አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///

ፀሀፊዋ አለምን አቁማ ወደዳኛው ቢሮ ተራማዳ በራፉን በጥንቃቄ አንኳኳች እና ወደውስጥ ገባች…ብዙ ሳተቆይ ተመልሳ ወጣችና ወደአለም ቀርባ …በአጭሩ

‹‹ሊያይሽ ተስማምቷል ››አለቻት፡፡

"አመሰግናለሁ።" አለችና እሷን አልፋ ወደ ክፍሉ ገባች።

"ወ.ሮ አለም …በዚህ ጊዜ ስለምንድነው የምታናግሪኝ?" ዳኛ ዋልልኝ ኮቱን ከመስቀያው ላይ እየጎተተ ነበር የሚያናግራት። "ያለ ቀጠሮ ሰው ቢሮ የመግባት መጥፎ ልማድ ያለሽ ይመስላል። እንደምታየው እኔ ልወጣ ነው። ልጄ ስርጉት ያለ እኔ እራት መብላት አትወድም እና እሷን ማስጠበቅ ለእኔ አሳፋሪ ነው።"

"ሁለታችሁንም ይቅርታ እጠይቃለሁ ክቡር ዳኛ… ለፀሀፊዎ እንደነገርኩት ጉዳዬ በጣም አስቸኳይ ስለሆነብኝ ነው ።"

"እሺ…ልስማው?"

"መቀመጥ እንችላለን?"

" ቆሜ መስማት እችላለሁ …ምን ልትነግሪኝ ፈልገሽ ነው?"

"የእናቴ አስከሬን ተቆፍሮ እንዲወጣ እና  ዳግም የፎረንስክ ምርመራ እንዲደረግበት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲሰጡልኝ እፈልጋለሁ."

ዳኛው ቀስ ብሎ ወንበሩ ላይ ተቀመጠ። አለም ግልፅ የሆነ ጭንቀት ተመለከተችበት።

"ይቅርታ፣ ምን አልሺኝ?፧"

"ክቡር ዳኛ  ያልኩትን እንደሰሙኝ አምናለሁ፣ ግን ጥያቄዬን መድገም አስፈላጊ ከሆነ፣ አደርገዋለሁ።"

ዳኛው  እጁን አወዛወዘ። "አይ. ቸሩ ጌታ አይሆንም. አንድ ጊዜ መስማት በቂ ነው…ለምን እንዲህ አይነት አስቀያሚ ነገር ማድረግ ፈለግሽ?"

"የመፈለግ ጉዳይ ሳይሆን ግድ ሆኖብኝ ነው, በጣም  አስፈላጊ ነው ብዬ ባላምን ኖሮ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልጠይቅም ነበር."

"አስቲ ተቀመጪና…  ምክንያቶችሽን አስረጂኝ።››

"እናቴ ላይ ወንጀል ተፈጽሟል ፣ነገር ግን ትክክለኛው ፍርድ ተገኝቷል ብዬ አላምንም ።"

"እንደዛ ማድረግ አትችዬም " ብሎ ጮኸ።
"አልሰማሽም።ከአመታት በኃላ ድንገት ከመሀከላችን ተገኘሽ፣ ወዲያው መሠረተ ቢስ ውንጀላ ይዘሽ ትረብሺኝ ያዝሽ፣ ለበቀል ቆርጠሻል።"

"ይህ እውነት አይደለም" ስትል ለመከላከል ሞከረች ፡፡ " ለመሆኑ ሀለቃሽ ግርማ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል?"

"አሱ ለጊዜው የለም ..ለጥቂት ቀናት እረፍት ወሰዶ ወደ አዲስአበባ የሄደ ይመስኛል።›› ዳኛው ተናደደ።

" ለማንኛውም ጥያቄሽ … ጥሩ ሀሳብ አይመስለኝም››

" ክቡር ዳኛ ማስረጃ እንድፈልግ ይፈቅዱልኛል?"

"ምንም ማስረጃ አታገኚም" ሲል አፅንዖት ተናገረ፡፡

"ከእናቴ አስከሬን የተወሰነ መነሻ ሚሆነን መረጃ ልናገኝ እንችላለን."

" የተገደለችውና ሬሳዋ የተገኘው እኮ ከዛሬ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ነበር ።"
"በዚያን ጊዜ ለሬሳ ምርመራ ለማድረግ ቴክኖሎጂዎች አልነበሩም… ..በአሁኑ ጊዜ ግን ነገሮች የተለዩ ናቸው፡፡እኔ በግሌ ጎበዝ የተባለ የፎረንሲክ ስፔሻሊስት አውቃለሁ።አሁን ለሚከሰቱ የወንጀል ድርጊቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ከእሱ ጋር የመስራት እድል ነበረኝ …እሱና ጎደኞቹ በጣም ውጤታማ ናቸው ..በዛን ወቅት ባለው ቴክኖሎጂ ሊገኝ ያልቻለ የሆነ ነገር ሊያገኝልን እንደሚችል ዋስትና እሰጥዎታለሁ።››

"ጥያቄሽን እንደጥያቄ እወስደዋለሁ።››

"መልሱ ለዛሬ ማታ ቢደርስልኝ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው ።"

" ይቅርታ ወ/ሪት አለም ማድረግ የምችለው በአንድ ጀምበር አስብበት እና በጠዋት መልሱን እሰጥሻለው።እስከዛው ሀሳብሽን ለውጠሽ ጥያቄውን እንደምትሰርዢ ተስፋ አደርጋለሁ።"

"አላደርገውም።››

ዳኛው ከተቀመጠበት ተነሳ። "ደክሞኛል፣ በዛ ላይ ርቦኛል፣ እናም በዚህ የማይመች ቦታ ላይ ስላስቀመጥሺኝ ተበሳጫችቻለሁ።" የክስ አመልካች ጣት አነጣጥሮባት። "እኔ እንደህ አይነት የተጨመላለቀ ነገር አልወድም."አላት፡፡

" ይህ በጣም አስፈላጊ ባይሆን እኔም አላደርገውም ነበር."

"አስፈላጊ አይደለም."

"እኔ ደግሞ እንደሆነ አምናለሁ" ስትል በግትርነት መለሰች።

" አሁን፣ በቂ ጊዜዬን ወስደሻል። ይሄኔ ልጄ ስርጉት ተጨንቃለች።››

‹‹ ደህና ይሁኑ ብላ ።"ከክፍሉ ወጣች።
///
አለም ቀጥታ  ወደመኪናዋ አመራችና ወደቤቷ ነው የነዳችው… መንገድ በትራፊክ ስለተጨናነቀ ወደቤቷ ለመመለስ ረጅም ጊዜ ነበር የወሰደባት፡፡

ክፍሏ ገብታ አልጋዋ ላይ ተዘርራ ትንሽ እረፍት ለመውሰድ ሞከረች…ከዛ ተነሳች….ማስታወሻዎቿን እንደገና ለመገምገም ሞከረች….ወዲያው ሰለቻት፡፡ ቴሌቪዥኑን ለመክፈት ወሰነች። ሪሞቷን አነሳችና ከፈተች፡፡ፊልም ላይ አደረገችውና ሰውነቷን ለመለቃለቅ ልብሷን አወላልቃ ወደሻወር ቤት ሄደችና መታጠብ ጀመረች……ታጥባ ከመጨረሷ በፊት አንድ ሰው በሯን ሲያንኳኳ ሰማች… እርጥብ ፀጉሯን በፎጣ ጠቅልላለች። ረጅምና ነጭ ካባዋን አደረገችና እና ወገቧ ላይ ያለውን መቀነት ለማሰር እያስተካከለች ወደሳሎን ሄደችና በበራፉ ቀዳዳ በማጮለቅ ማንነቱን ለማረጋገጥ ሞከረች፡፡

የሰንሰለት መቆለፊያው እስከሚፈቅደው ድረስ በሩን ከፈተችው "እንኳን ደህና መጣህ ኩማንደር ምነው በሰላም?"

