አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ሁለት ሳምንታት ያህል በጉጉት ጠበቀች፡፡ እንዳሰበችው ግን አቶ
መሠረት ሀሳቡን ቀይሮ ሥራ እንድትጀምር ሳይሆን፤ ማስረጃዎቿን በጊዜ መጥታ የማትወስድ ከሆነ፣ ቢጠፋ ተጠያቂ ያለመሆኑን ገልጸ፧ ለመጨረሻ ጊዜ
ስልክ አስደወለላት፡፡ በዚህ ጊዜ ተስፋ ቆርጣ ማስረጃዎቿን ልታመጣ ሄደች፡፡ የተመለሱላትን የትምህርት ማስረጃዎች
ጠቅልላ ከቤት ስትደረስ፤ ሰውነቷ ጥላሸት መስሎ፣ ውበቷ ጠፍቶ፤ እሷ
አትመስልም ነበር፡፡

እናቷ በአልጋ ላይ እንደተጋደመች የልጇን ሁኔታ ስትመለከት፤ ልቧ ተሸበረ፡፡ ከበሽታዋ የበለጠ በዕድሜ ያልበሰላች ሴት ልጇ ለመከራ በመጋለጧ ውስጥ አንጀቷን ሀዘን እያኘከው.......

“ለዚህ የዳረግኋት እኔ ነኝ” በሚል ስሜት እራሷን ጠላች፡፡

ከሽቦ አልጋው ላይ ትራሱን ወደላይ ሳብ፣ ጥርሶቿን ንክስ፣በማድረግ፤ የውስጥ ድካም ስሜቷን ውጣ ቀና አለች፡፡ ትህትና እናቷን ጉንጫን ሳም አደረገችና፤ እኒያ እንደ ሕጻን ልጅ ጥርስ ወተት የሚመስሉት ጥርሶቿን ብልጭ አደረገችላት፡፡

“አንዱዓለሜ አልመጣም እማዬ?” ስትል ጠየቀቻት፡፡
“አንቺ እንደወጣሽ የወጣ ነው ትሁቴ” ስትል መልስ ሰጠቻት እናቷ፡፡
“አሁን እንዴት ነሽ እማይዬ ተሻለሽ?” ትኩሳቷን በመዳፏ እየለካች ጠየቀቻት፡፡ ወደ እናቷ ቀረብ ብላ እየተቀመጠች።
“ምንም አልል፡፡ ዛሬ ከወትሮው ቀለል ብሎኛል። አታስቢ”
“እህህ ....” አለችና በረጅሙ ተነፈሰች፡፡
“ምነው ትሁቴ? መልክሽ ሁሉ ልውጥውጥ አለበኝሳ?” እሷም
ልጇን በስስት እየደባበሰች የሆነችውን እንድትነግራት ጠየቀቻት።
የገጠማትን አሳዛኝ አጋጣሚ ነግራት የበለጠ ልታሳዛናት አልፈለገችም፡፡
“ምንም አልሆንኩ፡፡ በእግሬ ብዙ መንገድ ስለሄድኩ ደክሞኝ ነው” ዋሸቻት፡፡

“ምነው የኔ እመቤት ሰውነትሽ ሁሉ ልውጥውጥ ብሎ እያየሁት? ተይ የሆንሽው ነገር አለ፡፡ አትደብቂኝ?” በልምምጥ ዐይን አይኗን እያየቻት፡፡ ዐይኖቿ እንኳንስ የእናቷን የሌላውን አንጀት የመብላት ልዩ ተፈጥሮአዊ ውበት አላቸው፡፡

