አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#የድንቄ_ኑዛዜ (መጨረሻው) “እኔኮ የራሴ ሚዛን እያለ የእጅሽ ሚዛንነት አይገባኝም?”ይላታል፤ አታዳምጠውም፡፡ ቤቷ ገብታ እንደፊቷ ወዝ የጠገበች ማሰሮዋ ውስጥ ትጨምርና በላዩ ላይ ጨው በተን አድርጋ እሳት ትማግድበታለች። ጠዋት ስራ ስትሄድ የጣደችው ጨጓራ በኩበትና በእንጨት ስትመጣ ገራም ሆኖ ይጠብቃታል፡፡ አሁን ጨጓራ የምትጥደው ለኔ ብቻ እስከሚመስለኝ ድረስ የምመገበው እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ቁራጭ ጨጓራ…»
#እስካለን

#እስካለን
ክፋት ተንኮልን ትተን - ቀና አስተሳሰብ ቢኖረን፣
#እስካለን
የራሳችንን ላብ እንጂ - የሌሎችን ባያስመኘን፣
#እስካለን
ጭንቅላታችን ሩቅ ቢያስብ - የወደፊቱን ቢጠቁመን፣
#እስካለን
ከሆድ ፍቅር አስወጥቶ - የሐገር ፍቅር ቢያድለን፣
#እስካለን .....
የሰው እጅ ማየቱ ቀርቶ - ይሄኔ የት በነበርን።

🔘በሙሉቀን🔘
👍1
#እባብ_ሆይ

በምላስሽ የያዝሽው መርዝ :-
አንድም መድሐኒት ሆኖ - የታመመን ይፈውሳል
አንድም አጥፊ መርዝ ሆኖ - ጤነኛ ፍጡር ይገድላል።

እንግዲህ ምርጫው ያንቺ ነው :-
ወይ መድሐኒት ሁኝና - ተዋደን እንፍጠር ህብር
ወይንም መርዝሽን መርጠሽ -
በተገናኘን ቁጥር
ስንጨፋጨፍ እንኑር።
#እንዴት_ይሄን_አታውቂም!?

የሰው ልጅ ታሪክ ሲመረመር
እኩይና ጥሩ ሰው ነበር፡፡
እኩዮች አፈር ለብሰዋል
ጥሩዎች ሞት ድል ነስተዋል::
እንዴት ይሄን አታውቂም!?

በቅርቡ እንኳን በቅርቡ - የታየ የተነገረ
በጎረቤታችን ምድር የሰው ደም ጎርፎ ነበረ፡፡
ወንድም በወንድሙ ላይ - ስለምን ሞት አነገሰ?
ለምን የንፁሃን ደም - በየጎዳናው ፈሰሰ?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?

የባቢሎን ስልጣኔ - ባለመግባባት ፈራርሷል
ኢያሪኮን የመሰለ ግንብ - በጩኸት ተደረማምሷል
ብቻውን የቆመ አንበሳ - በጅቦች መንጋ ተበልቷል
የተባበሩ ጉንዳኖች - የመሬትን ሆድ ቀደዋል፡፡
እንዴት ይሄን አታውቂም!?

ቂም በቀል ያረገዘች ልብ - ሰላምን ልታቅፍ አትችልም
ሰላምን ያላገኜች ነብስ - ፍቅርን አታስተምርም:
ፍቅር የራቃት ህይወት - የምትሰራው ቤት ጥላቻ
በጥላቻ የተሞላች ቤት - አማራጫ መፍረስ ብቻ::
እንዴት ይሄን አታውቂም!?

እንዴት ይሄን አታውቂም!?
ካወቅሽስ ምነው ችላ አልሽው?
ማፍረሱን ነው የናፈቅሽው?
መፍረሱን ነው የፈለግሽው?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
እንዴት ይሄን አታውቂም!?
እ.ን.ዴ.ት ይ.ዴ.ን ኢታ.ው.ቂ.ም!?
እንዴት!!???

🔘በሙሉቀን🔘
#ሰው_አፈር

አዕዋፍ በሰማይ ላይ ሲበሩ
በማራኪ ዜማቸው ሲዘምሩ፤
ውብ ተፈጥሯቸው ይደንቀኛል
እኔም ወፍ በሆንኩ ያሰኘኛል፡፡

እንስሳትም በየፊናቸው
ተመሳስለው ከአካባቢያቸው ፤
በጎጡ በስርጓጉጡ
ሲሽሎከሎኩ ሲሮጡ፤
ውብ ተፈጥሯቸው ይስበኛል
ፈጣሪ ስራው ይደንቀኛል፡፡

አንዱ ከዛፍዛፍ ሲዘል - ሌላው በመሬት ሲንፏቀቅ
አንዱ በሰማይ ሲበር - ሌላው ውሐ ውስጥ ሲሞላቀቅ፤
አንዱ ጮማውን ሲቆርጥ
ሌላው ደግሞ ሳሩን ሲግጥ፤
ልዩነታቸውን መመልከት - ሲሽቀዳደሙ ማየት
አቻ የሌለው ቲያትር - ተፈጥሯዊ ድንቅ ተውኔት።

ታዲያ
ከዚህ ሁሉ ውብ ተፈጥሮ - ከዚህ ሁሉ ትዕይንት
ለተመልካች የሚደንቀው - የሚገርመው አስቂኝ ትርዒት
አፈር -አፈርን ሲንቅ
አፈር - ከአፈር ሲተናነቅ፣
አፈር - በአፈር ላይ ሲያሴር
አፈር - ለአፈር ሲቆፍር..
..እንደ አፈር ቁጭ ብሎ ማየት።

🔘?🔘
#አይ እብዱ

“ሐገሬ አይዞሽ ባይ አጥታ
በራስ ወዳዶች ተሞልታ፤
እውነት ለማውራት ብቸገር
ከህግ ውጭ ሆኜ ልናገር፡፡”
አለ እብዱ::

“ወጣት በድንጋይ ስወግር - ወላጅ ስሳደብ ዝም አሉኝ
“መንግስት' ብየ ስጀምር - ሁሉም አፌን አፈነኝ፡፡”
አለ እብዱ::

“መንግስት ማለት ህዝብ ነው - አህዛብ የመሰረቱት
ስለዚህ ህዝብን ልሳደብ -
ህዝብ ሆይ ለሆድህ አትሙ........ት!!”
አለ እብዱ::

አገርህ ብዙ ልጅ ወልዳ - ጥሩ ልጅ ተርባ እያየህ
ለሆድህ እናትህን ምትሸጥ - ዳግማዊ ይሁዳ አንተ ነህ!”
አለ እብዱ፡፡

አይ እብዱ፡፡

🔘በሙሉቀን🔘
#ተይ_ማነሽ_ተይ_ማነሽ!

ተይ ማነሽ ተይ ማነሽ
ተይ ማነሽ ተይ ማነሽ
አስተውለሽ ርገጭ - ተራመጅ እያየሽ
በትዕግስት አልጋ ላይ -
የተኛ ልብ አለ ትቀሰቅሻለሽ፡፡

የራሱን ለማድመቅ - የጎረቤት መብራት እያደበዘዘ
የራሱን ለማሞቅ - የሌላውን ጎጆ እያቀዘቀዘ
ማን ወደ ፊት ሄደ? - ማን ሩቅ ተጓዘ!?
ማን ሃጃው ሞላለት? - ማን ግቡን አሳካ?
ማን ሰላም አገኜ ሰው እየነካካ!?

ተይ ማነሽ ተይ ማነሽ
ተይ ማነሽ ተይ ማነሽ
አስተውለሽ ርገጭ - ተራመጅ እያየሽ
በመቻል መስክ ላይ ~
የረጋ ቁጣ አለ ታደፈርሻለሽ፡፡

የሰው ልጅ ውድቀቱ የሰው ልጅ በሽታ
“እኛ ማለት ትተው እኔ ያሉ ለታ::
በሰፊ ምድር ላይ በጠባብ መሄጃ
“እኔ እኔ ማለትሽ ማዋጣቱን እንጃ፡፡

🔘በመሉቀን🔘
👍1
#ፉግር (እድለ-ቢስ)

ጅብ አያ ልክስክስ ፤
ካሰበው እስኪደርስ
የልቡን እስኪያደርስ፣
አንከስ
አንከስ
አንከስ....
አንክሶም አልቀረ፣
መጣ ተመልሶ
የልቡን አድርሶ፡፡

ማሙሽ እንኳ መጥቆ
በማልቀስ ፍላጎት - እንደሚሟላ አውቆ ፤
ልቡ የሻታትን - እስኪያገኛት ድረስ
ማልቀስ
ማልቀስ
ማልቀስ....
አልቅሶም አልቀረ፣
ተሳካ ምኞቱ
በየዋህ እናቱ፡፡

ልቤ ግን ፋግሩ፣
ወይ ላይዝ አንክሶ
ላያገኝ አልቅሶ
ከሄደበት ቦታ-
እያጨበጨበ መጣ ተመልሶ፡
#ከኔ_በፊት_ሙቺ

ፍቅሬ የኔ እመቤት
የኔና አንቺ መውደድ - የ'ኔና አንቺ ፍቅር
ሩቅ እንደ ሰማይ - ግዙፍ እንደ ምድር
ጥልቅ እንደ ውቂያኖስ - ጣፋጭ እንደ ቴምር::

አንቺ እኔን ስትወጂኝ፣
እኔ አንቺን ስወድሽ ፣
ዘመን ተቀይሯል፤
ሰፊው አገር ጠቧል፤
አቧራው ጨቅይቶ - የረጠበው ደርቋል፤
ምድር በጣም ግላ - ሰማይ ጥላው ሳስቷል፧
ንዋይ ተወጥሮ - የሰው ክብር ላልቷል፤
ፍቅሬና ፍቅርሽ ግን - እያደረ ጠብቋል፤
እያደር ታድሷል፤
ይኼው እዚህ ደርሷል፡፡

ታውቂያለሽ ይህች ዓለም
አንድ መንገድ ብቻ ለሷ አልተፈጠረም፡፡
ለደስታ ሐዘን አለ
ለእሳትም ውሐ አለ
ብርሐን ነው ሲሉ - ወዲያው ይጨልማል
ሰውም አለ ሲሉት - በሞት ይሽነፋል፡፡

እና የኔ ፍቅር
እውነትን መናገር - አንዳንዴ ቢመርም
የእኔና አንቺ ፍቅር - ከምድር ቢገዝፍም
ከቴምር ቢጣፍጥም
ህይወት አለንና ከሞት አናመልጥም፡፡

መሞትን ሳስበው
ካንቺ ተነጥሎ - እንዴት ነው ሚኖረው?'
ስል እጠይቃለሁ፡፡

“አንተ የሌለህበት - ለኔ ህይወት ማለት
እንደመታሰር ነው - በእጅ አሙቅ ሰንሰለት
በናፍቆት መንገብገብ - በሀዘን መሰቃየት::”

ያልሽኝን ሳስታውሰው

“ይህ ፈጣሪ ሚሉት
በፈጠራት ምድር - ፍቅርን ከፈቀደ
ጥላቻን ከጠላ - ሰላም ከወደደ
ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ - የትም ይሁን የትም
የተፋቀረ ሰው - መሞት የ ለ በ ት ም!!”
እላለሁ::

ቢሆንም

ቢ ሆ ን ም
መሪር ሐቅ አይቀርም፡፡

እና የኔ እመቤት
ሞት የሚሉት ዕጣ - ቆርጦ የመጣ ዕለት
ቢቻል ሁለታችን - አንድ ላይ እንሙት፡፡
ካልሆነ ግን ውዴ
እንደ ሞት ፈጣሪ - እኔ እንደሱ አይደለሁ
ስላንቺ አስባለሁ - ለፍቅሬ እሳሳለሁ
ቀድሜሽ ከምሞት - ብትሞቺ እመርጣለሁ፡፡
ካንቺ በፊት ሞቼ - ከምትኖሪ እያዘንሽ
ስቃይሽ የኔ ይሁን -
አዝኜ ማቅ ልልበስ - ከኔ በፊት ሞተሸ፡፡

🔘በሙሉቀን🔘
#ነገር_በምሳሌ

#እንበሳ፡-
በራሱ እምነት ስላለው - ስለማይኖር ተደብቆ
ምንን ለምን እንደሚያድን - ያውቀዋልና ጠንቅቆ፣
መዳፎቹን የማይሞሉ - የአይጥ መንጋ ተሰባስበው
ቢርመሰመሱ ቢጮሁ አንበሳውን ዙሪያ ከበው፣
እንዳያመልጠው ዋናው አደን - የአይጥን መንጋ ሲያሯሩጥ
አላርፍም ቢሉም አይጦቹ - ቢጮሁ ቢሉ ሲጥ ሲጥ
ፀጥ!!!

#ውሻ፡-
እፊቱ ላይ ድመት ቆማ - እንደ ነብር ብትጮህበት
አካሏ አብጦ - ጸጉሯ ቆሞ - ተገትራ ብታፈጥበት፣
ያውቀዋልና ውሻው - ድመቷን እንደሚረታ
ጫፉን እስካልነካችው - አፍንጫው ስር ተጠግታ፣
ብትነፋፋ፣ ብትኮፈስ፣ ብትዘል፣ ብትፈርጥ፣ ብትወራጭ
ጭጭ!!!

አንዳንድ #ሰውም፡-
አንዱ በዚህ ሲቦጭቀው
አንዱ በዚያ ሲያመናጭቀው
በጆሮቹ እየሰማ - እየሳቀ ዝም የሚለው፣
አይደለም ቃላት ጠፍቶበት አይደለም ስለበሸቀው
ስራ የፈታ ቢያወራም - እሱ ራሱን ስለሚያውቀው፡፡
እሉ ራሱን ስለሚያውቀው - ሰው ስለሱ ብዙ ቢልም
ዝም!!!

🔘በሙሉቀን🔘
#ያምር_ነበር?

የውስጣችንን ብቃት
የውስጣችንን ክፋት፣

ማስመሰል የማይቀይረው
መቀላመድ የማያከስመው፣

ማንም ሰው እንደዲያነበው
ክፉ ደጉን እንዲለየው፣

ግንባራችን ላይ በአጭር ነገር
ሚፃፍ ቢሆን ያምር ነበር?

🔘በሙሉቀን🔘
#ተቃርኖ

“አንዳንዱ ያወራል
አንዳንዱ ይሰራል፤
የሰራው ሲያልፍለት
የሚያወራው ያፍራል!”
ይላል የእኛ አባባል፡፡

እውነታው ሲታይ ግን፡-
'ሚያወራው ይወራል
“ሚሰራው ይሰራል፤
በፖለቲካ ዓለም
የተገላቢጦሽ - ህይወት ይቀጥላል፡፡
#ቆንጆ_ነሽ!!!

ውብዬ
ውቢቷ!
መልከ መልካሚቷ!
ልቤ በጣም መታ - አንቺን አንቺን አለኝ
እኔ አላማረኝም - ወደድኩሽ መሰለኝ::
ወድጀሽ ወድጀሽ
ውበትሽን ለማድነቅ - ብዕር አንስቻለሁ
ምን ብየ ልጀምር?
ሁለመናሽ ያምራል - ቃላት አጥቻለሁ፡፡

ግን የማውቀው ነገር
አንቺን የሚያወድስ - አንቺን የሚዘክር
ሺህ ጊዜ ቃል ባጣ - ሺህ ጊዜ ብቸገር፣
“በውበትሽ ፈዘው - ወፎች አዜሙልሽ
ስምሽን እየጠሩ - ቅኔ ተቀኙልሽ፡፡”
ብየስ አልክብሽም
ወፎች ወፍን እንጂ - አንቺን አያውቁሽም፡፡

ውሸት ምን ያደርጋል:-
ሺህ ጊዜ ብወድሽ
ሺህ ጊዜ ባደንቅሽ
“ውበትሽን እንዳዩ - እየተገረሙ
እንስሳት ስገዱ - እፅዋት ዘመሙ
ንቦች ተከተሉሽ - ጠረንሽን ሊቀስሙ:: ”
እያልኩ አልዋሽሽም
አላወድስሽም::
ታውቂያለሽ
አውቃለሁ
ውበትሽ ልዩ ነው::
ግን ምንም ብደነቅ
አንቺን ለማዳነቅ
ውበትሽን እንዳየ - ሰማይ ዝቅ አለልሽ
ጨረቃ ደመቀች - ፀሐይ አጀበችሽ
ክዋክብት ቦረቁ - እየተከተሉሽ፡፡”
እያልኩ ያለ ህጉ - ያለ ተፈጥሯቸው- አንቺን አልክብሽም
እንዲያውም እንዲያውም
ክዋክብት ጨረቃ
ፀሐይና ሰማይ
ከነመፈጠርሽም አያስታውሱሽም፡፡

ግን አንድ እውነት አለ:-
አንቺ ባለፍሽበት - በሄድሽበት ሁሉ
ሰዎች ስራ ፈትተው - ወደ አንቺ ያያሉ፡፡

ሐቅ ነው
እውነት ነው
በመንገድ የሚያዩሽ - የአዳም ዘሮች ሁሉ
አንቺን ያደንቃሉ
አንቺን ይመኛሉ፡፡

ነገር ግን ውቢቷ!
መልከ መልካሚቷ!
የሰውን ስብዕና - የሰውን ቁንጂና
እንስሳት እፅዋት - አያውቁትምና፣
ጨረቃ ብትወጣ - ፀሐይ ብታበራ
ክዋክብት ሲያደምቁት - ውበትሽን በጋራ፣
በሰማይ በምድር -
ያንቺን ቆንጆ መሆን - ግዑዝ አያውቀውም
ሰውን ሰው ብቻ እንጂ - ሌላ አያደንቀውም፡፡
እናም ተቀበይኝ
ውበትሽ ማርኮኛል - ውበትሽን ላድንቀው
መልክሽ እንደሚስብ -
ዛላሽ እንደሚያምር፣
የውበትሽ ነገር -
እንደሚያነጋግር፣
እኔ ብቻ ሳልሆን - ሁሉም ነው የሚያውቀው::
ቆንጆ ነሽl!

🔘በሙሉቀን🔘
#የአንድ_አውሮጳዊ_ምኞት

ትኑር እንጂ አፍሪካ!
ይኑር እንጂ ደሃ!
ዛፎች ተጨፍጭፈው - አፈሩ ቢፋቅም
ወንዞች ሁሉ ደርቀው - መሬት ብትነጥፍም፣

ትኑር እንጂ አፍሪካ!
ይኑር እንጂ ደሃ!
ምድረ በዳ ቢሆን - ጫካ የነበረው
የውቂያኖስን ግት - ውሐ ቢናፍቀው፣

ወይናደጋው አየር - በሐሩር ቢተካ
ለምለሙ መሬቴ - ቢደርቅ በፋብሪካ፣
ይኑር እንጂ ደሃ!
ትኑር እንጂ አፍሪካ!
ለኔ ሚስማማኝን - አየር እገዛለሁ፤
በድልቡ ገንዘቤ - ነብስ እለውጣለሁ፣
አፍሪካ አትደጊ - ኑሪልኝ አፍሪካ
ተስማሚ መሬትሽን - አይንካው ፋብሪካ፡፡
እንዴት ናችሁ #የአትሮኖስ ቻናል ተከታታዮች ሁሉ ሰላም ነው እኔ የሚወጣው ሰው ብዝዝዝት አለብኝና ምንድን ነው ነገሩ ይሄ ሁሉ ሰው ተገዶ ነው ወደ ቻናሉ የገባው ወይስ ምን አጠፋው ብዬ #ቁዝዝዝም ብያለሁ እስቲ ካላችሁት መሃል ምክንያቱን የሚያውቅ ቢያሳውቀኝ ወረታውን እከፍላለው😃