ኮስተር ብሎ"በሩን ክፈቺ" አላት

"ለምን?"

" ካንቺ ጋር መነጋገር አለብኝ።"

"ስለ ምን?"

‹‹ወደ ውስጥ ካስገባሺኝ እነግርሻለሁ።
አለም  አልተንቀሳቀሰችም."በሩን  ልክፈት  ወይስ  ምን?"እለች  ከራሷ  ጋር  ሙግት ገባች፡፡ግድግዳ ላይ የተንጠለጠለውን ሰዓት ተመለከተች….ለሶስት እሩብ ጉዳይ ይላል፡፡
"እዚያው ሆነህ ላናግርህ እችላለሁ።"

"በሩን ክፈቺ" ብሎ ጮኸ።

‹‹ሰውነቴን እየታጠብኩ ነበር."አለም ሰንሰለቱን አላቀቀችና በሩን ከፍታ ወደ ጎን ቆመች።

"አንድ ሰው እየጠበቅሽ ነበር?"

"አይደለም."

ኮፍያውን ከጭንቅላቱ አወለቀና ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ … ወደ ወንበር ሄዶ ተቀመጠ እና ወደ ቴሌቭዥን ስክሪን ተመለከተ፣ ልብስ ያልለበሱ ጥንዶች ተቆላልፈው ይሳሳማሉ ። ካሜራው የወንዱ ከንፈር ከሴቷ ጡት ጋር ሲጣበቅ እያሳየ ነው፡፡

"ስለአቋረጥኩሽ መናደድሽ አይገርምም።››አላት ሪሞቱን አነሳችና አጠፋችው "አያየሁት አልነበር."
"በራፍሽን ለሚያንኳኳ ሰው ሁል ጊዜ በርሽን ትከፍቺያለሽ?"

"በዚህ ከተማ ውስጥ ከፍተኛው የህግ አስከባሪ የፖሊስ መኮንን ነህ። አንተን ማመን ካልቻልኩ ማንን ማመን እችላለሁ?ይልቅ በዚህ ማታ ለምን መጣህ? እስከ ጠዋት ድረስ መጠበቅ አልቻልክም?"

"ዳኛ ዋልልኝ ደውሎልኝ ስለጠየቅሽው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነገረኝ.››

በንዴት ሲመታ የነበረው ልቧ በፍጥነት ቀዘቀዘ፣ "በዚህ ከተማ ውስጥ የግል የሚባል ነገር የለም ማለት ነው?"ብላ ጠየቀች፡፡

"ብዙ አይደለም"

"በከተማው ክልል ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው የእናንተ ቡድን ሳይፈቅድለት ማስነጠስ የሚችል አይመስለኝም።"

"እንደፈለግሽ ተርጉሚው …አንቺ ዙሪያችን እየተሸከረከርሽ ጉድጓዳችንን ስትቆፍሪ ምን እንድናደርግ ጠብቀሽ ነበር?"

"የእናቴን መቃብር እንዲከፈት ማድረግ ትክክለኛ የግድያዋን መንሴ ለማወቅ ወሳኝ እርምጃ ነው ብዬ ባላስብ ኖሮ የምረበሻት ይመስላችኋል?" ሞቅ ባለ ስሜት ጠየቀች ።

‹‹አንቺ ቋሚንም ሆን ሟችን ከመረበሽ ውጭ ምን ስራ አለሽ?››

"አምላኬ ሆይ ጥያቄውን ማቅረብ እንኳን ቀላል ብሎኝ ያደረኩት ይመስልሃል? እና ዳኛው ከ አንተ እና ከሰዎች ሁሉ ጋር መማከር ለምን አስፈለገው?"

‹‹ለምን ብለሽ ትጠይቂያለሽ እንዴ?… ተጠርጣሪ ስለሆንኩ ነዋ?"

"ዳኛው በዚህ ጉዳይ ከአንተ ጋር መወያየቱ ሞያዊ ሥነ ምግባር የጎደለው ሽማግሌ መሆኑን ነው የሚያሳየው "

"እኔ እኮ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ነኝ፣ አስታውሺ?"
39👍4