አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
579 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

አቤል ወላጆቹን ትቶ ወደ ትዕግሥት በሐሳቡ መጓዝ ስለጀመረ ዐይኑን ቦዘዝ እንዳደረገ ዝም አለ ።

ምነው ? ”አሉ ዮናታን ፥ አንዳች ስሜቴን የሚጎዳ ነገር የተናገሩ መስሎአቸው ተደናግጠው ። ሐሳባቸው ዘሎ
ያረፈው እናቱ ወይም አባቱ ሞተዋል ከሚል ግምት ላይ ነበር ። ይህን ደግሞ ከአሁን በፊት አልነገራቸውም ፡ ግራ ተጋቡ።

“ ምንም አይደለም ”አላቸው ከሐሳቡ ባነነና ። እርስዎ ለእኔ ያለዎት ክብርና ፍቅር እየታሰበኝ ነው ።ለእኔ መድከምዎ አንሶ ወላጆቼን ሊረዱልኝ ሲያስቡ ... ”

“ ይህ ውለታ ሆኖ ካሳሰበህ ተሳስተሃል ” አሉት ዮናታን “ይህ ማንኛውም ዜጋ ሊያደርገው የሚገባ ነገርም ነው ። ማስተማር ለእኔ ግዴታ ሳይሆን ፥ የመንፈስ ክብርና ኩራት የሚሰጠኝ መስክ ነው ። እናም ጥሩ ተማሪዬን ጥሩ
ቦታ ወይም የሙያ ዘርፍ ላይ ለማየት እንጂ የማስተማር ግዴታዩን ለመወጣት ብቻ አይደለም የማስተምረው ። መረዳዳት ያስፈልጋል ። ደግሞም አጥብቀን አናስበውም እንጂ
ከመረዳዳት ውጪ የሆነ እንቅስቃሴ ምን ታገኛለህ ? ሁሉም የግል ጎጆ ቢቀልስም፡ የሕይወት እንቅስቃሴው የጋራ ነው። ማኅ
በረሰብ ከሌለ ግለሰብ የሚባል ነገር የለም " ምኑን ከምን አርጎ ሊንቀሳቀስ ? ነገሩ ይህ ሆኖ ሳለ ከግል ኑሮአችን በመነሳት የምናደርገው፥ ማኅበራዊ ግንኙነት ከመረዳዳት እንጻር
አጉልተን አናየውም እንጂ ኑሮአችን በመረዳዳት የተሳሰረ ነው።

ዮናታን ከልባቸው እየተመሰጡ ንግግራቸው እየጎላና እየረቀቁ ሲሔድ ፥ የአቤልን እንባ አደረቀው ። አፉን ከፍቶ
ነበር የሚያዳምጣቸው ።

“እሺ እንግዲህ 'እንዳሉት 'አሁን ያለኝ ምርጫ ትምህርቴን ማቋረጥ ነው ። እናም አቋርጠዋለሁ ” አለ የሜዝት
በሚመስል ጉልህ ድምፅ "

«« አዎ ! ቆራጥነት ያስፈልጋል አሉ ዮናታን
“ቆራጥ ካልሆንክና ውሳኔ መውሰድ ካልቻልክ ሕይወትህ የተመሰቃቀለ ይሆንብሃል ። አብዛኛውን ጊዜ ሕይወት የባለ ቤቷን ቆራጥነት ትፈታተናለች የቆራጥነትና ወሳኝነት ትርጉም የሚገባህ ውጤቱን ካየህ በሁዋላ ነው ። አይዞህ
በአንተም ሆነ በወላጆችህ ላይ የሚደርስ ጊዜያዊ ችግር ቢኖር በጋራ እንወጣዋለን አንተም ነገ ትልቅ ሰው እንደምትሆን
አትጠራጠር ። ”

በፊት ያንዣብብ የነበረው የጭንቀት ደመና ከአቤል ፊት ሳይ እየጠፋ መሔዱን ሲመለከቱ ዮናታን ደስታ ተሰማቸው
ጥረታቸው ዋጋ እንዳገኘ እድርገው ገመቱ።

“ እሺ ፤ ለማቋረጥ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች ላሟላ ”ብሎ አቤል ከተቀመጠበት ተነሣ ።

