አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
578 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
በየደቂቃው ከጭንቅላቴ የሚፈልቀውን ዝባዝንኬ ሳላስቀር፣ በአጠገቤ ውል ያለውን ሳይቀር ነበር የምተነፍስለት። እንዳልቆም አድርጎ ያፍረከረከኝ፤ ያሳለፍነውን፣ ያገዘፍኩትን ነገር አንድ ሳይቀር ነው አሳንሷት የሄደው፡፡ ትረካ የሌለው መለያየት፣ ውጣ ውረድ የሌለው ፍቺ፣ የማይተነፈስ ሕመም ለማይታይ ጠባሳ ይዳርጋል፡፡ እንዴት በዚህ መጠን ተራ ይሆናል? እንዴት እየተፍለቀለቅሁ የምተርከውን ትዝታዬን እንደዚህ ያባክነዋል?

እንዴት ጥሩ ምክንያት አይፈበርክም?

እንዴት አካሄዱን ወዝ አያላብሰውም?

በዚህ መጠን ተራ አድርጎኝ እንዴት ይሄዳል? ያውቅ የለ ማን እንዳሳደገኝ፤ ለክብሬ ለግንኙነታችን ያለኝን ቦታ እያወቀ።

እችን ብቻ ነበር የምናክለው?

አብረን ስንሆን የእኔ ነው ብዬ አይደል እርቃኔን የተንጎማለልኩት?

የነበረን ነገር ቢያይል አይደለ ድክመት እና ስጋቴን መግለጼ?

ያሳለፍነውን ውብ ጊዜያት ካለጥንቃቄ በአካሄዱ ተረማምዶበት ነው ያናወዘኝ፣ እንጂ'ማ መለያየት ተፈጥሯዊም አይደል? ነፍስስ ኵስጋ ይለይ የለ? መሄዱ አይደለም፣ አካሄዱ ነው መላቅጡ የጠፋ ዱካክ ውስጥ የዘፈቀኝ።

አወዳደቃችን ውስጥ የጠያችን ግዝፈት እና ተራነት አሻራ በጉልህ አለ፡፡ ምን አለ አለሳልሶ ቢጥለኝ? ምን አለ ሲተወኝ ይሉኝታ ቢስ ባይሆን፡፡ አብረን በነበረን ጊዜ እንደምወደው እያንዳንዱ ዳናዬ ምስክር ነበር። ሰው ለሚወደው አይደለም ላሸነፈው ጠላቱ እንኳ ይራራ የለ?

ምን አለ ራርቶልኝ ቢሆን...

ምን አልባት እኮ የእኔ ብቻዬን የመሆን ፍርሀት ሲያርደኝ መለማመጤን አይቶ ነው ለእኔ ያለው ስሜቱ የተከለለበት፤ ምን አልባት ከእኔ የተሻለ ሰው አግኝቶ በእጁ እስኪያረጋት ወረት አውሮት ነው።

ምን አልባት እንዲህ መሙለጭለጭ ማንነቱ ይሆን ይሆናል። እሱ እንዳልሄድበት ከመጣው መንገድ በላይ እኔስ አልሄድኩም? ለእናቴስ የጀመርኩትን የደበቅኋት፣ የማትወደውን የሆንኩት ነገ ስነግራት አታፍርብኝም ብዬ አይደል? ከራስ ሰው ጋ መንዘላዘል ትዝታውም ሁኔታውም ይጣፍጣል ብዬ አይደል ከእናቴ የዘወትር ስጋት ራሴን ጥዬ ያገኘሁት?

ይሂድ! መሄዱ አይደለም ያጎሳቆለኝ!

ይሄ ማለቂያ የሌለው የምን አልባት ጉዞ ነው ከሰውነት ተራ ያወጣኝ። ምን አልባት ቃል ገድፌ የማይወደውን ብዬ፣ ወይ ምን አልባት ያልዋልኩበትን ነግረውት ይሆን? ወይ የሆንኩትን አገዛዝፈው አሻክረውት ይሆን? ይሄ እና ሌሎች የምን አልባት መላምቴ ነው ጭንቅላቴን ያጣበበው፤ እንዲህ እንደባተልኩ አልቀርም፤ እረሳዋለሁ። ያኔ እዚህ የዘራውን እዛ ሲያጭድ መሰስ እያለ ይመጣል፤ ያኔ የእኔን የምን አልባት የመላምት ችንካርን ይቀምሰዋል።"

ተሾመ ረጋ ብሎ ነበር የሚመለከተኝ። ሶልያና ያለችውን ሳነብ አንዱም ቃል አልለሰለሰኝም። ልቤን የጥፋተኝነት ስሜት ሸቀሸቀኝ። እያነበብኩ እንባዬ ሲንከባለል ተሾመ ተረጋግቶ ከመቀመጥ በቀር ምንም አላደረገም። ስቃይህ ከስቃይዋ አይበልጥም ብሎ ይሆናል።

ሶልያና ሕመሟን ከመቼ ጀምሮ ነው እንዲህ ለሰው ማጋራት የጀመረችው? አንዳንድ በደል የሌለንን ማንነት እና ባሕሪ ይወልዳል ማለት ነው።

አለሌ ብሆንም ስንቴ እየወደድኩ ተትቻለሁ፤ እየለመንኩ ተረግጫለሁ፤ ከእኔ የተሻለ ጋ ሄዳለች ብዬ ናፍቆቴን ፊት ነስቻለሁ። ጭር ያለ ስፍራ ተሸጉጬ አልቅሻለሁ። በሌላ አሳብቤ ተነጫንጫለሁ። ስንት ጓደኛ ሽምግልና ልኬያለሁ፤ የኔ ያድርጋት ብዬ ጸልያለሁ፤ አለመፈለጌን ለመርታት አነቃቂ ንግግር ሰምቻለሁ፤ ሴት እንዲህ ነች ብዬ ተቦትርፌያለሁ። ጥላኝ ማን ጋ እንደሄደች እያሰብኩ አርሬያለሁ።

ቃሏን እያጣቀስኩ ከስሻለሁ፤ ናፍቄ ረግሜያታለሁ። ይሄ እንዲህ ሆኖ ሳለ የሚወዱትን በገዛ ፍቃድ እንደመተው ያለ ሕመም ግን የትም የለም!

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢209
#አንዲት_ዕድሜ_ለስንት_ትሆናለች

በጨዋታችን መሀል "ባል ፈልግልኝ" አለችኝ ምን ዓይነት? አልኳት።

“ጥሩ ፀባይ ካለው ይበቃኛል።" የምሯን እንደሆነ ሁለ ነገሯ ይናገራል። ጉጉቷ አንጀቴን በላው።

ፍቅረኛ ኖሮሽ ያውቃል? አልኳት።

ጥያቄውን ለማለስለስ ስታገል በደረቁ ወጣብኝ።

“ዛሬ ነገ እያለ ሕልሙ ላይ ተመስጦ ድክመቴን እያጎላ፣ እያሳጣ ከዛሬ ነገ እንጋባለን እያለ ቀኔን ዕድሜዬን በልቶ ተልካሻ ምክንያቶችን ጠቃቅሶ ተለየኝ። አሁን ሌላ ከእኔ በአስር ዓመት የምታንስ ጉብል አግብቶ ወልዶ ይኖራል"

ምናለ ...

ካልወደድካት፣ ካላገባሃት ብትተዋት፤ ቀኗን ባታኝከው! ውበቷ ሳይደበዝዝ፣ የከጀለችውን አማርጣ በጊዜዋ ታግባ፡፡ ጊዜ ለሴት ልጅ ከወንድ ልጅ የበለጠ ትርጉም አለው።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍2110🥰2
    ዓይንሽ እሳት ሳቅሽ እሳት እጀሽ እሳት
ታዲያ ምን ይገርማል ባንቺ ቃል ብሳሳት?
    አይንሽ ውኃ ሳቅሽ ውኃ እጀሽ ውኃ
  ታዲያ ምን ይገርማል ብሆንሽ አምሀ?
    በጋና ክረምቱ ዝናብና ውርጩ
ሳቅሽ ነው እላለሁ የአቡሻኽር ምንጩ?
                     እሰይ...

             ከቤቴ እወጣለሁ
             ከደጄ እወጣለሁ
            ዶፍ ይውረድ በላዬ
     ሳቅሽ እንደዝናብ ካሳደገኝ ብዬ ፡፡

            ደስታ ሲያስገመግም
             ሰኔ ሲያስገመግም
   ዮም ፍሰሐ ኮነ በኤልያስ ግርግም፡፡

ወረደልህ  ቢሉኝ ደመና በክስተት
    ዘነበልህ ቢሉኝ ወለላና ወተት
ሲደመም ቢኖርም እግዜርን ላመነው
            ታዲያ ለኔ ምነው
ሳቅሽ ተነጥሎ ተዓምር የሆነው?

             ስንት ለመዘነ
             ስንት ለፈተነ

ሲደመም ቢኖርም እግዜርን ላመነው
           ታዲያ ለኔ ምነው
ሳቅሽ ተነጥሎ ተዓምር የሆነው?

            ስንት ለመዘነ
            ስንት ለፈተነ
  ስንት ለወጠነ ለኔ አይነት አለቃ
ከዚህ ሁሉ ሜዳ እንዴት እጅሽ በቃ?

ሞትም ባንቺ ፉጨት አልሰማም ካልጠራኝ ህይወት ባንቺ ፉጨት አልሰማም ካልጠራኝ
    እስኪ ጠይቂልኝ ካንቺ እንደሰራኝ !!!

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
13👍1
#አይሸጥም

እቤቴ ሊጠይቀኝ የመጣ ሁሉ፤ አጠገቤ ያለ ባለ ፎቅ ሁሉ፤ ባጋጣሚ የሚደልል እና በድለላ የሚኖርበት ሁሉ፤ ዘመድ አዝማድ ሁሉ፤ የመኖርያ ቤቴን ስፋት ከሰፈራችን መዘመን እና ከቦታ ዋጋው መናር ጋር እያስተያዩ “አትሸጪውም?” ይሉኛል፡፡

ብሸጠው የማገኘውን ሰምቼው የማላቀውን ገንዘብ መጠን ይነግሩኛል መልሴ ሳላወጣ ሳላወርድ አንድ ነው እሱም አ ል ሸ ጠ ው ም ብቻ እነሱ ግን ከመወትወት ሰንፈው አያቁም። አንዳንዱ “እሺ እማማ እርሶ ይሄን ያህል ይበሉን እና እንግዛዎት” ይሉኛል፤ ግን የእውነት... አክሱም ወይ ላሊበላ አልያ ደግሞ ፋሲለደስ በስንት ቢሸጥ ያዋጣል? ታሪክ ይሸጣል?

ይሄ ግቢ እኮ ባሌ ሽኮረመመ ጃጰማኘ ያጣጣምንበት፤ ፍቅር የዘራንበተ፤ፍቅር ያጨድንበት የተጨቃጨቅንበት የተኮራረፍንበት የተመካከርንበት ያቀድንበት ያዘንበት የሳቅንበት የወለድንበት ስፍራ ነው።

ይሄ ስፍራ እኮ የጸነስኩት ልጆቼ ያሳደኩበት፤ ልጆቼ ፀሐይ ያሞኩቅበት፤ ልጆቼን የገረፍኩበት፤ ልጆቼን ያስታረቅኩበት ልጆቼን የዳኘሁበት እዚህ ግቢ እዚ ቤት ነው!!

ቤትሽን ሽጭልኝ የሚሉኝ መስሏቸው ነው? አይደለም! ታሪክሽን ነው ልግዛሽ ያሉኝ! ይሄ ስፍራ ለኔ ጥዑም የትዝታዬ መዓዛ የሚያውደኝ ቦታ ነው፡፡ ከዋናው Vila ጎን ከዛ ከምትታየው ጥንጥዬ ክፍል ተነስተን ተካሰን ተበድረን ታግለን ነው ያስፋፋነው!!

አቅም የሆነኝ፣ የሕይወት ጣዕም ያልተሟጠጠብኝ ትላንቴ ላይ ተተክዬ ነው፡፡ ትላንትሽን ሽጭልኝ ነው የሚሉኝ፤ እኔ ከትላንቴ ውጪ ምን አለኝ?? እዚ እረጭ ያለ ግቢ ውስጥ የልጆቼ የጨቅላነት፣ ጩኸት እና የጨዋታቸው ጫጫታ ይሰማኛል፡፡

ይሄ ቤት ልክ እንደ ዋርካ ሥራሥር ትዝታዎቼ ውስጥ ጠልቋል። ጠዋት ጠዋት በሬ ላይ ቁጭ ብዬ የምሞቀው ፀሐይ ከየትም ስፍራ ካለችው ፀሐይ የበለጠ ምቾት አላት።

ከቤቴ ውስጥ ልጆቼን፣ ባሌን የማያስታውሰኝ የትኛው የቤት ክፍል ነው? የትኛው የግቢዬ ጠርዝ ይሆን?

የቱም!

ትላንቷ ላይ ለከተመች አሮጊት ታድያ ይሄ ምን ያህል ገንዘብ ይተካላታል?

ለዚህ ነው ትላንቴን የማልሸጠው!

