አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አንተ_የሌለህ_ጊዜ

ተማሪ እያለን ለብዙ ጊዜ የፍቅር ሕይወትን ተጋርተናል፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ ትልቅ ሰው ከሆንን፤ የተለያየ የሕይወት መሥመር ውስጥ ከሰመጥን፣ አጀንዳዎቻችን ከተቀየሩ፣ ፍላጎት እና ሕልማችን ሌላ ከሆነ በኋላ በድንገተኛ ግጥምጥሞሽ ሥራ አገናኘን፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ከብዙ ዓመታት በኋላ ስንገናኝ አድገን፣ በስለን ስለነበረ የወዳጅነት ሰላምታ ሰላም ተባባልን፡፡ ሁለታችንም አይናችን የጣት ቀለበት ሲያስስ ተገጣጠምን፤ ሁለታችንም አግብተናል። ያገናኘን ሥራ ላይ ተጠመድን፣ ደጋግሞ ሥራ አገናኘን፤ ደጋግመን 'email' ተለዋወጥን።

አንድ ቀን ማኪያቶ እየጠጣን ከላይ ከላይ እየተጨዋወትን በሕይወቷ ስላለፈችበት ፈታኝ ጊዜ ማወቅ ፈለግሁ። ለምን የመጣችበትን አስቸጋሪ ሕይወቷን ለማወቅ እንደፈለግኩ አላውቅም።

የህይወትሽ አስቸጋሪ ጊዜ መቼ ነበር አልኳት?

አየችኝ፤ በትንሹ ፈገግ አለች፤ ፈገግ ስትል ዲምፕል አላት፤ ጥርሶቿ እንደ ድሮው ያምራሉ። ከፊት ለፊት በግንባሯ የመጡትን ዘለላ ጸጉሮቿን በቄንጥ ወደኋላ መለሰቻቸው።

ዝም ብዬ ስመለከታት...

“አንተ የሌለህ ጊዜ። ማለቴ የተውከኝ ለታ" አለችኝ። ስትቀልድ መስሎኝ ሳቅሁ። “እማ ትሙት" አለችኝ። በእናቷ ምላ ዋሽታ አታውቅም፡፡ ግርምቴን መደበቅ አልቻልኩም፤ ሁለ ነገሬ ጆሮ ሆነ

አየኋት

“ያ ጊዜ ላልበሰለችው ሄርሞን ፈታኝ ጊዜዋ ነበር። እወድህ ነበር፤ እያንዳንዱ ነገሬ ከአንተ ጋ ተሳስሮ ነበር። ውጤት መጣልኝ፣ ክፍለሀገር ተመደብኩኝ፤ ምክንያቱን ባላወቅኩት ምክንያት ራቅከኝ፤ ሁሉ ነገር ላይ ስልጣን የሰጠኸኝ ልጅ ገሸሽ ስታደርገኝ የማደርገው ጠፋኝ። በጨቅላ ጭንቅላቴ ቀልብህን እንደ ድሮ ወደ እኔ ለመመለስ ባተልኩ፤ ግን አልሆነም።

ወደ ተመደብኩበት ዩኒቨርስቲ ወደፊት መራመድ እንደመብረር እየከበደኝ ሄድኩ። ቀልቤን፣ ሳቄን ትቼ ነበር የሄድኩት። አዲስ ቦታ መልመድ ለእኔ ቀላል እንዳልሆነ ታውቃለህ፤ ሁሉ ነገሬን ላንተ እንደማነበንብ ታውቃለህ። ስላ'ንተ ለሁሉ እንደማወራ ታውቃለህ፤ ጓደኞቻችን ሁሉ የጋራ ነበሩ። ዶርም ሜቶቼ ለሚያወሩት ቋንቋ ባዳ ነበርኩ፤ አብሮነታቸው ሲደራ ባይተዋርነት አራቆተኝ፤ የማይወዱኝ ይመስለኛል።

“የካምፓስ ምግቡ አልተስማማኝም፤ አዲስ ዩንቨርስቲ በመሆኑ ሁሉም ነገር ገና ነበር፡፡ ናፍቆት ገላዬን በላው። ምግቡ ስለማይስማማኝም ብዙ አልበላም። ሰለልኩ፤ የጨጓራ ሕመም ጨፈረብኝ"

መቼ ደውለሽልኝ ታውቂያለሽ? በእኔ የምታውቂው ሰው ሆኖ ማን አለ ያልዘጋሽው? አልኳት ኮስተር ብዬ!

“እንደማትፈልገኝ ሁሉ ነገርህ ይናገር ነበር፤ ስልክህ ረጅም ሰዓት ይያዛል፤ በፍጥነት ተቀያየርክ፤ ለስሜቴ መጠንቀቅ አቆምክ። እንደቀለልኩብህ ድርጊትህ ይናገር ነበር። አንተ ላይ ስልጣን አልባ እንደሆንኩ አሳየኸኝ። ነገሮችን ለማስተካከል በአፍላ ጭንቅላቴ ተፍጨረጨርኩ። ጓደኞቼ ሊሰሙኝ እንጂ መንገድ ለማሳየት ጥበብ እና ልምዱ አልነበራቸውም። ታላላቆቼ ጋ በዛ ዕድሜዬ በዚህ ጉዳይ የማውራት ስልጣኔ አልዳበረም፤ ነውር ነበር።

ሸሸሁ!

የባሰ የቀዘቀዘ ድምጽ እንዳልሰማ ሸሸሁ፤ አዲስ የተወዳጀሃት ልጅ እንዳለች ስድስተኛ ስሜቴ አንሾካሾከልኝ። ስደውል በእሷ ፊት ተራ ጓደኛዬ ነች ዓይነት ወሬ እንዳታወራኝ ሰጋሁ። አትደውይልኝ እንዳትለኝ ስለሰጋሁ ሸሸሁ።

ላ'ንተ ያለኝ ፍቅር የባሰ አጣጥለኸኝ እንዳይቋጭ ስለሳሳው ሸሸሁ!

የጋራ ጓደኞቼ በልቤ ያለውን ፍርሀት እንዳይነገሩኝ ሁሉንም ዘጋኋቸው « አነባቸው የነበሩ ፍቅር ነክ ልብ-ወለድ ጽሑፎች ውስታዬን ተስቅሰው ናፍቆቴን እንዳያባብሱት ማንበብ አቆምኩ፤ የፍቅር ፊልሞች ትዝታዬን ገላልጠው እንዳያሳምሙኝ ማየት ተውኩ፤ ያች ሄርሞን ከመሸሽ ውጪ የመጋፈጥ አቅም አልነበራትምና ሸሸች።

የጀመርኩት የ"psychology" ትምህርት ካለ ምርጫዬ ስለነበር ችግር ሲገጥመኝ የምሸሸግብህ፣ የምታጽናናኝ አንተ ስትለወጥብኝ፣ ስትገፋኝ የልቤን የማጫውተው ጓደኛ አለመኖሩ፣ የምግቡ አለመስማማት፣ የጨጓራ ሕመሜ ኑሮዬን አጠየፈው። ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን . ረጅም ሰዓት እቀመጣለሁ፣ ስብከት አዳምጣለሁ፣ ጉባኤ እከታተላለሁ::

ፆታዊ ፍቅር ስለሌለው፣ የሁሉ ነገር መሠረት ክርስቶስ እንደሆነ ስለሚነገር፣ በፈተናው የጸና የተባረከ ነው ስለሚባል፣ ብዙ ነገሮች በዲያቢሎስ ስለሚላከክ፣ የጭንቀታችን ችግር መፍቻ ጸሎት፣ ንሰሃ መሆኑን በአማረ፣ እና በሚጣፍጥ ቋንቋ ስለሚያስተምሩ ጣፈጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስን የሙጥኝ አልኩ። ችግሮቼ እየቀለሉኝ መጡ። አዳዲስ ሃይማኖተኛ ጓደኞች ተወዳጀሁ።

የመጀመሪያ ዓመት ጨርሼ ስመጣ ግሬይ ሱሪ፣ ቀይ ቲሸርት አድርገህ ቆመህ አየሁህ። ሳይህ ከእስራቴ፣ ከሱሴ መላቀቄ ነው የተገለጠልኝ። የሆነ ቀጫጫ ልጅ፣ ኖርማል ወንድ፣ ለአይን የማይሞላ ልጅ አየሁኝ። ለካ ችግራችንን የምናይበት መንገድ የገዘፈ ስለሆነ ነው ከችግራችን በታች የምንሆነው።

ዕውቀትና ልምድ ያለው ሰው መውጫ መሰላሉን ስለማርዮን ነው ለካ እንቅፋታችን የሚፈነጭብን። ርግጥ ከስቃይ የምናገኘው ጥበብ ያበስለናል። ከስኬት ከምናገኘው እውቀት ከውድቀት የምናገኘው ጥበብ እጅግ ትልቅ ነው።

ያኔ ሳይህና ሰላም ስልህ የተሰማኝ ስሜት አስገረመኝ፤ እረስቼህ ነበር። አንድ የማውቀውን ሰው ሰላም እንደማለት ነበር ያ ወቅት የሕይወቴ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር፤ ነገር ግን በዛ ፈታኝ ወቅት ያዳበርኩት ብስለት ለቀሪው ሕይወቴ ጫንቃ እያበቀልኩበት ነበር።

ጸጥ አልኩ፣ ትንሽ ጸጸት፣ ትንሽ ግርምት፣ ትንሽ | ግርታ ተደማምሮ ሁካታ ቢሞላብኝም ፀጥ አልኩ።ዝምታ ከመላምት ውጪ የሚያስተላልፈው አንድም ተጨባጭ መልእክት የለምና ፀጥ አልኩ።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍91