አትሮኖስ
282K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
497 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ኑረት_ሂደት_ሂደት

ከገላ ተቆርጦ ዕትብቴ ሲቀበር፤
ለአፈር ማንነቴ
ለሞት ቀብድ ነበር።

ታዲያ...
ምነው ተዘነጋኝ?!

ዳግም የሚቀበር
ቀሪ ገላ እንዳለኝ፤
ትምክህተኛ ሆኜ
በኑረቴ ዘመን
የራቅኩኝ ቢመስለኝ፤
ያው...
አሁንም
ቀብድ የተያዘብኝ ቁራጭ እትብት ነኝ!።

🔘ልዑል ሀይሌ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍51
#ትወጂኛለሽ!!!

እኔ እየፈራሁሽ፣ ልቤ እየደፈረሽ
እኔ እየናኩሽ ፣ ልቤ እያከበረሽ
እኔ እየጠላሁሽ ፣ ልቤ እያፈቀረሽ
ከራሴ ስጣላ...
እኖራለሁ እንጂ ፣ የልቤን ሀቅ ይዤ
አንድም ቀን አልፎልኝ....
ልቤን እንደልቤ ፣ አላውቅም አዝዤ፡፡
አንቺም ልክ እንደኔ...
ልብሽን እንደልብ ፣ ማዘዝ አትችይም
ልብሽ ይወደኛል ፣ ጠላሁህ ብትይም፡፡
ባትወጂኝም እንኳን
የመጥላትሽ መጠን ፣ የቱን ያህል ቢያክል
አንቺን አላምንሽም ፣ ልብሽ ነው ትክክል፡፡
ትወጂኛለሽ!!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍2