አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////
አለም መተኛት አቅቷት እየተገለበጠች ባለችበት ጊዜ ነበር ስልኩ የጮኸው፡፡ሰዓቱ እኩለ ለሊት በመጠጋቱ የተነሳ ጥሪው በጣም ነበር ያስደነገጣት ። የራስጌ መብራቱን በማብራት የስልኩን እጄታ አነሳችና ጆረዋ ላይ ለጥፋ ጎላ ባለ ድምፅ "ጤና ይስጥልኝ" አለች፡፡ቀደም ብሎ ስታለቅስ ስለቆየች ድምጿ የሻከረ ነበር
"ሰላም ››መለሰላት፡፡

"አወቅሽኝ ወ.ሪት አለም "

ልቧ በደስታ ዘለለ፣"አንተ እንደገና? በዚህ ውድቅት ለሊት ከእንቅልፍ ያስነሳኸኝ ደህና ነገር ልትነግረኝ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ" አለችው።እምቢተኛ ምስክሮች ብዙ ጊዜ የሚናገሩትን ነገር አስፈላጊነት ሲጠቀስላቸው ለመናገር እንደሚበረታቱ ከልምድ ታዝባለች፡፡

"ከኔ ጋር ድብብቆሽ አትጫወቺ …. ማወቅ የምትፈልጊውን በጠቅላላ አውቃለሁ። "

"ለምሳሌ ምን?"

"ለምሳሌ እናትሽን ማን እንደገደላት››

አለም አተነፋፈስዋን በመቆጣጠር ላይ ትኩረት አደረገች።

" ይመስለኛል ዜናው አስደምሞሻል››

"ታዲያ ንገረኝ ማን ነበር?"

"እመቤት ደደብ እመስልሻለሁ እንዴ? ኩማንደሩ ቀደም ሲል ስልክሽን አለማስጠለፉን በምን አውቃለው ?"

"ይመስለኛል….በጣም ብዙ ፊልሞችን አይተሃል?››

‹‹ተረቡን አቁሚና ይልቅ በፅሞና አድምጪኝ ….ነገ ማታ አንድ ሰዓት ሸዋበር የሚገኘው ደንበል ሆቴል እንገናኝ" በማለት ሰዓቱንና ቦታውን ነገራት፡፡

"እንዴት ላውቅህ እችላለሁ?"

"እኔ አውቅሻለሁ"

ሌላ ነገር ከመናገሯ በፊት ስልኩን ዘጋው። አለም በአልጋው ጠርዝ ላይ ለጥቂት ጊዜ ተቀምጣ ጨለማውን እያየች ደርቃ ቀረች። ልትጎዳ እንደምትችል የነገራትን የኩማንደሩ ማስጠንቀቂያ አስታወሰች። የእርሷ ምናባዊ አእምሮ በሴት ላይ ብቻ ሊደርስ የሚችለውን አሰቃቂ ነገር ሁሉ አስተናገደ። በተኛችበት ሆና በላብ ተጠምቀው ነበር።
///
የከተማው የፖሊስ አዛዥ እንፋሎት የሚትገለግበትን ቡናውን አንስቶ ጠጣ። ምላሱን አቃጠለው። ግን ግድ አልነበረውም። በጣም በከፋ መንገድ የካፌይን ማነቃቂያ ያስፈልገዋል
‹‹ስለማን ነው የምናወራው?›› ሲል በግል ቢሮው ደጃፍ ላይ ቆሞ የነበረውን ምክትሉን ጠየቀ ..

" ስለአቃቢ ህግ ፅ/ቤት ነው››

"ስለ ወ.ሪት አለም እያወራህ ነው ?" ምክትሉ መለሰ " አዎ ጌታዬ ስለእሷ ነው።" "እሺ ምን አዲስ ነገር አለ?"

"  የእናቷን  የሬሳ  ምርመራ  መዝገብ  አስወጥታ  ዠለመመርመር  ወደ  ተክለሀይማኖት ቤ/ክርስቲያን ሄዳለች ››

"ምን?"

"አዎ ጌታዬ እንዲከታተሏት የመደብናቸው ፖሊሶች  ናቸው ደውለው የነገሩኝ፡፡››

‹‹በል አሁኑኑ ደውልላቸውና ወደእነሱ እየመጣሁ እንደሆነ ንገራቸው››

ገመዶ ኮቱን ከተሰቀለበት አንስቶ ቢሮውን ለቆ ወጣ…፡፡ ትምህርት ቤቶችን እና አብዛኛዎቹን የንግድ ድርጅቶች እንዲዘጉ ያደረጋቸውን የፀጥታ ችግር ቢኖርም ግድ አል ነበረውም። ሰልፈኛውን እየሰነጠቀ እና ወንበር እያሳበረ ወደሆስፒታል ነዳው፡፡

"የት ነው ያለችው?" እንደደረሰ ኩማንደሩ ጮኸ፣..አንድ አነስተኛ ቢሮ መሰል ክፍል ውስጥ ቁጭ ብላ ከአስተዳዳሪው ጋር ስታወራ ተመለከታ…ወደእዛው ተንደርድሮ ሄደ፡፡
ምንም ፍቃድ ሳይጠይቅ ሰተት ብሎ ገባና " ምን እየሰራሽ ነው ?"አንቧረቀባት፡፡ "እንደምን አደርክ ኩማንደር"አለችው ለስለስ ብላ፡፡

"ጥያቄዬን መልሺልኝ?"

‹‹ምን እያደረኩ እንደሆነማ በደንብ ታውቃለህ?››

"በአንቺ ምክንያት ሴትዮዬ ስራዬን መስራት አልቻልኩም….ከተማዋ በበጥባጭ ጎረምሶች ተረብሻ ያንን ማረጋጋት ሲጠበቅብኝ እኔ አንቺን በየመቃብር ቤቱ እከታተልሻል። ለማንኛውም እንዴት እዚህ ደረስሽ?"

" እየነዳሁ።"

በንዴት በጠረጴዛው ላይ የተበተኑትን ፋይሎች አያመለከተ"ይህ ሁሉ ምንድን ነው?"ሲል ጠየቃት፡፡

" መዛግብት ነዋ…..እናቴ ስትቀበር ለአገልግሎት የተከፈሉ ካርኒዎች እና መሰል መረጃዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ያንን እያዩልኝ ነው፣ ፡፡

"አስገድደሽው ነው?::"

‹‹እኔ እንደዚህ ያለ ነገር አላደረኩም..እንዴት ነው ምታስበኝ…?ደፍሬ አባቶቼን የማስገድድ ይመስልሀል?."

" ታዲያ የፍተሻ ማዘዣ ፍቃደሽን አልጠየቁሽም?"

ካህኑ‹‹ልጆቼ ይቅርታ እስኪ እናንተ አውሩ እኔ መጣሁ››ብለው ከመቀመጫቸው ተነሱና ክፍሉን ለቀውላቸው ወጡ … ገመዶ ወደሷ ቀረበና በንዴት ክንዷን ጨምድዷ ያዘ፡፡

‹‹ምን እያደረክ ነው?››

‹‹ቄሱን የሆነ ነገር ብዬ ከማስቀየሜ በፊት ቀጥ ብለሽ ቦታውን ለቀሽ ውጪ››

‹‹ለምንድነው እንደዛ የምታደርገው?››

‹‹ነገርኩሽ እኮ..አሁን ተከትለሺኝ ትሄጂያለሽ ወይስ…የማደርገውን ቆመሽ ትመለከቻለሽ?››

ትኩር ብላ አየችው … ፊቱ እንደ ተራራ ሰንሰለታማና ወጣ ገባ ነው፣በአጭሩ ቋጥኝ ይመስላል፣ ነገር ግን እስካሁን ካጋጠሟት በጣም ማራኪ ወንዶች ውስጥ አንዱ ነው።አብረው በሚሆኑበት ጊዜ ሁሉ፣ ስለ እሱ፣ ስለ ሰውነቱ ታስባለች፡፡ የእሷ ለእሱ ያላት መስህብ ሥነ ምግባር የጎደለው እና ከዛም አልፎ እንዝላልነት እንደሆነ ታውቃለች። መጀመሪያ የእናቷ ፍቅረኛ ነበረ።ያንን በደንብ ታውቃለች ..ሆኖም ብዙ ጊዜ እሱን ለመንካት ትፈልግ ነበር። ትናንት ማታ በምታለቅስበት ጊዜ እንዲያባብላት ትፈልግ ነበር። ወደመኝታ ቤቷ ተከትሏት እንዲገባም ፈልጋ ነበር…ደግነቱ እሱ በተሻለ ብቃት እራሱን የመቆጣጠር ችሎታ ነበረው እና ምንም ሳያደርግ ትቷት ሄደ።

‹‹የሰሎሜ ሬሳ እንደተቃጠለ ነግሬሻለሁ።››
"አንተ እና ዳኛው  ጭንቅላታችሁን አንድ ላይ አድርጋችሁ እያሻጠራችሁ መሆኑን ማወቄ የተመቸኝ ይመስልሀል?።››

"ነገሮችን መገመት ያስደስትሻል?."

"ጁኒየር እናቴ ሬሳ መቃጠሏን ለምን አልነገረኝም?እንደተቀበረች ነበር የነገረኝ ››

‹‹እኔ እየዋሸሁሽ ይምስልሻል….?ለምን ብዬ?" " አስከሬኑ እንዳይወጣ ስለምትፈልግ ነዋ።"

"ሬሳው እንዳይወጣ ለምንድነው የምፈልገው? በእኔ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?"

ፍርጥም ብላ "የእድሜ ልክ እስራት" በማለት መለሰችለት፡፡ "የፎረንሲክ ሪፖርቱ አንተን ነፍሰ ገዳይ መሆንህን የሚያመለክት ፍንጭ ከሰጠን ወደወህኒ መወርወርህ የማይቀር ነው።››

" “አህ...” አለ..ደም ስሯቹ ሲግተረተር እየታዘበች ነው፡፡ "አንቺ ጠበቃ አይደለሽም, ጠንቋይ አዳኝ ነሽ."

"ወንጀል ባይኖር ኖሮ ያ እውነት ሊሆን ይችላል….ግን አንድ ሰው ወደዚያ በረት ውስጥ ገብቶ እናቴን ወግቶ ገድሏታል..እና እስከአሁን ለጥፋቱ የሚመጥን ቅጣት አላገኘም።››

"በእስክሪፕት ደረጃ ትክክል ነሽ" አለ እየተሳለቀ።

"ጋሽ ፍሰሀ ፣ ጁኒየር ወይስ እኔ የቀዶ ጥገና መሳሪያ ይዘን እናትሽን እንደወጋናት ነው ግምትሽ? ለምን በባዶ እጃችን አንገቷን አንቀን አንገድላትም??"

"ሁላችሁም ጎበዝ ስለሆናችሁ።ከመካከላችሁ ወንጀሉን የፈፀመው ሰው እንደዛ ያደረገው ወንጀሉን የአእምሮ ሚዛናዊ የተዛባ ሰው ያደረገው እንዲመስል ፈልጎ ነው።››

‹‹አመንሽም አላመንሽም …እኔ አላደረግኩም

"በብስጭት መለሰላት፡፡

"ታዲያ ማን እንዳደረገው ማወቅ አትፈልግም? ወይስ ነፍሰ ገዳዩ የምትወደው ሌላ ሰው እንዳይሆን ትፈራለህ ?"ስትል ሞጋች ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

‹‹አይ ማወቅ አልፈልግም" ሲል በአጽንኦት መለሰላት፡፡

"እኔ ግን ገዳዩን እስካገኝ ድረስ ምርመራዬን አላቋርጥም..››

ሊመልስላት አፉን ሲከፍት አንድ ግራ እግራቸው ሸንከል የሚል አዛውንት አንድ ያረጀች መዝገብ ይዘው ወደውስጥ ሲገቡ ሲመለከት አፉን መልሶ ከደነ፡፡
43👍1