#በራ_የመስቀል_ደመራ
በራ የመስቀል ደመራ
የአደይ ችቦ እየፋመ እየጋመ
ኢዮሃ እያስገመገመ እየተመመ
#የመስቀል_ደመራ_በራ
በራ የአዲስ ዘመን ችቦ
በመስከረም ሰብል አብቦ
ከዋክብቱን ፈነጠቀ
ርችቱን አንፀባረቀ
ተኳለ አዲስ ደመቀ
መልኩን በቀለም አዝርእት፤ በጥበብ
አጥለቀለቀ።
ሸለቆው ተንቆጠቆጠ፡ ተራራው አሸበረቀ
ኢዮሃ ኢዮሃ አበባዬ፡ ምድር ሕይወት አፈለቀ፡፡
ነጋ፡ የአዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ፡ ፀደይ አረብቦ
ሌሊቱ እንደጎሕ ቀደደ፤ ጨለማው እንደቀን
ጠራ
እንደውቅያኖስ ዕፅዋት፤ እንደጠፈር ኮከብ
ደራ
ምድር ሥጋጃ ለበሰ፤ የጌጥ አልባሳት ተቀባ
ሰማይ በእልልታ አስተጋባ
ኢዮሃ መስከረም ጠባ፡፡
ነጋ የአዲስ ዘመን ችቦ፤ ምድር ሕይወት
አፈለቀች
የምሥራች አዝርእቷን፤ አዲስ ቡቃያ ወሰደች
የአደይ አበባን ለገሠች
ለአዲስ ዘመን አዲስ ብርሃን፤ አዲስ
መስከረም ገበየች
#ነጋ የአዲስ ዘመን ችቦ
#ፈካ ፀደይ አረብቦ
#በራ
የመስቀል ደመራ፡፡
🔘ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን🔘
💚💛❤️
በራ የመስቀል ደመራ
የአደይ ችቦ እየፋመ እየጋመ
ኢዮሃ እያስገመገመ እየተመመ
#የመስቀል_ደመራ_በራ
በራ የአዲስ ዘመን ችቦ
በመስከረም ሰብል አብቦ
ከዋክብቱን ፈነጠቀ
ርችቱን አንፀባረቀ
ተኳለ አዲስ ደመቀ
መልኩን በቀለም አዝርእት፤ በጥበብ
አጥለቀለቀ።
ሸለቆው ተንቆጠቆጠ፡ ተራራው አሸበረቀ
ኢዮሃ ኢዮሃ አበባዬ፡ ምድር ሕይወት አፈለቀ፡፡
ነጋ፡ የአዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ፡ ፀደይ አረብቦ
ሌሊቱ እንደጎሕ ቀደደ፤ ጨለማው እንደቀን
ጠራ
እንደውቅያኖስ ዕፅዋት፤ እንደጠፈር ኮከብ
ደራ
ምድር ሥጋጃ ለበሰ፤ የጌጥ አልባሳት ተቀባ
ሰማይ በእልልታ አስተጋባ
ኢዮሃ መስከረም ጠባ፡፡
ነጋ የአዲስ ዘመን ችቦ፤ ምድር ሕይወት
አፈለቀች
የምሥራች አዝርእቷን፤ አዲስ ቡቃያ ወሰደች
የአደይ አበባን ለገሠች
ለአዲስ ዘመን አዲስ ብርሃን፤ አዲስ
መስከረም ገበየች
#ነጋ የአዲስ ዘመን ችቦ
#ፈካ ፀደይ አረብቦ
#በራ
የመስቀል ደመራ፡፡
🔘ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን🔘
💚💛❤️
#በራ_የመስቀል_ደመራ
የአደይ ችቦ እየፋመ እየጋመ
ኢዮሃ እያስገመገመ እየተመመ
የመስቀል ደመራ
በራ።
በራ የአዲስ ዘመን ችቦ
በመስከረም ላብል እብቦ
ከዋከብቱን ፈነጠቀ
ርችቱን አንጸባረቀ
ተኳለ አዲስ ደመቀ
መለኩን በቀለም እዝርእት በጥበብ አጥለቀለቀ
ሸለቆው ተንቆጠቆጠ፥ ተራራው አሸበረቀ
ኢዮሃ ኢዮሃ አበባዬ! ምድር ሕይወት አፈለቀ።
ነጋ፥ የእዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ፥ ፀደይ አርብቦ
ሌሊቱ እንደጎሕ ቀደደ፥ ጨለማው እንደ ቀን ጠራ
እንደውቅያኖስ ዕፅዋት እንደጠፈር ኮከብ ደራ
ምድር ሥጋጃ ለበሰ፥ የጌጥ አልባሳት ተቀባ
ሰማይ በእልልታ እስተጋባ
እዮሃ መስከረም ጠባ።
ነጋ የአዲስ ዘመን ችቦ፥ ምድር ሕይወት አፈለቀች
የምሥራች እዝርእቷን፥ እዲስ ቡቃያ ወለደች
የአደይ አበባን ለገሠች
ለአዲለ ዘመን አዲስ ብርሃን፥ አዲስ መስከረም ገበየች።
ነጋ፥ የአዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ፡ ፀደይ እረብቦ
በራ፥
የመስቀል ደመራ።
መስከረም - ፲፱፻፳፫ - መስቀል አደባባይ
🔘ፀጋዬ ገብረመድህንን🔘
የአደይ ችቦ እየፋመ እየጋመ
ኢዮሃ እያስገመገመ እየተመመ
የመስቀል ደመራ
በራ።
በራ የአዲስ ዘመን ችቦ
በመስከረም ላብል እብቦ
ከዋከብቱን ፈነጠቀ
ርችቱን አንጸባረቀ
ተኳለ አዲስ ደመቀ
መለኩን በቀለም እዝርእት በጥበብ አጥለቀለቀ
ሸለቆው ተንቆጠቆጠ፥ ተራራው አሸበረቀ
ኢዮሃ ኢዮሃ አበባዬ! ምድር ሕይወት አፈለቀ።
ነጋ፥ የእዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ፥ ፀደይ አርብቦ
ሌሊቱ እንደጎሕ ቀደደ፥ ጨለማው እንደ ቀን ጠራ
እንደውቅያኖስ ዕፅዋት እንደጠፈር ኮከብ ደራ
ምድር ሥጋጃ ለበሰ፥ የጌጥ አልባሳት ተቀባ
ሰማይ በእልልታ እስተጋባ
እዮሃ መስከረም ጠባ።
ነጋ የአዲስ ዘመን ችቦ፥ ምድር ሕይወት አፈለቀች
የምሥራች እዝርእቷን፥ እዲስ ቡቃያ ወለደች
የአደይ አበባን ለገሠች
ለአዲለ ዘመን አዲስ ብርሃን፥ አዲስ መስከረም ገበየች።
ነጋ፥ የአዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ፡ ፀደይ እረብቦ
በራ፥
የመስቀል ደመራ።
መስከረም - ፲፱፻፳፫ - መስቀል አደባባይ
🔘ፀጋዬ ገብረመድህንን🔘