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
32👏4
#አንተ_የሌለህ_ጊዜ

ተማሪ እያለን ለብዙ ጊዜ የፍቅር ሕይወትን ተጋርተናል፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ ትልቅ ሰው ከሆንን፤ የተለያየ የሕይወት መሥመር ውስጥ ከሰመጥን፣ አጀንዳዎቻችን ከተቀየሩ፣ ፍላጎት እና ሕልማችን ሌላ ከሆነ በኋላ በድንገተኛ ግጥምጥሞሽ ሥራ አገናኘን፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ከብዙ ዓመታት በኋላ ስንገናኝ አድገን፣ በስለን ስለነበረ የወዳጅነት ሰላምታ ሰላም ተባባልን፡፡ ሁለታችንም አይናችን የጣት ቀለበት ሲያስስ ተገጣጠምን፤ ሁለታችንም አግብተናል። ያገናኘን ሥራ ላይ ተጠመድን፣ ደጋግሞ ሥራ አገናኘን፤ ደጋግመን 'email' ተለዋወጥን።

አንድ ቀን ማኪያቶ እየጠጣን ከላይ ከላይ እየተጨዋወትን በሕይወቷ ስላለፈችበት ፈታኝ ጊዜ ማወቅ ፈለግሁ። ለምን የመጣችበትን አስቸጋሪ ሕይወቷን ለማወቅ እንደፈለግኩ አላውቅም።

የህይወትሽ አስቸጋሪ ጊዜ መቼ ነበር አልኳት?

አየችኝ፤ በትንሹ ፈገግ አለች፤ ፈገግ ስትል ዲምፕል አላት፤ ጥርሶቿ እንደ ድሮው ያምራሉ። ከፊት ለፊት በግንባሯ የመጡትን ዘለላ ጸጉሮቿን በቄንጥ ወደኋላ መለሰቻቸው።

ዝም ብዬ ስመለከታት...

“አንተ የሌለህ ጊዜ። ማለቴ የተውከኝ ለታ" አለችኝ። ስትቀልድ መስሎኝ ሳቅሁ። “እማ ትሙት" አለችኝ። በእናቷ ምላ ዋሽታ አታውቅም፡፡ ግርምቴን መደበቅ አልቻልኩም፤ ሁለ ነገሬ ጆሮ ሆነ

አየኋት

“ያ ጊዜ ላልበሰለችው ሄርሞን ፈታኝ ጊዜዋ ነበር። እወድህ ነበር፤ እያንዳንዱ ነገሬ ከአንተ ጋ ተሳስሮ ነበር። ውጤት መጣልኝ፣ ክፍለሀገር ተመደብኩኝ፤ ምክንያቱን ባላወቅኩት ምክንያት ራቅከኝ፤ ሁሉ ነገር ላይ ስልጣን የሰጠኸኝ ልጅ ገሸሽ ስታደርገኝ የማደርገው ጠፋኝ። በጨቅላ ጭንቅላቴ ቀልብህን እንደ ድሮ ወደ እኔ ለመመለስ ባተልኩ፤ ግን አልሆነም።

ወደ ተመደብኩበት ዩኒቨርስቲ ወደፊት መራመድ እንደመብረር እየከበደኝ ሄድኩ። ቀልቤን፣ ሳቄን ትቼ ነበር የሄድኩት። አዲስ ቦታ መልመድ ለእኔ ቀላል እንዳልሆነ ታውቃለህ፤ ሁሉ ነገሬን ላንተ እንደማነበንብ ታውቃለህ። ስላ'ንተ ለሁሉ እንደማወራ ታውቃለህ፤ ጓደኞቻችን ሁሉ የጋራ ነበሩ። ዶርም ሜቶቼ ለሚያወሩት ቋንቋ ባዳ ነበርኩ፤ አብሮነታቸው ሲደራ ባይተዋርነት አራቆተኝ፤ የማይወዱኝ ይመስለኛል።

“የካምፓስ ምግቡ አልተስማማኝም፤ አዲስ ዩንቨርስቲ በመሆኑ ሁሉም ነገር ገና ነበር፡፡ ናፍቆት ገላዬን በላው። ምግቡ ስለማይስማማኝም ብዙ አልበላም። ሰለልኩ፤ የጨጓራ ሕመም ጨፈረብኝ"

መቼ ደውለሽልኝ ታውቂያለሽ? በእኔ የምታውቂው ሰው ሆኖ ማን አለ ያልዘጋሽው? አልኳት ኮስተር ብዬ!

“እንደማትፈልገኝ ሁሉ ነገርህ ይናገር ነበር፤ ስልክህ ረጅም ሰዓት ይያዛል፤ በፍጥነት ተቀያየርክ፤ ለስሜቴ መጠንቀቅ አቆምክ። እንደቀለልኩብህ ድርጊትህ ይናገር ነበር። አንተ ላይ ስልጣን አልባ እንደሆንኩ አሳየኸኝ። ነገሮችን ለማስተካከል በአፍላ ጭንቅላቴ ተፍጨረጨርኩ። ጓደኞቼ ሊሰሙኝ እንጂ መንገድ ለማሳየት ጥበብ እና ልምዱ አልነበራቸውም። ታላላቆቼ ጋ በዛ ዕድሜዬ በዚህ ጉዳይ የማውራት ስልጣኔ አልዳበረም፤ ነውር ነበር።

ሸሸሁ!

የባሰ የቀዘቀዘ ድምጽ እንዳልሰማ ሸሸሁ፤ አዲስ የተወዳጀሃት ልጅ እንዳለች ስድስተኛ ስሜቴ አንሾካሾከልኝ። ስደውል በእሷ ፊት ተራ ጓደኛዬ ነች ዓይነት ወሬ እንዳታወራኝ ሰጋሁ። አትደውይልኝ እንዳትለኝ ስለሰጋሁ ሸሸሁ።

ላ'ንተ ያለኝ ፍቅር የባሰ አጣጥለኸኝ እንዳይቋጭ ስለሳሳው ሸሸሁ!

የጋራ ጓደኞቼ በልቤ ያለውን ፍርሀት እንዳይነገሩኝ ሁሉንም ዘጋኋቸው « አነባቸው የነበሩ ፍቅር ነክ ልብ-ወለድ ጽሑፎች ውስታዬን ተስቅሰው ናፍቆቴን እንዳያባብሱት ማንበብ አቆምኩ፤ የፍቅር ፊልሞች ትዝታዬን ገላልጠው እንዳያሳምሙኝ ማየት ተውኩ፤ ያች ሄርሞን ከመሸሽ ውጪ የመጋፈጥ አቅም አልነበራትምና ሸሸች።

የጀመርኩት የ"psychology" ትምህርት ካለ ምርጫዬ ስለነበር ችግር ሲገጥመኝ የምሸሸግብህ፣ የምታጽናናኝ አንተ ስትለወጥብኝ፣ ስትገፋኝ የልቤን የማጫውተው ጓደኛ አለመኖሩ፣ የምግቡ አለመስማማት፣ የጨጓራ ሕመሜ ኑሮዬን አጠየፈው። ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን . ረጅም ሰዓት እቀመጣለሁ፣ ስብከት አዳምጣለሁ፣ ጉባኤ እከታተላለሁ::

ፆታዊ ፍቅር ስለሌለው፣ የሁሉ ነገር መሠረት ክርስቶስ እንደሆነ ስለሚነገር፣ በፈተናው የጸና የተባረከ ነው ስለሚባል፣ ብዙ ነገሮች በዲያቢሎስ ስለሚላከክ፣ የጭንቀታችን ችግር መፍቻ ጸሎት፣ ንሰሃ መሆኑን በአማረ፣ እና በሚጣፍጥ ቋንቋ ስለሚያስተምሩ ጣፈጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስን የሙጥኝ አልኩ። ችግሮቼ እየቀለሉኝ መጡ። አዳዲስ ሃይማኖተኛ ጓደኞች ተወዳጀሁ።

የመጀመሪያ ዓመት ጨርሼ ስመጣ ግሬይ ሱሪ፣ ቀይ ቲሸርት አድርገህ ቆመህ አየሁህ። ሳይህ ከእስራቴ፣ ከሱሴ መላቀቄ ነው የተገለጠልኝ። የሆነ ቀጫጫ ልጅ፣ ኖርማል ወንድ፣ ለአይን የማይሞላ ልጅ አየሁኝ። ለካ ችግራችንን የምናይበት መንገድ የገዘፈ ስለሆነ ነው ከችግራችን በታች የምንሆነው።

ዕውቀትና ልምድ ያለው ሰው መውጫ መሰላሉን ስለማርዮን ነው ለካ እንቅፋታችን የሚፈነጭብን። ርግጥ ከስቃይ የምናገኘው ጥበብ ያበስለናል። ከስኬት ከምናገኘው እውቀት ከውድቀት የምናገኘው ጥበብ እጅግ ትልቅ ነው።

ያኔ ሳይህና ሰላም ስልህ የተሰማኝ ስሜት አስገረመኝ፤ እረስቼህ ነበር። አንድ የማውቀውን ሰው ሰላም እንደማለት ነበር ያ ወቅት የሕይወቴ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር፤ ነገር ግን በዛ ፈታኝ ወቅት ያዳበርኩት ብስለት ለቀሪው ሕይወቴ ጫንቃ እያበቀልኩበት ነበር።

ጸጥ አልኩ፣ ትንሽ ጸጸት፣ ትንሽ ግርምት፣ ትንሽ | ግርታ ተደማምሮ ሁካታ ቢሞላብኝም ፀጥ አልኩ።ዝምታ ከመላምት ውጪ የሚያስተላልፈው አንድም ተጨባጭ መልእክት የለምና ፀጥ አልኩ።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
31👍17
#አዲስ_መንገድ

ቁንጅናዋ ብዙ ሰው የሚስማማበት ዓይነት ነው። ቆንጆ እንደሆነች ታውቃለች፤ ግን ቆንጆ ስትባል ደስ ይላታል። ሴት ልጅ በየትኛውም ዕድሜ ቆንጆ መባልን አትጠላም፤ ሴት ልጅ መደነቅ ድክመቷ ነው መሰለኝ። በእርግጥ መደነቅ እና ትክክል መባል የሰው ሁሉ ድክመት ይመስለኛል።

ምንም እንኳን የገላዋ አሠራርም ለአድናቆት እንዲመች አድርጎ ያበጃጃት ቢሆንም፣ ሴቶች በሚወዷቸው እንደማይጨክኑ ኤልዳና እኔ እንዳላገኛት መንገድ አለመዝጋቷ ምስክር ነው። እኔ ሞኝ የምባል ዓይነት ሰው ነኝ መሰለኝ፤ ለቀልድ እንኳን ሞኝ ስባል አራስ ነብር ነው የምሆነው። እንዲሁ በቃ ክፍ...ት ነው የሚለኝ።

ሞኝነት ድክመቴ ባይሆን ሞኝ ስባል እስቅ አልነበር? አሁን ቀጫጫ አይደለሁም፣ ቀጫጫ ብባል ግን እስቃለሁ እንጂ አልናደድም፤ ስለዚህ ሞኝ ነኝ ማለት ነው እላለሁ። አንዳንዴ ደግሞ እንደዚህ ከተመራመርኩ እኮ ሞኝ አይደለሁም እላለሁ።

ዘይገርም!

አንዳንዴ ሰዎች ጭንቅላቴ ስል ሲሆንባቸው ትኩር ብለው ያዩኛል፤ በቂላቂልነቴ 'save' አድርገውኝ ባይሆን ኖሮ እንዴት እንደዚህ አሰበ ብለው ሲገረሙብኝ አይናቸው ላይ መች አስተውል ነበር? ሰው ድክመቱን ባያሻሽለው እንኳን

ጥንጥም ይገባዋል ማለት ነው፤ ያ ማለት ደግሞ he might be denying the hard fact deliberately

ኤልዳና ጋ ብዙ ቀን እደውላለሁ፣ ሲያሻት ብቻ ስልኬን ታነሳለች፤ ከደወለችልኝ የሆነ ነገር ፈልጋ ነው፤ ቢሆንም ደስስ ይለኛል! ኤልዳና ከእኔ ጋ ስታወራ አወራሯ ፆታዊ ነገር የለውም፣ መሽኮርመም ሆነ ደርባባነት አይታይባትም። ምንም ፆታዊ ፍላጎት ስለሌላት ይሆን?

አላውቅም!

አግኚኝ ስላት ሀገር እንደምታስተዳድር ዓይነት ነው ባተሌ መሆኗን የምትነገርኝ። የግል ዩኒቨርስቲ እያስተማርኩ፣ ትልቅ ፕሮጀክት እየመራሁ እኔ እንኳን እንደእሷ ስለመባተል አላወራም።

ተሳክቶልኝ ኦር ፈልጋኝ ያገኘችኝ ጊዜ ደግሞ ነጻ መሆን አልችልም። አክብጄ ስለማያት ጨዋታ አይመጣልኝም፡፡ ባገኘሁት አጋጣሚ ቀልቧን ለመሳብ እባዝናለሁ። በቃ እዛው ከእኔ ጋ እያለች ከሌላ ሰው ጋ ስልክ ታወራለች፡፡ ፊቴ ለምታወራው ወንድ ሲሆን ደግሞ ደርበብ እሽኩርምም ስትል አስተውላለሁ፡፡ ሞኝ ስለምመስላት ይሄን የምረዳ አይመስላትም ወይም ሳይታወቃት በደመ ነብስ ነው ሁኔታዋ እና አነጋገሯ የሚቀየርባት፤ አንዳንዴ ለምንፈልገው ነገርአድራጎታችን ከዕውቅናችን ውጪ ይሆን የለ።

ትንሽ ለመጫወት እሞክራለሁ፤ ቀላል ወሬ ታወራልኛለች። ከዛ የማይመለስ ብር ትበደረኛለች፣ ከዛ እንቅ አድርጋ ትስመኛለች፤ ደስስስስስ ይለኛል፡፡ ጓደኞቿ ጋ ሆና ካገኘኋት በጣም እንደምወዳት እሷ ደግሞ ከምንም እንደማትቆጥረኝ፤ ለብቻቸው የነገረቻቸውን በማስረጃ እያጣቀሰች እና እየቀለደችብኝ ታሳየቸዋለች። እነሱ ደግሞ አምነንሻል፣ ገብቶናል ለማለት ያሽካካሉ።

አሁን እንደው የሚወደን ሰው ላይ እማኝ አስቀምጦ ማልመጥ ምን የሚሉት ሥልጣኔ ነው?!

“ኮትህን የት ገዛኸው" አለችኝ አንድ ጓደኛዋ ሽሙጥ እንዳልሆነ እንዳያሳብቅ ፊቷን እየተቆጣጠረችው። አይን ደግሞ አይዋሽ፣ አይኗ ያስታውቃል፡፡ ለበኋላ የሚሆን ቧልት እያድቦለቦለች ነው።

ዝም አልኳት። አሁን ሰው መርጦ እና ወዶ በለበሰው ኮት የለበሰው ሰው ፊት ማላገጥ ትክክል ነው??

ጓደኞቿ እኔ ላይ ያላቸው ንቀት ምንጭ የምወዳት ኤልዳና መሆኗን ነጋሪም መስካሪም አያስፈለገኝም። ተሰብስበው ሳገኛቸው ከሚጨንቀኝ ነገሮች አንዱ እጄን የት እንማደርገው ነው። ኪሴ ውስጥ እከተዋለሁ ወይ አጣምራለሁ አልያም የግራ እና የቀኝ ጣቶቼን አቆላልፋለሁ፤ በእሱ ራሱ ይቀልዳሉ።

ፍቅር ተአምራዊ መሆኑ ማሳያዬ ይሄ ሁላ እየገባኝ አለመሸሼ ነው! እኔ ለእሷ ክፉ አይደለሁ! ከሁሉም ሰው በላይ ስለምወዳት አይደል የተበደረችኝን እንደረሳሁ ሆኜ ሌላ ቀን እንደገና የማትመልስልኝን ገንዘብ የማበድራት፤ ለዛውም ላይ ታች ብዬ የማመጣውን ገንዘቤን!!

መውደዱ የእውነት እንደሆነ የሚታወቅ ሰው ላይ ይሾፋል?

ሰው ላይ መቀለድ አራድነት ነው?

ስለማታውቀኝ ነው እኮ ማጣጣል እንደማይጥለኝ፣ ስንቴ በትግሎቼ እንደወደቅኩ፣ ወድቄ ሳለሁ ቆሜ ስለምታገለው እንደማሰላስል!

ለዚህ ነው ይሄ ሁላ ነገሯ እየገባኝ፣ አይኗ ሲከፈት ሞኝነቴ ጥበብ እንዳለው ትረዳለች ብዬ መጠበቄ፤ የድንቁርናዋ ምንጩ አለማስተዋል እንደሆነ የምረዳላት፤ ከብልግናዎቿ መሀል መልካምነቷን ለራሴ እንደምነግር አልገባትም። ክፉ ቀን ቢመጣባት አብራ ከምታላግጥብኝ ጓደኞቿ የበለጠ እንደምረዳት፤ ከአጠገቧ እንደማልጠፋ አልገባትም።

ሰው በረከቱ ላይ እንዴት ያላግጣል? መወደድ በረከት አይደለምን?

ፍቅር የሚወዱንን ብቻ መውደድ አይደለም፤ ለዛ ነው የምወዳት፤ የቀን ጉዳይ ነው እንጂ ፍቅሬ አንድ ቀን ይጋባባታል።

ያ አንድ ቀን እንዲመጣ ደግሞ ...

ትላንት ባልሞከርኩት መንገድ መምጣት አለብኝ፤ ለተመሳሳይ አወዳዳቅ ተመሳሳይ የአተጋገል ስልቶች ምክንያት ናቸው፡፡ ጥበብ ማለት የሚፋለመንን መረዳት ብቻ ሳይሆን መቅደምም ጭምር ነው። ከትላንት የተሻለ ውጤት መጠበቅ ያለብኝ ትላንት በሄድኩበት መንገድ ካልመጣሁ ብቻ ነው።

እጅ መስጠት ውስጥም ደማቅ ድል አለ!!!

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
20👍12
#የዕውቀት_መንገድ

ገጣጣ ነች፤ ስትስቅ አፏን ከፍታ ነው፤ አሳሳቋን ከማንም ጋ ብትሆን አትቀይረውም። ስንት ቀን እኔ ባለሁበት የሚያምርጥርስ አይታ ስታደንቅ አይቻታለሁ። የሌለውን ያላጣጣለ እሱ ትልቅ ሰው ነው!!!

ፎቶ ላይ ገጣጣነቷን ለመደበቅ ጥረት ስታደርግ አይቻት አላውቅም። ራስን የመሆን እና ራስን የማወቅ ጥግ ራስን መቀበል ነው። አንድ ዕለት ሆን ብዬ ግንባሯ ላይ ፍንክት ስላለባት እና በሻሽ፣ በሻርፕ ስለምትደብቀው ልጅ ስነግራት "በዙሪያችን ያሉ ሰዎች እንዲቀበሉን እኛ ቀድመን ራሳችን መቀበል አለብን፤ ደካማ ሰው ነው ድክመት ላይ የሚመሰጠው፤ በራሱ የማይተማመን፣ የሚያሳቅቀው ነው ጉድለት የሚያስሰው። የማይለወጥ ነገርን መቀበል ከራስ ጋ ያዋሕዳል። ያየነውን ጥሩ ነገርበትክክለኛው ሰዓት ማንጸባረቅ በራስ መተማመን ይባላል።
በራሳቸው የማይተማመኑ ሰው ማሳነስ ላይ ሲረማመዱ የሚውሉ ናቸው::"

"በራሳቸው የማይተማመኑ ድኩማኖች አላግጠው አሸማቀዋት ነው ራሷን ያልተቀበለችው፡፡ አስተዳደጓ ላይ ራስን ስለመሆን፣ ራስን ስለማወቅ እና ራስን ስለማሸነፍ ማንም ስላላሰረጸባት ነው፡፡ ማንም በጀርባዬ ስለገጣጣነቴ ሲንሾካሾክ ባይ ውስጤ አይታወክም፣ ድብርት አይንጠኝም፤ ምክንያቱም ራሴን ተቀብዬዋለሁ። ድሃን ድሃ ስትለው ከተንጨረጨረ ድህነቱን እንዳይቀበል ትምህክተኝነቱ ጋርዶታል ማለት ነው። መስታወት ላይ ስቆም ጥርሴን ስደብቅ ምን እንደምመስል በከንፈሬ እየደበቅኩ ለማየት አልጥርም፡፡ በአደጋ፣ በበሽታ፣ በዕድሜ መግፋት አካል እንደሚዛነፍ፣ እንደሚጎድል እና እንደሚበላሽ አውቀዋለሁ። እንደዚህ እያልኩ ግን ተጽናንቼ አላውቅም፤ መጽናናትም አማራጭ የማጣት መንገድ ነውና። ተጽናንተህ፣ አለባብሰህ፣ ራስህን አሞኝተህ የተውከው ነገር ባስታወሱህ አልያም ባስታወስከው ቁጥር ምቾት አይሰጥህም። ዘለቄታዊ መፍትሔ ራስን መቀበል ነው፤ አስተዋጽኦ ባላበረከትኩበት ነገር ስለምን እመሰጣለሁ?" እያለች ስታወራኝ እርጋታ እና ትህትና ተላብሳ ነው፤ ዕውቀት ነጻ እንደሚያወጣ ይኸው

እውነቱን ለማውራት ገጣጣነት ያምርባታል።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
20👍9👏6🥰5
#ጥሎ_መሸነፍ

አስቤበት፣ አሰላስዬ ልተዋት፣ አልፈልግሽም ልላት አቅጄ አግኝቻት ችላ ስትለኝ ፍቅሬ ይጨምራል። ስለ ማንም ግድ እንደሌላት ስትጠቁመኝ እልህ እጋባለሁ።

ልበ ሙሉነቷ፣ ካለ'ኔ መቆም እንደምትችል ሳስብ ልቤ ይርዳል። አንዳች የማላውቀው ኃይል አብሪያት እንድሆን ይታገለኛል። አሁን በቀደም ፀሐይ ስትሸሸግ፣ ሰማዩ ሲጠቁር፤ ከባቢው ሲሰክን፤ አንዲት ለስላሳ ሙዚቃ ያለበት ሬስቶራንት አገኘኋት። አልዘነጠችም ፈታ ብላለች፤ ፈታ ብያለሁ።

አብሪያት መሆን እንደማልፈልግ ጫፍ ጫፉን አሳየኋት። ነገ የምንኖረው የጋራ ሕልም እንደሌለን ጠቆምኳት፤ ምንም ሳይመስላት በፈገግታ ደስ እንዳለህ አለችኝ። ደስስ አላለኝም፤ ሲደብራት አባብላታለሁ ያልኩት የቃላት ጋጋታ ሟሟ። ድብርት ሲያቀዘቅዘኝ ታውቆኛል። ቅዝቃዜውን ለመርታት ያዘዝኩትን አልኮል በአንድ ትንፋሽ ጨለጥኩ። በልቤ ያለውን እውነታ ለማን ብናገር ያምናል፤ ልጣላት መጥቼ፣ ለመጣላት ዳር ዳር ስል ምንም አልመሰላትም ብሎ ሐሳብ መቀየር ምን ይሉታል።

ሳምኳት ሳመችኝ ተሳሳምን አትወጅም እያልኩ መጨቅጨቅ ጀመርኩ፤ እወድሃለሁ በይኝ አልኳት እወድሃለሁ አለችኝ።

ቆይ ከወደደችኝ ለምን እንደማልፈልጋት ምልክት ስሰጣት አልከፋትም? ለምን እንደምታፈቅረኝ አልዘበዘበችም፤ ቅርአለኝ። አሽናፊነት የሚመጣው ተጋጣሚ የሚፈልገውን ባለመስጠት ነው። የምንፈልገውን የምናገኘው እራሳችንን ከምንፈልገው ነገር ባለማሳነስ ነው። እውነቷን ነው በልመና የምታስቀረው ፍቅረኛዋ ምን ይጠቅማታል። ራሷን ከእሱ በታች አድርጋ የእሷ የምታደርገው አጋሯ ምን ይበጃታል።

ነጋ፣ ፍቅር በልተን፣ ፍቅር ሰርተን ስንነሳ፣ ስንዋሃድ አትለየኝ ትለኛለች ብዬ ጠበቅኳት። በፍቅር ሳመችኝ፤ እንዳደረኳት ሆነችልኝ፤ እንደሳምኳት ሳመችኝ፤ ምንም አላለችኝም፡፡ ሳበኝ፤ የምፈልገውን አለመስጠቷ ሳበኝ፤ እንደምጠብቀው አለመሆኑ ውስጤ ሲሸነፍ ታውቆኛል።

ጭንቅላቴን ተቆጣጠረችው፡፡ ሰው ምን ዓይነት ውሻ ፍጡርነው ስል ተበሳጨሁ፤ አልፈልግም ብትለኝ፣ ብታለቅስ እንዴት ነበር የምታበየው? ስንት ሕግ ነበር የምደረድረው? እንዴት ነበር ከማማው ላይ ተፈናጥጬ ቁልቁል የማያት? እንዴት ነበር እኔ ትልቅ፣ ግዙፍ ሰው መሆኔን እዘበዝብላት የነበር? ጥበቧ እንዳልታበይባት ከለለኝ፣ ልበሙሉነት መሥመራችንን የማቅለል አቅሙ ግዙፍ ነው፡፡

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍1810🔥8🎉1
                      ጭራሽ....
                 ደሞ ልብ እንዳለው
                ሴት ላፍቅር እላለው?
                 ደሞ ነፍስ እንዳለው
            ቅኖና ንስሀ ምናምን እላለው?
                   ደሞ ሰማሻቸው?
                  ለመልኩ ለዓይኑ
                 ግድ የለውም ሲሉ

                   ጎኑ ላለ ተድላ...
                   ጎኑ ላለ ለቅሶ...
                   ጎኑ ላለ ዕድር...
                   ጎኑ ላለ ዕቁብ...
               የለውም አንዳች ቁብ

                  ሲሉ ሰማሻቸው?
        ፂሙ ቢንዠረገግ መሬት ቢዘረጋ
     እሱ ግድ የለውም አፈር ቢሆን አልጋ

               ሲሉ ሰማሻቸው?
               ዝም አትበያቸው

               ዝም አትበያቸው
"በየትኛው ነብሱ ይሄን ሁሉ ያስብ?"
             ብለሽ ጠይቂያቸው

              ዝም አትበያቸው

               ዝም አትበያቸው
"በየትኛው ነብሱ ይሄን ሁሉ ያስብ?"
            ብለሽ ጠይቂያቸው

  በየትኛው ነፍሴ ከትላንቴ ልማር
  በየትኛው ነፍሴ ከትላንቴ ልማር
አንቺን አገኝ ብዬ አሲዤው በቁማር

          አስመልሺኝ እስቲ...

ደሞ ልብ እንዳለው ሴት ላፍቅር እላለው?!


🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍10🔥51
ውድነሽን ሲነካብኝ በልጅነት አጥንቴ ሳይጠነክር፣ ትከሻዬ ሳይሰፋ፣ አካሌ ሳይጎለማ ለመታገል እንደተዘጋጀሁ እረሳው። እግዜር ሊበቀለው የራሱን ፊት እንደሰጠኝ፣ የራሱን ጥጋብ እንዳወረሰኝ አልተገለጠለትም ነበር። እግዜር ሲቀጣ ሂደቱን የውጤቱ ቀን ነው የሚገልጸው።

ያነቅኩበትን አንዱን እጄን ለቅቄ፣ እጄን ጨብጬ በኃይል አራት ጊዜ ያህል ደጋግሜ ሰነዘርኩ። ቤቱ ተንቀጠቀጠ፣ እናቴ ጮኸች፣ ቤት ውስጥ የነበረው ሰው ሊይዘኝ ስለፈራ ለመነኝ...