“ ግሩም ! ” አሉ ዮናታን ሐሳቡን በመደግፍ ለማቋረጡ ተግባር የምረዳህ ነገር ካለ ብቅ ብለህ አማክረኝ ፡

አቤል እጅ ነሥቶ ሲወጣ በቆራጥነት ስሜት ግንባሩን አኮማትሮ ነበር ። በሐሳቡ የታየው ነገር ይህን “ የሥቃይ
ግቢ ” በአስቸኳይ ለቅቆ መውጣት ብቻ ነበር ። አንድ የሆነ ተቃራኒ ስሜት ጭንቅላቱን ቢከብደውም እስኪወጣ ድረስ ቀውል አልተከሠተለትም ።

ዮናታን ከደስታቸው ብዛት የሚይዙ የሚለቁትን አትተው ፊታቸው የተቀመጡትን ወረቀቶች ያለ ምንም ዓላማ ወዲያ ወዲህ ያገላብጡ ጀመር ፡ አቤል ሐሳባቸውን መቀበሉን የመጀመሪያው ደረጃ አድርገው ወሰዱት የዕቅዳቸው መጀመሪያ እንደ ተሳካ አድርገው በመገመት በጥረታቸው ረኩ ።

“ እሺ እንግዲህ ፡ ትምህርቱን አቋረጠ ። ከዚያ በኋላስ ምን መደረግ አለበት?” በማለት ዮናታን ፥ አቤልን ከተጠመደበት የዐይን ፍቅር ሕመም ለማዳን የሚቀጥለው ደረጃ ምን መሆን እንዳለበት ማሰብ ጀመሩ ። ይህን ሐሳብ በማውጣትና በማውረድ ላይ እንዳሉ በሩ ተከፈተ ።

ቀና ሲሉ አቤል ነው ፊቱ ከስሏል ዐይኖቹ ቀልተዋል በሆነ ስሜት ከራሱ ጋር የተጣላ ይመስላል ከኋላ እንደ ተባረረ ሰው እየቻኮለ ነበር በሩን የከፈተው።

ይቅርታ ያድርጉልኝ ለምን እንደ ዋሸሆዎት አላውቅም። ምናልባት ፈርቼዎት ይሆናል ትምህርቴን ማቋረጥ የለብኝም ብሞክርም አልችልም አላቸው ወደ ውስጥ ሳይገባ በሩ ላይ ቆሞ።

ዮናታን ግር አላቸው ምን ሰይጣን ነው በአንዴ ሐሳቡን ያስቀለበሰው ለጊዜው
የሚመልሱትም ሆነ የሚጠይቁት ነገር እልነበራቸውም።

አቤል ሐሳቡን የቀየረው በሩን ወጥቶ ገና ጥቂት እንኳን ሳይራመድ ነው ። ክፍል ውስጥ ሆኖ ከዮናታን ጋር ሲስማማ ከውስጡ ሲጫጫነውና ሲከብደው የነበረው ተቃራኒ ስሜት ገና ከመውጣ እውነት አሁን ትምህርትህን አቋርጠክ ይህን ትእግስት ያለችበትን ግቢ ልትለቅ ነው? እውነት ከትእግስት ጋር ሳትተያይ ውለህ ማደር የምትችል ይመስልሃል?
የዐይን ፍቅረኛህን ትተህ የት ልትደርስ? እያለ እንደ ጥላ ተከተለው ። አቋርጣለሁ እያለ ቀድሞ ሲፎክር የነበረው ሁሉ ባዶ ጩህት ሆኖ አገኘው ትእግሥትን ጥሎ
ወዴት ?

