አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አይ_ሽብሬ
:
:
:
አግብቼ ከእናት ከአባቆይታችን በወጣሁ ከአራት ዓመታት በኋላ ይሄ ሆነ። ሁሌ እሁድ እሁድ ከሰአት እንደማደርገው የሁለት አመት ተኩል ልጄን ማክዳን ይዤ ፣ ለእኔ እናትና አባቴ ፣ ለእሷ ደግሞ አያቷቿ ቤት ገባን።

ቆይታችን እንደ ሁሌ ነበር። አባዬ ማክዳን ጉልበቱ ላይ አሳፍሮ ይወዘውዛታል። ትስቃለች። እማዬ ለአምስት ሰው እንዲበቃ አድርጋ የሰራችውን ምግብ፣ ብቻዬን ጥርግ አድርጌ ስላልበላሁ ትነጫነጫለች።

እኔ ደግሞ አንዴ ቲቪ ላይ የምታወራውን ራኬብን፣ አንዴ ደግሞ በሣቅ የምትንፍቀፈቀውን ልጄን በስስት በፍቅር ዐያለሁ።

ዐስራ አንድ ሰአት ገደማ ሲሆን እንደተለመደው ቡና ቀራረበና ቤቱ መጫጫስ ጀመረ።

በእናቴ ''እንዲህ አድርጊ...እሱን...እጠቢ...ያኛውን አምጪ...ይሄንን ውሰጂ'' ታጅባ ቡናውን የምታፈላው ሰራተኛችን፣ ቴሌቪዢኑን እና ጀበናና ሲኒዎቿን አፈራርቃ እያየች በዝምታ ተቀምጣለች። ማክዳ እንቅልፍ ጥሏት የአባዬን ጋቢ ለብሳ ሶፋው ላይ ለጥ ብላለች።

እማዬና አባዬ የሳምንቱን ''አዳዲስ ወሬ'' በቡና እያወራሩዱ ያቀርቡልኝ ጀመር።

''ይሄ ሰፈር አሁንስ መላ ቅጡ ጠፋ፣ በቃ...! እንደሌላው ሰው ጨክነን ሸጠን መውጣት አለብን...'' አለ አባዬ። አባዬ በቀድሞው ሰላማዊ ሰፈራችን ''መበላሸት'' መማረሩ አዲስ አደለም። ይሄ ወሬ አግብቼ ከመውጣቴ በፊት በየቡናው የሚነሳና የሚጣል ነው። በመሰላቸት መታኘክ የማይፈልገውን ፈንዲሻዬን እንደማስቲካ አኝካለው
ቡናዬን ፉት እላለሁ።

''አሁንማ ለየለት እንጂ! ጭራሽ በራችን ላይ መቆም ጀመሩ እኮ!''

አለች እማዬ።

ይሄም የተለመደ ነገር ነው። የእማዬና የአባዬ ወሬ ልክ በካሴት ተቀርፆ ተደጋግሞ እንደሚሰማ ሁሉ ከጥቃት አረፍተ ነገሮች መቀዳደም ውጪ ሁሌም መገመት የሚችል ፤ ሁሌም አንድ ነው። በመታከት በወጉ ያልፈኩ ፈንዲሻዎችን ከሰሀኑ ላይ አፍሼ በጥርሴ ለመስበር እታገላለሁ። በመቀዝቀዝ ላይ ያለውን ቡናዬን ፉት እላለሁ።

''ሽጠን መሄድ አለብን ዝናሽ...በቀኝ ማሳጅ ቤት፣ በግራ መጠጥ ቤት ጎረቤት አድርገን እስከመቼ እንኖራለን....መሸጥ አለብን....!'' አባዬ ቀጠለ። ቀዝቃዛ ቡናዬን ጭልጥ አድርጌ ጨረስኩና ስኒውን ለልጅቱ ወሰድኩላት። ደንገጥ ብላ ብድግ አለችና ተቀበለችኝ፣

''ሦስተኛ ትተጫለሽ?'' አለችኝ።

''አይ... በቃኝ....'' አልኩና ቦታዬ ተመልሼ ተቀመጥኩ።

''እስቲ ሄለንዬ፣ ደህና ደላላ ፈልጌ...'' አለ አባዬ ቁጭ ከማለቴ።

''አይ አባ...'' አልኩና ዝም አለኩ።

''ምንድን ነዉ አይ አባ?'' ቆጣ ብሎ መለሰለኝ።

''የእናንተ ነገር እንሸጣለን ስትሉ ስንት ጊዚአችሁ ...እኔም....ዳግምም ስንት ደላላ አመጣንላችሉ....ዝም ብላችሁ ነው...'' አልኩኝ ሶፋዬ ላይ እየተመቻቸው።