ያቺ የውበት ንግሥት የሆነች ልጅ ፤ ሰሞኑን ጉስቁልቁል ብላ ብትመለክት፤ እናቷ ግራ ተጋብታ ነው የከረመችው፡፡
“ሰሞኑን ሁሉ ልክ አይደለሽም፡፡ ከእኔ አልጋ ከያዝኩት የበለጠ ገመምተኛ የመሰልሽው አንቺ ነሽ አኮ!፡፡ ይቅር ምን አባቱ፤ እሱ የፈጠራትን ነፍስ መልሶ ሊወስዳት ካሰበበት ቀን ላንጨምር፤ ላንቀንስ፤በከንቱ እራስሽን መጣልሽ ጥሩም አይደል፡፡ የምን መጨነቅ ነው? የኔ እመቤት?”
“እንደሱ አይደለምኮ እማዬ፤ አንቺማ አሁን ድነሽ እንደምትነሺ አልጠራጠረም፡፡ በቃ እውነቱን ልንገርሽ?” የእናቷን ሁኔታ ስትመለከት ልትደብቃት አልቻለችም፡፡
“እስቲ ንገሪኝ ምን ሆነሽ ነው?” ለመስማት ጉጉት አለች፡፡
“ያ ተስፋ አለው ብዬሽ የነበረው መ/ቤት አንቀበልሽም ብሎ ማስረጃዬን ስለመለሰልኝ፤ ትንሽ ተናድጄ ነው” ነገሩን ቀለል አድርጋ የውስጥ ብሽቀቷን በተላበሰቸው የውሽት ፈገግታ አለሳልሳ ነገረቻት፡፡
“እልም ይበል! ጦስሽን ይዞ ይሂድ! ሌላ ትሞክሪያለሽ፡፡ ላንቺ ያለውን መቼም አታጭው?” አጽናናቻት፡፡

በእውነቱ ከሆነ የገጠማትን ችግር ለእናቷ በመንገሯ ቀላል የሚል ስሜት ተሰምቷት ነበር፡፡ አሁን አሁን ሁሉም ነገር እየመነመነ በመሄዱ ሳይሆን አይቀርም ድሮ ሴቱን የሚወደው ልጅ ትንሹ አንዱዓለም እንኳን ውጭ ማምሸት ጀማምሯል፡፡ የእናቱን የማቃሰት ድምጽ እየሰማ መሰቃየት፤
ሳያስበው በውስጡ መጥፎ ስሜት እየፈጠረበት ስለሄደ፤ ከጓደኞቹ ጋር
ተጨዋውቶ፤ አመሻሽቶ፣ መግባቱን እና አንዳንድ ጊዜም ውጭ ማደርን
አዘወተረ፡፡ ከእናቷ ሥር የማትጠፋው ትህትና ብቻ ነች።
በዚህ ላይ ለእናቷ የሚታዘዘው የመድሃኒት ብዛቱ ለጉድ ነው፡፡ዋጋው ደግሞ እዚያ ላይ ነው፡፡ ሰማይ ጥግ!! ይህ ሁሉ ከየት
ይመጣል? የገቢ ምንጩ እንደሆነ ነጥፏል፡፡ በቤታቸው ውስጥ ያለችው
አንዲት ላም የምትታለብ ቢሆን ኖሮ፤ ወተቷ ተሽጦ፤ ትንሽ ትደጉም ነበር፡፡ በቤት ተወልዳ ያደገችው ጋሬ ግን በዕድሜ ብዛት ይመስላል፤ ማህፀኗ ዘር አላፈራም ካለ ከርሟል፡፡ ዘመድስ እናንተዬ? ለክፉ ቀን የሚሆን ዘመድም ለካ አንድ ነገር ነው፡፡ ለዚህ ችግር የሚሆን ዘመድስ የቱ ነው ከነሱ የተሻለው? በሃሣቧ ዳሰሰች፡፡ ማንም የለም፡፡

አዲሱ ገበያ አካባቢ የሚኖሩት የእናቷ ታላቅ እህት አክስቷ ወ/ሮ ጤናዬ ትዝ አሏት፡፡ ትዝታ ብቻ! እሳቸውም ቢሆኑ የአንድ የሁለት ቀን ችግሯን ሊሸፍኑላት ይችሉ ይሆናል፡፡ ለሌላው ግን አቅም የላቸውም፡፡ የሚኖሩት በጡረታ ገንዘብ ነው፡፡ ከልጆቻቸው ጉሮሮ ተርፋ ጠብ የማትል።

ኤዲያ! አይ ድህነት? እግዚአብሔር ድህነትን ነበር ወይስ ድሃን ነበር ማጥፋት የነበረበት? ብስጭትጭት አለች፡፡ ከእግዚአብሔርም ጋር ለመኳረፍ ዳዳት፡፡ ግን “ይቅር በለኝ አምላኬ አንተ ታውቃለህ የተሻለውን አምጣ” አለችና በልቧ ፀሎት አደረሰች፡፡
“እስቲ ምናምን አፍሽ ላይ ጣል አድርጊ የኔ እናት?” አለቻት እናቷ።

