት ይኖራችኋል፡፡ ይህ ደግሞ የሚያከራክር አይደለም፡፡ የኛ ጋዜጠኞች ደግሞ ዋዛዎች አይደላችሁም፡፡

“እ…እ”
“ሙች ሙች ከምሬ ነው:: ሌላውን ብንተወው እንኳን… ለየግላችሁ ያላችሁ ዕውቀት የሚናቅ አይመስለኝም:: ብቻ እስቲ ነይና እይው።”

“እረ በናትሽ ሳይጠሩኝ ሰተት ብዬ ቤታቸው ስሄድ ምን ይለኛል?

“በደስታ የሚፈነድቁት ርብቃ ሙች! አዲስ ሰው በመጣ ጊዜ ምን ያህል እንደምንደሰት ብታውቂ… አዲስ አስተያየት፤ አዲስ አመለካከት ማለት ነው!”

“ግን ታመሹ እንደሆነ?”
“ምንም ችግር የለም። መኪና የሚይዙ ስላሉ ሁላችንን በየቤታችን የሚጥሉን እነሱ ናቸው፡፡ እሱ አያሳስብሽ…እሺ በቃ እንሂድ… እሺ?” ውጥር አድርጋ ያዘቻት፡፡

“ግን… እንጄ.…” እያለች ነበር ርብቃ ለመሄድ የተስማማችው::

ታክሲ ተሳፍረው በንፋስ ስልክ መስመር ወደ ጎተራ አቅጣጫ አመሩ፡፡ መሃል ላይ ሶስና “እዚህጋ ይበቃናል፡፡” ብላ ታክሲውን አስቁማ ሲወርዱ ሊጨልም ዳድቶት ነበር፡፡ አንድ ሰዓት ከአሥር፡፡

“አርፍደናል፤ከአንድ ሰዓት በፊት መገኘት ነበረብን፡፡” አለች ሶስና ከዋናው መንገድ በስተግራ ተገንጥሎ ሽቅብ ወደሚወጣ መንገድ እያመራች።
ጎን ለጎን እየተራመዱ በዝምታ ቀጠሉ። ከአንድ ግራጫ ቀለም ከተቀባ
የብረት በር አጠገብ ሲደርሱ ሶስና ጠጋ ብላ መጥሪያውን ተጫነችው።

አራት ማዕዘን ቅርፅ ያላት ትንሽ የስርቆሽ በር ተከፈተችና አንድ ሰው አጮልቆ ተመለከታቸው። ሶስና ምንም ሳትናገር ጠጋ ብላ ፊቷን አሳየችው፡፡ የስርቆሽ በር ተዘጋችና ዋናው የብረት በር ተከፈተላቸው፡፡ ገቡ፡፡

ርብቃ ከማታውቀው ቤት ሳትጠራ በመምጣቷ እፍረት ቢሰማትም
ውስጥ ገብታ ጉዷን እስክታየው ቸኮለች። ከፊት ለፊት ያለው ቤት ትልቅ ሳይሆን ቀልብጭ ብሎ በጥሩ ሁኔታ የተያዘ ይመስላል፡፡ ምናልባት በቅርብ
ጊዜ የተሰራ ስለሆነም ሊሆን ይችላል፡፡ ከፊት ለፊት የሚታዩት ሁለት
መስኮቶች ተዘግተዋል፤በግቢው ውስጥ ከጥግ እስከጥግ እንደምንጣፍ
የተነጠፈው አስፋልት መሐል የሚታይ የአትክልት ዘር የለም፡፡ ቤቱ
ሕይወት ያለበት አይመስልም፡፡
የገዛ ቤቷ እንደሆነ ሁሉ ሶስና ነይ፡፡ አይዞሽ አትፍሪ” እያለች የዋናውን ቤት የፊት በር ከፍታ ገቡ፡፡ ከውስጥ የተቀበሳቸው ጨለማ ነበር፡፡
በጠባቧ መተላለፈያ ውስጥ ባለው ደብዘዝ ያለ ብርሃን ሦስት የተዘጉ በሮች
ይታያሉ፡፡ ስልክ የተቀመጠበት ትንሽ ጠረጴዛና ወንበር ጥግ ይዘዋል፡፡
በተረፈ ምንም የለም:: ድንገት የታፈነ የሚመስል ድምፅ በስተቀኝ በኩል
ካለው በር ጀርባ መጣ፡፡ ሰዎች የሚነጋገሩ ይመስላል በለሆሳስ፡፡

ነይ እንጅ…” አለች ሶስና በስተቀኝ ወዳለው በር እያመራች፡፡ ርብቃ
ከተል አለቻት፡፡

ከውስጥ የተቀበላቸው ክፍል ከመተላለፊያው የተሻለ ብርሃን ያለበት
ቢሆንም እዚያም ያለው ጨለማ ለአይን የሚከብድ ነበር፡፡ እራቅ ካለ ማዕዘን
የቆመው ባለ ረጅም ቋሚ መብራት ድብዝዝ ያለ ብርሃን ይተፋል፡፡ ከቋሚ
መብራቱ ቀይ ጨርቅ የሚፈሰው ብርሃን ቤቱን ፍም አስመስሎታል፡፡

“ይቅርታ ስላረፈድን፡፡ አንደምን ዋላችሁ።” አለች ሶስና በደፈናው፡፡

በሳሎኑ ክፍሉ ውስጥ ሰዎች ተቀምጠዋል፡፡ ወዲያ ማዶ የተዳፈነው
ቀይ ብርሃን አጠቃላይ ቁመናቸውን እንጅ ገፅታቸውን ጥርት አድርጎ አያሳይም።

“ዛሬ አዲስ እንግዳ ይዤ ነው የመጣሁት።” አለች ሶስና የርብቃን
እጅ ይዛ ወደ ሳሎኑ እየተጠጋች፡፡
ማናቸውም ድምፅ አላሰሙም፡፡ በተቀመጡበት “ጭንቅላታቸውን
እያነቃነቁ ስምምነታቸውን ሲገልፁ ርብቃ በጨለማ ውስጥ ሸንጎ የተቀመጡ
አማልክት መሰሏት።
ሶስና ከማናቸውም ጋር አላስተዋወቀቻትም::የርብቃን ስም አልተ
ናገረችም፡፡ አንድ ፎቴ ላይ እንድትቀመጥ ካመለከተቻት በኋላ ከወደጥግ ካለ
ጠረጴዛ ላይ ወደ ተቀመጠች አነስተኛ ማቀዝቀዣ ሄዳ ከፈተቻት፡፡ ለአንድ
አፍታ ከማቀዝቀዣዋ ውስጥ የወጣው ብርሃን በሳሉን ክፍል ውስጥ ሲናኝ
ርብቃ ከፊት ለፊቷ የተቀመጡትን ሦስት ሰዎች ተመለከተቻቸው… ሁለቱ
ወንዶች ሲሆኑ በስተቀኝ ዳር ያለችው ሴት ነች… በስተግራዋ