ሌላው ከዚ በፊት በቻናላችን ላይ #ሁቱትሲ የተሰኘ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሰለ ሩዋንዳ የዘር ፍጅት የሚያወሳውን መፅሐፍ በተከታታይ ማቅረባችን ይታወሳል አብዛኛችሁም አንብባችሁ አስተያየት ሰታችሁኛል አሁን አገራችን ያለችበትን ሁኔታ እያወሱ ስጋታቸውንም የገለፁ አሉ።አሁን ደሞ በ #ኢስማይል ቤህ የተፃፈውን አስከፊውን የሴራሊዮን የእርስ በእርስ ጦርነት የሚያሳይ #የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ የሚለውን መፅሀፍ በተከታታይ ላቀርብላችሁ ፈልጌ ነበር ግን የቻናሉ ቤተሰቦች በየቀኑ ሲቀንስ ሳይ ሃሳብ አስቀየረኝ ምክንያቱም ማዘጋጀቱ በጣም አድካሚ ነው ተከታታዩ ከሌለ ደሞ ዋጋ የለውም አሁን የናንተን አስተያየት እፈልጋለው ምን ያህላችሁስ የመከታተል ፍላጎት አላችሁ ከታች VOTE እንድታደርጉ አስቀምጠዋለሁ በተጨማሪም በአስተያየት መስጫው አስተያየታችሁን እጠብቃለሁ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ የሚለው መፅሀፍ

#ይቅረብ 👍

#አይቅረብ 👎

ለአስተያየት👉 @atronosebot
👍2
#የአንዲት_ፉንጋ_ታሪክ

አንዲት መልከ ጥፉ፡-
ተደግፋ ቆማ ፣
ውበቷን ቀይሮ ፣
ውብ አርጎ የሚያሳይ ፣
አታላይ መስታወት ፣
ተሰባሪ ጠርሙስ፤

በስው ለመወደድ፣
ተስፋዋን አድርጋ፣
ድንገት በሚጠፋ ፣
ድንገት በሚከዳ፣
ህይወት በሌለው ቁስ ፤

(እንደተመኘችው)
ብዙ አድናቂ አገኜች - ወዳጅ ጎረፈላት
ስታነባ አነቡ - ስትስቅ ሳቁላት::

(ከአመታት በኋላ)
በመደገፍ ብዛት፣
መስታዎቷ ነቅቶ፣
ስንጥቅጥቅ እያለ - ወድቆ ስለጋየ፣
የዛች ቆንጆ መሳይ፣
የእውነት ገፅታዋ፣
በመስታወት ሳይሆን - በአደባባይ ታየ፡፡

(ታዲያ ይሄን ጊዜ)
ውበቷ የውሸት፣
ሐዘኗ የውሸት፣
ፈገግታዋ ውሽት፣ ...
በውሸት መኖሯን - ሰዎች ስላወቁ፣
ውሸታም!” እያሉ፣
ንቀዋት አለፉ፣
በአስቀያሚነቷ - እየተሳለቁ፡፡

ውሽታም !!!

🔘በሙሉቀን🔘
#የሰው_ነገር (1)

በዚህች
ውሸት በነገሰችበት
እውነት አንገቷን በደፋችበት ፤
ያወራ በሚከብርባት
የሰራ በሚገፋባት
..........ደሴት ውስጥ

በዚህች
አህዛብ ባልተማረባት
የተማረም በማያውቅባት፤
ልብሷን በተገፈፈች
እርቃኗን ገጣ በቆመች
...........ደሴት ውስጥ

በዚህች
መጠላለፍ በበዛባት
ጭፍን ፈራጅ በሞላባት፤
ሆድ ዕቃ በገዘፈባት
ህሊና በኮስሰባት
..........ደሴት ውስጥ

በድንን ሳይሆን ህይወትን
ቅርጥፍ አድርጎ የሚበላ
........
ሰው ራሱ ነው የሰው ምስጥ፡፡

🔘በሙሉቀን🔘
👍1
#የሰው_ነገር (2)

በዚህች
በሰው በተገነባች
በሰው በተከበበች ፤
ስለሰው ተብላ ተፈጥራ
ስለ ሰው ስትል በኖረች
..........ደሴት ውስጥ

በዚህች
ሰዎች በመጠቁባት
ተመራምረው ባወቁባት፤
ግዙፍና ሩቅ እያለች
ትንሽ መንደር በመሰለች
.............ደሴት ውስጥ

በዚህች
በህብረ ቀለም ተውባ
በተፈጥሮዋ አብባ፤
ሰርክ አዲስ በሚታይባት
ተዓምር በሚሰማባት
...........ደሴት ውስጥ

ለሰው ልጅ ራሱ ሰው ነው
ችግርን አብሮ ተካፍሎ
......ለህይወት ተስፋን የሚሰጥ፡፡

🔘በሙሉቀን🔘
#ያላንቺ

እኔ ማለት ያላንቺ፡-
ጥፍር እንደሌለው ጣት
ወኔ እንደሌለው ወጣት
ጭብጥ እንደሌለው ቲያትር
እንደማይቀደስበት ደብር
ነኝ!

