አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሰላሳ_አንድ ( #የመጨረሻ_ክፍል )
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
ከአንደኛው መጽሀፍ መሀል ያየቻቸው ሁለት ፎቶዎች ግን ተስፈንጥራ አልጋዋን ለቃ ወለሉ ላይ እንድትቆም አደረጋት…፡፡.ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው..የምታየውን ማመን አልቻለችም..የኮማንዳሩና የወላጅ እናቷ ፎቶ ነው…አንዱ ፎቶ ሁለቱም በዋና ልብስ ሆነው ሙሉ በሙሉ አቅፎት መዋኛ ገንዳ ውስጥ ሆነው የተነሱት ነው…ሌላው ደግሞ ከንፈር ለከንፈር እየተሳሳሙ…… ይሄን ያህል ሄደዋል ብላ አታስብም ነበር ..ስልኮን አነሳችና ደወለች..እሮዝ ጋር ነው..ተነሳ..?
‹‹አሁኑኑ እፈልግሻለው››
‹‹ምነው ልጄ ምን ሆንሺብኝ..?››
‹‹መቀባጠሩን ተይና በአስቸኮይ ኩማደሩ ቤት ነይ››ስልኩን ጠረቀመችው
ሮዝ የለበሰችውን የለሊት ቢጃማ እንኳን ለመቀየር ጊዜ ማባከን አልፈለገችም…ብን ብላ ነው ግቢውን ለቃ ወደኩማንደሩ ቤት የበረረችው ..ልጄን… ልጄን ምን አደረክብኝ....?የሳሎኑን በር በርግዳ ከፈተችና ወደውስጥ ገባች…
‹‹ምን አደረገብኝ ..?ምነ ሆንሺብኝ ..?ተንደርድራ ልትጠመጠምባት ስትል ገፍትራ ከላዬ አራቀቻት….››
‹‹ይሄ የመቼ ፎቶ ነው....?››ሄለን ነች ጠያቂዋ
‹‹የቱ..? እኔጃ..››ግራ ተጋብታ መለሰች
በእጇ የያዘችውን ፎቶ ወረወረችላት .ደረቷ ላይ አርፎ ወደመሬት ወደቀ… ጎንበስ ብላ አነሳችውና ተመለከተችው..
‹‹እሺ መንም አልጀመርንም ብለሽኝ አልነበር..?››ሄለን ነች በሽሙጥ የጠየቀቻት
‹‹ያው ድሮ እኮ ነው…ግን ከተለያየን ብዙ አመት አልፎናል..?››
‹‹በቀደምለታ የመጣሽው እንታረቅ ልትይው ነበር....?››
‹‹አረበፍጽም ..ስንለያይ ተጣልተን ስለነበረ ቂም ይዞብኛል..አንቺን በማጥቃት እንዳይቀለኝ ስለፈራው ከአንቺ እንዲርቅ ልለምነው ነው…››
‹‹ኦኬ አሁን በጣም ገባኝ….ለመሆኑ ኩማደሩን እንደማፈቅረው ታቂያለሽ..?››
‹‹አታደርጊውም ልጄ..እኔ በህይወት እያለው አታደርጊውም››
‹‹አትጠራጠሪ አደርገዋለው..እንደውም ማግባት ሁሉ የምፈልገው እሱን ነው››
‹‹አረ ተይ ልጄ…እራስሽን ወጥመድ ውስጥ ለምን ትከቺያለሽ....?እሱ እኮ ውስጡ በቀል እንጂ ፍቅር የለበትም…..››
እሱ እኔን አይመለከተኝም…እንደውም እኔም አንቺን ለመበቀል ስለምፈልግ ጥሩ አጋጣሚ ነው…ለመሆኑ ምን ያል ብትበድይው ነው .. ..?ለነገሩ አንቺ አይደለሽ ምንም ብታደርጊው አይደንቀኝም….ለማንኛመው ከዛሬ ጀምሮ በመሀከላችን እንዳትገቢ ልነግርሽ ነው..አሁን የድሮ ፎቶሽን ይዘሽ ወጭልኝ…;››
‹‹በፈጠረሽ ልጄ›› እግሯ ላይ ተደፋች..