በእርግጥ ቡጢዬን ያሳረፍኩት ከፊቱ ጎን ያለው ግድግዳ ላይ ነው፤ ግድግዳው ተሰነጣጠቀ፤ ግዝፈቴ ይሆን፣ ብስጭቴ ይሆን፣ ግድግዳችን ስለማይረባ ይሆን አላውቅም!!

“ተው ልጄ ተው" አለኝ...

ድሪባ ለካ መለመን ይችላል። ወይም ዕድሜ ሲገፋ፣ አቅሙ ሲደክም ልመና ለምዷል፤ መኖር ለካ ብዙ መገለጫችን ያልሆነ ነገርን ጨምሮ ያስለምዳል።

የተሰማኝን ማውራት ብችል ኖሮ ምን ታድርግህ? ምን አድርጊ ነው የምትላት? ዕድሜ አያስተምርህም?አይበቃህም? እለው ነበር። ማድረግ የቻልኩት ሸፋሽፍቴ ላይ የተሞጀረ እንባ ማሳየት ብቻ ነበር!!

ስላልታደለ እንጂ አውሬው ልጁ እሱን ነበር ሊከላከለው የሚገባው፤ ስላልታደልኩ እንጂ ያሳደገኝን ሰውዬ እንደጠላቴ አልቆጥረውም ነበር።

ለቀቅሁት... ለመጀመሪያ ጊዜ መግዘፌ አስጠላኝ። ትናንት አቅም አልባ እያለሁ እናቴን ለማዳን ስፍጨረጨር የነበረው ስሜት ይሻል ነበር። ፍቅር ማለት ለሚያፈቅሩት ሲሉ ከማይችሉት ጋ መታገል እንጂ የሚያሸንፉትን ማሸማቀቅ አይደለም። ስለቀው እንባው እንደ እኔ ሽፋሽፍቱ አልገደበውም አለቀሰ። ያ ሞገሳሙ ድሪባ፣ በድምጹ የሚያርበደብደው፣ ተነሳበት የሚባለው፣ የሚለመነው፣ የሚለምኑት ጎረቤቶች ፊት ሲለመንለት ጊዜ አለቀሰ።

ለካ አርጅቷል፣ ለካ አቅሙ እየከዳው ነበር፣ ለካ ማስበርገግ ሱስ ሆኖበት ነው። መለመን ምን ምን እንደሚል፤ መበርገግ በገዛ ልጁ ምን እንደሚመስል በጎፈነነ ስሜት ውስጥ ሆኖ አየው። ድሪባ ሲያለቅስ ሳየው ዘመናት ሙሉ ከሽፋሽፍቴ ወርዶ የማያውቀው እንባዬ ጉንጬ ላይ ሲሄድ ታወቀኝ። ለምን ይሄን ያህል እስኪያለቅስ አሳዝኜው፣ ተፈታትኜው አንቄው ሳለ ሽጉጡን አውጥቶ ካልገደልኩት ብሎ አልተገላገለም።

ውድነሽን ባይነካብኝ ኖሮ መቼ አዋርደው ነበር? ደግሞስ ምን አገባኝ ሚስቱ አይደለች? ደግሞ ሲያመው ትደነግጥ የለ፤ ሲያማት የእኔን ያህል መጨነቁ ይታይ የለ።


እሷስ መቼ እንደምትጠላው ሰምቼ አውቃለሁ ? መቼ ስለጥፋቱ ለልጆቿም ሆነ ለሌላ ስታወራ መቼ ሰማሁ ? መቼ አጠጣጥላው አይቻት አውቃለሁ...መቼ??

ከድሪባ ጋር በፀባይ የምንመሳሰል መስሎኝ ነበር እውነቱ ግን እኔ አውሬ ነኝ።

እንባዬ በጉንጬ እየወረደ ስልኬ ጠራ የሚስቴ እናት ናቸው አንስቼ ሄሎ ስል "ሮብሰን የወንድ ልጅ አባት ሆነካል። መልኩ ደሞ ቁርጥ አንተን መንታ ነው የምትመስሉት አለችኝ።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
27👏4
ቤተሳይዳ ሞንዳላ መልከ መልካም፣ ዞማ ጸጉር ያላት ሴት ናት ግን ዋነኛ የሴት መልክ የሆነው ሆደ ቡቡነት አላደላትም። በረባው ባልረባው አትሸበርም፣ ዛሬ ደብሮታል፣ ትንሽ አመም አድርጎታል፣ ደክሞታል እንኳን ብላ መናገር እና መሞገት የምትፈልገውን ነገር  አታሳድርም። ይሉኝታ አያጠቃትም፤ ዓላማዋን ለማሳካት የሚያናውዛት የስሜት መውጣት እና መውረድ የለም፤ ብርቱ ነች እንደ ማሽን።

ስሜቷ በቀላሉ አይነበብም፤ ሲዶክካት እንደ እኔ በወዳጆቿ አትታከክም። ተመሳሳይ ነገር አይተን የምናተኩርበት እና የምንተነትነው ትንተና አራምባ እና ቆቦ ነው። በቀላሉ ሰው አይሸውዳትም፤ ጥንቁቅ ናት፤ እያወራች ዙሪያዋን ታጠናለች፤ ከሚነገራት ጀርባ ያለውን ታነፈንፋለች።

ቤተሳይዳ ታኮራለች ግን ስሜት አልባ ናት።

አሁን ግጥም አይገባትም፤ ሥነጽሁፍ ለእሷ የሥራ ዘርፍ ብቻ ነው ብሎ ቅሬታ ማቅረብ ተገቢ ነው? ግን እኔ ቅር ይለኛል፤ ድራማ፣ ዘፈን፣ ፊልም፣ ቲያትር እና ግጥም የማይወድ ሰው ቤተሳይዳ ብቻ ነች የገጠመችኝ። ቆይ እንዴት እና በምን ተሸጋግሬ ነው ፍቅረኛዬ፣ ከዛ ሚስቴ የሆነችው?

በእርግጥ ጉብዝናዋ ማርኮኝ ነው፡፡ ችግሩ ጉብዝና ብቻውን ስኬትን እን'ጂ ደስታን አያመጣ፤ ሁኔታዋ ሁሉ ቁጥብ ያደርገኛል። መደጋገፍ፣ መሳሳቅ፣ ተረባ፣ ፉክክር፣ ቀልድ እና ጨዋታ የደራበት ቤት ውስጥ ነው ያደግሁት። ምን ያደርጋል የቤተሳይዳ ባል ሆንኩ። ቀልድ አይገባትም ብሎ ለሽማግሌ አይነገር፤ ቀልድ ይግባሽ፣ ይሄ ያስቃል ሳቂ ተብሎ አይገሰጽ።

ቅዳሜ ረፋድ ላይ 'ቴክ አዌይ' ያስደረግነውን ፒዛ መኪና ውስጥ እየበላን ሳለን የቤተሳይዳን አይን ስከተለው አንዲት ከልጆች ገሸሽ ብላ ጥግ ላይ እኛን የምትመለከት ልጅ ላይቀርቷል፤ ልጅቷ በአካልም በአለባበስም ከልጆቹ ኮስመን ብላለች፤ ጠራቻት እና መጣች።

"ደህና ነሽ ሚጣ"

"ደህና"

"ማነው ስምሽ?"