ለዮናታን ቃል መግባታ አሳዝነው ። እንዴት እንደሚያስተባብላቸወ በማሸበ ቆሞ ተጨነቀ። ሆኖም ዮናታን ያቋርጣል በሚል ተስፋ ልባቸውን ሞልተው እንዳይቀመጡ ቶሎ ተመልሶ ማስተባበል
ነበረበት እራሱን እየረገመ ነው የተመለሰው ምነው? ተስማምተን አልሔድክም እንዴ? ምን ነካህ? ” አሉት ዮናታን በተደናገጠ ስሜት።

አዎ በሃሳቦዎ ተስማምቼ ነበር የወጣሁት ነገር ግን አርቄ ሳስባት ፈተና ተፈትኜ ዕድሌን መሞከር አለብኝ ?” አላቸውና መልስ ሳይጠብቅ ፊቱን አዙሮ ሔደ።

«ስማኝ እንጂ አቤል ! ቆይ እስቲ ?” አሉት ዮናታን ከተቀመጡበት ተነስተው ሊከተሉት እየሞከሩ ዝም ብሏቸው ካጠገባቸው መጭ አለ።

ዮናታን በብስጭት ፈዘው ቀሩ ለሰም ሰው እኔ ምን አስጨነቀኝ ? ” የሚል ተፈታታኝ ሐሳብ መጣባቸው
ተስፋ የመቁረረጥ ስሜት ተስማቸው አኳኋኑ አናደዳቸው ግን ሁኔታን ባስታወሱ ጊዜ ልባቸው ሊጨክን አልቻለም ። እድራጎቱ አንድም የልጅነት አሊያም የፍቅር ቡሶት ነው ደመደሙ።

ቢሮእቸውን ቆልፈው ቀጥታ ወደ አቶ ቢልልኝ ቢሮ አመሩ አረማመዳቸው የሩጫ ያህል ነበር ። በመንገዳቸው
ላይ ሦስት ያህል የሚያውቋቸው ሰዎች ሰላምታ ሳይሰጡ ማለፋቸው አልታወቃቸውም።

ከከባቢልልኝ ቢሮ እንደ ደረሱ ሰላምታ እንኳን ሳይለዋወጡ አረእስተ ጉዳያቸውን አነሱ።

«ቢልልኝ የዚያን ልጅ ጉዳይ ሁላችሁም ቸል ማለታችሁ ነው ?

አቶ ቢልልኝ ! የዮናታን አርእስቱ ስለ አቤል ጉዳይ መሆኑ ለመገመት ጊዜ አልወሰደባቸውም።

የአቤልን ነገር ነው ?...ችላ ማለት አይደለም ኮ እኔ በበኩሌ የዐቅሜን እየመበከርኩ ነው። ሆኖም የልጁ ሁንታ
አስቸኳይ መፍትሔ የሚገኝለት አልሆነም።

"እንዴት ? ” አሉ ዮናታን ፡ ለመቀመጥ ወንበሩን እየሳቡ።

እስቸኳይ መፍትሔ ለማግኘት ልጁ ምቹ አይደለም ቢልልኝ ወደ ጉዳዩ ጠልቀው ሲገቡ ፊታቸው እየተለዋወጠ አዎ አቤል ግልጽ አይደለም ። አንዳንዱ ሰው ሰላፈቀራት ሴት ላገኘው ሰው ሁሉ በየደቂቃው ካላወራ አይሆንለትም ፤ ሌላ አርዕስት የለውም ። ሁሌ ሰው ለሰ
ፍቅር መፍትሔ የሚፈልግለት ይመስለዋል አንዳንዴ ደግሞ ለማንም ሳያዋይ ፍቅሩን ራሱ ዋጥ አርጎ ውስጥ ውስጡን
መቃጠል ይመርጣል ። ሌላ ሰው ለሱ ፍቅር ጤናማ አመለካከት ያለው አይመስለውም የአቤል በደረጃ ከመለየቱ በቀር ይሄኛውን ይመስላል ሁሉም አይነት ግን አስተዳደግና አካባቢን የተመረኮዘ መሠረት ይኖረዋል።

"ታዲያ አሁን የአቤል ነገር እንዴት ይሻላል ?” አሉ ዮናታን ፥ በተጨነቀና በተቻኮለ ስሜት ።

“ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ መፍትሔ ያገኛል ” አሉ ቢልልኝ፡ “ ጊዜ ! ጊዜ ይወስዳል ። የሥነ ልቡና ጥናት
ሥራ ዘዴና ትዕግሥት ይጠይቃል አቤል ፥ ሌላው ቀርቶ የግል የሕይወት ታሪኩን ለመናገር ፈቃደኛ አልሆነም
ስለዚህ ሥራችን