እኔ ማለት ያላንቺ፡-
እንዳላለቀ ግጥም
እንደማይጨበጥ ህልም
ኗሪ እንደሌለበት ቤት
ህይወት እንደማይኖርበት ደሴት
ነኝ!

እኔ ማለት ያላንች፡-
ጣፋጭ ነገር የሚመረኝ
ለስላሳው የሚሻክረኝ
ብሩህ ቀን የሚደብተኝ......
በቃ
ምንም ነገር ደስ ማይለኝ
እኔ ያላንቺ ምንም ነኝ!!

🔘ሙሉቀን🔘
#ትወደኛለህ_ወይ?”

እኔምልሽ ውዴ፡-
ላንቺ የምሆነውን - ልብሽ እያወቀው
ስወጣ ስገባ -
“ትወደኛለህ ወይ?”- ምትይኝ ለምን ነው???

ትወደኛለህ ወይ?”
ምን ልመልስልሽ?
ምን ብየ ልንገርሽ?
“እኔ አንቺን ምወድሽ
እንደ ገነት አለም - እንደ ስውር ቦታ
ማንም አይደርስበት - የፍቅሬን ከፍታ::
እኔ አንቺን ስወድሽ:-
ልክ እንደ ልጅነት፣
እንደ እናት ጡት ወተት፤
እንደ ከረሜላ ፣
እንደ ማር ወለላ፤
ብላ ብላ ብላ
ብልሽ ታምኛለሽ?
አምነሽ ትኮሪያለሽ?

ትወደኛለህ ወይ?”
ቀላል እወድሻለሁ!
ከመውደድም አልፈሽ - ሱስ ሆነሽብኛል
ለሰከንድ ከራቅሽኝ - ፍቅርሽ ያዛጋኛል፡፡
ብቻ ምን ልበልሽ
ከምነግርሽ በላይ - በጣም እወድሻለሁ
አያድርገውና
አ.ያ.ድ.ርገውና
ድንገት አንቺን ባጣ - ራሴን አጠፋለሁ::
ብልሽ ታምኚኛለሽ?
አምነሽ ትኮሪያለሽ ???

ላንቺ የምሆነውን ልብሽ እያወቀው
ስወጣ ስገባ
“ትወደኛለህ ወይ?” ምትይኝ ለምን ነው??

“ትወደኛለህ ወይ?”

ምን ልመልስልሽ?
ምን ብየ ልንገርሽ?

እውነት ለመናገር
ተመቸሽኝ እንጂ፣ገና አልወደድኩሽም
በብዙ ነገርሽ፣ አልረካሁብሽም::
እንዲያውም
እንዲያውም
በዚህ አካሄድሽ፣ በዚህ አካሄዴ
አይቀርም አንድ ቀን፣ ሌላ ሴት መውደዴ!'
ብልሽ ታምኛለሽ?
አምነሽ ታኮርፊያለሽ?

“ትወደኛለህ ወይ?”
“በይ እውነቱን ስሚ:-
በዕርግጥ ለጋሱ አምላክ - ውበት አድሎሻል
ታዲያ ምን ዋጋ አለው
ለመወደድ ሚሆን- ፀባይ ይጎድልሻል::
ጸባይሽ ጸባየ- ካልተገጣጠሙ
ውህድ ካልፈጠሩ- በሃሳብ ካልተስማሙ
አይቼሽ
አይቼሽ
ጥርግ ነው ምለው - ባለሽበት ትቼሽ!”

ብልሽ ታምኝኛለሽ?
አምነሽ ትርቂያለሽ?
ከምታይው በላይ ጆሮሽን ታምኛለሽ ??
እ???

ምን ልልሽ መሰለሽ :-
ለኔ አይነቱ ምስኪን
ራሱን እያደማ
እንቅፋትሽን ሁሉ - ቀድሞሽ ለሚለቅም
ትወደኛለህ ወይ?”
ተብሎ አይጠየቅም።
አይጠየቅም።

🔘ሙሉቀን🔘
1