"ሃይማኖት"

ፒዛውን በእጇ እያመለከተች “ልስጥሽ“

"አዎ"

ሰጠቻት። የልጅቷ አበላል ያሳዝናል

ቤተሳይዳ "ርቦሽ ነበር?” ስትላት በብዙ ወደ አፏ ከከተተችው ፒዛ ጋ ለመዋጥ እየታገለች ጭንቅላቷን በአወንታ ነቀነቀች።

ቤተሳይዳ የሰጠቻትን ፒዛ ስትጨርስ ጠብቃ

“ከማን ጋ ነው የምትኖሪው?"

“ከዘመድ ጋ“

ቤተ ሳይዳ አብረዋት ሲጫወቱ የነበሩት ልጆችን እየጠቆመች “እነዛ ማናቸው"

“የምኖርባቸው የዘመዶቼ ልጆች"

ጣልቃ ሳልገባ አንዴ ወደ ቤተ ሳይዳ አንዴ ወደ ጎስቋላዋ ልጅ አያለሁ በዝምታ።

ስሜት አልባዋ ቤተሳይዳ እንባዋን እየታገለች "That was the story of my life" አለች ትክዝ ብላ፤ በመጨረሻም ለልጅቷ የቀረውን ፒዛ ሰጥታት ስማት ቻው አለቻት።

“ሥራ እያገዝኳቸው እንድማር የሩቅ ዘመዶቼ በልጅነቴ አምጥተውኝ እነሱ ጋ ነበር ያደግኩት። የምኖርበት ቤት ውስጥ የተሰበረ እቃ፣ መከደን ኖሮበት ያልተከደነ፣ ያልጠበቀ ቧንቧ፣ መጥፋት ኖሮበት ያልጠፋ TV፣ ወድቆ ያልተነሳ ኩባያ፣ ስሕተት ሁሉ፣ ልክ ያልሆነ ነገር ሁሉ በእኔ ይላከካል። በየሰበቡ ስደለቅ፣ ስረገም እና ፍጹም ሆኖ ለመገኘት ስዳክር ነበር ያደግኩት።
ታላላቆቼ፣ እኩዮቼ፣ ታናናሾቼ ሁሉም እኔን ያሸንፉኛል። ሁሉም እኔ ላይ ይበረታሉ፣ ሁሉም ይወቅሰኛል፣ ሁሉም ይረግመኛል፣ ጨዋታቸው ውስጥ አያስገቡኝም፤ እኔ የቤት ሥራ እሠራለሁ፣ ለተበላሸ ነገር ኃላፊነት እወስዳለሁ፣ ባገኘሁት ቀዳዳ ደግሞ አጠናለሁ። ዘመኔን ሙሉ ከቤት
ሰራተኝነት ለመውጣት ከተወቃሽነት ለመዳን ራሴን ስከላከል ነው ያደኩት።

የቅድሟ ልጅ የለበሰችው አመዳም ሙሉ ቀሚስ ዓይነት ገላዬ ላይ እስኪመስል ድረስ ብዙ ዓመት ለብሻለሁ። የጥናት ጊዜ ለነገ ለማስተረፍ ሥራ አላሳድርም እስከ ሌሊት እሰራለሁ: አይደክማት እሷ ባቡር ነች ይሉኛል። ሌሊት ስተኛ ወገቤ እንዴት እንደሚንቀጠቀጥ እኔ እና እመብርሃን ነበርን የምናውቀው." ብላ እንባዋ አመለጣት:: ለመጀመሪያ ጊዜ የቤተሳይዳን እንባ አየሁ። ከአለት ላይ ውሃ የፈለቀ ያህል በግርምት አየኋት፡፡ ለማባበል አልሞከርኩም፡፡ ያለፈችበት የአስተዳደግ መንገድ ቢያሳዝነኝም፣ እንባዋን ሳይ ግን ከሐዘን ይልቅ ለደስታ ቀረበ ስሜት ነበር የተሰማኝ፡፡

የሐዘን ይሁን የለስላሳ ደስታ ያለየሁት እንባዬ ሲታገለኝ ቃል ሳልናገር አቀፍኳት፡፡ አንገቴ ሥር ሽጉጥ ብላ ተንሰቀሰቀች፡፡ ቤተሳይዳ ሙሉ ሰው ሆነች፣ ሴትነቷን አየሁ፡፡

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
16😢16🔥2
እቺን ላንብብልሽ
ብዙ ካልኩት መሃል :
እቺን ልበልልሽ ስሚኝ አንዲቱን ቃል :

ማሰቤ ሲጠና
ብዕሬን አንስቼ ከሞነጫጨርኩት :

ትውስታዬ ሲግል
ቁራጭ ወረቀት ላይ በቃል ካሰፈርኩት
መጠማቴ ሲብስ
ሺ ደብዳቤ ፅፌ ጎኔ ከከመርኩት :
ትዝታዬ ሲያይል
በግጥሜ ገፆች ላይ ከትቤ ካኖርኩት :

እቺን ላንብብልሽ
ብዙ ካልኩት መሃል :
ከሁሉም ከሁሉም ስሚልኝ እቺን ቃል :

'ና...ፍ....ቀ.......ሽኛል'

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍7
ከሌላ ወንድ ጋ ሻይ ለመጠጣት እቅዷን የማትነግረኝ የነበረች ልጅ ዛሬ ሁለተኛ ለመውለድ ከባሏ ጋ ያወጡትን እቅድ በእርጋታ እየተረከችልኝ እኔም በጣም ጥሩ እያልኩ እየሰማኋት ነው። ተመሳሳይ ድርጊት በጊዜ እና በቦታ ልዩነት ምክንያት የሚያሰቅልም የሚያስጨበጭብም ይሆናል?

ያኔ በሰው ሚስት ስብሰከሰክ፣ አካኪ ዘራፍ ስል እጣ ፈንታዬ ፈገግ እያለብኝ ነበር ማለት ነው? ሳላገኛት ሁለት ቀኔ ናፈቀችኝ እኮ እያልኩ ያዙኝ ልቀቁኝ ስልስ በፈገግታ ማን ይሆን ያየኝ? አለማወቅን የመሰለ ነገር ምን አለ? ነጋችንን ብናውቅ ኖሮ ማን በሕይወት እንዲህ ተመስጦ ይባትል ነበር?

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
16🔥6👏1