ምን እህል ይበላላታል? እንዲያው ውሃ በብርጭቆ ቀዳችና ጅው አደረገችው፡፡

ከዚያም ብድግ ብላ ለእናቷ ቡና ለማፍላት ልብሷን ቀያየረችና በክሰል ማንደጃው ውስጥ ከሰል ጨማመረች፡፡ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከሰሉ ተቀጣጠለ፡፡ ወዲያው ቡናውን መቁላት ጀመረች፡፡ ጉድ ነው መቼም የፍጥነቷ ነገር አይነሣ! ያ ከጥቂት ጊዜ በፊት ቅዝቅዝ ብሎ የነበረውን ጓዳ ሞቅ አደረገችው፡፡
እግዚአብሔር የሰጣትን ፀጋ እናት በስስት እያስተዋለች።
“አንተ ጠብቅልኝ የኔ ጌታ፡፡ ይህንን . ከአቅሟ በላይ የምታስበውን እስቲ አንተ በቸርነትህ ሸክሙን አቅልላት” ስትል ፈጣሪዋን ለመነች፡፡ በዚህ ሁኔታ እናቷን ቡና ካጠጣችና፤ እህል ቢጤ አፏ ላይ
ካደረገችላት በኋላ፤ ወደ አክስቷ ሄዳ ስለማንኛውም ልታወያያቸው
ፈለገች፡፡
አንዱዓለም እንደሆነ ብቅም አላለም፡፡ ጥናት ላይ ይሆናል ስትል አሰበች፡ በትምህርቱ ጠንካራ ነው፡፡ ምናልባት አሁን አሁን ባመጣው አዲስ ፀባይ ምክንያት ትምህርቱን ችላ ካላለው በስተቀር። ወደ ማምሻው ላይ ፊቷን ተጣጥባ፤ ልብሷን እንደገና ከለወጠች
በኋላ፤ ፀጉሯን አበጣጠረችና፤ አክስቷ ዘንድ ለመሄድ ወጣች።
መቼም ያያት ሁሉ ምራቁን ሳይውጥና በዓይኑ ሳይልጣት አያልፍም፡፡ ቀስ ብላ ዳገቱን ተያይዛዋለች፡፡ በሷ ተቃራኒ ከላይ ወደታች የሚወርዱ ሁለት ጐረምሶች እየቀረቧት መጡ፡፡
“ታያታለህ ይህችን?” ለጓደኛው ጠቆም አደረገና ፊጋ በሬ ይመስል የሾለ ግንባር ያለው አጠር፤ ፈርጠም ! ያለ ጐረምሣ ነው፡፡
“እንዴት ታምራለች በናትህ?” ይሄኛውም በትህትና ውበት ተደነቀ፡፡
“እንልከፋት?”
“በናትህ አንተ ልከፋት፡፡ እኔማ ምኑን እለክፋታለሁ፡፡ለራሴ ተለክፌ የተፈጠርኩ አስቀያሚ ፍጡር? " አለና ጓደኛውን በሳቅ
አፈነዳው፡፡ በከርከሮ ፊት አሣማ ቆንጆ ነው ሆነና እንጂ! እሱም ያው
ነበር

“ምን ልበላት?” ሹክ አለው፡፡ እሷ እንደምትሰማ ሁሉ ድምፁን ዝቅ አድርጎ።
“አጠገባችን ስትደርስ ከዚህ በፊት እንደሚተዋወቅ ሰው ሆነህ ሰላም በላትና፤ አድራሻዋን ተቀበላት”
ምኑንም ሳይዙት፣ የመልከፊያው ርዕስ ሳይመረጥ፣ አጠገባቸው ደረሰች፡፡ አጠገቡ ስትደርስ ጭራሽ ውበቷ ልዩ ሆነበት፡፡ ፈራትም ትንፋሽ ሳያወጣ ቀረ፡፡ ትህትና አልፋቸው ሄደች ጥቁሩ ልጅ በጓደኛው ድርጊት እየሳቀ.....”
“እሺ የኛ ለካፊ! የእንቁራሪት ልብ ይዘህ ነው' ልብ እንዳለው ሰው ልልከፍ የምትለው?አሽሟጠጠው፡፡
ትህትና ስለሷ እንደሚሟገቱ መች አውቃ? በሃሣብ ተውጣ እናቷን ለማዳን የገንዘብ ማግኛ ምንጩ ውል ጠፍቶባት፣ በሃሣቧ እያወጣችና እያወረደች
👍32