''አይ....! አሁንስ በቅቶናል ሄለንዬ.. ትላንት የሆነውን ባየሽ ታምኚኝ ነበር!'' አለች እማዬ፣አለች እማዬ ስኒዋን ለልጅቷ እየመለሰች።

''ትላንት ደግሞ ምን ተፈጠረ?'' አልኩኝ ብዙ ሳልጓጓ።

ጡረተኞቹ እናትና አባቴ ትንሹን ትልቅ አድርገው የማየት አባዜ አለባቸው። ''መቼ እለት በራችን ላይ ትልቅ የመኪና አደጋ ተፈጥሮ ካሉ ፣ ሁለት ቪትዞች ተነካክተው ነበር ማለት ነው። ''አጎትሽ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ላይ ነው '' ካሉ ሐኪም ቤት ውሎ ቤቱ ገብቷል ማለት ነው....

እማዬ ሰራተኛችንን አየት አደረገቻት። ሂጂ ማለቷ ነው። ሚስጥር ልናወራ ስለሆነ እቃሽን ሰብስበሽ ሂጂ ማለቷ ነው። ልጅቱ የሰው በማይመስል ፍጥነት እቃዎቿን በሙሉ ሰብስባ ወጣች።

አሁን ጓጓሁ።

''ምን ተፈጠረ ?'' አልኩ ደግሜ።

እማዬ የሚያጓጓ ወሬ ልትናገር ስትል እንደምትቀመጠው፤ ሰውነቷን ሁሉ ሶፏው ጫፍ ላይ ሰብስባ ተቀመጠችና ድምጿን ዝቅ አድርጋ፣ ማታ ማታ እዚህ ዋናው መግቢያችን.. አስፋልት ዳር የሚቆሙት ሴቶች የሉም?'' አለችኝ።

''እ...'' አልኩ ጉጉቴ እየናረ።

''ትላንት ማታ አምሽተን ስንመጣ ሺብሬን አያት!'' አባዬ ጭንቅላቱን ቀስ እያለ ግራና ቀኝ ወዘወዘ። ሲያዝን የሚያደርገው ነው።

''ሽብሬ...ሽብሬ የኛ?'' አልኩኝ ማመን እየተሳነኝ።

''እህስ!..ራሷ ናት። መኪናችንን ስታይ አወቀችን መሰለኝ ሸሽታ ብትሄድም በደንብ አይቻታለሁ!'' አለች እማዬ ከበፊቱ ጮክ ብላ። ''ከዚህ ከወጣች ወዲህ፣ ከእንግዲህ ሰው ቤት በቃኝ ብላ መሸታ ቤት እንደምትሰራ ሰምተን ነበር ግን እንዲህ ለይቶላታል ብዬ አላሰብኩም ነበር...አቤት አቤት!'' እማዬ ወደ ጣራ እያየች ተናገረች። ፈጣሪን ማየቷ ነው።

''ለነገሩ እንደዛ እንደልጃችን አድርገን ስናያት የሠራችንን ስራ ያየ ሰው መጨረሻዋ እንደዚህ ቢሆን አይደንቀውም...! ያሳዝናል ብቻ....''

አለ አባዬ።

ደነዘዝኩ።

ሺብሬ መጨረሻዋ እንዲህ ሆነ ? ስምንት አመት ወደ ኋላ ሄጄ የሆነውን ሁሉ አስታወስኩ።

ሞላሌ ከሚባል ሀገር መጥታ እኛ ቤት በሠራተኝነት ስትቀጠር ከዐስራ አምስት አመት አትበልጥም ነበር። እኔ ደግሞ ዐስራ ስምንት ሞልቶኝ ነበር። ፍልቅልቅ እና ደስተኛ፣ ገራገርና ታዛዥ ልጅ ነበረች።ከእኛ ቤት በፊት ሠራተኛ ሆና አታውቅም ሲሉ ትዝ ይለኛል። የተባለችውን ነገር በፍጥነትና በጥራት ትሠራ ስለነበር። እናቴ፣ ለእኔ በሚቀርብ መጠን ትወዳት ነበር ።

እኔ የተውኳቸው ልብስና ጫማዎች ይሰጧታል። ለዓመት በዓል ለእኔ አምስት ነገር ከተሰራ ለእሷ ደግሞ አንድ ነገር ይገዛላታል። የቤተሰብ ሽር ሽር ስንሄድ ሳይቀር ከእኔና ከወንድሜ ዳግም ጋር መኪና ውስጥ ቦታ ይኖራታል።

እንወዳት ነበር። እወዳት ነበር። ታናሼ ብትሆንም የምበላውን ሠርታ ስለምታቀርብልኝ፣ የምለብሰውን አጥባ ስለምትቶክስልኝ፤ የምተኛበትን አንጥፋ ስለምታሰናዳልኝ፣ የምወዳት እና የምትንከባከበኝ ታላቅ እህቴ ትመስለኝ ያህል እወዳት ነበር። ለዘላለም እኛ ቤት የምትኖር ይመስለን ነበር። እንደዚ ግን አልሆነም ለምን?

