አትሮኖስ
281K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
487 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አመውዴ

እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
በግ ማይጠፋው ቤት
ዶሮም አልታረደ
ዘይት ዋጋው ንሮ
እህል ተወደደ
ለነገሩ ይሁን
ቀን ነግቶ ይመሻል
እንኳን ኑሮ ቀርቶ
አንቺም ተወደሻል

እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
የቤታችን ቲቪ
ሪሞቱ ጠፍቶበት
የመኪናው መንገድ
አህያ ሄዶበት
ዕምነበረዳችን
ድንጋይ ተጠርቦበት
ያ ፅዱ ጎዳና
ተዝረክርኮልሻል
ለነገሩ ይሁን
አንቺም ሰው ጥለሻል

እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
በአውቶቡስ ፌርማታ
ባቡር ተጠበቀ
ሌባው እየኮራ
ፖሊስ ተደበቀ
ጥርስ ያለው አይስቅም
ድዳሙ እየሳቀ
ለነገሩ ይሁን
ቀን ነግቶ ይመሻል
እንኳን ሌላው ቀርቶ
አንቺም የኔዋ ጉድ
የኔን ልብ ሰርቀሻል

እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
በዝግ ቤት ውስጥ ሆኜ
ብጠብቅሽ እንኳ
.

.


.
በራችን ተንኳኳ!!


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

🔘ልዑል ሀይሌ🔘

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
6😁1
#እየመቱህ_ስራ

በህይወት ዘመንህ በስኬትህ መሀል
ለመነሳት መውደቅ ይጠበቅብሀል
ተቸገር ግድ የለም አይከፋ ልብህ
ከእንቅልፍህ ለመንቃት መተኛት አለብህ
ከፍ ብለህ ታይተህ እንድትኖር በኩራት
ይጠበቅብሀል ዝቅ ብሎ መስራት

ራሱን ዝቅ አድርጎ ችግር የሚፋለም
በግድ የሚሰራ እንደ ሚስማር የለም
በአናፂው ጉልበት በሀይል ተመትቶ
አይከፋም አንዴም ይሰራል ተጎድቶ
ውጤታማ እስክትሆን ፍሬ እስክታፈራ
አንተም እንደ ሚስማር እየመቱህ ስራ


  #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
6👍1