‹‹ምንም ብታርጊ ሀሳቤን አታስቀይሪኝም…ምን አልባት በአንድ ነገር..››
‹‹ምንድነው ልጄ …የፈለግሽውን ጠይቂኝ..ከዚህ ሰይጣን ራቂለኝ እንጂ ያልሺኝን ሁሉ አደርጋለው››
‹‹ያው የእኔን ጥያቄ ታውቂያለሽ… ተመሳሳይና የማይቀየር ነው…የአባቴን ማንነት ከነገርሺኝ እተወዋለው…››
‹‹አባቴን....?››ከተደፋችበት ተነሳችና መቀመጫ ይዛ ተቀመጠች
‹‹አዎ ንገሪኝ..ከእሱ እንድርቅ ከፈለግሽ ንገሪኝ››
‹‹እሺ ቁጭ በይ….ነግርሻለው››
ሁለቱም ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀመጡ
‹‹እንግዲያው ንገሪኝ ካልሽ ምርጫ የለኝም ነግርሻለው….ግን ለምትሰሚው ነገር እራስሽን አዘጋጂ››
‹‹ግድ የለሽም መግቢያውን ተይና ወደዋናው ታሪክ በቀጥታ ግቢልኝ››
‹‹ይሄውልሽ ልጄ ግማሽ ዕድሜዬን ይሄንን ታሪክ ለሌላ ሰው ይቅርና ለእኔው ለእራሴው ለመናገር ስሸሸው የኖርኩትን ነገር ነው፡፡ይሄው ዛሬ ሳልወድ በግድ ለመናገር ተገድጄያለው፡፡እስከዛሬ ነገሩን ሚስጥር አድርጌው የኖርኩት ለእናቴ ስል ነበር..አሁን ደግሞ ለመናገር የተገደድኩት ለአንቺ ለልጄ ስል ነው..ከእናቴ ስሜትና ደህንነት ይልቅ የልጄን ስሜት እና ደህንነት አስቀድሜ ነው..መቼስ አናቴ ልጅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስለምታውቅ ይቅር ትለኛለች ብዬ አስባለው፡፡
ማንኛውም የሰው ልጅ በትዝታ ፈረስ ፊቱን ወደ ኃላው አዙሮ ትናንትናውን ሲያይ መዝለል የሚፈልገው ወይም አለማሰብ የሚመኘው ወይም ምነው ባልኖርኩት ኖሮ ብሎ የሚጠየፈው በጊዜዎች ክፍተት መሀከል የተከወነ ጨለማ ታሪክ ይኖረዋል፡፡የእኔን የተለየ የሚያደርገው ግን ያለፈ ህይወቴ ውስጥ የተከሰተው ጠባሳ አይደለም መሰረዝ እንዲደበዝዝ ማድረግ እንኳን የማይቻል ስለሆነ ዕድለኛ አይደለውም፡፡
ልጄ አንቺ ለእኔ ማለት የበደሌ ምልክት፤ የክስረቴ ትርፍ ነሽ፡፡ሰው ህይወቱን የሚያሳጣው …ማንነትን የሚያወድመው ነገር ከስሮ በዛው ልክ ህይወቱን የሚያለመልምለት እና ለመኖሩ ምክንያት የሆነ ነገር ያተርፋል…እኔ ማለት እንዲያ ነኝ..የነገ ተስፋዬን፤ለመኖር የሚረዳኝን ሞራሌን፤ማንነቴን አጥቼ በምትኩ ግን አንቺን አገኘው፡፡
‹‹አረ የምትይው ነገር ምንም እየገባኝ አይደለም…››መለሰችላት ሄለን
‹‹የእኔ ህይወት ለእኔም ለእራሴ ብዙ ጊዜ አይገባኝም፡፡ግን ቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ልግባ፡፡አንቺን የወለድኩሽ ተደፍሬ ነው፡፡መቼ? ገና 15 ዓመት ሳይሞላኝ፡፡ማን የደፈረኝ ይመስልሻል..?የምትወጂው አጓቴ ነው፡፡ላስተምርሽ ብሎ ከእናቴ በአደራ ተቀብሎ አዲሳባ ወስዶ ደፈረኝ ..አስረገዘኝ …››
‹አጎቴ!!!!.. አጎቴ ማለት የማዬ ወንድም … አንቺን››
‹‹አዎ አጎቴ እኔን …ያ ማለት ደግሞ አንቺ የእሱ ልጅ ነሽ… አባትሽ ነው፡፡
‹‹እኔ አላምንም…››ሄለን ምትሆነው ምትናገረው ነገር ጠፋት
‹‹ልጄ ነፍስ ካወቅሽበት ጊዜ አንስቶ አባቴ ማን ነው ?ብለሽ ስትጠይቂኝ..የተለያየ ሰበብ እየፈጠርኩ ልነግርሽ ያልቻልኩት ነገሩ ለሰሚውም ግራ ሰለሆነብኝ ነው፡፡ ልጄ እስቲ አስቢው በገዛ አጐቴ ተደፍሬ አንቺን እንደወለድኩሽ ስትሰሚ በአንቺ ሰነ-ልቦና ላይ የሚያደርሰውን መረበሽና ተፅዕኖ በምን ማረጋገጥ እችላለው? እንደእኔ ስብርብር ብትይብኝስ.?.ከሁሉም በላይ ደግሞ ይሄ ጉዳይ እናቴ ጆሮ ይሄ ዜና ቢደርስስ ?የገዛ መንትያ ወንድሟ ከመሀጸኖ ፈልቅቃ አምጣ የወለደቻትን እና አደራ አሳድግልኝ ብላ ያስረከበቻትን ጨቅላ ልጆን በድልዱም ቢላዎ ገዝግዞ እንዳረዳት እና ህይወቷን እንዳበከተባት ብትረዳ በድንጋጤ ህይወቷ ባያልፍ እንኳን ጨርቋን ጥላ ማበዶ ይቀራል ብለሽ ታስቢያለሽ…?.ለዚህ ነው ከአንቺ ጋር ስጋጭ እና ስጣላ የኖርኩት፡፡ ለዚህ ነው እራሴን እንደ ጥፋጠኛ አስቆጥሬ ስባልግ እና ስንዘላዘል በገዛ ስህተቴ እደወለድኩሽ እዲታሰብ አድርጌ ግማሽ ዕድሜዬን እንደጋጠወጥ እና እንደ አለሌ ሸርሙጣ እየታሰብኩ በመኖር እራሴን ያሰቃየውት...እርግጥ አልዋሽም ሸርሙጣ የሚለው ስም አይገባኝም አልልሽም..በደንብ ይገባኛል..፡፡ግን በሽታ ሆኖብኝ ነው፡፡ከመደፈሬ ጋር የተፀናወተኝ እኔ እራሴ የምጠየፈው እና የምፀፀትበት ክፉ በሽታዬ ነው፡፡
ልጄ እንግዲህ እውነቱ ይሄ ነው፡፡አባትሽ የምትወጂው አጐትሽ ነው..ከአሁን ቡኃላስ እሱን መውደድሽን ትቀጥያለሽ…?እንግዲህ እሱ የአንቺ ጉዳይ ነው፡፡እኔን ግን ካጠፋውት በላይ ስቀጣ የኖርኩ ሚስኪን እናት ነኝና እባክሽ ይቅር በይኝ እና ቀሪ ህይወቴን ትንሽም ቢሆን ተስፋ እንዲኖራት እርጂኝ፡፡ከእዚህ ሰውዬ ራቂ..እሱን በጣም በድዬዋለው….ሊያገባኝ ሲዘጋጅ ነው ጥዬው ወደአዲስ አበባ የገባውት ..ስለዚህ ለአመታት ሊበቀልኝ ሲጥር እደነበረ አውቃለው..እና ልጄ ….
…ሄለን ከተቀመጠችበት ተነስታ ተንደርድራ ነው እግሯ ላይ የተደፋችባት….‹‹እማዬ የምትችይ ከሆነ ይቅር በይኝ..ባክሽ ይቅር በይኝ››እየነፈረቀች ተማፀነቻት
ሮዝ ከገባችበት መደንዘዝ ውስጥ እንደምንም ነቃችና እሷም ተከትላት ቁጢጥ በማለት ልጆን ከተደፋችበት አንስታት አቀፈቻት… አገላብጣ ሳመቻት ‹‹ልጄ ….ልጄ
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በክፍለማርያም

...ያንቺ ነዉ ሲል አፋጠጣት
ቤዛዊት አንዴ ፍፁምን አንዴ አባቷን አፈራርቃ እያየች
የተረገመ ፍቃዱን በዉስጧ እየረገመች መሬት ላይ የወደቀዉን
ጡት ማስያዣ አንስታ እና ንዴቷ እየተቀሰቀሰ አይኗን
እያጉረጠረጠች
"ያንተ ነዉ ልስጥህ ...አንተ ሴታሴት ወረኛ" ጥፍሮቿን አሹላ ወደ ፍቃዱ ተጠጋችዉ
ፍቃዱ አዋረድኳቸዉ ብሎ መዋረዱ እየታየዉ አመጣጧ እያስፈራዉ ወደ አባቷ ቀስ እያለ መጠጋት ጀመረ
"አረ ተረጋጊ ሴትዮ"
አፉ ላይ የመጣለትን ቃል እያወራ
ፍፁም ለመገላገልም አልተነሳም አልጋዉ ጠርዝ ላይ ተቀምጦ
የጥፋተኝነት እና ደግ አረኩ በሚል ሁለት የተቃረኑ ሀሳቦች
ተዉጦ ከሀሳቡ ያነቃዉ ብርጭቆ ከግድግዳ ጋር ሲጋጭ
የሚያሰማዉ ድምፅ ነበር
"ኳኳ ከሽሽሽሽሽ"
ፍቃዱ በሩን በርግዶ እየተንደፋደፈ ወጣ አባቷ በድንጋጤ ተዉጠዉ አንገታቸዉን አቀርቅረዉ እና ፍጥርጣሪዉን ፈርተዉ።

አይናቸዉን ጨፍነዉ ቆይተዉ
ልጃቸዉን በልመና አስተያየት እያዩዋት
"ተረጋጊ ልጄ በቃ"
እያሉ መለመን ጀመሩ መታመሟ እየመሰላቸዉ እየፈሩ
በንዴት የጦፈችዉ ቤዛዊት የወረወረችዉ ብርጭቆ
ፍቃዱን ስላላገኘዉ እና እልኋ ስላሎወጣላት ግላ
"ሁለተኛ ይሄን የተረገመ ሰዉ ማየት አልፈልግም"
እጆቿ እየተንቀጠቀጡ እና የታችኛዉን
ከንፈሯን ወደ አፍዋ ዉስጥ ስባ በጥርሶቿ ነክሳ።
በትክክለኛዉ ስዓት አንዳንዴ ጥፋትን ለመሸፈን ሌላ ጥፋት
ማጥፋት የመጀመርያዉ ጥፋትን ያደበዝዝልናል
ሰዓቱን ካልጠበቀ ደሞ በሁለት ስህተት ቅጣት ያስጠይቀናል
መልካም ነገርም እንደዚህ ነዉ በትክክለኛዉ ስዓት
ጥሩ ነገር ላይ ሌላ ጥሩ ነገር ማስራት እና ድጋሜ ጥሩ ማሰብ
የመጀመርያ ደስታችንን አስረስቶ ወደ እጥፍ ድርብ ወደ ሆነ ደስታ ዉስጥ ይከተናል።

አባቷ ልጃቸዉ ቤዛዊትን እየለመኗት ይዘዋት እየወጡ ነዉ
ዞራ ፍፁምን ተመለከተችዉ ምን ማረግ ይችላል ከአባቷ ነጥቆ ማስቀረት አይችል እየከፋዉ እና እያዘነ ለመሰናበት
እጆቹን አየር ላይ አነሳ እስዋም በአይኖቿ እንባ እየቀረሩ እያየችዉ
አባቷ አቅፈዉ እንደያዟት ወደ ዉጪ ወጣች የቤዛዊት አባት እግሬ
አዉጭን ብሎ የሮጠዉን ፍቃዱን በአይናቸዉ እየፈለጉት ነበር
ቤዛዊት የአባቷ መኪና ዉስጥ ገብታ ስትቀመጥ ወረቀት እና
እስኪርቢቶ ስላገኘች ፊቷ ፈገግ እያለ የሆነ ነገር ሞነጫጭራ ፅፋ
ኪሷ ዉስጥ አባቷ እንዳያዩዋት ከከተተች በኋላ
"የረሳሁት እቃ አለ መጣሁ.."
አባቷን ብላቸዉ ከመኪናዉ ወርዳ ወደ ፍፁም ቤት መሮጥ ጀመረች።

ፍፁም ቤዛዊት እንደወጣች ብቸኝነት ቀንድ አዉጥቶ መልክ ኖሮት
ሰፈረበት ከፋዉ
ወራቶች እያለፉ ስለሆነ በዚህ ወቅት የትም ትምህርት ቤት
ተቀጥሮ ማስተማር እንደማይችል ሲያስበዉ ከአልጋ ወደ አልጋ
ቦታ እየቀያየረ እየመሰለዉ አዘነ
ቤዛዊትም የእሱ ትሁን አትሁን ግራ በገባዉ ሁኔታ ስትታመም
ሲሻላት አብሯት ከጎኗ እንዳይሆን መሰናክል ሲበዛበት
ይባስ ብለዉ ቤተሰቦቿ ጣልቃ እየገቡ እረፍት እና ደስታ ስለነሱት
ተስፋ ወደ መቁረጥ እየሄደ እየተጨነቀ ሲያስብ በሩ ተበርግዶ
ተከፍቶ ቤዛዊት እየፈጠነች ገብታ ሀይሏን በሙሉ ትከሻዉ ላይ
ጥላበት ካቀፈችዉ በኋላ እና ከንፈሩን በፍጥነት ለኮፍ አርጋ
ስማዉ እንደለመደችዉ ከኪሷ የተጣጠፈ ወረቀት አዉጥታ
ሰጥታዉ በገባችበት እየፈጠነች ወጣች።
ከወጣች በኋላ ወረቀቱን ገልጦ አነበበዉ የቦታ ስም ተፅፎበታል
አቅጣጫዉን እና ነገ ሶስት ሰአት እንገናኝ ይላል
አንብቦት ሲጨርስ ደስ እያለዉ በጀርባዉ ጋደም አለ።

ቤዛዊት ቤቷ ስትደርስ መሳቅ መጫወት አበዛች ቤተሰቦቿ
ደስ እያላቸዉ መሽቷ ለእንቅልፍ ወደየአልጋቸዉ ተለያዩ
እስዋ ግን ስለነገዉ እያብሰለሰለች የባንክ ደብተሯን ኪሶ ዉስጥ
ከትታዉ በለበሰችዉ ሱሪ አልጋዋ ላይ ወጣች።

ነፋሻማ አየር ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ ሀገር መዉጫ መስመር
በአካባቢዉ የበቀሉት ዛፎች በንፋስ ይወዛወዛሉ ዛፎቹ ላይ ያሉት
የወፍ ዝርያወች ቢንጫጩም ዜማ አላቸዉ
እማማ ስንቅነሽ ቤዛዊትን በራቸዉ ላይ ቆማ ሲያገኟት
የሞተች ልጃቸዉ መቃብር ፈንቅላ እንደወጣች ተደስተዉ እያዩዋት
"ልጄ ልጄ የምትመጪ አልመሰለኝም
የኔ የዋህ የኔ ምስኪን"
እያሉ አቀፏት

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