ሺብሬ እኛ ቤት በገባች በዓመት ከምናምኑ አባዬ ለእማዬ ለሃያኛ የጋብቻ በዓላቸው የገዛላት እና ድግሱ ላይ በመዐት ሰው ፊት የሰጣት የወርቅ ሀብል ጠፋ። በዚያ ግዜ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ብር የፈጀ ሃብል ነበር።

እማዬ አቅሏን ሳተች። አበደች። አባዬ ብስጭቱ ከልክ አለፈ።

እኔ እና ዳግም ቃላችንን ሰጠን። በፊትም በጨዋነት ያሳደጓቸውና እስከዛሬ አንዲትም እቃ ንክች አድርገው የማያውቁት ጎረምሳ ልጆቻቸው በዚህ እንደማይጠረጠሩ የሚያውቁት እማዬና አባዬ ዐይናቸውን ማን ላይ ጣሉ? ያቺ መከረኛ ሽብሬ ላይ።

''ካንቺ ውጪ ማን ወሰደው ይባላል? እያዳፋሁ ፖሊስ ጣብያ ወስጄ ላስገርፍሽ ሃብሉን ውለጂ!'' ብለው አዋከቧት።

እንባዋ እስከዛሬ ትዝ ይለኛል።ከአንድ ሰው ዐይኖች በዚያ ፍጥነት ያ ሁሉ እንባ ሲወርድ፣ እስከዛሬ አላየሁም። ከማልቀስ ብዛት ዐይኖቿ ሽንቁር ያወጡ ይመስል ነበር።

በሀገሯ ታቦቶች ሁሉ ማለች፣ ተገዘተች። ግን ማንም አላመናትም። ክሯን ይዛ፣ ''ከዋሸሁ ሦስቱ ስላሴዎች እዚሁ ሦስት ቦታ ይቆራርጡኝ'' ብላ ማለች።ግን ማንም የሰማት አልነበረም። ከዚህ በኋላ የሆነው ሁሉ ባሰብኩት ቁጥር እንደ አዲስ ያመኛል። ከስምንት ዓመት በኋላም እንደ ትኩስ ቁስል ይመዘምዘኛል። እረፍት ይነሳኛል። እማዬና አባዬ እያካለቧት፣በእንግድነት የመጣው ዘመዳችን በእርግጫ እየመታት፣ ወንድሜ ዳግም ሌባ ብሎ እየጮኸባት፣ ፖሊስ ጣብያ ብለው ይዘዋት ሄዱ።

ቤቱ ውስጥ ብቻዬን ስሆን መኝታ ቤት ገባሁና አርቄ ፍራሼ ስር የደበኩትን የእማዬን የወርቅ ሀብል አውጥቼ ያዝኩትና ያለ ገደብ አነባሁ። አንድ ሺ ሰባት መቶ ብር
👍6
#አይ እብዱ

“ሐገሬ አይዞሽ ባይ አጥታ
በራስ ወዳዶች ተሞልታ፤
እውነት ለማውራት ብቸገር
ከህግ ውጭ ሆኜ ልናገር፡፡”
አለ እብዱ::

“ወጣት በድንጋይ ስወግር - ወላጅ ስሳደብ ዝም አሉኝ
“መንግስት' ብየ ስጀምር - ሁሉም አፌን አፈነኝ፡፡”
አለ እብዱ::

“መንግስት ማለት ህዝብ ነው - አህዛብ የመሰረቱት
ስለዚህ ህዝብን ልሳደብ -
ህዝብ ሆይ ለሆድህ አትሙ........ት!!”
አለ እብዱ::

አገርህ ብዙ ልጅ ወልዳ - ጥሩ ልጅ ተርባ እያየህ
ለሆድህ እናትህን ምትሸጥ - ዳግማዊ ይሁዳ አንተ ነህ!”
አለ እብዱ፡፡

አይ እብዱ፡፡

🔘በሙሉቀን🔘